Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የወንጌል አገልጋዮች

 - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  ሕብረት በልዩነተ

  እግዚአብሔር ልዩ ልዩ ያሠራር መንገድ ስላለው ለተለያዩ ሠራተኛቹ ልዩ ልዩ ስጦታ አድሏቸዋል፡፡ አንዱ ሠራተኛ መልካም ተናጋሪ ቢሆንም ሌላው የወጣሰት ደራሲ ይሆናል አንዱ ከልቡ የሚሀልይ ጸሎት አዘውታሪ የሆነ አንደሆን ሌላው በመረዋ ድምጹ የሚዘመር ዘማሪ ይሆናል፡፡ ሌላውም ቃለ እግዚአብሔርን በግልጽ የሚያስረዳ መምህር ሊሆን ይችላል፡-: ከሠራተኛው ጋር አብር ስለሚሰራ እያንዳንዱ ስጦታ የእግዚአብሔር ኃይል ነው፡፡ እግዚአብሔር ለአንዱ የጥበብን ለሴላው ዕውቀትን፤፣ ለአንዱም ሣፃሣይማኖትን ቢሰጥም ሁሉም በአንድ አለቃ ስር ይሠራሉ። የተለያዩ ስጦታዎች የተለያየ የሥራ ዓይነት ይፈጥራሉ፡፡ ግን «በሁሉም ዘንድ የሚሠራው አንድ አምላክ ነው፡፡› ሠራተኞቹ የተሰጣቸውን ስጦታ እንዲያስተባብሩ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፡፡GWAmh 323.3

  አንዳንዶች የሴላው ሰው ስጦታ ከነርሱ በጣም የላቀ ሆኖ ስለሚሰማቸው መተባበር ያስፈራቸዋል፡፡ ነገር ግን የተለያዩ ችሎታ ያላቸው ሰዎች የተለያየ ጥረት እንደሚያስፈልጋቸው ቢገነዘቡና አንዱ ወንጌላዊ ሲያስተምራቸው የማይችለውን ሌላው ሊያስተምራቸው መቻሉን ቢገነዘቡ በተስፋ ተጽናንተው ተባብሮ ለመሥራት በተነሳሱ ስጦታዎቻቸው ወይም ችሎታዎቻቸው ምንም ያህል ቢለያዩ የሚመሩት በአንድ መንፈስ ነው፡፡ በሁሉም አነጋገርና ሥራ ደግነትና ፍቅር ይገለጣል፡፡ ሁሉም የተመደበለትን የሥራ ምድብ በታማኝነት ሲያካዚድ ክርስቶስ ተከታዮቹ አንድ እንዲሆኑ የጸለየው ጸሎት መልስ ያገኛል፡፡ ዓለምም ደቀመዛሙርቱ መሆናቸውን ያውቃል፡፡GWAmh 324.1

  በመተማመንና በመተዛዘን የእግዚአብሔር ልጆች ሊተባበሩ ይገባል፡፡ የእግዚአብሔርን ሰዎች በንግግሩ ወይም በሥራው ) የሚሞክር ሰው የአምላክ ሥራ ተቃራኒ ነው፡፡ ብጥብጥና መለያየት፣ መጠራጠርና አለመተማመን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከታየ ክርስቶስን ለማክበር አይቻልም፡፡ አገልጋዮቹ እርስ በርሳቸው ክርስቲያናዊ ፍቅር እንዲኖራቸው እግዚአብሔር ፈቃዱ ነው፡፡ እውነተኛ ሃይማኖት ልብን ከክርስቶስ ጋር ብቻ ሳይሆን ከሰዎች ጋር በማይቁረጥ ሕብረት የስተሳስራል፡፡ ክሰዎችና ከክርስቶስ ጋር መተባበር ስንማር ሥራችን ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ይመራል፡፡GWAmh 324.2

  በታላቅ ከተማዎች የሚሠሩ ሠራተኞች የተሰጣቸው የሥራ ክፍል በጥንቃቄ በማካሄድ መልካም ውጤት ለማግኘት ይጣጣሩ፡፡ በዕምነት በመናገር ሰዎችን በሚሜስቡበት መንገድ ይሥሩ፡፡ በራሳቸው አስሳሰብ በመምራት የሥራውን መስክ አያጥቡት፡፡ ካሁን ቀደም ይህ አድራጎተ ባለመፈጸሙ ለሥራችን መጎተት ምክንያት ሆ ልGWAmh 324.3

  አንድ ሰው ራሱን እንደወታደር አለቃ በመቁጠር ይህን ሥሩ፣ ይህን አትሥሩ በማለት በራሱ ፈላጭ ቆራጭነተ ሰዎችን ወደርሱ አስጠግቶ ለመዋቅጣጠር መሞከር የለበትም፡፡ በክርስቶስ ጊዜ የነበሩት ካህናትና ገዥዎች ይሠሩት የነበር ይህን ነው፤ ነገር ግን ከመንገድ የወጣ አሠራር ነበር። ዕውነቱ በልባቸው አድሮ ትምህርቱን ለመከታተል የቆረጡ ነፍሳት የክርስቶስ ሀብት አንጂ የሰው ግዥ አይደሉም፡፡ ሰዎች በእናንተ ላሳይ አንዲተማመኑ በማድረግ ከዕውቀትና ከጥበብ ምንጭ ትለዩአቸዋላችሁ፡፡ ፅምነታቸውን በአምላክ ላይ ብቻ ሲጥሉ ሲያድጉ ይችላሉ፡፡GWAmh 325.1

  ምንም ያህል በከፍተኛ ዕውቀት የተራቀቀ ቢመስለው አንድ ሰው ከመንፈስ ቅዱስ ዘንድ ካልተማረ በመንፈሣዊ ይዞታ ደንቆሮ ነው፡፡ የተደቀነበትን አደጋና አደጋውን ለመጋፈጥ ብቁ አለመሆኑን ተገንዝቦ በርሱ ሙሉ በሙሉ ያመነበትን ለመጠበቅ ለሚችለው፣ መንፈስ ቅዱስን ሊያድል ለሚችለው፤ በጥቅር መጎናጸፊያ ለሚያጎናጽና፤ ልጁን ለኃጢዓተኞች እንደላከ ስለ እግዚአብሔር ለመመስከር ሰሚያስችላቸው ለክርስቶስ መገዛት አለበት፡፡ ከልባቸው ያመነ ሁሉ በክርስትና አንድነት ይተሣሰራሉ፡፡ በእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን መለያየት አይነር፤ በአማኛዩቹም ላይ የጭቆና አስተዳደር አይፈጸምባቸው፡፡ በሚደረገውና በሚነገረው ሁሉ የክርስቶስ ገርነት ሊታይበት ይገባዋል፡፡GWAmh 325.2

  የእያንዳንዱ ዕውነተኛ ቤተ ክርስቲያን መሠረት ክርስቶስ ነው፡፡ ጥበቃውና ጥንቃቄው እንደማይለየን በማይሻረው ተስፋው አማካይነት ነግሮናል፡፡ የክርስቶስ የበላይነት ለዘለዓለም ነው፡፡ የሕይወት፣ ይበርታት፣፤ የጽድቅና የቅድስና ምንጭ እርሱ ነው፡፡ ይህን ሁሉ የሚለግሥላቸው የሸሰክማቸውን ክብደት ተገንገበው ገርነትንና ትህትናን ከርሱ ለመማር ለሚፈቅዱ ብቻ ነው፡፡GWAmh 325.3

  የማንኛውም አገልግሉት ዓላማ ክርስቶስን ከና: ከፍ ማድረግ ነው፡፡ የዕውነተኛ ሥራ ፍፃሜ ይህ ነው፡፡ ክርስቶስን በማሳየት ራሳችን በርሱ ውስጥ መስሸስግ ነው፡፡ ዋጋ ያለው መስዋዕትነት ይህ ነው፡፡GWAmh 325.4

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents