Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የአድቬንቲስት ቤት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ክፍል ፪—የሕብረተሰብ ብርሃን

    ምዕራፍ አራት—አድማሰ-ሰፊው የቤተሰብ ተጽዕኖ

    የክርስቲያን ቤተሰብ የተግባር ትምህርት ምሣሌ ነው፦ የቤተሰብ ተልዕኮ ከአባላቱ ያለፈ መሆን አለበት። የክርስቲያን ቤተሰብ የላቀውን እውነተኛየሕይወት መርህ በተግባር የሚያሳይ ይሁን። ከእንዲህ ዓይነት ቤት የወጡ አባላት የተማሯቸውን ትምህርቶች ለሌሎች ያካፍሉ። መልካም የሕይወት መመሪያዎች ለሌሎች ቤተሰቦች ሲተዋወቁ ከፍ ከፍ የሚያደርግ ተጽዕኖን በህብረተሰቡ ውስጥ ይፈጥራሉ።1Ministry of Healing, p. 352.AHAmh 14.1

    አባላቱ ጨዋና ትሁት የሆኑበት ቤት ለመልካም ነገር ተምሣሌነቱ ጥልቅና ሰፊ ነው። በእንደዚህ ዓይነት ቤት የተገኘውን ውጤት ሌሎች ቤተሰቦች ልብ ይሉታል። የተቀመጠላቸውን ምሣሌም በመከተል የራሳቸውን ቤተሰብ ከሰይጣናዊ ተጽዕኖ ይጠብቃሉ። ለእግዚአብሔር ፈቃድ ትኩረት የሚሰጥበትን ቤት መላእክት ሁልጊዜ ይጎበኙታል። በመለኮታዊ ፀጋ ኃይል ሥር ያለ ይህ ቤት ለደከሙና ለዛሉ የእምነት መንገደኞች የመነቃቂያ ቦታ ይሆናል። ጥንቁቅ በሆነ ጥበቃ እራስ(self ) እኔነቱን ከማወጅ ይታቀባል። ትክክለኛ ልማዶች ይቀረጻሉ። የሌሎችን መብት የመጠበቅ ጥንቃቄም ይደረጋል። በፍቅር የሚሠራውና ነፍስን የሚያነፃው እምነት መሪ በመሆን ቤተሰቡን ሁሉ ይቆጣጠራል። በእንደዚህ የተቀደሰ ተምሣሌነት ያለው ቤት ሥር በእግዚአብሔር ቃል መሠረቱን የጣለ የወንድማማችነት መመሪያ በስፋት ይታወቃል፤ ይከበራልም።2Letter 272, 1903.AHAmh 14.2

    ሥርዓት ያለው ቤተሰብ ተጽዕኖ፦ ለአንድ ቤተሰብ የሱስን ወክሎ መቆም፤ በማያምን ህብረተሰብ መካከል የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ መጠበቅ ቀላል ነገርአይደለም። ለሰዎች የታወቅንና የምንነበብ ሕያው መልእክት ልንሆን ይጠበቅብናል። ይህ ሥራ አስፈሪ የሆኑ ኃላፊነቶችን የያዘ ነው።3Testimonies for the Church, Vol. 4, p. 106.AHAmh 14.3

    አንድ ሥርዓት ያለውና የታረመ ቤተሰብ እስካሁን ከተሰበኩት ስብከቶች ሁሉ በላቀ ሁኔታ ስለ ክርስቲያናዊነት ይናገራል። የእንደዚህ ዓይነት ቤተሰብ ወላጆች የእግዚአብሔርን አቅጣጫ በመከተል የተሳካላቸው ማስረጃ የሚሆኑ ሲሆን፤ልጆቻቸውም በቤተ-ክርስቲያን ጌታን የሚያገለግሉ ይሆናሉ። ተጽዕኖአቸው እየበረታ ይሄዳል። ሲሰጡም በበለጠ ይለግሱ ዘንድ እንደገና በገፍ ይጨመርላቸዋል። ልጆችም ከቤት የተማሩትን ለሌሎች በማካፈል ለወላጆቻቸው ረዳት ይሆኑላቸዋል። የሚኖሩበት አካባቢም ይጠቀማል፤ ለዘመንና ለዘለዓለም በልጽገውበታልና። ቤተሰቡ በሙሉ በጌታ ሥራ ይጠመዳል። በእነርሱም መልካም ምሣሌነት የተነሣ ሌሎች መንጋውን - ያማረውን መንጋ - በመንከባከብ ረገድ ለእግዚአብሔር ታማኝና እውነተኛ እንዲሆኑ ያበረታታሉ።4Review and Herald, June 6, 1899.AHAmh 14.4

    የክርስትናን ኃይል ለዓለም ለማሳየት እንደ ማረጋገጫነት ሊቀርቡ ከሚችሉ ማስረጃዎች ሁሉ ሥነ-ሥርዓት እንዳለው ጨዋ ቤተሰብ ያለ የለም። ሌላ ምንም ነገር ሊመሰክረው በማይችል መንገድ እውነትን ይመሰክራል፤ እውነት በልብ ላይ ያለውን ተግባራዊ ኃይል የሚያሳይ ሕያው ምስክር ነውና።5Testimonies for the Church Vol. 4, p.304.AHAmh 15.1

    ወደር የማይገኝለት የክርስቲያን ቤተሰብ ሕይወት ቅምሻ ማለት በክርስትናቸው ምክንያት የሚገኘው ባህርይ ነው። ከመልካም መንፈሳዊ የቃል ምሥክርነት ይልቅ ተግባር አጉልቶ ይናገራል።1Patriarchs and Prophets, p. 579.AHAmh 15.2

    በዚህ ዓለም የእኛ ኃላፊነት…. ልጆቻችንና ቤተሰቦቻችን ምን ዓይነት ባህርይ መያዝ እንዳለባቸው በማወቅ፤ እንዴት እንደምናስተምራቸውም በመረዳት በማስተማሪያው ጠረጴዛ ኋላ ባንቆምም እንኳ በሌሎች ቤተሰቦች ላይ መልካም ተጽዕኖ የሚያሳድር ጉልበት እንፈጥራልን። ሥርዓት ያለው ጨዋ ቤተሰብ ከነጠረ ወርቅ ደግሞም ከወቄት የዖፊር ወርቅ ስፍር የከበረ ነው።7Manuscript 12, 1895AHAmh 15.3

    ግሩም እድሎች የእኛ ናቸው፦ በዚህ ምድር ያለን ጊዜ አጭር ነው። በዚህ ዓለም የምናልፈው አንድ ጊዜ ብቻ ነው። ከማለፋችን በፊት ግን የተሰጠንን ሕይወት በምንችለው ሁሉ እንጠቀምበት። ልንሠራው የተጠራንለት ሥራ ሀብትና ሥልጣን ወይም የተለየ ችሎታን አይጠይቅም። የሚፈለገው ደግና ራስን መስዋዕት የሚያደርግ መንፈስ፣ እንዲሁም ጽኑ ዓላማ ነው። ጭልጭል የምትል ትንሽ መብራት በቋሚነት የምትበራ ከሆነ (ብርሃንዋ በቂም ባይሆን) ሌሎች ፋኖሶችን (ኩራዞችን) ለመለኮስ ታገለግላለች። የተጽዕኖ ክልላችን ጠባብ ሊመስል፣ ችሎታችን ዝቅተኛ፤ አጋጣሚዎቻችን ጥቂት፤ ይዞታችንም ውስን ሊሆን ይችላል። ሆኖም በራሳችን ቤት ውስጥ ያሉትን እድሎች በእምነት ከተጠቀምንባቸው ግሩም አማራጮች ሁሉ የእኛ ናቸው። ልባችንንና ቤታችንን ለመለኮታዊው የሕይወት መመሪያ ከከፈትን ሕይወት ሰጪ ለሆነው ኃይል የመተላለፊያ ቱቦ እንሆናለን። ባዶነትና ረሃብ በሞላበት በአሁኑ ዘመን ከቤታችን ሕይወትን መልካምነትንና ፍሬያማነትን የሚያመጣ ጅረት ይፈስሳል።8Ministry of Healing, p. 355.AHAmh 15.4

    ፈሪሃ-እግዚአብሔር ያላቸው ሰዎች ከራሳቸው ቤተሰብ ወደ ሌሎች የሚያሰራጩት ተጽዕኖ ልክ በሦስት መስፈሪያ ዱቄት ውስጥ እንዳለ እርሾ ነው።9Signs of the Times, Sept. 1894.AHAmh 15.5

    በቤት ውስጥ አጥጋቢ በሆነ ሁኔታ የተከናወነ ሥራ ሌሎችም በተመሳሳይ ደረጃ እንዲሠሩ ያስተምራል። ለእግዚአብሔር ያለን የታማኝነት መንፈስ እንደ እርሾ ነው፤ በቤተ-ክርስቲያን ሲታይም በሌሎች ላይ ተጽዕኖ በመፍጠር በሁሉም ቦታ ክርስትና ምን እንደሚመስል ምሥክር ይሆናል። ልበ-ሙሉ የሆኑ የክርስቶስ ወታደሮች ሥራ ተጽዕኖው ድንበር-የለሽ ነው። የአገልግሎት መንፈስ በቤተ-ክርስቲያኖቻችን የጠፋው ታዲያ ለምንድን ነው? ምክንያቱ! የቤተሰብ ቅድስና ቸል ስለተባለ ነው።10Review and Herald, Feb. 1895.AHAmh 15.6

    ቁጥጥር አልባ የሆነ ቤተሰብ ተጽዕኖ፦ በተገቢው መንገድ ያልተገራ ቤተሰብ ተጽዕኖው ሰፊ ነው። የህብረተሰብ አጥፊ ነው። ቤተሰብን ህብረተሰብንና መንግሥትን የሚነካ የክፋት ማዕበል የሚያከማች ነው።11Patriarchs and Prophets, 579.AHAmh 16.1

    ለሌሎች በምንም ዓይነት ተጽዕኖ በማንሆንበት ሁኔታ በዚህ ዓለም ልንኖር አይቻለንም። አንድ የቤተሰብ አባል እራሱን (እሱነቱን) በራሱ ውስጥ ደብቆ ሌሎቹ የቤተሰቡ አባላት መንፈሱና ተጽዕኖው እንዳይደርስባቸው ማድረግ አይችልም። በፊቱ የሚንፀባረቀው ነገር እንኳ የክፋት ወይም የመልካም ተጽዕኖ አለው። ወኔው ንግግሩና ድርጊቱ እንዲሁም የሚያሳየው ጠባይ ሁሉ ለሌሎች በማያጠራጥር ሁኔታ ግልጽ ነው። በራስ-ወዳድነት ውስጥ የሚኖር እርሱ፣ ነፍሱን ወባ በበዛበት አየር የከለለ ነው። በክርስቶስ ፍቅር የተሞላ ከሆነ ግን ርኅራኄና ደግነት የሚያሳይ፤ ለሌሎች ስሜት የሚጨነቅና ከግብረ-አበሮቹም ጋር ያለ ግብዝነት፣ በለዘብታ፣ በፍቅርና በደስታ ስሜት የሚነጋገር ይሆናል። ለየሱስ እንደሚኖር፤ በየቀኑ ከእግሩ ሥር ሆኖ እንደሚማር፣ ብርሃኑንና ፀጋውን እንደሚቀበል በግልጽ ይታያል። ለጌታም እንዲህ ማለት ይችላል “ማዋረድህም አበዛኝ’’። 12The Youth’s Instructor, June 22, 1893.AHAmh 16.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents