Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የአድቬንቲስት ቤት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ክፍል ፲፩—ልጆች - ታናናሾቹ ሸሪኮች

    ምዕራፍ አርባ ስምንት—ሰማይ ለልጆች የሚሰጠው ግምት

    ልጆች በክርስቶስ ደም የተገዙ ናቸው፦ ክርስቶስ ለልጆቻችሁ ትልቅ ዋጋ በመስጠት ሞቶላቸዋል። በደሙ እንደተገዙ አድርጋችሁ እዩዋቸው። በትዕግሥትና በጽናት ለራሱ ለክርስቶስ አሠልጥኗቸው። በፍቅርና በታጋሽነት ሥርዓት አስይዟቸው። እንደዚህ በምታደርጉበት ጊዜ ለእናንተ የደስታ ዘውድ ለዓለም ደግሞ የሚንቦገቦጉ ብርሃን ይሆናሉ። 1Signs of the Times, April 3, 1901.AHAmh 197.1

    እግዚአብሔርን የሚወድና የሚፈራ ከሁሉም በዕድሜ የሚያንስ ልጅ፣ በእርሱ [በአምላክ] እይታ እጅግ ከተማረውና በተሰጥኦው ተወዳዳሪ ከሌለው ሆኖም ታላቁን መዳን ቸል ካለ ሊቅ የበለጠ ነው። ልባቸውንና ሕይወታቸውን ለእግዚአብሔር የቀደሱ ወጣቶች፣ ከሁሉም ዕውቀትና ጥበብ ምንጭ ከሆነው ጌታ ጋር እራሳቸውን ያስተሳሰሩ ናቸው። 2Messages to Young People, p. 329.AHAmh 197.2

    መንግሥተ-ሰማያት እንደነርሱ ላሉት ናትና፦ በክርስቶስ የሚያምን የታናሹ ሕፃን ነፍስ በእርሱ [በእግዚአብሔር] እይታ ዙፋኑን እንደ ከበቡት መላእክት ነፍስ የከበረ ነው። ወደ ክርስቶስ ሊወሰዱና ለክርስቶስ ሊሠለጥኑ ይገባል። በሆዳምነትና ከንቱ ፍላጎትን በማርካት ሳይሆን በመታዘዝ መንገድ ሊመሩ ይገባቸዋል። 3Review and Herald, March 30, 1897.AHAmh 197.3

    ክርስቶስ ለደቀ-መዛሙርቱ በሕፃን ልጅ አማካይነት ሊያስተምራቸው የወደደውን ግሩም ትምህርት ብንማር የማንወጣቸው የሚመስሉ ስንት ችግሮቻችን ሙሉ በሙሉ ድራሻቸው በጠፋ ነበር! ደቀ-መዛሙርቱ ወደ ክርስቶስ ቀርበው ጠየቁት:- “በመንግሥተ-ሰማያት የሚበልጥ ማን ነው?…. የሱስም ሕፃን ጠራ በመካከላቸውም አቆመው። አለም። እውነት እላችኋለሁ። ካልተመለሳችሁ እንደ ሕፃናትም ካልሆናችሁ ወደ መንግሥተ-ሰማያት አትገቡም። እንደዚህም ሕፃን እራሱን ያዋረደ እርሱ ነው በመንግሥተ-ሰማያት የሚበልጥ።” 4Manuscript 13, 1891.AHAmh 197.4

    የእግዚአብሔር ንብረት ለወላጆች በአደራ ተሰጥቷል፦ የልጆች ሕይወትና ሕልውናቸው ከወላጆች የተወሰደ ይሁን እንጂ ሕይወት ያገኙት በእግዚአብሔር ረቂቅ ኃይል ምክንያት ነው - እግዚአብሔር የሕይወት ምንጭ ነውና። ልጆችን የግል ንብረቶቻችን አድርገን ልንቆጥራቸው እንደማይገባን ሊታወስ ያስፈልጋል። ልጆች የእግዚአብሔር ቅርሶች ናቸው፤ አርነት የማውጣት እቅዱ እኛንም እነርሱንም ያካትታል። ልጆች በጌታ እንክብካቤና ተግሳጽ ሥር ያድጉ ዘንድ ለዘመንና ለዘለዓለም ሥራ ብቁ ይሆኑ ዘንድ እንዲያሳድጓቸው ለወላጆች በአደራ የተሰጡ ናቸው። 5Signs of the Times, Sept. 10, 1894.AHAmh 197.5

    እናቶች ሆይ ታናናሾቹን ልጆቻችሁን በልስላሴ ተንከባከቧቸው። በአንድ ወቅት ክርስቶስ ሕፃን ልጅ ነበር። ለእርሱ ስትሉ ለልጆቻችሁ ክብር ስጡ። እንደ ቅዱስ ዕቃ ተመልከቷቸው። ሆኖም ሊሞላቀቁ እንደ ብርቅዬ የቤት እንስሣ እንዲታዩና እንዲመለኩ ሳይሆን ሕይወታቸው የከበረና ንጹህ ይሆን ዘንድ እንዲማሩ ነው። የእግዚአብሔር ንብረት ናቸው፤ ይወድዳቸዋል፤ ፍጹም ግድፈት-የለሽ ባህርይ ይመሠርቱ ዘንድ ለመርዳት ወላጆች ከእርሱ ጋር እንዲተባበሩ ጥሪ ተደርጎላቸዋል። 6Signs of the Times, Aug. 23, 1899.AHAmh 197.6

    እግዚአብሔርን በሠላም መገናኘት የምትፈልጉ ሁሉ አሁን መንጋውን በመንፈሳዊ መብል መግቡ፤ እያንዳንዱ ልጅ የዘለዓለም ሕይወትን የመውረስ እድል አለውና። ልጆችና ወጣቶች የተለዩ የእግዚአብሔር ሀብቶች ናቸው። 7Letter 105, 1893.AHAmh 198.1

    ወጣቶች በእውነት ተመስጠው ክህሎቶቻቸው የእነርሱ እንዳልሆኑ ሊገነዘቡ ይገባል። ብርታት ጊዜና እውቀት በውሰት ያገኟቸው ሀብቶች ናቸው፤ የእግዚአብሔር ናቸው፤ ለከፍተኛ ጥቅም ሊያውላቸውም የእያንዳንዱ ወጣት ቁርጥ ሐሳብ መሆን ይገባዋል። ወጣት ማለት እግዚአብሔር ፍሬ ያፈራልኛል ብሎ የሚጠብቀው ቅርንጫፍ፤ መዋለ-ንዋዩ ሊበዛለት የተገባው መጋቢና የዓለምን ጥቅጥቅ ጨለማ በብርሃን የሚሞላ መብራት ነው። እያንዳንዱ ወጣት እያንዳንዱ ልጅ ለእግዚአብሔር ክብርና የሰውን ዘር ከፍ ከፍ ለማድረግ የሚሠራው ሥራ አለው። 8Education, pp. 57, 58.AHAmh 198.2

    ወደ ሰማይ የሚወስደው መንገድ ለልጆች አቅም የተመቸ ነው፦ የሱስ ጉድለቶቻችንን እንደሚያውቅና ከኃጢአት በቀር የሁሉም ነገሮቻችን ተጋሪ እንደሆነ አይቻለሁ። ስለዚህ ለችሎታችንና ለጥንካሪያችን ገጣሚ የሆነ መንገድ አዘጋጅቶልናል። እንደ ያዕቆብም በሕፃናት ብርታት መጠን በእኩል ፍጥነት አብሮ ያዘግማል፤ በአብሮነቱ ምቾት ሊያነቃቃን የዘለዓለም መሪያችን ሊሆን ይፈልጋል። የመንጋውን ትንንሽ ጠቦቶች አይንቅም፤ ቸልም አይልም፤ ወደ ኋላም ሲቀሩ ትቷቸው አይሄድም። ከነልጆቻችን ትቶን በፍጥነት አልተራመደም፤ ኦ በፍጹም! ከሕፃናት ጋር እንኳን ወደ ሕይወት አቅጣጫ እኩል ይጓዛል። በስሙ በቀጭንዋ መንገድ ልጆቻቸውን ይመሯቸው ዘንድ ወላጆች ይጠበቅባቸዋል። እግዚአብሔር እንድንከተለው የሚፈልግብን መንገድ ከልጆች ጥንካሬና ችሎታ ጋር የተመጣጠነ ነው። 9Testimonies for the Church, Vol. 1, pp. 388, 389.AHAmh 198.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents