Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የወንጌል አገልጋዮች

 - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  ወንጌላዊና ተግባረ-ዕድ (የእጅ ሥራ)

  ጳውሎስ ለተመለሱት አማኞች የእግዚአብሔርን ሥራ ለመደገፍ የገንዘብ መዋጮ ማስፈለጉን ገልጦ አስተማራቸው፡፡ «ለሥራው ዋጋም መክፈል እንደሚገባው” ተናግሯል፡፡ ግን በእየቦታው እአየተዘዋወረ ሲያስተምር የራሱን ኑሮ ለማካሄድ የአጅ ሥራ ይሠራ ነበር፡፡GWAmh 148.4

  በተሰሎንቄ ጳውሎስ ከማስተማሩ በላይ ለዕለት ጉርሱ የአጅ ሥራ መሥራቱን አናነባለን ለቤተ ክርስቲያን አባሎች እንዲህ ሲል ይጽፍላቸዋል፡፡ «የክርስቶስ ሐዋርያት ስንሆን ልንክዳችሁ ስንችል ከእናንተ ቢሆን ወይም ከሌሎች ክብርን ከሰው አልፈለግንም፡፡ ወንድሞቼ ሆይ ድካማችንና ጥረታችን ትዝ ይላችኋልና፤ ከእናንተ በአንዱ አንኳ አንዳንከብድበት ሌሊትና ቀን አየሠራን፣ የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ ሰበክን:› በሁለተኛው መልዕክቱ ደግሞ እንዲህ ይላቸዋል፡፡ «ከእናንተ ዘንድ በአንዱም እንኳን አንዳንከብድበት ሌሊትና ቀን በድካምና በጥረት አየሠራን እንኖር ነበር አንጂ ከማንም እንጀራ አንዲያው አልበላንም፡፡ ይህም እኛን ልትመስሉ ራሳችንን እንደ ምሣሌ እንሰጣችሁ ዘንድ ነበር አንጂ ለሥልጣን ስለሆንን አይደለም፡፡›»GWAmh 148.5

  ጳውሎስ ወደ ቆሮንቶስ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሄድ ሰአንግድነት የሄደባቸው መስሏቸው ጠረጠሩት፡፡ በባህር ዳርቻ የሚኖሩት ግሪኮች ብልጥ ነጋዴዎች ነበሩ፡፡ በአንድ የሥራ መስመር በሚገባ ሠልጥነው ገንዘብ ማትረፍ ከፍተኛ ዓላማቸው ነበር፡፡ በማንኛውም መንገድ ገንዘብ ማትረፍ መቻል ብልጥነት ጳውሎስ ጠባያቸውን ያውቅ ነበርና ወንጌልን የሚያስተምር ገንዘብ ለመሰብሰብ ነው ብለው አንዲጠረጥሩ አልፈለገም፡፡ ከቀሮንቶስ አማኞች ገንዘብ የመቀበል መብት ሲኖረው ሥራው በአጉል ጥርጣሬ እንዲበላሽ ስላልፈለገ ገንዘብ አልተቀበለም፡፡ የመልዕክቱ ኃይል አንዳይደክም አለመግባባት የሚያመጡትን ምክንያቶች ሁሉ ለማስወገድ ይጣጣር ነበር፡፡GWAmh 149.1

  ቆሮንቶስ ሲደርስ እርሱ የሚሠራውን የአጅ ሥራ መሥራት የሚችሉ አኪላስና ጵርስኪላ የተባሉ ባልና ሚስት ከሮማ ተባብረው ስለመጡ አገኛቸው፡፡ ቀላውዲዎስ አይሁዶች በሙሉ ሮምን እንዲለቁ ባወጣው አዋጅ ምክንያት ተባርረው በቆሮንቶስ የድንኳን ሥራ ሞያ አቋቁመው ይኖሩ ጳውሎስ ስሰአእነርሱ በቂ ምርምር ካደረገ በኋላ ከማያምኑ ጋር ተቀላቅለው አምነታቸወጦ- አንዳይላሳ የሚፈልጉ መሆናቸውን ተገንዝቦ አብሮ መኖር ጀመረ፡፡ «በየሰንበቱ በመቅደስ አይሁዶችንና ግሪካዊያንን ያስተምር ነበር፡፡›»GWAmh 149.2

  በኤፌሶን ለሦስት ዓመታት ባስተማረበት ጊዜ አገልግሉቱን ቀጥሏል፡፡ ሁለተኛውን የወንጌል ጉዞውን ሲጨርስ አኪሳስና ጵርስኪላ ኤፌሶን ጋር ተጓዙ::GWAmh 149.3

  የወንጌልን ሥራ ያጓድላል በማለት የጳውሎስን የአጅ ሥራ የነቀፉ ነበሩ፡፡ ጳውሎስ ታላቁ ሐዋርያ በወንጌል ሥራው ላይ የአጅ ሥራ ለምን ጨመረ? ለሥራው ደሞዝ መቀበል አይችልም ኖራልን?” ቢጻፍ ዝናን ለማያስገኝ የድንኳን ሥራ ለምን ጊዜ ወሰነለት? ጳውሎስ ግን በእጅ ሥራ ያሳለፈውን ጊዜ አንደባከነ አልቆጠረውም፡፡ ከአኪላስ ጋር ሲሠራ ሳለ ከታላቁ መምህር ጋር ግንኙነቱን አያቋርጥም ነበር፡፡ በተቻለው መጠን ዕርዳታ ለሚያስፈልገው ዕርዳታ ይሰጣል፡፡ አእምሮው መንፈሣዊ ነገርን ከማሰላሰል አያርፍም፡፡ አበረውት ለሚሠሩት መንፈሳዊ ትምህርት ያስተምራቸው በሠራተኛነቱና በትጋቱ ምሣሌነትን ለሌሎች አሳየ። በሥራው የማይቀልድ ትጉ ሠራተኛ ነበር፡፡ «ጌታን ለማገልገል በመንፈስ የተቃጠለ” (ሮሜ 12፡11) ነበር በሥራው ሰዓት፣ በሌላ ጊዜ ሊያገኛቸው የማይችላቸውን ሰዎች ያስተምር: በዕለት ተግባሩ ጌታ መከበር አንዳለበት ይገልጥ ነበር፡፡ በሥራ ተይዘው የነበሩት አጆቹ ወንጌላዊነቱ ከሚፈቅድለት ተግባር ሌላ አልነኩም ነበር፡፡GWAmh 149.4

  ወንጌላዊያን ሥራ በዛብን አያሉ የሚያጉረመረሙ ከሆኑ እስቲ የጳውሎስን የሥራ ቦታ በመንፈስ ይጎብኙ፡፡ ያ የተክበረ ሐዋርያ የዕለት ጉርሱን የዓመት ልብሱን ለማግኘት ሲሰራ ሲተረትር፣ ሲቀድና ሲሰፋ ይመልከቱ፡፡GWAmh 150.1

  ሥራ በረከት አንጂ መርገም አይደለም፡፡ የስንፍና ሀሳብ አምነትን ከማጉደፉም በላይ መንፈስ ቅዱስን ያሳዝናል፡፡ የታቆረ ውኃ ይስታል፤ የሚወርድ ወንዝ ወይም የሚፈልቅ ምንጭ ግን ለአካባቢው በረከት ከመሆኑም በላይ ለዓይን ያስጎመጃል፡፡ ጳውሎስ የጉልበት ሥራን የሚንቁ ሰዎች አንደሚደክሙ ያውቅ ነበር፡፡ ወጣት ወንጌላዊያን አካላቸውን በሥራ ቢያፍታቱት አስቸጋሪውን የወንጌል ሥራ ሲጋጠሙት ብርታት አንደሚያገኙ ጳውሎስ ሊያስተምራቸው ፈለገ፡፡ መላ የአካል ክፍሉቹን በሥራ ባያፍታታቸው ኖሮ ለሥራው ኃይል እንደሚያንሰው ያውቅ ነበር፡፡GWAmh 150.2

  ለወንጌል ሥራ የሚሰለፉ ሰዎች ሁሉ መሉ የገንዘብ ፋላጎታቸውን በቤተክርስቲያን ትክሻ ላይ መጣል የለባቸውም፡፡ እንዲህ ከሆነ የወንጌላዊው ልዩ ልዩ ችሎታዎች ወድቀው ይቀራሉ፡፡ በበኩሉ ያለውን ብርቱ ጥረትም ያቆማል፡፡ የወንጌልን ሥራ ለማስፋፋት የተመደበው ገንዘብ ደሞዝ ለማግኘት ብቻ በሚሰብኩና በመንፈላሰስ ለመኖር በሚሉ ሰዎች ማለቅ የለበትም፡፡GWAmh 150.3

  የወንጌል አገልጋይ ለመሆን የሚሹ ወጣቶች ጳውሎስ በቆሮንቶስ፣ በተሰሎንቄ፤ በኤፌሶንና በሌሎች ቦታዎች ካከናወነው አገልግሎት ቋሚ ትምህርት ሊያገኙ ይችላሉ፡፡ ጎበዝ ተናጋሪ ቢሆንና የተለየ ሥራ ለመፈጸም በእግዚአብሔር ቢመረጥም ጳውሎስ የአጅ ሥራን ችላ አላለም፡፡ ለሚወዳቸውም መስዋዕት ለመሆን ወደኋላ አላለም፡፡ ለቆሮንቶስ ሰዎች ሲጽፍ «እስከዚህ ሰዓት ድረስ እንራባለን፤ እንጠማለን፣ እንራቆታለን፣ ሲያሳድዱን አንታገሣለን፤ በገዛ እጃችን እየሠራን እንነሣለን፤ ሲሰድቡን አንመርቃለን፣ ሲያሳድዱን እንታገሣለን፤ ክፉ ሲናገሩን እንማልዳለን፡፡» (በኛ ቆሮ. ቁ.12GWAmh 150.4

  ክታላላቅ መምህራን አንዱ የሆነው ጳውሎስ እጀግ በጣም የተክበረውንና እጅግ በጣም የተዋረደውን ሥራ በአንድ ላይ አጣምሮ አከናወነ፡፡ ጌታን ሲያገለግል አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የእጀ ሥራ ይሰራ ነበር፡፡ የሆነ ሆኖ የወንጌልን ተቃዋሚዎች ለመከራከር ወይም አዲስ የወንጌል ሥራ ለመቋቋም ምቹ ጊዜ ሲያጋጥመው የአጅ ሥራውን ጣል እርግፍ አድርጎት ይሄዳል። ትጋቱና ሠራተኛነቱ ለሰነፎችና ምቾትን ለሚሹ ተግሣጾች ናቸው፡፡GWAmh 151.1

  አንዳንድ ወንጌላዊያን ሁሉንም የአካል ክፍሉቻቸውን አኩል ስለማያሠራቸው ሥራ የበዛባቸው የአካል ክፍሎች ሲያልቁ የማይሠሩት የአካል ክፍሎች ከመቀመጣቸው የተነሳ ይዝጋሉ፡፡ የተሟላ ጤና ለማግኘትና በቂ ብርታት ለመቀበል አእምሮም ሆነ አካል ተገቢ ሥራውን በትክክል ማካሄድ አለበት፡፡ በሕይዎት ያለው ነገር የአካላት ክፍሎቹ በሙሉ ሥራ ተሰጥቷቸዋል፡፡ በተሽከርካሪው ውስጥ ያለው እያንዳንዱ መንኮራኩር የተመደበለትን ሥራ መሥራት አለበት፡፡ ሁሉም ክፍሎች እርስ በርሳቸው ይደጋገፋሉ፡፡ አኩል አንዲያድጉ ከተፈለገ ሁሉም መስነፍ የለባቸውም፡፡GWAmh 151.2

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents