Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የወንጌል አገልጋዮች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ወጣት ወንጌላዊያን ከነባር ወንጌላዊያን ጋር ተባብረው ሲሠሩ

    በቂ ልምድ ያገኙ ዘንድ ወጣቶች ከቆዩ ወንጌላዊያን ጋር መቀናጀት (መጐዳኘት) አለባቸው፡፡ ነፍሳትን በተሳካ ዘዴ እንዴት ሊመልሱ አንደሚችሉ ለማሰልጠን ልምድ ያላቸው ወንጌላዊያን፣ ያልለመዱትን ወደሰፊው መከር ሊወስዱአቸው ይገባል፡፡GWAmh 62.1

    ወንጌላዊያኑ ወጣቶችን ሲያለማምዱ በፍቅርና በትዕግሥት መሆን አለበት:: ወጣቶቹ ወንጌላዊያኑ በሥራ ዘመናቸው ዕውቀት አንዳተረፉ ለመገንዘብ በአክብሮት መማር ይገባቸዋል፡፡ ለቤተክርስቲያን መሪዎችና መካሪዎች ጴጥሮስ የሚከተለውን ምክር ለግሷል፡፡GWAmh 62.2

    «በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፡፡ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ አንጂ በግድ ሳይሆን በበጐ ፈቃድ አንጂ መጥፎን ረብ በመመኘት ሳይሆን ጐብኙት፣ ለመንጋውም ምሣሌ ሁኑ አንጂ ማህበሮቻችሁን በኃይል አትገስጹ፡ የአረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብር አክሊል ትቀበላላችሁ፡፡ እንዲሁም ወጣቶች ሆይ፣ ለሽማግሌዎች ተገዙ፣ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትህትናን አንደልብስ ታጠቁ፡፡ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፣ ለትሁታን ግን ፀጋን ይሰጣል»፡፡ (፲ኛ ጴጥ. 5 ፡ 2-5)GWAmh 62.3

    ሸማግሌዎች በእግዚአብሔር ትዕዛዝ አየተመሩ መልካም መምህራን ይሁኑ:: ወጣቶችም፣ ሽማግሌዎች ስላስተማሯቸው ከመብት ቆጥረውት የተቻላቸውን ያህል ይከታተሉ፡፡ ኤልያስ በነቢያት ትምህርት ቤቶች የአሥራኤልን ወጣቶች አንዳስተማረ ሁሉ ዛሬም አንዲሁ መሆን ይገባዋል፡፡ ሁሉን ነገር በዝርዝር ማስተማር አይቻል ይሆናል፡፡ ግን እውነተኛው አምላክ ማመላከት ይቻላል፡፡GWAmh 62.4

    ጳውሎስ ወጣቶችን ማስተማርን ታላቅ ግምት ሰጥቶታል፡፡ ከበርናባስ ጋር የወንጌል ስርጭት አድርገው ሲመለሱ ያቋቋሟቸውን ቤተ ክርስቲያናት ሲጐበኙ ለሥራው የሚያስለጥኗቸው ወጣቶች ይፈልጉ ነበር፡፡ ለወንጌል ሥራ ወጣቶችን ማሰልጠን ጳውሎስ ከሥራው አንዱ ክፍል አድርጐት ለወደፊቱ ኃላፊነትን ለመሸከም ትከሻቸው ይበርታ ዘንድ ወንጌልን ሲያስተምር ይዚቸው ይዞር ሲለዩት አለመርሳቱን ለማረጋገጥ መሞከሩ ለቲቶስና ለጢሞቴዎስ የጻፋቸው ደብዳቤዎች ማስረጃዎች ናቸው፡፡ «ብዙ ሰዎች የመሰከሩለትን ከእኔም የሰማኸውን ሌሎችን ደግሞ ሊያስተምሩ ለሚችሱ ለታመኑ ሰዎች አደራ ስጥ፡፡› (2 ጢሞ. 2:2)GWAmh 62.5

    ይህ የጳውሎስ አድራጐት ወንጌላዊያን ታላቅ አራአያነት አለው፡፡ ወንጌላዊያን ሲሳካላቸው የሚችል ኃላፊነትን ሁሉ ራሳቸው በመሸከም ሳይሆን ወጣቶችን አሰልጥነው ትከሻቸው በኋላፊነት አንዲበረታ ሲያደርጉ ነው፡፡ በሥራው ልምድ ያላቸው ሰዎች ወጣቶችን አንዲያሰለጥኑ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፡፡GWAmh 63.1

    የሚሰለጥነው ወጣት አሠልጣኙን መሉ በሙሉ ለመምሰል መጣር የለበትም፡፡ የራሱ የሆነ መለዮ ሊኖረው ይገባል፡፡ የሚሰጠውን ትክክለኛ ትምህርት በራሱ አስተሳሰብ ሲሠራበት ይገባል አንጂ አንደ መኪና የተነገረውን በሙሉ መገልበጥ የለበትም፡፡ ከታላቁ መምህር ከክርስቶስ የመማር መብት አንዳለው አይዘንጋ፡፡ አስተማሪው እግዚአብሔር ከሚለው ጋር የማይዋሃድ አስተሳሰብ ሊያስተምረው ቢሞክር በትህትና ለበላይ ባለሥልጣን ያመልክት፡፡GWAmh 63.2

    በዚህ አኳኋን ተማሪው ሰመምህሩ በረከት ሊሆን ይችላል፡፡ ተግባሩን በትህትና ማከናወን አለበት፡፡ ማንም ቢያሳስተን ስንሳሳት እግዚአብሔር አልተሳሳታችሁም አይለንም፡፡GWAmh 63.3

    ወጣቶች ክፉና በጐን በዘመን ብዛት ከለዩ ወንጌላዊያን በረከት ማግኘት አለባቸው፡፡ ከእግዚአብሔር ሰዎች መካከል ችግር ቢነሳ እነዚህ ቀደምት ሰዎች የዱሮ ታሪክ በማውሳት ሕዝቡን ሊያጽናኑ ይችላሉ፡፡ ሠይጣን ያለፈውን ታሪክና ክንውንነት ሲያፈራርስ በሚፈልግበት በአሁኑ ክዘመን በዕድሜ ጠና ያሉ፣ በዕምነት የጠነከሩ ቀደምት ሰዎች በምክራቸው ማበረታታት ይገባቸዋል፡፡GWAmh 63.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents