Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የወንጌል አገልጋዮች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የማሰልጠኛ መሣሪያዎች

    ለልዩ ዝግጅት ፈጣን ዘዴ ያስፈልጋል፡፡ በየንዑስ መሥሪያ ቤቶቻችን ለሥራው ለተሰለፉ ሰዎች፣ በደንብ የተደራጀ ማሠልጠኛ መኖሩ በጣም ጠቃሜ ነው:: በታላላቅ ከተማዎች መልካም ማሰልጠኛዎች አሉ፡፡ ግን በቂ አይደሉም::GWAmh 46.6

    በአገርም ሆነ በውጭ አገር ለሚሰጠው አገልግሎት ሠራተኞችን በአጥጋቢ ሁኔታ ለማቅረብ በቂ ማሰልጠኛዎች ያስፈልጋለ፡፡ ወንጌላዊያን ወጣቶችን ከማሰልጠንና ከማስተማር ወደኋላ ማለት የለባቸውም፡፡ በአንድ ተፈላጊ ቦታ እውነትን ለማስተዋወቅ ጥረት ሲደረግ የቆዩ ወንጌላዊያን አዲሶቹን ተባባሪዎቻቸውን በደንብ ለማሰልጠን ብቁና ንቁ ሆነው ቢገኙ ይጠቅማል፡፡ መጽሐፍ ሰጭዎችና የቤት ለቤት ወንጌላዊያን ጠቃሚነታቸው መናቅ የለበትም፡፡GWAmh 47.1

    ልዩ የወንጌል ጥረት የሚያደርጉ ሠራተኛቻችን አብዛኛውን ጊዜ ስብከት ብቻ በመስጠታቸው ይሳሳታሉ፡፡ ስብከቱ ቀነስ ብሎ ማስተማሩ መብዛት አለበት፡፡ ሕዝብን ማስተማር፣ ወጣቶችንም እንዴት አንደሚሠሩ በደንብ ማስተማር ይጠቅማል፡፡ ወንጌላዊያን መጽሐፍ ቅዱስን ሲያስተምሩ ውጤት እንዲያገኙ በታሰበበት ዘዴ ማስተማር አይርሱ፡፡ አዲስ አማኛችና ለጋ ሠራተኞች ምክርና ማጽናናት ቢያገኙ አይጠሉም፡፡GWAmh 47.2

    አንድ ሰው በሥራው መልካም ውጤት ለማግኘት ቢፈልግ ጸሎት ያዘወትር:: ወንጌላዊ የጦር አለቃውን ድምዕ መለየት አንዲችል በእርሱና በአምላኩ መካከል ያለው ግንኙነት ግልጽና ነፃ መሆን አለበት:: መጽሐፍ ቅዱስ በትጋት መጠናት ይገባዋል፡፡ የጌታ የቃሉ እውነት ወርቅ በላይ ፈጦ አይገኝም:: በብዙው መማስና መቀፈር አለበት::GWAmh 47.3

    ቅዱስ ጥናት አእምሮን በእውቀት ማበልጸግ ብቻ ሳይሆን የአእምሮ ብስለታችን አበርትቶ ስለዘለዓለማዊ ኖሮ ያለንን አስተያየት ያሰፋልናል፡፡ ሕይወታችን በጽድቅ ፋና የተመራ እንደሆን ሳናውቀው የጨዋና የደግ ሰው ጠባይ ይኖረናል፡፡GWAmh 47.4

    ለጌታ ሥራ ብቁ ሆኖ ለመገኘት የሚፈልግ ሰው ከሰይጣን ጉርበትና አርቆ መለኮታዊ ዕውቀት አንዲያገኝ ከሚያስችለው ማህበር ጋር መቀላቀል አለበት፡፡ እግዚአብሔር ከተወደደው ደቀሙዝሙር ከዮሐንስ ጋር ለመገናኘት ሲፈልግ ከዓለም ምስቅልቅል ተለይቶ በጳጥሞስ ደሴት ብቸኛ እንዲሆን አደረገው፡፡ ዮሐንስ መጥምቁ የጌታን መንገድ ለማዘጋጀት የሚረዳውን መልዕክት ለመቀበል ብቻውን በበረሃ ኖረ፡፡GWAmh 47.5

    አእምሮአችንን ከእግዚአብሔር ሥራ የሚያርቅብንን ማንኛውንም አንቅፋት መሸሸ አለብን፡፡ በተለይ በዕምነታቸው ለጋ የሆኑና የክርስትና ልምዳቸው ያልዳበረ በራሳቸው በመተማመን ወደፈተና መገሥገሥ አይበጃቸውም፡፡ በትክክል የሚራመዱት የሱስን ካጠገባቸው የማይለዩት ብቻ ናቸው:: እግዚአብሔር የሚፈልግባቸውን ዕድገት ሊያገኙ ይችላሉ፡፡GWAmh 47.6

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents