Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የወንጌል አገልጋዮች

 - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  ምዕራፍ 3—ተፈላጊ ዝግጅት

  የወጣቶች በአገልግሎት ላይ ዝቅ አድርጎ የሚያስገምት አንድም ምክንያት መኖር የለበትም፡፡ ሥራውን ዝቅ አድርገው የሚገምቱ ሰዎች ክርስቶስን ማዋረዳቸው ነው:: ከሁሉም የላቀው ሥራ ወንጌላዊነት ነው:: ከወንጌል አገልጋይነት የበለጠ በእግዚአብሔር ፊት የተቀደሰ ሥራ የሰም፡፡GWAmh 38.1

  …………..ሥራ ማቃለል አይገባም፡፡ የወንጌልን ሥራ ዝቅ ካላለ ወጣቶቻችን ወደ ወንጌል አገልግሎት ለመግባት ወደኋላ አያፈገፍጉም፡፡ በአንዳንድ የተሳሳተ አመራር ወጣቶቻችን እግዚአብሔር ከሚፈልግባቸው መስመር ሊወጡ ይችላሉ:: አንዳንዶች የወንጌል አገልጋይ ሊሆኑ ሲገባቸው የሕክምናን ትምህርት አንዲከታተሉ ማደፋፈሪያ አግኝተው ይሆናል፡፡ ጌታ በወይን ቦታው የሚሠሩ ብዙ አገልጋዮች ያስፈልጉታል፡፡ «ምሰሶዎችን አበርታ፣ በዓለም ኩሪያ ታማኝ አገልጋዮች ይኑሩህ» የሚል አነጋገር አለ፡፡ ወጣቶች ሆይ! እግዚአብሔር ይጠራችኃል፡፡GWAmh 38.2

  ክርስቶስን የሚያፈቅር፣ ሰፊ አስተሳሰብ ያለው የወጣቶች ሠራዊት ያስፈልጋል፡፡ ከዕውቀታችሁ ብዛት ይልቅ ለሥራው ያላችሁ ናፍቆት ተፈላጊነቱ ያመዝናል፡፡ የወንጌል አገልግሎት በተማሩ ሲቃወንት ብቻ ሊካሄድ አይችልም፡፡ ንግግር አሳማሪዎችና ነገር አዋቂዎችም ተፈላጊነታቸው እስከዚህ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር የሚፈልገው ሙሉ ሰውነታቸውን ለእርሱ አስረክበው ከመንፈሱ ለመማር የሚሹትን ነው፡፡ ለክርስቶስና ለሰብዓዊ ዝምድና የሚያስፈልጉ ሰዎች ራሳቸውን በሙሉ የሚያስረክቡ ስድብንና ነቀፌታን የማይፈሩ ቆራጦች ናቸው፡፡GWAmh 38.3

  ብርቱዎች መሆን አለባቸው፡፡ ራሳቸውን ቀድሰው ለማቅረብ ከአምላክ ጋር ቃል ኪዳን ይግቡ፡፡ የወንጌል ሥራ፣ የሰነፎች ተግባር አይደለም፡፡ የእግዚአብሔር አገልጋዮች አገልግሎታቸውን በጉልህ ማሳየት አለባቸው፡፡ አፈግፋጊዎች አይሆኑም፣ ግን ወደፊት በመግፋት ታማኝነታቸውንና ሙሉ ኃይላቸውን ለሥራው መስፋፋት ምክንያት ያደርጉታል፡፡ ከመማር አይቆጠቡም:: በተፈለጉበት ጊዜ ቀጥ ብለው የተፈለገውን መስዋዕትነት ለመፈጸም ሕይወታቸውን ብዙ ዝግጁ አድርገው መጠባበቅ አለባቸው፡፡ ላጥና ወይ ልጸልይ. ብሰው በወላዋይነት የተፈለጉበትን ጉልህ የሥራ መስክ ማሰተጓጐል የለባቸውም፡፡ አምላክ በሕይወታቸው በመንፈስ የበሰጸጉ ሰዎች ያስፈልጉታል፡፡GWAmh 39.1

  እያንዳንዱ ሠራተኛ አምላክ ባዘዘው መንገድ ሲራመድ የሚችለው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ከላይ የሚያበረታውን ኃይል ሲቀበል ብቻ ነው:: የእግዚአብሔር ቃል ራሱን ቀድሶ ባስረከበ ወጣት አገልጋይ ልቦና ውስጥ ይኖራል፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር የማያቋርጥ ግንኙነት ካለው እንደ እርሱ ያለ ፈጣን፣ ብርቱና እውነተኛ የለም፡፡GWAmh 39.2

  አንደ እነዚህ ያሱ ሰዎች ዋና ሥራቸው የክርስቶስን ዳግም ምጻት ማብሠር ነው:: ሰዎችን ወደ መጨረሻው የወንጌል ድግሥ፣ ወደ በጉ ሠርግ ማደም አለብን፡፡ በሽህ የሚቆጠሩ ወንጌል ያልደረሳቸው ሰዎች መልዕክቱን መሥማት አለባቸው፡፡ «እግዚአብሔር ይህን መልዕክት እንድታደርሱ አልጠራችሁምን?” በማለት አንደገና ወጣቶችን እማጸናለሁ፡፡GWAmh 39.3

  ለመገልገል ሳይሆን ለማገልገል ወንጌላዊያን የሚሆኑ ወጣቶች ስንት ናቸው? ዱሮ ለአንድ ሰው አንኳን ተጨንቀው «ጌታ ሆይ ይህን ነፍስ አንድመልስ እርዳኝ» የሚሉ ብዙዎች ነበሩ፡፡ ዛሬ ግን እንዲህ ያሉ ሰዎች የሚገኙት ዘንቦ ተባርቆ (አልፎ አልፎ) ነው:: የኃጢዓተኞችን ጥፋት ተገንዝበው የሚሠሩ ስንት ናቸው? ጳውሎስ ስለጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን «ስለ እኔም እግዚአብሔርን ያከብሩ ነበር” (. 1፡24) ሲል ስለ እኛም እንዲህ ያለው አነጋገር እንዲባልልን መጣር አይገባንም ወይ? በሙሉ ልባቸው ለሚሹት እግዚአብሔር የሚያድጉበት መንገድና ምክንያት አያጣላቸውም፡፡GWAmh 39.4

  የሥራ ቦታዎችን ለማዘጋጀትና ሠራተኞችንም ለማሰልጠን የእግዚአብሔርን የበላይነትን መገንዘብ ይፈለግብናል፡-: ወንጌላዊያን እውነቱ ከታየባቸው ሰዎች ጋር በፀሎት ይጠመዱ፡፡ ክርስቶስ ሁል ጊዜ ከእናንተ ጋር መሆኑን አትዘንጉ:: ቁምነገረኛውንና ትሁቱን ሠራተኛውን ለማበርታት እግዚአብሔር ፀጋውን ይለግሣል፡፡ ከዚያ በኋላ ያረፈባችሁን የአምላክ ብርሃን ማንጸባረቅ የራሳችሁ ፋንታ ነው፡፡ ይህን የሚፈጽሙ ለጌታ ከሁሉም ሥጦታ አበረከቱ ማለት ነው: የመዳንን የምሥራች ለሌሎች የሚያካፍሉ ሰዎች ልባቸው በምሥጋና መንፈስ ይሞቃል፡፡ ገላትያ 1:24:GWAmh 40.1

  የወንጌላዊያን ቁጥር፤ መጨመር አንጅ መቀነስ የለበትም፡፡ አሁን አንድ ወንጌላዊ ብቻ ባለበት የወንጌል ሥራ ሌሎች ፃያ ያስፈልጋሉ፡፡ እነዚህ ሃያዎቹ በእውነት በጌታ መንፈስ የሚመሩ ከሆኑ ሌሎች ሃያ የሚያስፈልጉት ሰፊ ሥራ ያስገኛለ፡፡GWAmh 40.2

  የክርስቶስ ክብርና ሥራ ይህን ያህል ቀጥተኛ ነው:: ተከታዮቹ የሰዎች ፍቅር አንደሳባቸው መጠን የወንጌልን ሥራ ለማስፋፋት ይችኩላሉ፡፡ ሰብዓዌው አቅማችን ሊያከናውነው ማይችለው ታላቅ ሥራ መለኮታዊ ዕርዳታውን አምላክ ይልክልናል፡፡ ተስፋችንና ልባችን ለማንፃት መንፈስ ቅዱሱን ይልክልናል፡፡ አንደፋላጐቱ ሥራውን ለሰማካሄድ ተፈላጊውን መሣሪያ ሁሉ ያዘጋጅልናል፡፡ ከእግዚአብሔር ምክር አንድትሹ እነግራችሏኋለሁ፡፡ በፍጹም ልባችሁ ፈልጉት .«የሚላችሁንም ሁሉ አድርጉ::» (ዮሐ. 2፡5)GWAmh 40.3

  በትክክል የሠለጠነ ወጣቶች የሚገኙበት የወንጌል ሠራዊት ሥራውን እንዴት ባፋጠነው እና የኃጢዓትና የሐዘን ፍጻሜ ቶሎ በደረሰ ነበር! ልጆቻችን የኃጢዓትና የሥቃይ ንብረት በመውረስ ፋንታ ‹የጻድቃንን ርስት፤ - የዘለዓለምን መኖሪያ፣ ዘ ኗሪዎቹ አመመኝ ደከመኝ የማይሉበትን፣ የልቅሶ ድምፅ ለዘለዓለም የማይሰማበትን» የዘለዓለም ርስት በወረሱ ነበር! ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ፤ በዚያም የሚቀመጥ ታምሜአለሁ ከዚያም ወዲያ የለቅሶ ድምጽና የዋይታ ድምፅ አይሰማለትም» (መዝ. 37፡29፣፤ ኢሳ. 33፡24፣ 65፡19)GWAmh 40.4

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents