Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የወንጌል አገልጋዮች

 - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  መቀባተ

  «በአንጾኪያ ባለቸው ቤተ ክርስቲያን ነቢያትና መምህራን ነበሩ፤ እነርሱም በርናባስ ኔጌር የተባለውም ስምዖንም... ሳወልም ነበሩ፡፡ እነዚህ ጌታን ሲያመልኩና ሲጦሙ መንፈስ ቅዱስ ሳወጠልንና በርናባስን ለጠራኋቸው ሥራ - ለዩልጎኀ አለ፡» ለአሕዛብ ወንጌላዊያን (ሚሲዮናዊያን) ሆነው ከመላካቸው በፊት በጾምና በጸሎት ራሳቸውን ለእግዚአብሔር አቅርበው አጅ በመጫን ለሥራው ተመረቁ፡፡ ከቤተ ክርስቲያን የማስተማር ሥልጣን ብቻ ሳይሆን፤ የማጥመቅና ቤተ ክርስቲያን የማቋቋም ሥልጣን ተቀበሉ፡፡GWAmh 294.5

  የክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን በዚያን ጊዜ አንድ ተፈላጊ የታሪክ ጊዜ እየጀመረች ነበር፡፡ ወንጌልን ለአሕዛብ ማወጅ ተፈላጊ ሰለነበር ቤተ ክርስቲያኗ በሙሉ ኃይሏ መሥራት ጀምራ ነበር፡፡ይ ህን ሥራ ለመሥራት የተሰለፉት ሐዋርያት ተቃውሞ፣ ቅናትና ስደት ያጋጥማቸው ነበር፡፡ በአይሁድና በአሕዛብ መካከል የቀመውን «የጥል ግድግዳ» ለማፍረስ ሲሞክሩ አንደካሃዲ ይቆጠሩ ነበር፡፡ የወንጌል መልዕክትኛነት ሥልጣናቸውንም ብዙ አይሁዶች አይቀበሉትም ነበር፡፡ ሠራተኞቹ የሚደርስባቸውን ችግር እግዚአብሔር አስቀድሞ አውቆታል፡፡ ይሀንም በማወቅ ከጉባዔው ለይተው አንዲያቋቁሟቸው አዘዘ፡፡ የወንጌልን የምሥራች ለአሐዛብ አንዲያዳርሱ የተሰጣቸው ሥ'ልጣን በሁሉ ዘንድ :GWAmh 295.1

  ጳውሎስና በርናባስ አስቀድመው በአግዚብሔር ስለተመረጡ የአጅ መጫን ሥኑሥርዓቱ ለብቁነታቸው ምንም የሰጠው ተጨማሪ ጸጋ አልነበረም፡፡ ሥኑሥርዓቱ የአንድን ሰው ለተለየ ሥልጣን መሾሙን የሚያመለክት መግለጫ ነበር፡፡ በዚህ አማካይነት የቤተ ክርስቲያኑ ማህተም በእግዚብሔር ሥራ ላይ ታተመ ማለት ነው፡፡GWAmh 295.2

  ለአይሁዶች ይህ ዓይነት ሥኑሥርዓት ትርጉም ነበረው፡፡ የአይሁድ አባት ልጆቹን ሲመርቅ አጆቹን በላያቸው ይጭንባቸው ነበር፡፡ አንድ እንሰሳ ለመሥዋዕትነት ሲቀርብ ለክህነት ማዕረግ የተመረጠው ሰው እጁን በእንሰሳው ላይ ይጭንበት ነበር፡፡ በአንጾኪያ የነበሩት ቀሳውስት አጆቻቸውን በበርናባስና በጳውሎስ ላይ ለተመረጡበት የተለየ ሥራ ብቁ ሆነው አንዲገኙ እግዚአብሔር እንዲባርካቸው መጠየቃቸው ነበር፡፡GWAmh 295.3

  ቆይቶ ግን የአጅ መጫን ሥርዓት እንዳልሆነ ሆነ፤ አጅ የሚጫንባቸው ሰዎች በአንድ ጊዜ ኃይል አግኝተው ማንኛውንም መንፈሳዊ አገልግሎት ይሰጣሉ ተብሎ መገመት ጀመረ፡፡ ግን እነዚህ ሁለት ሐዋርያት በተመረጡበት ታሪክ ውስጥ የአጅ መጫኑ ሥኑሥርዓት ኃይልና ብቁነት ጨመረላቸው የሚል ቃል አላገኘንም፡፡ እጅ እንደተጫነባቸውና የወደፊት ሥራቸውን በቁርጥ እንደተነገሩ ብቻ እናነባለን፡፡GWAmh 295.4

  የጳውሎስና የበርናባስ በመንፈስ ቅዱስ መመረጥ እግዚአብሔር ለሥራው የተለዩ ሰዎችን እንደሚመርጥ ያመለክታል፡፡ ከጥቂት አመታት በፊት ጳውሎስን መድኃኒታችን ከተገናኘው በኋላ ወዲያው በደማስቆ ከሚገኙት አዲስ ከተቋቋሙት ክርስቲያናት ጋር ተገናኘ፡፡ የተመለሱት ፈሪሳዊያን በቂ የክርስትና ልምድ ስለነበራቸው ቤተ ክርስቲያኗ በጨለማ ውስጥ አልነበረችም፡፡ መለኮታዊ ትዕዛዝ በሚገባ አንዲክበር እግዚአብሔር ጳውሎስን ወንጌልን ለአሕዛብ ለማዳረስ የተመረጠ ዕቃዬ ብሎ ከተናገረ በኋላ እንድትሾመው ለቤተ ክርስቲያን ሥልጣን ሰጣት፡፡ በአንጾኪያ ያሉት መሪዎች በጾምና በጸሎት ላይ ሳሉ «በርናባስንና ጳውሎስን ያገለግሉኝ ዘንድ ጸልዩልኝ አላቸው፡፡»GWAmh 296.1

  እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን የብርሃን ማስተላለፊያ በማድረግ ሀሳቡን ፈቃዱን በእርሷ አማካኝነት ይገልጣል፡፡ ለተለየ አገልጋዩ ከቤተ ክርስቲያን ሀሳብ ጋር የማይስማማና ብቻውን የሚያካሂደው ሥራ አይሰጠውም፡፡ ወይም ቤተ ክርስቲያንን በጨለማ ውስጥ ትቶ ቤተክርስቲያንን የሚመለከተውን ዕውቀት በሙሉ አንድ ሰው ብቻ አይሰጥም አምላክ በጥበቡ በራሳቸው ከመመካት ይልቅ እርስ በርሳቸው እንዲደጋገፉ አድርጎ አገልጋዮቹን ያቀርባቸዋል፡ በግለ ችሎታቸው ብቻ የሚተማመኑ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አልጠፉም፡፡GWAmh 296.2

  ትምክህት ለሥራው እግዚአብሔር የመረጣቸውን ሰዎች ከመታዘዝና ከመከተል ይልቅ ከወንድማማች ምክክር አውጥቶ ብቸኛ አንደሚያደርግ አልገባቸውም፡፡ እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያኑ የተለየ ሥልጣንና ኃይል ሰጥቶታል፡፡ ይህን ሥልጣንና ኃይል የናቀ የእግዚአከብሔርን ቃል እንዳዋረደ ይቆጠራል፡፡GWAmh 296.3

  የራሳቸውን ችሎታ የበላይ አድርገው የሚመለከቱ በአደገኛ ሁኔታ ላይ ናቸው፡፡ ሥራውን አንዲያስፋፉ ከሾማቸው ሰዎች እነዚያን ነፍሳት መለየት የሠይጣን የተጠና ዓላማው ነው፡፡ በሥራው ላይ የሾማቸውን የእግዚአብሔር አገልጋዮች መናቅ አግዚአብሔር ነፍሳትን ለማዳን ያቋቋመውን ሥኑስርዓት መንቀፍ ነው፡፡ አንድ ሠራተኛ ከቤተ ክርስቲያን ተለይቼ በቀጥታ ከአምላክ የመጣልኝን ብርሃን ለሰዎች አበራለሁ ብሎ ካሰበ ሰይጣን አታልሎ ሊጥለው ከጅሎታል ማለት ነው፡፡ አምላክ በጥበቡ ያዘጋጀው መንገድ አማኞች እርስ በርሳቸው ተቀራርበው ክርስቲያን ከክርስቲያን ጋር ቤተ ክርስቲያንም ከቤተ ክርስቲያን ጋር አንድ እንዲሆኑ ነው፡፡ ያን ጊዜ የሰብዓዊ መሣሪያነት ከመለኮት ጋር ይስማማል። ሁሉም ለመንፈስ ቅዱስ ይገዛና አማኞች በሙሉ በተደራጀና መንገድ በያዘ ጥረት የወንጌልን የምሥራች ለዓለም ያዳርሳሉ፡፡GWAmh 297.1

  ጳውሎስ የመመረጡን ሥኑሥርዓት ለሥራው አዲስ ምዕራፍ እንደከፈተለት አድርጎ ቆጠረው፡፡ በክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያገለገለውን የሐዋርያነት ሥራውን ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ነው የቆጠረው፡፡GWAmh 297.2

  ክርስቶስ ካረገ በኋላ ለሚቀጥሉት ሥራቸው የቤተ ክርስቲያን አባሎች የተዘጋጁ አሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ከተመረቁ በኋላ ነበር፡፡ የምረቃው ቃል እንዲህ «ወደ ተራራም ወጣ ራሱ የወደዳቸውን ወደርሱ ጠራ፤ ወደ ርሱም ከርሱም ጋር እንዲኖሩ ለመስበክ ሊልካቸው» (ማር. 3፡13-14) እግዚአብሔርና መልዓክት ይህን ሥኑሥርዓት በደስታ ተመለከቱ፡፡GWAmh 297.3

  አብ የሰማይ ብርሃን ከነዚህ አንደሚበራ አወቀ፡፡ ስለልጁ የሚናገራቸው ቃላት እስከዓለም ፍጻሜ ድረስ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንደሚያስተጋቡ አወቀ፡፡GWAmh 297.4

  ደቀመዛሙርቱ ከእርሱ ያዩትንና የሰሙትን ለመመስከር የክርስቶስ ምስክሮች ሊሆኑ ተመረጡ። ሥልጣናቸው ክክርስቶስ ቀጥሎ ሰዎች ካገኙት ሥልጣን ሁሉ ይበልጣል፡፡ ሰዎችን ለማዳን ከእግዚአብሔር ጋር እንዲሠሩ ሆኑ በብሉይ ኪዳን አሥራ ሁለቱ አበው የአሥራኤል ልጆች ወኪል ሆነው እንደቆሙ፤ በሐዲስ ኪዳን ደግሞ አሥራ ሁለቱ ሐዋርያት የወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን ወኪሎች ሆነው ቆመዋል፡፡GWAmh 297.5

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents