Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የወንጌል አገልጋዮች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ለታመሙ መፀለይ

    የወንጌል ዋናው ሥራ ማደስ ስለሆነ እግዚአብሔር አገልጋየቹን የታመሙትን፣ ተስፋ የቆረጡትን አና የተቸገሩትን አንዲያበረታቱ ይፈልጋል፡፡ አገልጋዮቹ የጸጋው አሳላፊዎች ስለሆኑ በእነርሱ አማካኝነት የማዳን ኃይሉን ይሠራበታል፡፡ የታመሙትን በሃይማኖት ክንድ አቅፈው ወደ አዳኛችን ማቅረብ ተግባራቸው ነው፡፡GWAmh 134.1

    የሥጋና የመንፈስ ደዌን ሰመፈወስ መሣሪያ አድርጎ ይጠቀምባቸው ዘንድ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ጌታን በግልጽና በቅርብ ለማየት መቻል አለባቸው፡፡ የሄይማኖትን ገመድ ለመጨበጥ ይችሉ ዘንድ ከበሽተኞች ጋር መጸለይ መብትና ግዴታቸው ነው : ለሚሰቃዩ የሰው ልጆች እንዲህ ዓይነት አገልግሎት የሚሰጡትን የእግዚአብሔር መልአክት ይቀርቡአቸዋል፡፡GWAmh 134.2

    የሕሙማንን ተማዕጽኖ ሳይንቅ ከመሰኮታዊ አለኝታ ጋር የሚያገናኝ የእግዚአብሔር ወኪል ዘለዓለማዊ ታላቅ ሥራ ፈጸመ ማለት ነው፡፡ በሸተኞቹን ከክርስቶስ በተሰጠው ተስፋ በሃይማኖት ሲያበሥራቸው የራሱ መንፈሳዊ ሕይወት ይበረታለታል፡፡GWAmh 134.3

    በሕግ ተላላፊነታቸው ሥጋዊ በሽታ አንደደረሰባቸዉ የሚገነዘቡ ነፍሳት «ጌታ ሆይ እኔን ኃጢዓተኛውን ይቅር በለኝ፤ ልጅህም አድርገኝ” ይላሉ:: ይህን ጊዜ ወንጌላዌው የበሽተኛውን ሃይማኖት በማጠናከር የሱስ ኑዛዜውን ሰምቶ ደህንነትና ሰላም አንደሚሰጠው ያስገንዝበው፡፡ በእንዲህ ዓይነት ጭንቅ ላይ ለወደቀው ደዌ የመዳንን ተስፋ በትህትና የሚናገር የደህንነት ምንጭ ለሆነው አምላካችን አፈ-ንጉሥ ሆነ ማለት ነው፡፡ በአልጋ ቁራኛ በደዌ ዳኛ ለተያዘው በሽተኛ የሩህሩህነት ቃል ሲያሰማ፣ ጸሎት ሲያሳርግለት የሱስ ደግሞ የበኩሉን የአዳኝነት ሥራ ይፈጽማል፡፡ እግዚአብሔር በሰዎች. ከናፍር አማካኝነት ይናገራል፡፡ የሰውየው ልብ ይነካና ሰብዓዊ ፍጥረትና መለኮት ይግባባሉ፡፡GWAmh 134.4

    ወንጌላዊው በክርስትና ልምዱ የክርስቶስ የማዳን ኃይል ለሰዎች ደስታንና ተድላን አንደሚያመጣ አይዘንጋ፡፡ የደከመሙትንና ልባቸው የዛለውን ክርስቶስ ዕረፍት ለመስጠት አንደሚጠራቸው ማወቅ አለበት፡፡ የመድኃኒታችን ፍቅር ከአገልጋዮቹ ሳይለይ ለተቸገሩት ሰላምንና ዕርዳታን እንዲያስገኙ አንደሚጠቀምባቸው አይርሳ፡፡ ይህን ካልዘነጋ አምነቱ ይጸናል፤ ጸሎቱም አፋዊ ሳይሆን ልባዊ ይሆናል፡፡GWAmh 134.5

    ከዚያ በኋላ ዕርዳታውን ለሚጠይቁት ሁሉ የእግዚአብሔርን የማዳን ኃይል ያዘንብላቸዋል፡፡ የክርስቶስን የፈዋሽነት ታሪክ በመናገር ሕይወትና ብርሃን፣ መጽናናትና ሰላም ወደሆነው ወደ ታላቁ ሐኪም ያመላክታቸዋል፡፡ ተስፋ መቁረጥ አንደሌለባቸው፣፤ መድኅን እንደሚያፈቅራቸው፣፤ ራሳቸው ለእርሱ አደራ ቢሰጡ ሲያፈቅሩት እንደሚችሉና ጥበቃውና ቸርነቱ አንደማይለያቸው ያስተምራቸዋል፡፡ ተስፋ የሰጠን ክርስቶስ ከማንም የበለጠ ወዳጃችን መሆኑን በማስረዳት በተስፋው አንዲያምነበት ይገፋፋቸው:: የሰዎቹን የአስተሳሰብ ዝንባሌ ወደ ሰማይ ሲያመላክት መፈወስ የሚያውቀው አምላክ የምህረት ዘይቱን በሸተኛውን አንደሚቀባው አርግጠኛ ይሆናል፡፡GWAmh 135.1

    መለኮታዊ ፈዋሽ በበሽተኛው ክፍል ምንጊዜም አለ፡፡ በእውነተኛ ሃይማኖት የተጸለየውን ጸሎት ሁሉ ያደምጣል፡፡ የዱሮ ደቀመዛሙርት እንዳደረጉት ሁሉ ዘመናዊያን ደቀመዛሙርት ለበሽተኞች ሠው ጸለይ አለባቸው፡፡ «የሃይማኖት ጸሎት ደዌ ስለምትፈውስ” መዳን ይገኛል፡፡ (ያዕቀብ 5:15):GWAmh 135.2

    የእግዚአብሔር ቃል የተለየ ጸሎት ሕመምተኛን ሊፈውስ አንደሚችል ተናግሮናል፡፡ ግን የዚህ ዓይነት ጸሎት ልዩ ዝግድት ሳይደረግ መሞከር የለበትም፡፡ ለበሽተኛ የሚደረገው ጸሎት አብዛኛውን ጊዜ ይሆንልኛል በሚል ጥብቅ አምነት የተመሠረተ ነው፡፡GWAmh 135.3

    ብዙ በበሽታ የሚለክፉ በጥንቃቄ ጉድለት ነው፡፡ የተፈጥሮን ሕግ አክብረው ወይም ንጽህናን አዘውትረው አይኖሩም፡፡ ሌሎችም በመብልና በመጠጥ ወይም በስሰባበስና በሥራ የጤናን ሕግ ይተላለፋሉ፡፡ የአእምሮ ድካም ወይም የአካል መጎሳቆል አብዛኛውን ጊዜ የሚመጣው በኃጢዓት ነው:: እንደነዚህ ያሉት ሰዎች ጤናቸውን አንደገና ሲያገኙ አምላክ ምንጊዜም ከጸለይሁ ጤናዬን ይመልስልኛል በሚል የተሳሳተ አስተሳሰብ አጉል ያልተስተካክለ የኑሮ ዘይቤአቸውን ይቀጥላሉ፡፡ እግዚአብሔር አውቆ ጤናቸውን የሚበድሉትን በመፈወስ ተአምር ከፈጸመ በኃጢዓታቸው አንዲቀጥሉ አደፋፈራቸው ማለት ነወ፡፡GWAmh 135.4

    ጤናን የሚቃወሙ አድራጎቶችን አንዲተው ሰዎች ካልተማሩ የእግዚአብሔርን ፈዋሽነት ማስተማር ክንቱ ድካም ነው፡፡ ለጸሎታቸው ለማግኘት ክፉ መሥራትን ትተው መልካም ማድረግ መማር አለባቸው፡፡ አካባቢያቸው ንጽህና ያልጎደለው፥ ይዞታቸው ፍጹምና የሚታይበት መሆን : የእግዚአብሔርን የተፈጥሮና መንፈሣዊ ሕጎች ማክበር ተገቢ ነው፡፡GWAmh 136.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents