Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የወንጌል አገልጋዮች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    በሃይማኖት መጽደቅ

    ‹የክርስቶስን ጽድቅ የተቀበልነው በጸጋ እንጅ በደግነታችን አይደለም› የሚለው አስተሳሰብ በጣም የተከበረ ነው፡፡ የእግዚአብሔርና የሰው ጠላት የሆነው ሰይጣን እውነት በእውነትነቱ አንዲገለጽ አይፈልግም፡፡GWAmh 100.2

    ምክንያቱም ሰዎች እውነቱን ከተረዱ ኃይሉ አንደሚደክም ስለሚያውቅ ነው:: በሰዎች አእምሮ ውስጥ ጥርጥር፣ አለማመንና ጨለማ አንዲሰፍን ለማድረግ ከቻለ፣ የእግዚአብሔርን ልጆች በፈተናው ሊያጠምዳቸው መቻሉን ያውቃል፡፡GWAmh 100.3

    ሰዎች እግዚአብሔር በሙሉ ልብ ሊያሳምን የሚችል ሃይማኖት ሊበረታታ ይገባል፡፡ የእግዚአብሔር ሰዎች መለኮታዊ ኃይል እንደሚረዳቸው የሚያስተማምን ስሜት ሊያድርባቸው ይገባል፡፡ «ጸጋው በአምነት አድኗችኋልና ይህም የእግዚአብሔር ሥጦታ ነው አንጂ ከእናንተ አይደለም፡፡” በክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ጸጋ የዳኑ ሰዎች መልካሙን ገድል በሃይማኖት መጋደላቸውን ማቆም የለባቸውም፡፡ የክርስትና ምግባራቸውና ቃላቸው «የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢዓት ሁሉ ያነጻናል” ለማለት የሚያስችላቸው መሆን አለበት፡፡GWAmh 100.4

    የሶስተኛው መልአክ መልዕክት መንፈስና ኃይል ካለን ኦሪትንና ወንጌልን በአንድ ላይ ማስተማር አለብን:: ምክንያቱም ሁለቱም የሚደጋገፉ አንጂ የሚነቃቀፉ አይደሉም::GWAmh 100.5

    የአመፅን ልጆች አለቃቸው ሕግን እንዲረግጡ፣ በክርስቶስ አዳኝነት አንዲያላግጡ ያደርጋቸዋል፡፡ የታማኛቹን ልብ ደግሞ ከሰማይ የተላከ ኃይል ሕግን እንዲያከብሩ መድኃኒታችን መታዘዝን እንዲማሩ ያደርጋቸዋል፡፡ በእግዚአብሔር ሰዎች ሕይወት ውስጥ መለኮታዊ ኃይል ካላደረ በስተቀር የስህተት ትምህርት ደቀመዛሙርት ይሆናለ፡፡ በብዙዎቹ ሕይወት ውስጥ የክርስቶስ ጽድት አንደጨርቅ ወልቆ ይወድቃል፡፡ እምነታቸውም ፍሬቢስ ይሆናል፡፡GWAmh 100.6

    ሰሚዎች ጥብቅ ሃይማኖት ይኖራቸው ዘንድ ወወንጌላዊያን በቤተ ክርስቲያንም ውስጥ ሆነ በውጭ ክርስቶስን በግልጽ ማስተዋዋቅ አለባቸው፡፡ ሰዎቹ ክርስቶስ አዳኛቸውና ጽድቃቸው መሆኑን ማወቅ አለባቸው፡፡ ክርስቶስ የስዎች መመኪያና ተስፋ መሆኑን እንዲያምኑ ማድረግ የሰይጣን የታሰበበት ተንኮል ነው:: ምክንያቱም የክርስቶስ ደም የሚያነፃጡ፣ አምነጡበት ማመናቸጡን አንደ በእግዚአብሔር ፊት ለሚመሰክሩ ብቻ ነው፡፡GWAmh 101.1

    የቃየል መሥዋዕት እግዚአብሔርን ያስቆጣው የክርስቶስ ምሣሌነት ስለማይታይበት ነበር:: መልዕክታችን ሕግን ማስተዋወቅ ብቻ ሳይሆን የየሱስ ክርስቶስን ሃይማኖት ማዳረስ አለበት፡፡ በመንገዳችን ላይ የሚሰራው ብርሃን ሃይማኖታችን ያጐለምሰዋል። በፍርድ ቀን እንዳንኮነን የተሰጠንን ብርሃን ተከትለን ወደፊት እንራመድ፡፡ እውነቱ አንደተከሰተልን መጠን ግዳጃችንና ተግባራችን የበለጠ ተፈላጊ ሆኖ ይታየናል፡፡ ብርሃን በጨለማ ውስጥ የተደበቀውን ስህተት ገልጾ ይገሥፃል፡፡ ብርሃን የበራላቸው ሰዎች ሕይወታቸው ከብርሃን ጋር እንዲስማማ ሆኖ ይለወጣል፡፡ በጨለማ ምክንያት ኃጢዓተኝነታቸው ያልታወቀ መጥፎ ሥራዎች ሆነ ተብለው ካልተፈጸሙ በቀር ባለማወቅ አይሠሩም፡፡ ብርሃን አንዳገኙ መጠን ሰዎች መታደስ፣ መከበርና መሻሻል አለባቸው፡፡ ያለዚያ ብርሃን ከማግኘታቸው በፊት ከነበሩበት ይልቅ ግዴለሾችና ሐሳበ ግትሮች ይሆናሉ፡፡GWAmh 101.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents