Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የወንጌል አገልጋዮች

 - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  የከተማ ሚሲዮናዊ ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት

  ለጉባዔ ከሚሰጠው ተኩረት የማያንስ አገልግሎት ቤት ሰቤት ለሚሰጠው ትምህርት መሰጠት አስፈላጊ ነው። በታላላቅ ከተማዎች ውስጥ በጉባዔ ስብሰባ የማይገኙ የተለዩ ቤተሰቦች ይኖራሉ፡፡GWAmh 238.4

  ጠባቂ የጠፋውን በጉን እንደሚፈልግ ሁሉ እነዚህ ሰዎችም ይፈለጉ፡፡ ለእነርሱ ሲባል ከባድ የግል ጥረት መካሄድ ሊኖርበት ነው፡፡ የግል አገልግሉት ችላ ከተባለ ቢሠራባቸው ኖሮ ሥራውን ሊያራምዱ ይሻሉ የነበረ ብዙ አጋጣሚዎች ያልፋሉ፡፡GWAmh 239.1

  በጉባዔ በሚደረገው ንግግር የሰዎች የማወቅ ፍላጎት ይነሳሳል፡፡ እነዚህ ሰዎች በግል ቢረዱ ውጤቱ በበለጠ ያምራል፡፡ ዕውነትን ሰመርዳት የሚፈልጉ ሰዎች መጽሐፍዋ ቅዱስን ጠንቅቀው እንዲመረምሩ መነገር ይገባቸዋል፡፡ ጠንካራ መሠረት እንዲይዙ ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል፡፡ በእንዲህ ያለ የውሳኔ ጊዜ ሳሉ መጽሐፍ ቅዱስን በደንብ የሚያውቁ ሰዎች ቀርበው ከእግዚአብሔር ቃል በረከት ቢያካፍሏቸው ታላቅ ጥቀም ያገኛሉ፡፡GWAmh 239.2

  ለሠራተኞች ማሠልጠኛ ቢቋቋም በከተማ የሚደረገው ስብሰባ ውጤቱ ሲያምር ይችላል፡፡ ከዚህ የማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ጋር በሥራው ላይ ልምድ ያላቸው ልባቸውን በሙሉ ያስረከቡ ሰዎች ስብሰባ ይምሩ፡፡ አዲስ አማኛች ሲገኙ እነዚያ የሥራው መሪ የሆነት በጸሉትና በማበረታታት ያወቁትን ዕውነት እንዴት ከሥራ ላይ ሊያውሉት እንደሚችሉ ይንገራቸው፡፡ እንዲህ ያለ መልዕክት በጥበብና በብልፃት ቢካሄድ በጨለማ ውስጥ የሚያበራ መብራት ይሆናል፡፡GWAmh 239.3

  በከተማ ውስጥ የሜካሄሄድ የሚሲዮናዊነት ሥራ ዘላቂ ትምህርት ለማስተማር ጠቃሜ ነው፡፡ ነገር ግን የሚገኘው ውጤት ሁሉ ለእግዚአብሔር ክብር መሆኑን ኃላፊዎቹ ጠንቅቀው ማወቅ አለባቸው፡፡GWAmh 239.4

  በዚህ መልዕክት ጊዜ ወጣቶች ለጌታቸው አገልግሎት ለመስጠት ይማራሉ፡፡ ነገር ግን ከልባቸው ካልተሰለፉበትና ራሳቸውን ቀድሰው ካልሰጡ እነርሱን ለማሠልጠን የሚደረገው ጥረት በሙሉ ውድቅ ይሆናል፡፡ የእግዚአብሔርን ኃያልነት፣ የስራውን ክቡርነት አምነውበት ካልተሰለፉ በቀር ክንውንነት አያገኙም፡፡ በዕድሜ ለገፉ ሠራተኞችም ቢሆን ያው ነው። በእውነት ካልተቀደሱ በቀር ለበታቾቻቸው፣ የሚያሳድግ፣ የሚያጨምትና የሚያሻሸል ትምህርት ማካፈል አይችሉም፡፡ ሥራችን ከግዴለሽነት፣ ከአለመሙመቸትና ከመሳሰሉ መጥፎ ድርጊቶች ይራቅ፡፡ ከሥራችን ጋር ግንኙነት ያለው ነገር ሁሉ እንከን መሆን ይገባዋል፡፡ በሥራው ውስጥ ተካፋይ የሚሆን ሁሉ ለአማኞች ምሣሌነት ይኑረው፡፡ በርክት ላሉ ሰዓታት ከጌታ ጋር በግል መነጋገር ያሻል፡፡ ድል ለመቀዳጀት የሚቻለጡ አንዲያ ሲሆን ብቻ ነው፡፡ እያንዳንዱ የወንጌል ጥረት ነፍሳትን በፈተና እንዳይሸነፉ በሚገባ ለማጠንከር የታቀደ ይሁን፡ ያልተቀደሰው ፍላጎት ሁሉ በእግዚአብሔር ፀጋ አማካይነት ከቁጥጥር ስር መዋል ይገባዋል፡፡GWAmh 239.5

  በአንድ የሥራ ከፍላችን ሰኃላፊነት የታጨ ደህና ግምት የተሰጠው ሰው ታማኝነቱን ጥሎ ራሱን ለሰይጣን አሳልፎ ሰጥቶ የኃጢዓት መሣሪያ ሆኖ ቢገኝ ከሁሉ የከፋ ከሀዲ ማለት እርሱ ነው፡፡ ከእንዲህ ያለ የረከሰ ሰው ዘንድ ወጣቶች የጥፋት አራአያነት ሰምተው ይቀራሉ፡፡GWAmh 240.1

  የሚሲዮን ጣቢያ ኃላፊዎች የሆኑ ወንዶችና ሴቶች ራሳቸውን በንጽሕና ለመጠበቅና ወጣቶቸን በሚገባ ለመምራት አንዲችሉ ከአግዚአብሔኤር ጋር የቅርብ ግንኙነት ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ያን ጊዜ የወጣቶች ጠባይ ሳይበላሽ ያድጋል፡፡ የሚሰጡት ትምህርቶች የወጣቱን አስተሳሰብ በክርስትና መንገድ የሚያንጹ አነቃቂና አበረታች ይሁትነ፡፡ «በእርሱ ይህን ተስፋ የሚያደርግ ሁሉ እርሱ ንጹህ አንደሆነ ራሱን ያነዛል፡፡» (1ዮሐ. 3፡3) አምላክ በአምላክነቱ መጠን ንጹህ እንደሆነ ሰውም በሰብዓዊነቱ መጠን ንጽህ ሊሆን ይችላል፡፡ የሚችለውም ክርስቶስን የተስፋው ክብር ያደረገው እንደሆነ ነው፡፡ እንዲህ ከሆነ የክርስቶስን ጠባይ ቀስሞ የእርሱን ሕይወት ያሳያል፡፡GWAmh 240.2

  አንድ የሚሲዮን ጣቢያ በከተማ ሲቋቋም ሰዎች መደሰታቸውን በጠቃሚ ሥራ መግለጥ የሚሲዮን ሠራተኞች ባለ ኃይሳቸው የመስዋዕትነት ሥራ ይሠራሉ፡፡ ነገር ግን ብዙም አይክፈላቸው፡፡ በከተማ የሚካሄድ የወንጌል ሥራ ቀላል ወይም ገንዘብ ለማትረፍ የተቋቋመ አይምሰላቸው፡፡ የሚሲዮን ሥራ የሚጀመረጡ አብዛኛውን ጊዜ ገንዘብ በአጃቸው በሌለ እግዚአብሔር ለወደፊቱ ይሰጠናል ብለው በሚያምኑ ሰዎች ነው፡፡GWAmh 240.3

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents