Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የአድቬንቲስት ቤት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ምዕራፍ ሠላሳ—የቤተሰብ ጓደኝነት

    ወላጆች ልጆቻቸውን በደንብ ሊያውቋቸው ይገባል፦ አንዳንድ ወላጆች ልጆቻቸውን አይረዷቸውም፤ የተላመዱም አይደሉም። ብዙ ጊዜ በልጆችና በወላጆች መካከል ሰፊ ርቀት አለ። ወላጆች ወደ ልጆቻቸው ስሜት በሙላት ቢጠጉና በልባቸው ያለውን እንዲገልጡላቸው ቢያደፋፍሯቸው ጠቃሚ ተጽዕኖ ይፈጥሩባቸዋል።1Testimonies for the Church, Vol. 1, p. 396.AHAmh 129.1

    አባትና እናት ርኅራኄ በተሞላበት ሁኔታ አብረው ይሥሩ። ለልጆቻቸው ጓደኛ ይሁኑላቸው።2Manuscript 45, 1912.AHAmh 129.2

    በትክክለኛው መንገድ ይመሯቸው ዘንድ የልጆቻቸውን ፍቅርና እምነት ለማትረፍ መጠቀም ያለባቸው ውጤታማ መንገድ ምን እንደሆነ ሊያጠኑ ይገባቸዋል። የፍቅርን ጮራ በቤተሰቡ ላይ ሊያንፀባርቁ ይገባቸዋል።3Review and Herald, Aug. 30. 1881.AHAmh 129.3

    ማበረታታትና ማሞገስ፦ ሕፃናት አብሮነትን ይወዱታል፤ ብቻቸውን እምብዛም አይደሰቱም። ርኅራኄንና ለስላሳነትን ይናፍቃሉ። የሚያስደስታቸው ሁሉ እናታቸውንም የሚያስደስታት ይመስላቸዋል፤ ለዚያም ነው በሆነ ባልሆነው ወደ እናታቸው እየሄዱ ደስታቸውንና ሐዘናቸውን የሚገልጹላት። ለእነርሱ አጅግ አስፈላጊ የሚመስላቸው፣ ለእርስዋ ተራ ቢሆንም እንደቀላል ነገር ቸል ብላ ልባቸውን ልታቆስለው አይገባትም። የእርስዋ ርኅራኄና አዎንታዊ ምላሽ ዋጋ የማይገኝላቸው ናቸው። ይሁን ባይ ፊትና የማበረታቻ ወይም የሙገሳ ቃል በልባቸው ልክ እንደ ፀሐይ ብርሃን ያበራል፤ ቀኑን ሙሉ ደስተኞች ሆነው ይውላሉ።4Ministry of Healing, p. 388.AHAmh 129.4

    ወላጆች የልጆቻቸው ምሥጢር ተካፋይ ይሁኑ፦ እምነት እንዲጥሉባቸውና ልባቸውን ያሳዘነውን ሸክም በእነርሱ ላይ እንዲያራግፉ እንዲሁም የየዕለቱን ጥቃቅን ብስጭታቸውንና ፈተናቸውን እንዲያዋዩዋቸው ወላጆች ልጆቻቸውን ሊያበረታቱ ይገባል።5.Testimonies for the Church, Vol. 1, p. 391.AHAmh 129.5

    በቸርነታችሁ በመምራት ከልባችሁ ጋር አቆራኟቸው። ይህ ለልጆች እጅግ ወሳኙ ሰዓት ነው። ልታከሽፉት የሚገባችሁ ከእናንተ ሊያርቃቸው የሚችል ተጽዕኖ ይከብባቸዋል። ምሥጢረኛቸው እንዲያደርጓችሁ አስተምሯቸው። ችግራቸውንና ደስታቸውን በጆሮአችሁ ያንሾካሹኩላችሁ።6Id., p. 387.AHAmh 129.6

    ልጆች ከወላጆቻቸው ጋር የበለጠ ቢላመዱ ከብዙ ርኩሰት ይተርፋሉ። ልጆች ለወላጆቻቸው ሐሳባቸውን በሃቀኝነትና በግልጽ ማዋየት እንዲችሉ ያበረታቷቸው። በችግራቸውና ትክክለኛው አካሄድ የቱ እንደሆነ ግራ በተጋቡ ጊዜ እንደተረዱት መጠን ጉዳያቸውን ራሳቸው ወላጆቻቸው ፊት እንዲያቀርቡና ምክር እንዲጠይቁ ያደፋፍሯቸው። ነገሮቻቸውን በጥሞና የሚመረምርና አደጋውንም የሚጠቁም እንደ መልካም ወላጅ ያለ ማን ሊኖር ይችላል? ልዩ ጠባያቸውን እንደወላጆቻቸው አድርጎ ማን ሊረዳቸው ይችላል? ከህፃንነት ጀምሮ እያንዳንዱን የልጆችዋን የአዕምሮ ለውጥ እየተለማመደች ያሳደገቻቸው እናታቸው ወደር የሌላት መካሪያቸው ትሆናለች። የትኛው ባህርይ መገታትና መቆም እንዳለበት በአባት እንደምትታገዝ እናት ማን ሊናገር ይችላል?AHAmh 129.7

    “ጊዜ የለም”፦ “ጊዜ የለም” ይላል አባት “ልጆቼን ለማሠልጠን፣ ለማህበራዊም ሆነ ለቤት ውስጥ መዝናኛ ጊዜ የለኝም።” እንግዲያውማ የቤተሰብን ኃላፊነት መውሰድ አልነበረብህም፤ የተገባቸውን (የእነርሱ የሆነውን) ጊዜያቸውን በመቀማት ከእጅህ መቀበል የነበረባቸውን ትምህርት ትሰርቃቸዋለህ (ትዘርፋቸዋለህ)። ልጆች ካሉህ ከእናታቸው ጋር በህብረት ባህርያቸውን የመቅረጽ ሥራ አለብህ።8Fundaments of Christian Education, pp. 65, 66.AHAmh 130.1

    “ከልጆቼ ጋር የምሆንበት ጊዜ አጣሁ”…. ይህ የብዙ እናቶች ጩኸት ነው። እባክሽ በክርስቶስ ይዤሻለሁ በቀሚስሽ ላይ የምታጠፊውን ጊዜ በልክ አድርጊው፤ ልብስሽን የማስጌጡን ጉዳይ ተይው፤ ስልክ የመቀበልና የመደወል ልማድሽን እርሽው፤ ማለቂያ የሌለውን የተለያየ ዓይነት ምግብ መሥራትሽን አቁሚ። ነገር ግን ልጆችሽን ፈጽሞ፣ በምንም ዓይነት ሁኔታ ቸል አትበያቸው። ገለባ ለስንዴው ምንድን ነው? በእናንተና በልጆቻችሁ ህልውና ምንም ነገር ጣልቃ እንዲገባ አትፍቀዱ።9Signs of the Times, Apr. 3, 1901.AHAmh 130.2

    አንዳንድ ጊዜ እናቶች በብዙ ጭንቀት ጎብጠው፣ ጊዜ ወስደው በትዕግሥት ሕፃናትን ለማስተማር፣ ፍቅርና ርኅራኄ ለማሳየት የሚሳናቸው ሆኖ ይሰማቸዋል። ማስታወስ ያለባቸው ግን የአብሮነትና የርኅራኄ ጥማታቸውን የሚያረካላቸውን ጉድኝት በወላጆቻቸውወይም በቤት ካላገኙት፣ በፍለጋ ሌላ ምንጮችን ይቃኛሉ፤ አስተሳሰባቸውና የሚመሠርቱት ባህርያቸውም አደጋ ላይ ይወድቃል።10Ministry of Healing, p. 389.AHAmh 130.3

    በሥራም ሆነ በጨዋታ ከልጆቻችሁ ጋር፦ የተወሰነውን የትርፍ ጊዜያችሁን ለልጆቻችሁ ስጡ። በሥራቸውና በጨዋታቸው አብራችኋቸው በመሆን አመኔታቸውን አትርፉ፤ ከእናንተ ጋር ያላቸውን ጓደኝነት አጎልብቱ።11Counsels to Teachers, Parents, and Students, p. 124.AHAmh 130.4

    ወላጆች የማምሻውን ጊዜ ለቤተሰቦቻቸው ይገብሩት። ጭንቀትንና ውዝግብን ከቀኑ ክፋት ጋራ ይተዉት።12Christian Temperance and Bible Hygiene, p. 65.AHAmh 130.5

    ምክር ለገለልተኛና አምባ-ገነን ወላጆች፦ ከልጆቻቸው ወይም ከተማሪዎቻቸው ጋር በበቂ ሁኔታ ባለመግባባታቸው ወላጆችና መምህራን ትዕዛዛቸውንና ቁጥጥራቸውን ከመጠን ያለፈ የማድረግ አደጋ አለባቸው። እራሳቸውን አትንኩኝ ባይ በማድረግ ሥልጣናቸውን በቀዘቀዘና ርኅራኄ በሌለው አካሄድ የልጆቻቸውንና የተማሪዎቻቸውን ልብ ሊያሸንፍላቸው በማይችል መልኩ በመተግበር ገለልተኛ ይሆናሉ። ሆኖም ልጆችን ሰብሰብ አድርገው እንደሚወዷቸው ቢያሳዩዋቸው፣ በሁሉም ጥረታቸው በጨዋታቸው ጭምር ፍላጎት እንዳላቸው ቢገልጹላቸው፣ እንዲያውም አንዳንድ ጊዜ በመካከላቸው እንደ ልጅ ቢሆኑ ልጆቹን በጣም ያስደስቷቸዋል፤ ፍቅራቸውንና አመኔታቸውን ያተርፋሉ። ሳይዘገይም ልጆቹ የመምህራቸውንና የወላጆቻቸውን ሥልጣን ማክበርና መውደድ ይጀም ራሉ።13Testimonies for the Church, Vol. 3, pp. 134, 135.AHAmh 131.1

    መጥፎ ጉድኝቶች የቤት ተቀናቃኝ ናቸው፦ የህፃናትን አዕምሮ ለመወስወስ ሰይጣንና ሠራዊቱ ኃይለኛ ጥረት እያደረጉ ነው። በመሆኑም ልጆቻችሁን በግልጽ ክርስቲያናዊ ልስላሴና ፍቅር ልታስተናግዷቸው ይገባል። ይህም በእነርሱ ላይ ጠንካራ ተጽዕኖ ማሳደር ያስችላችኋል። ያልተገደበ እምነት ሊጥሉባችሁም ይፈቅዳሉ። የቤትንና የህብረተሰብን ደማምነት በልጆቻችሁ ዙሪያ ጠምጥሙ። ይህንን ካደረጋችሁ ልጆቻችሁ ከወጣት ጓደኞቻቸው ጋር ህብረት የመፍጠር እምብዛም ፍላጎት አያሳዩም…. አሁን በዚህ ዓለም ባለው ርኩሰት ምክንያት አስፈላጊ የሆኑ ገደቦች ሲጣሉባቸው ወላጆች እጥፍ ጥንቃቄ በማድረግ ልጆቻቸውን ከልባቸው ጋር በማቆራኘት ደስተኛ ይሆኑ ዘንድ እንደሚፈልጉ ሊያሳዩአቸው ይገባል።14Id., Vol. 1, pp. 387, 388.AHAmh 131.2

    በልጆችና በወላጆች መካከል ምንም ዓይነት የቀዝቃዛነት ወይም የዘገምተኝነት ገደብ ሊኖር አይገባም። ምርጫቸውንና ፈቃዳቸውን በመጠየቅና በመረዳት፣ ወደ ውስጣቸውም ሰርገው በመግባት ልባቸው ውስጥ ያለውን ነገር ጎትተው ማውጣት እንዲችሉ ወላጆችና ልጆች በደንብ መተዋወቅ አለባቸው። ወላጆች ሆይ ልጆቻችሁን እንደምትወዷቸውና ደስተኞችም ይሆኑ ዘንድ የማትፈነቅሉት ድንጋይ እንደሌለ አሳዩአቸው። እንዲህ የምታደርጉ ከሆነ የምትከለክሏቸው ነገሮች በዚህ በለጋ አእምሮአቸው ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድርባቸዋል። “እላችኋለሁና መላእክታቸው በሰማዮች ሁልጊዜ የሰማዩን የአባቴን ፊት እንዲያዩ” ያለውን እያስታወሳችሁ ልጆቻችሁን በልስላሴና በርኅራኄ አስተዳድሩ። መላእክት በእግዚአብሔር የተሰጣቸውን ሥራ ልጆቻችሁ ላይ እንዲተገብሩት ከፈለጋችሁ ድርሻችሁን በመወጣት ተባበሯቸው። በእውነተኛ ቤት ጥበብና ፍቅር መሪነት ያደጉ ልጆች ጓደኝነትንና ደስታን ፍለጋ አይቅበዘበዙም፤ ክፋት አይስባቸውም። በቤት ውስጥ የተንሰራፋው መንፈስ ባህርያቸውን ይቀርጻል። የቤት መጠለያቸውን ለቅቀው ዓለምን ሲቀላቀሉ ፈተናን ለመቃወም ጠንካራ ምሽግ ይሆናቸው ዘንድ መልካም ልማድንና መርሆን ይመሠርታሉ።15Ministry of Healing, p. 394.AHAmh 131.3