Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የአድቬንቲስት ቤት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ክፍል ፲፬—የነፍሳትን ደጃፍ መጠበቅ

    ምዕራፍ ስድሳ ስድስት—መጠበቅ ያለብን በሮች

    አይኖችን፣ ጆሮዎችንና የመናገር ችሎታን እግዚአብሔር ለምን ሰጠ?፦እግዚአብሔር ለሰዎች ዐይን የሰጣቸው የሚያስደንቁ ነገሮችን ከሕጉ ያዩ ዘንድ ነው። መልእክቱን በህያው ሰባኪ አማካይነት ያደምጡ ዘንድ የሚሰማ ጆሮ ሰጣቸው። ኃጢአት ይቅር ባዩን አዳኝ ክርስቶስን ያሳዩ ዘንድ የመናገርን ክህሎት ለሰዎች ሰጣቸው። ሰው ስለጽድቅ በልቡ ያምናል በአፉ ንስሐም ይድናል። 1Letter 21, 1899.AHAmh 292.1

    ሰይጣን ወደ ነፍስ መግቢያ ቀዳዳ እንዴት እንደሚያገኝ፦ ሰይጣን ድል እንዳይነሳቸው ሁሉም ሰው የስሜት ሕዋሳቱን ሊጠብቅ ይገባዋል፤ ወደ ነፍስ መግቢያ በሮች ናቸውና። 2Testimonies for the Church, Vol. 3, p. 507.AHAmh 292.2

    አእምሮአችሁን ተቆጣጥራችሁ፣ ከንቱና ብልሹ አስተሳሰቦች ነፍሳችሁን እንዳይበክሉት ከፈለጋችሁ በዐይኖቻችሁ፣ በጆሮዎቻችሁና በሁሉም የስሜት ሕዋሳት ላይ ታማኝ ዘበኛ ሁኑ። ይህንን እጅግ አስፈላጊ ተግባር ማከናወን የሚችለው የፀጋ ኃይል ብቻ ነው። 3 Id., Vol. 2, p. 561AHAmh 292.3

    ማስጠንቀቂያዎች፣ ማሳሰቢያዎችና ተግሳጾች እንዳይሰሙ ሰይጣንና መላእክቱ የስሜት ሕዋሳት ሽባ የሚሆንበትን ሁኔታ ለመፍጠር ሥራ ላይ ተጠምደዋል። እነዚህ ማስጠንቀቂያዎች ከተደመጡ ደግሞ በልብ ላይ ምንም ተጽእኖ እንዳያሳድሩ የረባ ሥራ እንዳይሠሩና ሕይወት እንዳይታደስ ይጥራሉ። 4Id., Vol. 5, p. 493.AHAmh 292.4

    ወንድሞቼ ሆይ! የእርሱ ተከታዮች እንደመሆናችሁ በብርሃን ትመላለሱ ዘንድ እግዚአብሔር ይጠራችኋል። የማስጠንቀቂያውን ደወል ስሙ። ኃጢአት በመካከላችን አለ፤ እንደ ጥፋቱ ኃያልነት ወይም አደገኝነት ግን አናስተውለውም። ፍላጎታቸውን ከማርካትና ከኃጢአት ጋራ ካላቸው ልምምድ የተነሣ የብዙዎች የስሜት ሕዋሳት ደንዝዘዋል፤ እኛ ግን ወደ ሰማይ ለመቅረብ መገስገስ አለብን። 5Id., Vol. 3, p. 476.AHAmh 292.5

    የሰይጣን ስልት የስሜት ሕዋሳትን ማደናበር ነው፦ የሰይጣን ተግባር ሰዎች እግዚአብሔርን ቸል እንዲሉ ት በመምራት ሐሳባቸውና አዕምሮአቸው በሌሎች ነገሮች እንዲማረክና በኃይል እንዲመሰጥ በማድረግ በሚያስቡት ነገር ውስጥ እግዚአብሔር እንዳይካተት ማድረግ ነው። የተማሩት ትምህርት አዕምሮን ግራ የማጋባትና ትክክለኛውን ብርሃን የመጋረድ ባህርይ ያለው ነው። ሰዎች የእግዚአብሔር ዕውቀት ይኖራቸው ዘንድ ሰይጣን ምኞቱ አይደለም። በዙሪያቸው ብርሃን እየተንቦገቦገ ሳለ፣ በአሠራር ዘዴውና በተውኔታዊ ችሎታው የወጣቶችን የስሜት ሕዋሳት ግራ በማጋባት ፍጡራን በጨለማ ውስጥ ቀርተው ቢጠፉ ይህ እጅግ ያስደስተዋል። 6Review and Herald, March 13, 1900.AHAmh 292.6

    ያለእኛ ፈቃድ ሰይጣን ወደ አዕምሮአችን ሊገባ አይቻለውም፦ መሸከም ከምንችለው በላይ እንደማንፈተን፣ ለእያንዳንዱም ፈተና ማምለጫ እግዚአብሔር እንዳዘጋጀልን ለሰዎች ፍንትው አድርገን ልናሳያቸው ይገባል። ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር ከኖርን አዕምሮአችን ራስ-ወዳድ የሆነ ምናባዊ ፍላጎትን እንዲያስተናግድ አንፈቅድለትም።AHAmh 293.1

    ሰይጣን ወደ አዕምሮ የሚገባበት ትንሽ ቀዳዳ ካገኘ እንክርዳድ ይዘራና የተትረፈረፈ ምርት እስኪያገኝ ድረስ ተንከባክቦ ያሳድገዋል። እኛ በፈቃዳችን በሩን ከፍተን እንዲገባ ካልጋበዝነው በስተቀር በሃሳባችን፣ በንግግራችንና በሥራችን ላይ ሰይጣን ይሠለጥንብን ዘንድ የሚያስችለው አንዳችም መንገድ የለም። ስንፈቅድለት በበሩ ወደ ውስጥ በመግባት እውነት በሥራ ላይ እንዳይውል በልብ ውስጥ የተዘራውን መልካም ዘር ይለቅማል። 7Review and Herald, July, 11, 1893.AHAmh 293.2

    ለፈታኙ ሁሉንም መግቢያ ቀዳዳ ድፈኑ፦ የክርስቶስን ስም የሚጠሩ ሁሉ ሊጠነቀቁ፣ ሊጸልዩና የነፍስን በር ሊጠብቁ ይገባቸዋል፤ ምክንያቱም እጅግ ጠባብ የሚባል አጋጣሚ (እድል) ካገኘ ሊያጠፋና ሊበክል ጠላት ምንጊዜም በሥራ ላይ ነው። 8Testimonies for the Church, Vol. 3, p. 476.AHAmh 293.3

    ሰይጣን የሚያቀርበውን ሐሳብ በማጤን ጥቅም ይገኝበት እንደሆነ በማሰላሰል ወዲያ ወዲህ ማለት ለእኛ አደጋ አለው። ኃጢአት ማለት በእያንዳንዱ ለሚፈጽመው ነፍስ ውርደትና ጥፋት ነው፤ ሆኖም የሚያሳውርና የሚያሳስት ባህርይ ያለው በመሆኑ በሥጦታዎቹ እየደለለ ያማልለናል። በሰይጣን መሬት ላይ ለመራመድ ከደፈርን ከኃይሉ የሚጠብቀን ምንም ዋስትና የለንም። ውስጣችን እንደሚነግረን ፈታኙ ወደ እኛ ሊደርስ የሚችልበትን እያንዳንዱን በር መዝጋት ይኖርብናል። 9Thoughts from the Mount of Blessing, p. 171.AHAmh 293.4

    በፈተና ጊዜ ከአንድ ስህተት፣ ከአንድ ችኩል እርምጃ የተነሣ የሚመጡትን አሰቃቂ መዘዞች ማን ያውቃል! መልካሙን ክፉ፤ ክፉውን ደግሞ መልካም እንደሆነ የምናይበት የራሳችን መንፈሳዊ ዐይን ትተን በእያንዳንዱ ደቂቃ በእግዚአብሔር ፀጋ ካልተከለልን በስተቀር ደህንነታችን ሊረጋገጥ አይችልም። ያለማመንታትና ክርክር የነፍሳችንን በሮች ለክፋት ዘግተን መጠበቅ አለብን። 10Testimonies for the Church, Vol. 3, p. 324.AHAmh 293.5

    እያንዳንዱ ክርስቲያን ሰይጣን መግቢያ ሊያገኝበት የሚችለውን የነፍስ በር በመጠበቅ ሁልጊዜ በተጠንቀቅ መቆም አለበት። እያንዳንዱን ኃጢአት የመሥራት ዝንባሌ በቆራጥነት በመቃወም ሲጥር ሳለ ለመለኮታዊ እርዳታ ይፀልይ። በጀግንነት በእምነትና በጽኑ ልፋት ማሸነፍ ይችላል። ማስታወስ ያለበት ጉዳይ ግን አለ፤ አሸናፊነትን ለመቀዳጀት ክርስቶስ በእርሱ እርሱም በክርስቶስ መኖር አለባቸው። 11 Id., Vol. 5, p. 47.AHAmh 293.6

    ርኩሰትን ከማንበብ ከማየትና ከመስማት ተቆጠቡ፦ አዕምሮ ወደ ተከለከሉ መልእክቶች እንዳይሳብ ወይም በማይረቡ ጉዳዮች ኃይሉን እንዳያባክን ይህ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ሐዋርያው [ጴጥሮስ] ለህዝቡ ሊያስተምር ሞክሯል። በሰይጣን መሣሪያዎች እንዳይያዙ የሚፈልጉ ሁሉ የነፍስን መግቢያ በር በደንብ መጠበቅ አለባቸው። ንጽህና የጎደለውን አስተሳሰብ የሚጭሩ ነገሮችን ከማንበብ ከማየትና ከመስማት ይቆጠቡ። አዕምሮአችን የነፍሳት ጠላት በሚያቀርበው ሐሳብ ተመስጦ በዘፈቀደ እንዲኖር መተው የለበትም። ለልብ ታማኝ የክብር ዘበኛ ሊቆምለት ይገባል፤ ያለዚያ በውጭ ያለው ርኩሰት በውስጥ ያለውን ክፋት ቀስቅሶ ነፍስ በጨለማ ውስጥ እንድትንከራተት ትሆናለች። 12 Acts of the Apostles, pp. 518, 519.AHAmh 293.7

    በዓለም እየተተገበረ ያለውን ርኩሰት እኛና ልጆቻችን ላለማየት ይቻለን ዘንድ መደረግ ያለበት ጥረት ሁሉ ይደረግ። እነዚህ ክፉ ነገሮች ወደ አዕምሮአችን እንዳይገቡ ዐይኖቻችን የሚያዩትንና ጆሮዎቻችን የሚሰሙትን በጥንቃቄ መጠበቅ አለብን። እኔ በበኩሌ በውስጡ የያዛቸው ዘበቶችና ስሜት ቀስቃሽ ነገሮች እንዳይታዩ በየዕለቱ ወደ ቤት የሚመጣውን ጋዜጣ ልደብቀው እፈልጋለሁ። በጋዜጣዎች በሚታዩ ብዙ ሕትመቶች ላይ የጠላት እጅ ያለበት ይመስላል። ክፋት ሁሉ ተፈልፍሎ ወጥቶ በጋዜጦች አማካይነት እርቃኑን ለዓለም ይቀርባል። 13Notebook Leaflets, Education, No. 1..AHAmh 294.1

    ብልሃተኛ ይሆኑ ዘንድ የሚፈልጉ ከእግዚአብሔር የሚመጣውን ጥበብ ያገኙ ዘንድ ያላቸው ሁሉ በዚህ ዘመን ላለው የኃጢአት እውቀት ቂሎች መሆን አለባቸው። ምንም ዓይነት ርኩሰት ከማየት ይድኑ ዘንድ ዐይናቸውን ይጨፍኑ። ንጹህ የሆነውን ሐሳባቸውንና ምግባራቸውን የሚበክለውን እውቀት ከማግኘት ይታቀቡ ዘንድ ጆሮአቸውን ይድፈኑ። ብልሹ ንግግሮችን ተናግረው በአፋቸው ተንኮል እንዳይገኝ ምላሳቸውን ይቆልፉ። 14Solemn Appeal, p. 76.AHAmh 294.2

    በሩን በመክፈት የመቃወም ኃይል ይደክማል፦ ሳትወድቁ የገደሉን አፋፍ ምን ያህል ተጠግታችሁ ጠርዙ ላይ መራመድ እንደምትችሉ ለማየት አትሞክሩ። ከመጀመሪያው የአደጋ ቅርበት ሽሹ። የነፍስ ጉዳዮች በማይረቡ ነገሮች ልትጫወቱባቸው የሚቻላችሁ አይደሉም። ባህርያችሁ አንጡራ ሀብታችሁ ነው፤ እንደ ወርቅ ዕቃ ተንከባከቡት። የግብረ-ገብነት ንጽህና ለራስ ክብር መስጠትና የመቃወም ጠንካራ ጉልበት ያለማቋረጥ በእጅጉ ሊበረታቱ ይገባል። ከጭምትነት አንድ እርምጃ ፈቀቅ ማለት አያስፈልግም፤ አንድ የመለማመድ ተግባርና አንድ ንዝህላልነት ለፈተና በር በመክፈት ነፍስን አደጋ ላይ ይጥላል፤ የመቃወምና የመቋቋም ኃይልንም ይቀንሰዋል። 15Medical Ministry, p. 143.AHAmh 294.3

    ሰይጣን የወደፊቱን ክብር ይጋርዳል፦ የሚመጣውን ዓለም ክብርና ውበት በመጋረድ ሁሉም ትኩረት በዚህ ምድር ሕይወት ነገሮች ላይ ብቻ እንዲያርፍ ሰይጣን ያላሰለሰ ሥራ እየሠራ ነው። ሐሳቦቻችን ጭንቀቶቻችንና ጥረቶቻችን ሙሉ በሙሉ በጊዜያዊ ነገሮች ላይ ሆኖ ስለ ዘለዓለማዊ እውነታዎች እንዳናይ ወይም እንዳናስተውል ሁኔታዎችን በማመቻቸት ረገድ ሰይጣ ን በእጅጉ እየጣረ ይገኛል። ዓለምና ጣጣዎቹ እጅግ ገዝፈውብን የሱስና ሰማያዊ ጉዳዮች በሐሳባችንና በፍላጎቶቻችን ውስጥ ያላቸው ድርሻ እጅግ አናሳ ሆኗል። አዎ የዕለት ተዕለት ኑሮአችን በንቃት ማከናወን ይገባናል። ሆኖም ለጌታ የሱስ ክርስቶስ ያለንን የተቀደሰ ፍቅር ከሁሉም በላይ ልናሳድገው ያስፈልገናል። 16Review and Herald, Jan. 7, 1890.AHAmh 294.4

    የሰማይ መላእክት ያግዙናል፦ አዕምሮን መቆጣጠር ይችሉ ዘንድ የመልካምም ሆነ የክፋት የማይታዩ ኃይሎች እየለፉ እንደሆነ ምንጊዜም ማስታወስ ይገባናል። በማይታይ ነገር ግን ብቃት ባለው ኃይል ይሠራሉ፤ ቅዱሳን መላእክት መንፈሳችንን በመቀደስ በልባችንና በአዕምሮአችን ሰማያዊ ተጽዕኖ እንዲያርፍ ይሠራሉ፤ ታላቁ የነፍስ በላጋራ ዲያብሎስና መላእክቱ ደግሞ ጥፋታችንን እውን ለማድረግ ያለማቋረጥ እየለፉ ነው…. ለማይታዩና ለማይስተዋሉ ጠላቶቻችን ጥቃት እንዳንጋለጥ ንቁና ትጉ መሆናችን እንዳለ ሆኖ ሳንፈቅድላቸው ሊጎዱን እንደማይችሉ ግን በጣም እርግጠኞች እንሁን። 17Review and Herald, July 19, 1887.AHAmh 295.1