Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የወንጌል አገልጋዮች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የጠባቂው ሥራ

    እውነተኛ ጠባቂ የበጎቹን ደህንነት፣ አመጋገብ፣ መሠማሪያ ይመለከታል፡፡ በጥበብ ይሠራል፡፡ ለእያንዳንዱ በግ ይጠነቀቃል፡፡ በተለይ ችግር የደረሰበትን አይረሳውም፡፡ «የሰው ልጅ ሊያገለግል፤ ነፍሱንም ለበጎች ቤዛ ሊሰጥ አንጂ አንዲያገለግሉት አልመጣም፡፡› (ማቴ 20፡28)GWAmh 118.1

    «እውነት አላችኋለሁ ባሪያ ከጌታው፤ መልአክተኛም ከላከው አይበልጥም፡፡ አንደሚገባ ነገር አልቆጠረም፤ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰው ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ: (ዮሐ. 13፡16፤ ፊለ.. 2፡ 7)፡፡ «እኛም ኃይለኞች የሆንን የደካሞችን ድካም እንሸከም፡፡ ራሳችንም ደስ አንዳናሰኝ ይገባናል፡፡ እያንዳንዳችን እንድናንጸው እርሱን ለመጥቀም ባልንጀራችንን ደስ እናሰኘው፡፡ ክርስቶስ ራሱን ደስ አላሰኘምና፤ ነገር ግን አንተን የነቀፉበት ነቀፋ ወደቀብኝ እንደተባለው ሆነበት፡፡› (ሮሜ. 15፡1-3)GWAmh 118.2

    እርዳታቸውን ወደሚሹት ባለመቅረባቸው ብዙ ሠራተኞች አይሳካላቸውም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ መሪነት እውነተኛውን ነገር መፈለግ አለበት፡፡ እውነቱን የሚመራመሩትን የትምህርት ቤት ተማሪዎችን ቀጥሮ በጥንቃቄ መምራት አለበት፡፡ ብዙ ሰዎች እውነት ነው ብለው ያመኑትን ሐሰተኛ ነገር ለመርሳት ጊዜ ይወስድባቸዋል፡፡ ያመኑበት የነበረው ስህተትነቱ ሲገለጥላቸው ግራ ይገባቸዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ከፍተኛ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል፡፡ በጥንቃቄ ማስተማር፣፤ ከእነርሱ ጋርና ለእነርሱ መጸለይ ተገቢ ነው:: በትህትና ማበረታታት፣ በገርነት መምራት የጠባቂው ተግባር ነው፡፡GWAmh 118.3

    ነፍሳትን ለማዳን የክርስቶስ ተባባሪ መሆን ታላቅ እድል ነው: ክርስቶስ በትዕግሥትና ራሱን በመካድ የወደቀውን ሰው ከሚደርስበት የኃጢአት አዘቅት ዋጋ ለማዳን ጥረት አደረገ:: ቃሉን የሚያስተምሩ ደቀ- መዛሙርቱ የመሪያቸውን አራአያነት ቢከተሉ ይጠቅማቸዋል፡፡GWAmh 118.4

    በአዲስ የሥራ ቦታ፣ ብዛትና ጸሎት መተባበራቸው በጣም ተፈላጊ ነው:: በቃል የሚስተምሩ ብቻ ሳይሆኑ በተግባራቸው እውነትን ለሌሎች የሚገልጡ ሰዎች ያስፈልጋሉ:: የክርስቶስ አገልጋይ መሆን የሚያኮራቸውና ተሸከሙ ያላቸውን መስቀል መሸከም የተማሩ ሰዎች በብዛት ይፈለጋሉ፡፡GWAmh 118.5

    አንድ ቄስ (ወንጌላዊ) የሚያገለግላቸውን ሰዎች በቅርብ ማወቁ ይጠቅመዋል፡፡ በቀላሉ ሲያስተምራቸው አንዲችል አስተሳሰባቸውን ማወቅ አለበት፡፡ ያን ጊዜ ተፈጥሮንና ሰዎችን በቅርብ ለሚከታተሉ ሰዎች የሚሰጠው የማስተዋል ጸጋ ይሰጠዋል፡፡GWAmh 119.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents