Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የወንጌል አገልጋዮች

 - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  ወጣቶች ለጭንቅ ቦታዎች ይፈለጋሉ

  ቤተ ክርስቲያን ወጣቶች አዲስ ለተቋቋመ ሥራ ኃላፊዎች ሊሆኑ መቻላቸውን ትጠራጠር ይሆናል፡፡ ወጣቶችን በደንብ አሠልጥነን በእንደዚህ ያለው ኃላፊነት ላይ መመደብ ከእግዚአብሔር የታዘዝነዉ- ግዴታችን ነው እላለሁ:: በወጣቶቻችን ላይ ዕምነታችን መጣል አለብን፡፡ የሥራ ልምድ ባላቸው ወንጌላዊያን እየተመከሩ ወጣቶቻችን ድፍረትንና መስዋዕትነትን ወደሚጠይቁ ጭንቅ የሥራ ቦታዎች ሊላኩ በወጣትነት ጊዜአቸው ያጋጠማቸውን የሥራ ዕንቅፋትና ክንውንነት እነዚህ አባቶች ለተከታዮቻቸው መተረክ አለባቸው፡፡ በወጣቶቹ ላይ የተጣለባቸው ዕምነት ሥጋዊና መንፈሣዊ ብርታታቸውን ያጉለምስላቸዋል፡፡GWAmh 51.3

  ወጣቶች በጥብቅ : እግዚአብሔር ወደሚስዮናዊ የሥራ መስኮች ይጠራቸዋል፡፡በቤተሰብ አስተዳደር ከተጠመዱት ይልቅ በመጠኑ የኃላፊነት ነፃነት ስላላቸው ሥራውን በሙሉ ኃይላቸው ሊያካሂዱ ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም ወጣቶች አዲስ አካባቢን በቶሎ ለመለማመድ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ችግር ቢያጋጥማቸው የበሰጠ የመቋቋም ኃይል አላቸው፡፡GWAmh 51.4

  በዘዴና ባለመሰልቸት ሰዎቹን ሊቃረቧቸው ይችላሉ፡፡ ብርታት የሚገኘው በሥራ ልምድ ነው:: ከአምላክ የተሰጣቸውን ችሎታ በሙሉ በሥራ ላይ የሚያውሉ ሰዎች ለሥራው አገልግሎት ተጨማሪ ችሎታ ይሰጣቸዋል፡፡ ያላቸውን ቀብረው የሚቀመጡ ግን ያላቸውም ይጠፋባቸዋል፡፡ እግርና እጅ ኖሮት ሳይሠራ ተጋድሞ የሚኖር ሰው ቆይቶ እነዚህን የአካላት ክፍሎች ልሥራባቸው ቢልም አይችልም፡፡ እንደዚሁም ከአምላክ የተሰጠውን መንፈሣዊ ችሎታ የማይገለገልበት ሰው መንፈሣዊ ሽባ ሆኖ ያርፋል፡፡ በዕውነት የሚጠነክሩና የሚጸኑ የሰውና የክርስቶስ ፍትር አድሮባቸው በቅንነት የሚሠሩ ብቻ ናቸው፡፡ እውነተኛ ክርስቲያን ለአምላክ የሚሠራው ተገፋፍቶ ሳይሆን ከልቡ፣ ለቀን ወይ ሰወር ብቻ ሳይሆን ዕድሜ ልኩን ነው፡፡GWAmh 52.1

  ጌታ ወንጌላዊያንን ይጠራል፡፡ ማነው አቤት የሚል? በጦር ሠራዊት ውስጥ የሚመለመሉት ሁሉ ጀኔራሎች፣ ሻምበሎች፣የመቶ አለቆች፣ ወይም የአሥር አሰቀች አይሆኑም፡፡ ሁሉም የመሪነት ኃላፊነት አይጣልባቸውም፡፡ ሌላ ሊፈጽሙ የሚገባቸው የሥራ ዓይነቶች: አንዳንዶቹ ቦይ በመቆፈር ምሽግ ይሥራሉ:: አንዳንዶቹ ዘብ ሲቆሙ ሌሎቹ መልዕክት ያደርሳሉ፡፡ በጥቂት አለቆች ሥራ ብዙ ተራ ወታደሮች ሲኖሩ ሠራዊቱ የተሟላ ይሆናል፡፡ የሥራዊቱ የሥራ መሳካት የሚወሰነው በእያንዳንዱ ወታደር ታማኝነት ነው፡፡ የአንድ ወታደር ወላዋይነት ወይም ከሃዲነት ለሠራዊቱ ውድቀት ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡GWAmh 52.2

  ሰእያንዳንዱ አንደ ችሎታው «ሥራውን የሰጠ” አምላክ የማንኛውንም ሰው ታማኝ አገልግሎት ያለዋጋ አይተወውም፡፡ ታማኝነትና አምነት የእግዚአብሔርን ደስታ የሚገልጥ የክብር ዘውድን ይዋዳጃል፡፡ ሰእያንዳንዱ ሠራተኛ «በሄዱ ጊዜ ዘራቸውን ተሸክመው እያለቀሱ ተሰማሩ፤ በተመለሱ ጊዜ ግን ነዶአቸውን ተሸክመው ደስ እያላቸው ይመጣለ-” (መዝ.126፡6) የሚል ተስፋ ተሰጥቶታል፡፡GWAmh 52.3

  የዳንኤልን አስተዳደግ ያደገ ማንኛውም ወጣት በአደባባይ ቅን ፍርድ ያሰማል፣ ወይም በቤተመንግሥት የነገሥታት ንጉሥ ምስክር ሊሆን ይችላል፡፡ ብቡዎች ወደ ወንጌል ሥራ ይጠራሉ፡፡ ዓለም በመላ ለወንጌል ሥራ ተክፍቶአል፡፡ ኢትዮጵያ አጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች::- ከቻይና ከጃፓን ከሌሎችም የዓለም ከፍሎች በኃጢዓት ልባቸው የተወጋ ሰዎች የወንጌልን ፅውነት ይሻሉ፡፡GWAmh 52.4

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents