Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የወንጌል አገልጋዮች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    «ራስህን የተፈተነ አድርገህ አቁም”

    ለእግዚአብሔር ሥራ ሠርተው ውጤት የሚያስገኙ ሰዎች : መምህራንና ወንጌላዊያን በጥብቅ ይፈለጋሉ፡፡ መጠነኛ የኮሌጅ ትምህርት ያላቸው ሰዎች አስገራሚ ሥራ መስራታቸው አይካድም፡፣ ግን የበለጠ ትምህርት ቢኖራቸው እንዴት የበለጠ ሥራ ባከናወኑ ነበር! ለወጣቱ ወንጌላዊ ጢሞቴዎስ ጳጡሎስ እንዲህ ይጽፍለታል፡፡ «የዕውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ፡፡› (2ጢሞ. 2፡15) ነፍሳትን ወደ ክርስቶስ የመመለስ ተግባር ጠንቃቃ ዝግጅት ያስፈልገዋል፡፡ ሳይሰለጥኑ ሥራውን ጀምሮ ይሳካልኛል ማለት ዘበት ነው፡፡ መካኒኮች፣ ጠበቆች፣ ነጋዴዎች ለእየሥራ መሥመራቸው በቂ ትምህርት ይዘው ይሰለፋሉ፡፡ ራሳቸውን በተቻለ መጠን ለሥራው ገጣሚ አድርገው ማቅረብ ደንባቸው ነው፡፡ ልብስ ሰፊዋን ሄዳችሁ ብትጠይቋት መልካም ቀሚስ ከመስፋቷ በፊት የደከመችውን ድካም ትገልጥላችኋለች፡፡ ቀያሹ (መሐንዲሱ) የመልካም ሕንፃ ንድፍ ከማዘጋጀቱ በፊት ያጠፋውን ጊዜ አይረሳውም፡፡ ማንኛውም የሥራ መሥመር ይኸው ነው::GWAmh 56.3

    የእግዚአብሔር ሠራተኞች ከማንኛውም የሥራ መስክ ይልቅ ላቅ (ብልጫ) ላለው ተግባራቸው ያነሰ ትጋት ማሳየት ይገባቸዋል አንዴ? ለሰዎች ዘለዓለማዊ ጥቅም የሚያስገኝ ትምህርት ለማስተማር ጥናት፣ ሰብዓዊ ርህራሄ፤ በጥንቃቄ የታሰበበት ፅቅድ ያስፈልጋል፡፡GWAmh 56.4

    የእግዚአብሔር ተባባሪ ሠራተኛች አብዛኛዎቹ የሥራቸው ትርጉም አልተስተዋላቸውም፡፡ የተፈለገውን ያህል ዝግጅት ሳይፈጽሙ ሥራውን በመጀመር የአምላክን ክብር ይቀንሳሉ፡፡ አንዳንዶቹ በዓለማዊ ዘዴ ከፍተኛ ዝግጅት ያገኙ እየመሰላቸው ክርስቶስ የሚፈልግባቸውን ትሁት መንገድ ችላ ይላሉ:: ወንጌላዊያን መሪና መካሪ ስለሆኑ ሰዎች ምሣሌነታቸውን እንደሚክተሉ መገንዘብ አለባቸው፡፡GWAmh 57.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents