Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የወንጌል አገልጋዮች

 - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  ክርክር (ውይይተ) አይናፈቅም

  ወጣት ወንጌላዊያን ክርክርን ማስወገድ አለባቸው፡፡ ምክንያቱም ለትህትና ሆነ ለመንፈሳዊ ዕድገት አይጠቅምም፡፡ አንዳንድ ጊዜ እውነትን በኩራት የሚቃወመን ጉረኛ በጉባዔ ማጋለጥ መልካም ነው፡፡ ነገር ግን ይህ በጽሑፍም ሆነ በቃል የሚካሄደው ክርክር ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ ከክርክር በ3ኋላ ወንጌላዊው የሕዝቡን ፍላጎት ለማነሳሳት ያለበት ኃሳፊሃት በበለጠ ይከብድበታል፡፡ የሕዝቡ ስሜት ስለሰለተነሳሳ ንቅናቄ መነሳሳቱን ማወቅ አለበት፣ በዚህም ተስፋ ሊቆርጥ አስይገባውም፡፡GWAmh 248.6

  ክርክር አብዛኛውን ጊዜ ወንጌላዊያንን ኩሮዎችና በራሳቸው የሚመኩ ያደርጋቸዋል፡፡ መቼ ይህ ብቻ፤ ክርክር ወዳጆች ሰመንጋ ጠባቂነት አይገቡም፡-፡ አስተሳሰባቸውን ለክርክር ስላሰለጠኑት ሁል ጊዜ የሚያሰላስሉ ማፍረጓ ቃላትን ነው፡፡ ስለዚህ ልቦች ለማጽናናት መልካም ቃላት ሊናገሩ አይችሉም፡፡GWAmh 249.1

  በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት የሌለው መልዕክት ሲያስተላልፉ ወንጌላዊያን የሚናገሩት ከእግዚአብሔር ቃል ጋር መስማማቱን ማረጋገጥ አለባቸው፡፡ ንግግራቸው ደረቅ መሆን : ንግግራቸውን በፍቅር አለዝበው፣ ለነፍሳት መዳን ከልባቸው ተቆርቁረው የሠሩ እንደሆን የእግዚአብሔርን ቃል ስለተ ቆራጭ አድርገው አቀረቡ ማለት ነው፡፡GWAmh 249.2

  ክርክርን ለማስወገድ አይቻልም፡፡ አንዳንዶች ተቃዋሚዎች ሲስነፉ ለማየት ክርክርን ይሻሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ ከሁለቱም በኩል የሚባለውን ስምተው በቅን ልቦና ለማመዛዘን ይፈልጋሉ፡፡ ነገር ግን በተቻለ መጠን ክርክር ቢወገድ መልካም ነው፡፡ በሀሳብም ቢሰያዩ በክርስቲያናት ልብ ሊኖር የሚገባውን የፍቅር መተሳሰር አስወግዶ ጠላትነትን ያበቅላል፡፡GWAmh 249.3

  በአሁኑ ዘመን ክርክር የሚፈልጉ ሰዎች ዕውነትን ለመርዳት ሳይሆን እንዲሁ በጉጉትና በስሜት ተነሳስተው ነው፡፡ በክርክር እግዚአብሔርን ለማክበር፤፣ እውነትንም ለማራመድ ብዙ ጊዜ አይቻልም፡፡ እውነትን ለመቀበልም ሆነ ለመንቀፍ ብዙ ክርክር አያሻም፡፡ የክርክር ችሎታን ለማሳየት ከተቃዋሚዎች ጋር ሠ።ከራክር ውጤቱ ስጉል ነው፡፡GWAmh 249.4

  የእውነት ተቃራኒዎች ለእውነት የቀቆቀመሙ'ትን አያጣጣሱ በኃጢዓት ጨለማ የተዋጡትን ወደባሰ ውድቀት ይመራቸዋል፡፡ ሁለቱም ተከራካሪዎች የክርክር ምላሳቸውን በማሾል አዳማጩ ያደናግሩታል፡፡ ከፍ: ያለ አለመጣጣም ይፈጠራል፡፡GWAmh 249.5

  ሥራቸው የከፋ ስለሆነ ብዙ ሰዎች ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ይመርጣሉ፡፡ ነገር ግን እንዲስተዋላቸው ሆኖ አእንዲያመዛዝ'ሃ-ት እድል ቢሰጣቸው ዕውነትን ለመቀበል የሚችሉ ብዙዎች ናቸው፡፡GWAmh 250.1

  የእግዚአብሔርን ታላቅነት፣ የቃሉን እውነተኛነት ዝቅ ለማድረግ ስህተትን ሸፋፍነው የሚያቀርቡትን ሰዎች ጥያቄ በማተም ወንጌላዊያኖቻችን አደገኛ ስህተት ይፈጽማሉ፡፡ አነቢህ በማታሰል ስህተትን ለሕዝብ የሚያስተምሩ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል ተስሚነት ይቀንሳሉ፡፡ ያልጠረጠሩትና በእምነታቸው ለጋ የሆኑት ከወጥመዳቸው ይገባሉ፡፡GWAmh 250.2

  እውነትን በመቃወም የተካሄዱ ክርክሮች በዕውቀት ያልገፉትን ያደናግራሉ፡፡ የሰዎች መንፈሳዊ ስሜት ከኃጢዓት ጋር በመለማመድ ይደንዛል፡ ራስን መውደድ፣ ስክለመታመንና ሌሎችም የተለያዩ የኃጢዓት ዓይነቶች ሰዎች ስለ ዘለዓለም ሕይወት ያላቸውን አስተሳሰብ ያደበዝዘዋል፡፡ የእግዚአብሔር ቃልም በሙሉ አይስተዋልም፡፡ ለሰዎች ሀሰተና እውነት ጎን ለጎን ሆነው ሲቀርቡላቸው ማንኛውንም ግልጽ እውነት በመጠራጠር ለመቀበል ያመነታሉ፡፡GWAmh 250.3

  ዕውነትን ለመረዳት፤ የእግዚአብሔርን ቃል ለመቀበል፣፤ ፈቃዱን ለመፈጸም የሚፈልጉና ተግባራቸውን በታማኝነት የሚያከናውኑ ሁሉ የተሰወረው ይገለጥላቸዋል፤ የጨሰመው ይበራላቸዋል፡፡GWAmh 250.4

  የእግዚአብሔርን ቃል ለመግለጥ ክርክር የሚያስፈልግ ከሆነ ክርክሩ በትህትናና በዘዴ መካሄድ አለበት፡ በጾምና በጸሎት፣ በኑዛዜ፣ ከልብ ጌታ አንዲረዳቸው መጠየቅ ይገባል። አምላክ ክብሩን በመግለጥ እውነት ድል አድርጋ ጠሰትን በሐሰትነት ለሰዎች ለማስረዳት አንዲችሉ ከልብ መሰለፍ ይገባል፡፡GWAmh 250.5

  በራሳችሁ ችሎታ ተማምናችሁ በተሟሟቀ ክርክር ውስጥ ለመግባት አትሞክሩ፡፡ የማታመልጡ ከሆናችሁ በእግዚአብሔር በመታመን ተክከራከሩ፤ በየሱስ ትህትና፣ ገርነትና በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ተሰለፉ፡ ፡ ገርና የዋህ ከሆነው ከክርስቶስ ተማሩ፡፡GWAmh 251.1

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents