Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የአድቬንቲስት ቤት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ምዕራፍ አሥራ ሦስት—የቤት ውስጥ ሥልጠና

    ለጋብቻ መዘጋጀት አስፈላጊ የትምህርት አካል ነው፦ ተግባራዊ የሆነ የቤት ውስጥ ግዴታዎች ተሞክሮና ዕውቀት ሳይኖር በምንም ተዓምር ጋብቻ መፈፀም የለበትም። ሚስትየዋ የሚሰጧትን ልጆች በትክክለኛ መንገድ ለማሠልጠን የሚያስችል የአዕምሮ ዝግጅትና ባህርያት ሊኖሩዋት ይገባል።1Pacific Health Journal, May, 1890.AHAmh 53.1

    በደንብ እንደተማሩ የተቆጠሩ፣ ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት በማዕረግ የተመረቁ ብዙ ሴቶች፣ የሕይወት ተግባራዊ ኃላፊነቶችን በተመለከተ ግን በአሳፋሪ ሁኔታ ገልቱ ናቸው። ለደስታቸው በጣም አስፈላጊ የሆነውን መልካም የቤተሰብ ቁጥጥር ማድረግ የሚያስችል የትምህርት ደረጃ ይጎድላቸዋል። ስለ ሴት አስፋ-ወሰንና ስላላት መብትዋ ያወራሉ፤ እራሳቸው ግን ሴት ለመባል ከሚያበቃቸው ደረጃ በጣም ዝቅ ያሉ ናቸው። በተለያዩ የቤት ውስጥ የሥራ ድርሻዎች ሥልጠና ማግኘትና ልቅም ያለ የቤተሰብ ኃላፊነት ዕውቀት ይኖራት ዘንድ የእያንዳንዷ የሔዋን ልጅ መብት ነው። በቤት ውስጥ እንደ ልዕልት ነግሣ የሚስትና የእናትነት ቦታን እንድትይዝ ስትጠየቅ ዝግጁ እንድትሆን፣ እያንዳንዷ ልጃገረድ በአንክሮ ልትሠለጥን ይገባታል። ልጆችዋን ልትመራና ልትቆጣጠር፤ አገልጋዮችዋን ልታዝ፤ አስፈላጊም በሆነ ጊዜ በራስዋ እጅ ቤተሰቡ የሚያስፈልገውን ልታዘጋጅ ትችል ዘንድ ብቁ መሆን አለባት። ስለ ሰው የአካል አደረጃጀት ዕውቀት ማግኘት፤ የንጽህና መርሆዎች፣ የምግብና የአለባበስ ጉዳዮች የሥራና የመዝናናት እንዲሁም ቁጥር ስፍር የሌላቸው ስለ ቤተሰቧ ደህንነት ስትል ሊያሳስቧት ወይም ሊያስጨንቋት የሚችሉ ነገሮችን ሁሉ የመረዳት መብት አላት። የከበሩ ቅርሶችዋን በማይታወቁ ዶክተሮችና ነርሶች እጅ ከመተው፣ ልጆችዋ ሲታመሙ እራስዋ ልታክመው የምትችለው ዓይነት በሽታ ከሆነ እንዴት መርዳት እንደምትችል የሚያሠለጥናት ትምህርት ማግኘት መብትዋ ነው። አስፈላጊ ግን ተራ የሆነ ሥራን መናቅ የእውነተኛ ጨዋ ወንድ ወይም ሴት ምልክት ነው የሚባለው አስተሳሰብ፣ እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥር ካስቀመጠው እቅድ ጋር የሚጣረስ ነው። ስንፍና ኃጢአት ነው። ሁልጊዜ ሊተገበሩ የሚያስፈልጋቸውን ኃላፊነቶች ቸል ማለት የስንፍና ውጤት ነው፤ ከእንደዚህ ዓይነት ሕይወት ለሚመጣው የመራራ ፀፀት ትዕይንት ምክንያት ነው።2Fundamentals of Christian Education, p. 75.AHAmh 53.2

    ወጣት ሴቶች ማብሰልና በተለይ የቤት ውስጥ ሥራዎችን መሥራት ያለባቸው የተቀጠሩ ሠራተኞች ናቸው ብለው ያምናሉ። በዚህም ምክንያት የሚያገቡና ቤተሰብ የሚመሠርቱ ልጃገረዶች ሚስትነትና እናትነት ይዞት የሚመጣውን ኃላፊነት በውል 54 የአድቬንቲስት ቤት አያውቁትም።3Ministry of Healing, p. 302.AHAmh 53.3

    ወጣቶች ለሚወለዱት ልጆች እንዴት እንክብካቤ ማድረግ እንዳለባቸው የማያውቁ ከሆነ ማግባት የለባቸውም - ይህ ሕግ መሆን አለበት። እግዚአብሔር የሰጣቸውን ይህን ቤት እንዴት እንደሚያስተዳድሩ ማወቅ አለባቸው። ለቤተሰባቸው ግንኙነት እግዚአብሔር የዘረጋውን ደንብ ካልተረዱ በስተቀር ለጌታም ሆነ ለእራሳቸው ያለባቸውን ኃላፊነት ሊረዱ አይችሉም።4Manuscript 19, 1887.AHAmh 54.1

    የቤት ውስጥ ሥራ ሥልጠና በኮሌጅ ትምህርት ውስጥ መካተት አለበት፦ በኮሌጅ የሚማሩ ወጣት ሴቶችና ወንዶች ሊያገኙት የሚችሉት የቤት ውስጥ ሕይወት ትምህርት የተለየ ትኩረት ሊሰጠው የተገባው ነው። ስንፍናን አሽቀንጥረው ጥለው ሊሠሩት የተገባቸውን ሥራ እንዲሠሩ መሠልጠናቸው ኮሌጅ እየተከታተሉ ላሉት ሁሉ ባህርያቸውን ለማነጽ እጅግ አስፈላጊ ነው። በዕለት ተዕለት ሕይወታቸው ሊሠሩት የተገባቸውን ሥራ ሊለማመዱት ይገባል። ሁሉም ነገር በአግባቡና በሥርዓት ሊከናወን ይገባል። ወጥ ቤቱና ሁሉም የቤቱ ክፍሎች ንጹህና የሚያውዱ መሆን ይጠበቅባቸዋል። መጻሕፍት ሊነበቡ በሚገባቸው ጊዜ ብቻ ይነበቡ፤ ማጥናት ከሚገባው በላይ በማጥናት የቤተሰብ ኃላፊነትን ቸል ማለት አይገባም። የመጻሕፍት ጥናት አዕምሮን በመመሰጥ የቤተሰብ ደህንነት የሚወሰንባቸውን የቤት ሥራዎች ሊያስተው አይገባም። እነዚህ ኃላፊነቶች ሲተገበሩ ዋዘኛነት፣ ቸልተኛነትና ዝርክርክነት ሊወገዱ ያስፈልጋል፤ ያለዚያ እነዚህ መጥፎ ልምዶች በሁሉም የኑሮአችን ደረጃዎች ይከሰቱና ሕይወታችን እርባና-ቢስ ያደርጉታል።5Testimonies for the Church, Vol. 6. pp. 169, 170.AHAmh 54.2

    የቤት አስተዳደር ዕውቀት ሊኖር ግዴታ ነው፦ የተማሪዎችን ጊዜ ወስደው የሚጠኑ ብዙ አይነት ጥናቶች ለጠቃሚነት ወይም ለደስተኛነት የሚያስፈልጉን አይደሉም። ነገር ግን እያንዳንዱ ወጣት የዕለት ተዕለት ተግባራትን በደንብ መለማመድ አለበት። አንዲት ወጣት ሴት የፈረንሳይኛ ቋንቋ፣ የሒሳብ ወይም የፒያኖ ትምርትዋን ልትተው ትችላለች፤ ነገር ግን ሞንሟና እንጀራ ልትጋግር፣ ጥሩ ግጣም ያላቸውን አልባሳት ልትሰፋ፣ ለቤት አስተዳደር የሚያግዙ ሥራዎችን ሁሉ ልትማር ግድ ይላታል።AHAmh 54.3

    የሁሉንም ቤተሰብ ጤንነትና ደስታ ለመጠበቅ እንደ ምግብ ማብሰል ሞያና ዕውቀት አስፈላጊ የሆነ ምንም ነገር የለም። በሥነ-ሥርዓት ያልተዘጋጀ፤ ለጤና ተስማሚ ያልሆነ ምግብ በማዘጋጀትዋ አንዲት ሴት የባልዋን ጠቀሜታና የልጆችዋን እድገት ልታስተጓጉል እንዲያውም ልታጠፋ ትችላለች። በሙያ እጦት ምክንያት ሊመጣ የሚችለውን ጉዳት ያህል፣ በአንፃሩ ደግሞ ለሰውነት የሚስማማ፣ ሊበሉት የሚያስጎመጅና እጅ የሚያስቆረጥም ምግብ በማዘጋጀት ትልቅ ሥራ ማከናወን ትችላለች። ስለዚህ በብዙ አቅጣጫ የኑሮአችን ደስታ የሚወሰነው ጥቃቅንና ተራ በምንላቸው ሥራዎች መተግበር ላይ ባለን ታማኝነት ነው።6Education, p. 216AHAmh 54.4

    ለንጽህና መርሆዎች ትኩረት ስጡ፦ የንጽህና መርሆዎች ለምግብ ዝግጅት፣ ለእንቅስቃሴ፣ ለልጆች እንክብካቤ፣ በሽተኞችን ለማስታመምና ለመሳሰሉት በተለምዶ ከሚሰጣቸው ቦታ እጅግ የበለጠ ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል።7Id., p. 197.AHAmh 55.1

    በንጽህና ትምህርት አዋቂ የሆነችው መምህርት በአንድ ሰው የግል ንጽህናና በዙሪያው ስላለው ፍጹም ንጽህና ማሻሻል የምትችለውን ሁሉ ለማድረግ ትጥራለች….ለጤና የሚስማማ የመኝታ ክፍል፤ ፍጹም ንጹህ የሆነ ወጥ ቤት፤ ዐይንን በሚስብ ሁኔታ የተዘጋጀ ለጤና የሚስማማ ምግብ የሞላበት ጠረጴዛ፣ ውድ በሆኑ የቤት ዕቃዎች ከተጨናነቀ ክፍል ይልቅ የቤተሰቡን ደስታ በመጠበቅ ረገድ ታላቅ አስተዋጽዖ እንዳለው፤ የብልህ እንግዳን አድናቆት በማትረፍም የላቀ እንደሆነ ተማሪዎችሽን አስተምሪያቸው። “ነፍስ ከመብል ትበልጣለችና ሥጋም ከልብስ” [ሉቃስ 12፡23] የሚለው ትምህርት የዛሬ አስፈላጊነቱ ከሺ ስምንት መቶ ዓመት በፊት በመለኮታዊው መምህር ከተነገረበት ጊዜ ያነሰ አይደለም።8 [ዋይት ‘ከሺ ስምንት መቶ ዓመት በፊት’ ያለችው መጽሐፉን ከጻፈችበት ጊዜ ተነስታ ነው።]8Id., p. 200.AHAmh 55.2

    የታታሪነትን ልምድ እንድታካብት ምክር የሚያስፈልጋት ልጃገረድ፦ አደጋ የሌለበት የጋብቻ ግንኙነት ከመመሥረትሽ በፊት፣ በጥብቅ ሊስተካከልና በቆራጥነት ልትቆጣጠሪው የሚገባሽ ልዩ ባህርይ አለሽ። የባህርይሽን ግድፈቶች እስክታስተካክይ ድረስ የማግባት ሐሳብሽን ከጭንቅላትሽ አውጭው፤ ያለዚያ ደስተኛ ሚስት ልትሆኝ አትችይም። ስለ ደንበኛ የቤተሰብ ሥራ ራስሽን ለማስተማር ቸል ብለሻል። የታታሪነት ልምድ ማጎልበት ጥቅምም አልታየሽም። በሥራ ወዳድነት የሚገኘው ደስታ አንድ ጊዜ ከዳበረ በኋላ ፈጽሞ አይጠፋብሽም። እንዲህም ሲሆን በሕይወትሽ ለሚገጥሙሽ መሰናክሎች ሁሉ የተዘጋጀሽና ኃላፊነትንም ለመውሰድ ብቁ ትሆኛለሽ፤ ሥራ መውደድን ትማሪያለሽ። አስፈላጊ የሆነ ሥራ በመሥራት የምትደሰቺ ከሆነ፣ አዕምሮሽ በምትሠሪው ሥራ ይጠመዳል፤ ከንቱና ብልጭልጭ ነገሮችን ለመመኘት ጊዜ አታገኚም። ለጠቃሚ ሥራ ያለሽ ዕውቀት ዕረፍት-የለሽ የሆነውን ያልረካ የአዕምሮሽን ጉልበት እንዲሁም ጤናማነትሽን በማገዝ ማዕረግ ይሆንልሻል፤ አክብሮትም ታተርፊያለሽ።9Testimonies for the Church, Vol. 3, p. 336.AHAmh 55.3

    የተግባር ትምህርት ጠቀሜታ ለልጃገረዶች፦ ወንድ ልጃቸው የወደፊት ሕይወቱን በተሳካ ሁኔታ ይመራ ዘንድ የሚያስችለው ሥልጠና እንደሚያስፈልገው ብዙ ወላጆች ያምናሉ። ሴት ልጃቸው ግን እራስዋን እንድትችልና ነፃነት እንዲኖራት የሚያስችላትን ትምህርት መማር የራስዋ ጉዳይ አድርገው ይወስዱታል። ሴት ልጅ የዕለት አንጀራዋን እንድታገኝ ከሚረዳት ውስጥ፣ በትምህርት ቤት የምታገኘው ተግባራዊ ትምህርት በጣም ጥቂቱን ነው። በቤት ውስጥ ሕይወትና በወጥ ቤት ስላለው ድንግርግሮሽ አስፈላጊው ትምህርት ካልተሰጣት፣ የወላጆች ሸክም - ዋጋ-ቢስ ሆና ታድጋለች….AHAmh 55.4

    ለእራስዋ መጠንቀቅ የተማረች ሴት ለሌሎችም እንክብካቤ ማድረግ ትችላለች። በቤተሰቧም ሆነ በማህበረሰቡ ውስጥ ፈጽሞ ጉዳት የምታመጣ አትሆንም። ሀብትዋ ቢያልቅ እንኳን ልትቀጠርበትና በሥርዋ ያሉትን ጥገኞችዋን ልትረዳ የሚያስችላት ሥራ ለራስዋ ፈልጋ አታጣም። ሴት ልጅ ሠርታ ልታድርበት የምትችል የንግድ ሥራ ሥልጠናም ያስፈልጋታል። አብዛኛው ሕዝብ ክብር የሚሰጣቸውን የሥራ ዘርፎች በመተው፣ ልጃገረዶች የቤት ጉዳዮችን ሊያስተዳድሩ የሚችሉበት ትምህርት፤ እንደ ምግብ አብሳይ፣ የቤት አያያዝ ሠራተኛና ልብስ ሰፊ በመሆን መሠልጠን አለባቸው። ቤተሰቧ ሀብታምም ሆነ ድኃ አንዲት የቤት እመቤት ልታውቀው የሚገባትን ሁሉ ማወቅ አለባት። ችግር ቢመጣ ለማንኛውም አስቸኳይ ጉዳይ የተዘጋጀች ትሆናለች። በአጭሩ በሁኔታዎች የተገደበች አትሆንም።10Health Reformer, Dec., 1877.AHAmh 56.1

    የቤት ውስጥ ሥራ ዕውቀት ለእያንዳንዷ ሴት ዋጋ የማይገኝለት ትምህርት ነው። በሚስትና በእናትየዋ የችሎታ ማነስ ምክንያት ሥፍር ቁጥር የሌላቸው ቤቶች ደስታቸው ጠፍቷል። ሴት ልጆች የሚማሩት ቀለም መቀባት፣ የተጌጠ ጥልፍ መጥለፍ፣ ሙዚቃ ወይም የሚሸነግል የቁጥር ቀመር ማወቅ፤ የራሳቸውን ልብስ እንደ መቁረጥ፣ መሥራትና መስፋት ወይም ለጤና ተስማሚ የሆነ ሊበሉት የሚያስጎመጅ ምግብ የማዘጋጀትን ያህል አስፈላጊ አይደሉም። አንዲት ሴት ልጅ ዘጠኝ ወይም አሥር ዓመት ሲሞላት ቋሚ የሆነ እርስዋ ልትሠራው የምትችለው ድርሻ ሊሰጣት ይገባል፤ በምትሠራው ሥራም ኃላፊነት በመውሰድ ተጠያቂ ልትሆን ይገባታል። ሴት ልጆቹን ምን ሊያደርጋቸው እንዳሰበ የተጠየቀ ብልህ አባት “ጊዜን በአግባቡ የመጠቀም ጥበብ እንዲማሩ፤ ጥሩ ሚስቶች፣ እናቶች፣ የቤት መሪዎች እንዲሁም ጠቃሚ የሕብረተሰብ አባል ለመሆን እንዲችሉ ግሩም በሆነችው እናታቸው ሥር እንዲሠለጥኑ እፈልጋለሁ።” ብሎ መልሷል።11Fundamentals of Christian Education, p. 74.AHAmh 56.2

    ባል የሚሆን ወጣት ቆጣቢና ታታሪ መሆን አለበት፦ በድሮ ጊዜ የነበረው ባህል፣ ጋብቻ ከመጽደቁ በፊት ሙሽራው በገንዘቡ ወይም እኩያ ንብረት እንዳቅሙ እጅ መንሻ ለሙሽራዋ አባት መክፈል ነበረበት፤ ይህ ለአዲሱ ጋብቻ እንደዋስትና ይቆጠር ነበር። አባቶች ገንዘብ አፍርቶ፣ ቤተሰብን አስተዳድሮ ለማያውቅ ወጣት የልጃቸውን ደስታ አሳልፎ መስጠት አስተማማኝ ነው ብለው አያምኑም ነበር። ሥራቸውን በሚገባ በመቆጣጠር ከብት ለማርባት ወይም መሬት ለመግዛት በቂ ትጋትና ጉልበት ከሌላቸው ሕይወታቸው እርባና ቢስ ሆኖ ይቀራል ተብሎ ይፈራ ነበር። ለሚያገቧት ወጣት ቤተሰቦች ለመክፈል ምንም ነገር ከሌላቸው የሚፈትናቸው እቅድ ተዘጋጅቶላቸው ነበር። የተፈለገውን ጥሎሽ(ማጫ) ሒሳብ ያህል ወጣቱ በወደዳት ኮረዳ አባት ቤት መሥራት ይፈቀድለት ነበር። በአገልግሎቱ ታማኝነቱን ካስመሰከረና በሌሎቹም ዘርፎች የተገባው ሆኖ ሲገኝ ለጋብቻ ጠያቂው ወጣትዋ በሚስትነት ትሰጠዋለች። በጥሎሽ መልክ የተቀበለውን በጋብቻ ሰዓት አባት ለሴት ልጁ ይሰጣት ነበር….AHAmh 56.3

    የጥንቱ ባህል አንዳንድ ጊዜ እንደ ላባን አግባብ በሌለው አኳኋን ቢተገበርም ጥሩ ውጤት የሚያስገኝ ነበር። ጋብቻ ጠያቂው ወጣት፣ ሚስቱን ለማግኘት ሲያገለግል ጋብቻው በችኮላ እንዳይፈጸም ያደርጋል፤ የፍቅሩን ጥልቀት ለመፈተን ዕድል ይፈጥራል፤ በተጨማሪም ለሚመሠርተው ቤተሰብ የሚያስፈልገውን ሁሉ ማቅረብ የሚችል መሆኑ ይፈተናል። በዚህ በእኛ ዘመን ተቃራኒውን ስለምናደርግ ብዙ መቅሰፍት እንዲወርድ ምክንያት ሆነናል።12 Patriarchs and Prophets, pp. 188, 189.AHAmh 57.1

    የገንዘብ አያያዝ ችሎታ የሌለው ወንድ ይቅርታ ሊደረግለት አይችልም። ስለ ብዙ ወንዶች - እርሱ የዋህ ተወዳጅ ለጋስና ጥሩ ክርስቲያን ሰው ነው ግን የራሱን ሥራ የማስተዳደር ብቃት የለውም ይባላል። ይህ ማለት ገንዘብ ወጪ በማድረግ ረገድ ይህ ሰው ገና ህጻን ነው ማለት ነው። እራስን የመቻል መርሆዎችን ሳያውቅና ልምምድ ሳያደርግ ነው ወላጆቹ ያሳደጉት።13Letter 123, 1900.AHAmh 57.2