Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የአድቬንቲስት ቤት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ ስድሳ አንድ—የቤተሰብ ገንዘብ አያያዝ መርሆዎች

    ገንዘብ በረከት ወይም እርግማን ሊሆን ይችላል፦ ገንዘብ የግድ መርገም ነው ማለት አይደለም፤ ከፍተኛ ዋጋ ያለው ነው፤ ምክንያቱም በተገቢው መንገድ ከተመደበ በነፍሳት ደህንነት ላይ በመሥራትና ከእኛ የባሰ ድኃ የሆኑትን በመባረክ መልካም ተግባር ሊያከናውን ይችላል። ለነገ በማይል ወይም ብልሃት በሌለው አጠቃቀም ገንዘብ ለባለቤቱ ወጥመድ ሊሆን ይችላል። ዝናውንና ምኞቱን ለማሳካት ገንዘቡን የሚያጠፋ ለራሱ እርግማን እንጂ በረከት አይሆንለትም። ገንዘብ የፍላጎት ቋሚ መፈተኛ ነው። ማንም በእርግጥ ከሚያስፈልገው በላይ ካለው በምናባዊ ምኞት የጌታውን የአደራ ገንዘብ በከንቱ የሚያባክን እምነተ-ጎደሎ አገልጋይ እንዳይሆን፣ የራሱን ልብ ያውቅና ሐሳቡን በትጋት ይቆጣጠር ዘንድ ጥበብና ፀጋ ሊለምን ይገባዋል።AHAmh 270.1

    እግዚአብሔርን ከሁሉም በላይ አብልጠን ስንወደው ጊዜያዊ ነገሮች በፍላጎቶቻችን ውስጥ ትክክለኛ ቦታቸውን ይይዛሉ። የእግዚአብሔርን በረከቶች በትክክለኛው መንገድ እንጠቀምባቸው ዘንድ በየዋህነትና በሐቀኝነት እውቀትን ብንሻ፣ ጥበብን ከላይ እንቀበላለን። ልብ ወደራሱ ምርጫና ዝንባሌ ሲያጋድል፤ ገንዘብ ያለ እግዚአብሔር ሞገስ ደስታን ሊያመጣ ይችላል የሚለው ሐሳብ ሲጠና፤ ገንዘብ በአምባ-ገነንነት ሰውየውን ይገዛዋል። ልበ-ሙሉነቱንና ክብሩን ወስዶ እንደ አምላክ ይመለካል። ክብር፣ እውነት፣ ጽድቅና ፍርድ በገንዘብ መሠውያ ላይ ይሰዋሉ። የእግዚአብሔር ትዕዛዛት ወደ ጎን ተገፍትረው ንጉሥ ገንዘብ (King Mammon) ያቋቋማቸው የዚህ ዓለም ልማድና የገንዘብ አጠፋፍ ባህል ተቆጣጣሪ ኃይላት ይሆናሉ። 1 Letter 8, 1889.AHAmh 270.2

    የቤት ባለቤትነት ዋስትናን ፈልጉ፦ የእግዚአብሔር ሕጎች ተከብረው ቢሆን ኖሮ በአሁኑ ሰዓት ያለው የዓለም ሁኔታ እንዴት የተለየ ይሆን ነበር። በግብረ-ገብነት፣ በመንፈስና በባህርይ መሻሻል ይኖር ነበር እንጅ ራስ-ወዳድነትና ከሌላው በላይ አስፈላጊ ነኝ ብሎ ማሰብ እንዲህ እንደ ዛሬው አይንፀባረቅም ነበር። በምትኩ እያንዳንዱ ሰው ለሌሎች ደስታና ደህንነት ግድ ይለው ነበር…. የድኃው መደብ በሀብታሞች የብረት ተረከዝ ሥር ተረግጦ በመኖር ፈንታ፤ ዓለማዊም ሆነ መንፈሳዊ ነገሮችን ለማቀድና ሥራ ላይ ለማዋል ሰዎች የሌሎቹን ጭንቅላት ከመጠቀም ይልቅ ለነፃ ሐሳብና ተግባር ዕድል ይኖራቸው ነበር።AHAmh 270.3

    የራሳቸው ቤት ባለቤት የመሆናቸው ሐሳብ ለመሻሻል ጠንካራ ፍላጎት እንዲያድርባቸው ያነሣሳቸው ነበር። ለራሳቸው ለማቀድና ለመፍጠር የሚያስችላቸውን ዕውቀት ሳይዘገዩ ይገበዩበትም ነበር፤ ልጆቻቸው የታታሪነትና የቆጣቢነት ትምህርት በቀሰሙ፣ ጭንቅላታቸውም እጅግ በሰፋ ነበር። የጠፋባቸውን የራስ ክብራቸውንና የግብረ-ገብነት ነፃነታቸውን አብዛኛውን መልሰው ባገኙና እንደባርያ ሳይሆን እንደ ነፃ ሰው በተሰማቸው ነበር። 2Historical Sketches of S.D.A. Foreign Missions, pp. 165, 166.AHAmh 270.4

    ከከተማ ወጥተው ወደ ገጠሩ በመሄድ ትንሽ ቁራጭ መሬት እንዲወስዱና ለራሳቸውና ለልጆቻቸው መጠለያ ይሠሩ ዘንድ ሕዝቦችን አስተምሩ። 3General Conference Bulletin, April 6, 1903.AHAmh 271.1

    ቤቶችን ስለመሸጥ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ፦ ቤቶቻቸውን ሸጠው ያገኙትን ለወንጌሉ ሥራ መስጠት ይገባቸው እንደሆነ ምክር ለመጠየቅ የሚጽፉልኝ ብዙ ድኃ ወንዶችና ሴቶች አሉ። የተራድኦ ገንዘብ የመሰብሰብ ፍላጎታቸው ልባቸውን እንደሚያውከውና ሁሉን ላደረገላቸው ለጌታ የሆነ ነገር ማድረግ እንደሚፈልጉ ይናገራሉ። ለእነዚህ እንዲህ እላለሁ፡- “ትንንሽ ቤቶቻችሁን እንድትሸጡ የእናንተ ኃላፊነት አሁን ላይሆን ይችላል፤ እራሳችሁን ይዛችሁ ወደ ጌታ ሂዱ። ኃላፊነታችሁን እንድትረዱ ጥበብ ታገኙ ዘንድ ጌታ በእርግጥ ልባዊ ፀሎታችሁን ይሰማል።” 4Testimonies for the Church, Vol. 5, p. 734.AHAmh 271.2

    ሕዝቦች ይኖሩበት ዘንድ ያሏቸውን ቤቶች አሁን እንዲሰጡት እግዚአብሔር አይጠይቅም፤ በሙላት ያላቸው ግን አሁን ሲጠራቸው ድምፁን የማይሰሙ ከሆነና ከዓለም ጋር ካልተለያዩ፤ ለእግዚአብሔር ሊሰው ፈቃደኛ ካልሆኑ፤ እነርሱን ያልፋቸውና ለየሱስ የትኛውንም ዓይነት ነገር ሊያደርጉለት ፈቃደኛ የሆኑትን ይጠራል። የእርሱን ዓላማ ለማሳካት ቤታቸውን መሸጥ ቢያስፈልጋቸው እንኳ ያደርጉታል። 5Review and Herald, Sept. 16. 1884.AHAmh 271.3

    ሊመሠገን የሚገባው ነፃነት፦ ሊመሠገን የሚገባው የነፃነት ምኞት አለ። የራሳችሁን ክብደት በመሸከም፣ የጥገኝነት ዳቦ ላለመብላት መጣር ትክክል ነው። ራስን የመርዳት ምኞትን የሚቆጣጠረው ጉጉት ታላቅና የከበረ ነው። የታታሪነት ልምድና ቆጣቢነት አስፈላጊዎች ናቸው። 6Testimonies for the Church, Vol. 2, p. 308.AHAmh 271.4

    ወጪና ገቢን (በጀትን) ማመጣጠን፦ ብዙዎች በጣም ብዙዎች በገቢያቸው መጠን ልክ ወጪያቸውን መገደብ እራሳቸውን አላስተማሩም። ከሁኔታዎች ጋር እንዲለማመዱ እራሳቸውን አያስተምሩም፤ ደጋግመው ደጋግመው በመበደር እዳ ይወርሳቸዋል፤ ግብረ-ገብነታቸው የወረደና ተስፋ የቆረጡም ይሆናሉ። 7Review and Herald, Dec. 19, 1893.AHAmh 271.5

    ወጫችሁን ሁሉ መዝግቡ፦ በሚስትና በእናት በኩል ያለው እራስን የማርካት ልማድ ወይም የችሎታና የብልሃት ማነስ፣ የጎተራው መራቆት የሁልጊዜ ምክንያት ሊሆን ይችላል። እንዲህም ሆኖ እናት የተቻላትን ሁሉ እየጣረች እንደሆነ ይሰማታል። ምክንያቱ ደግሞ የራስዋንም ሆነ የልጆችዋን ፍላጎት የመገደብ ትምህርት ስላልተማረች ነው፤ ወይም በቤት አያያዝ ጉዳዮች ችሎታውም ጥበቡም ፈጽሞ የላት ይሆናል። በዚህ ምክንያት አንድን ቤተሰብ ለማስተዳደር የሚያስፈልገው ገንዘብ ተመሳሳይ የአባላት መጠን ያለውን ሌላ ቤተሰብ ሊመግብ ከሚችለው እጥፍ ሊሆን ይችላል።AHAmh 271.6

    ሁሉም የወጪ ሂሳብ መዝገብ እንዲኖራቸው መማር ያስፈልጋቸዋል። አንዳንዶች ይህ አላስፈላጊ እንደሆነ ያስባሉ፤ ስህተት ነው። እያንዳንዱ ወጪ በትክክል መመዝገብ አለበት። 8Gospel Workers, p. 460.AHAmh 272.1

    የአባካኝነት ልማድ መቅሰፍቶች፦ ልጆቻቸውን ስለጥብቅ የቁጠባ ቁጥጥር እንዲያስተምሩ ወላጆችን እገስጽ ዘንድ በአባካኝነት ምክንያት የሚመጡትን መቅሰፍቶች እንዳይ እግዚአብሔር ፈቅዶ ነበር። በእርግጥ ለማያስፈልጋቸው ነገር የወጣ ገንዘብ ከትክክለኛ ጠቀሜታው የተዛባ እንደሆነ አስ ተምሯቸው። 9Christian Temperance and Bible Hygiene, p. 63.AHAmh 272.2

    የአባካኝነት ልማድ ካሉባችሁ ወዲያውኑ ከሕይወታችሁ ቆርጣችሁ ጣሏቸው። ይህንን ካላደረጋችሁ በስተቀር ለዘለዓለም የከሰራችሁ ትሆናላችሁ። ለልጆቻችሁ የምታወርሷቸው የቆጣቢነት፣ የታታሪነትና የአሳቢነት ልምዶች ከተትረፈረፈ ጥሎሽ የተሻሉ ድርሻዎች ናቸው።AHAmh 272.3

    በዚህ ምድር ተጓዦችና እንግዳዎች ነን። እግዚአብሔር እንድንገታው የሚፈልግብንን ፍላጎት በማርካት ገንዘባችንን አንጨርሰው። ፍላጎታችንን በመቆጠብ ለእምነታችን ገጣሚነታችንን እናሳይ። 10Review and Herald, Dec. 24, 1903.AHAmh 272.4

    ለአባካኝ ወላጅ የተሰጠ ተግሳጽ፦ ገንዘብህን በሥነ-ሥርዓት እንዴት እንደምትጠቀምበት አታውቅም፤ እንደ ገቢህ መኖርም አልተማርህም…. ዝንባሌህ እንደመራህ በነፃነት መጠቀም ትችል ዘንድ ገንዘብ የማግኘት ፍላጎትህ እጅግ ከፍተኛ ነው። አስተምህሮህና ምሣሌነትህ ለልጆችህ መርገም ሆኗል። እግዚአብሔርን የበለጠ እየረሱት፣ እርሱን ቅር የማሰኘቱም ፍራቻ እየቀነሰባቸው፣ ለቁጥብነት ያላቸውትዕግሥት እየተሟጠጠባቸው ሄዷል። ገንዘብ በቀላሉ በተገኘ ቁጥር አመስጋኝነት እየቀነሰ ይሄዳል።11Letter 8, 1889.AHAmh 272.5

    ከገቢው በላይ ለሚኖር ቤተሰብ፦ ወጫችሁ ከገቢያችሁ እንዳይበልጥ ተጠንቀቁ። ፍላጎታችሁን እሰሩ።AHAmh 272.6

    ገንዘብን በማውጣት ረገድ ባለቤትህም አንተን መሰል መሆንዋ፣ ትልልቅ ወጪዎችን ለማስወገድ ጥቃቅን ነገሮች ላይ ጥንቃቄ በማድረግ ልትረዳህ አለመቻልዋ እጅግ የሚያሳዝን ነው። አላስፈላጊ የሆኑ ወጪዎች በተደጋጋሚ በቤተሰቡ አስተዳደር ውስጥ ይታያሉ። ባለቤትህ፣ ልጆቻችሁ አቅማችሁ የማይፈቅደውን ልብስ ቢለብሱ ትወድዳለች፤ በዚህም ምክንያት ግብዝና ኩሩ የሚያደርጓቸው ምርጫዎችና ልማዶች በልጆቻችሁ ዘንድ ይጎለምሳሉ። የቆጣቢነትን ትምህርት ብትማሩ ኖሮ፣ ገንዘባችሁን በልቅነት የመጠቀማችሁ ልማድ ለራሳችሁና ለእግዚአብሔር ሥራ የሚያመጣውን ጥፋት ብታስተውሉ ኖሮ፣ የክርስትና ባህርያችሁን ወደ ፍጽምና የሚመራውን አስፈላጊ ልማድ ማግኘት በቻላችሁ ነበር። ይህንን እውቀት ካልቀሰማችሁ በስተቀር በሕይወት እስካሉ ድረስ ልጆቻችሁ ይህንን የተዛባ የትምህርት ይዘት ወርሰው ይኖራሉ….AHAmh 272.7

    ሀብታችሁን እንድታከማቹ ተጽዕኖ አላደርግባችሁም - ይህንን ማድረግ ሊከብዳችሁ ይችላል። የምመክራችሁ ግን የገንዘባችሁ አጠቃቀም በጥንቃቄ እንዲሆን፤ የዕለት ተዕለት ምሣሌነታችሁም ቁጠባን፣ እራስን መካድ እንዲሁም የምጣኔ ሀብት አያያዛችሁ ለልጆቻችሁ ትምህርት እንዲሆን ነው። በመርህና በምሣሌነት ልጆቻችሁ ሊማሩ ያስፈልጋቸዋል። 12Letter 23, 1888.AHAmh 273.1

    መሻቱን እንዲገዛ የተጠራ ቤተሰብ፦ ወንድሜና እህቴ ሆይ! ብዙ ልትማሩአቸው የሚገቧችሁ ነገሮች እንዳሉ አይቻለሁ። እንደአቅማችሁ መኖር አልቻላችሁም። መቆጠብ አልተማራችሁም። ከፍተኛ ደሞዝ ብታገኙ እንኳ ገንዘቡ ለረዥም ጊዜ እንዲቆይላችሁ እንዴት መጠቀም እንዳለባችሁ አታውቁም። አርቆ ከማሰብ ይልቅ ምርጫችሁንና ፍላጎታችሁን ታጤናላችሁ። አንዳንድ ጊዜ የወንድሞቻችሁ አቅም የማይፈቅደው ውድ ምግብ ላይ ብዙ ገንዘብ ታወጣላችሁ። ብሩ ሳይታወቃችሁ ነው ከኪሳችሁ የሚወጣው.... ሁለታችሁም ገና ልትማሩ የሚገባችሁ የቀራችሁ ትምህርት አለ፤ እርሱም መሻትን መግዛት ነው። 13Testimonies for the Church, Vol. 2, pp. 431, 432.AHAmh 273.2

    ወላጆች አቅማቸውን ያገናዘበ ኑሮ መኖር ይገባቸዋል። በምክርና በምሣሌነት ልጆቻቸውን በማስተማር መሻትን መግዛት እንዲያጎለብቱ መርዳት ይኖርባቸዋል። ለአዕምሮ እድገትና ለመንፈሳዊነት ልማድ ጊዜ ይኖር ዘንድ የሚቀርቡላቸው ነገሮች ጥቂትና ቀላል ይሁኑ። 14Review and Herald, June 24, 1890.AHAmh 273.3

    ማሞላቀቅ የፍቅር መግለጫ አይደለም፦ ለእነርሱ ያላችሁ ፍቅር የሚገለጸው የመኮፈስ ፍላጎታቸውን፣ የኩራት፣ የአባካኝነታቸውንና የታይታ ጥማታቸውን ስታረኩላቸው እንደሆነ ለልጆቻችሁ አታስተምሩ። አሁን በአዳዲስ ፈጠራዎች ላይ ገንዘብን ለማባከን ጊዜ የለም። የፈጠራ ችሎታችሁን ሀብታችሁን ለመቆጠብ ተጠቀሙበት። 15Testimonies for the Church, Vol. 6, p. 451.AHAmh 273.4

    ቆጣቢነት ከለጋስነት ጋር አብሮ ይሄዳል፦ በዚህ ዘመን ያለው ወጣት ተፈጥሮአዊ ዝንባሌ ቁጠባን ቸል በማለትና በማውገዝ ከጠባብነትና ከቆጥቋጣነት ጋር ያያይዘዋል። ሆኖም ቆጣቢነት ከሰፊና ነፃ አስተሳሰብ ዕይታዎች ጋር አብሮ የሚሄድ ነው፤ ይህ በማይተገበርበት እውነተኛ ለጋስነት ሊኖር አይችልም። የምጣኔ ሀብትን ጥናትና የጥቃቅን ነገሮች አያያዝን ትምህርት ማንም የበታች አድርጎ አይመልከተው። 16Id., Vol. 5, p. 400AHAmh 273.5

    ሌላኛው ጽንፈ-ሐሳብ፤ ጥበብ የጎደለው የንብረት አያያዝ፦ ሰውነት ቸል ሲባል ወይም ያለ አግባብ ሲጎዳ ለአገልግሎቱም ብቁ መሆን ሲሳነው እግዚአብሔር አይከብርም፤ የሚስማማና የሚያጠነክር ምግብ ለሰውነት ማቅረብ ከባለቤቱ ተቀዳሚ ኃላፊነቶች አንዱ ነው። የተመጣጠነ ምግብ ለማቅረብ ከመሰሰት፣ ርካሽ ልብስና የቤት እቃ መግዛት በእጅጉ የተሻለ ነው።AHAmh 273.6

    አንዳንድ ቤተሰቦች እንግዶችን ውድ በሆኑ ነገሮች ለማዝናናት ሲሉ ቤተሰቡ ለምግብ መግዣ የሚጠቀምበትን ገንዘብ በማውጣት፣ የመብል ገበታቸውን ያራቁታሉ። ይህ ብልሃት የጎደለው፣ የለየለት መጃጃል ነው። ጎብኝዎችን በማስተናገድ ረገድ ቀለል ያሉ ወጪዎችን ብቻ በማውጣት የቤተሰቡ ፍላጎት ተቀዳሚ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።AHAmh 274.1

    የገንዘብ የሞኝነት አያያዝና የተፈጠሩ ባህሎች ብዙ ጊዜ አስፈላጊ የሆኑ በጎነቶችንና በረከት የሚያመጡ አድራጎቶችን ከመፈጸም ይገድቡናል። ጠረጴዛችን ላይ በማንኛውም ቀን የሚቀመጠው ምግብ ያልተጠበቀ እንግዳ ቢመጣ እንኳን እናት ተጨማሪ ምግብ በማዘጋጀት እራስዋን ሳታጨናንቅ በጥሩ ሁኔታ ሊስተናገድበት የሚያስችል መሆን ይገባዋል። 17Ministry of Healing, p. 322.AHAmh 274.2

    የገንዘብ አያያዛችን ወደማያጠግብ መብል ፈጽሞ ሊመራን አይገባም። ተማሪዎች የተመጣጠነ ምግብ በገፍ ሊቀርብላቸው ይገባል። የማብሰል ሥራ የተሰጣቸው እነርሱ ትርፍራፊውን ሁሉ በመሰብሰብ ምንም ነገር እንዳይባክን ያድርጉ። 18Testimonies for the Church, Vol. 6, p. 209.AHAmh 274.3

    ገና ሊሠራ ያለው ታላቅ ሥራ አለና ቆጣቢነት፣ የአርቆ አሳቢነት ወይም የአስተዋይነት መገለጫ እንጂ ገብጋባነት አይደለም። 19Letter 151, 1899.AHAmh 274.4

    የሚስት ድካም ይቀልላት ዘንድ ምቹ ሁኔታ ይፈጠርላት፦ የወንድም ኢ(E) ቤተሰብ እጅግ ቁጥጥር የበዛበት የምጣኔ ሀብት አያያዝ መርህ የሚከተል ነው….ወንድም ኢ ሆን ብሎ ለበርካታ ቤተሰቡ አመቺ የሆነ የእንጨት ቤትና ወጥ ቤት መገንባት አልፈለገም፤ ምክንያቱ ደግሞ የእግዚአብሔርን ሥራ ወደ ፊት የሚያራምድ ገንዘብ በሚፈለግበት ጊዜ ለግል ምቾት ገንዘቤን አላጠፋም የሚል ነው። ነገር ግንለልጆቹ ግብረ-ገብነትና ጤና እንዲሁም ለሚስቱ ምቾትና የሥራ ቅለት ይህ መሆን እንዳለበት ላሳየው ሞክሬአለሁ። 20Letter 9, 188.AHAmh 274.5

    ለሚስት የግል ጉዳዮችዋ የሚፈቀድላት ገንዘብ፦ መረዳዳት ግዴታችሁ ነው። የእጅ ቦርሳዋን ማንገቻ ጨምድደህ ይዘህ ለሚስትህ ገንዘብ እምቢ ማለትህን እንደ መልካም ጠባይ እንዳትመለከተው። 21Letter 65, 1904.AHAmh 274.6

    ለሚስትህ በየሣምንቱ የተወሰነ ገንዘብ ፍቀድላት፤ ደስ የሚያሰኛትን ነገር ታድርግበት። ምርጫዋንና ችሎታዋን እንድትጠቀም እድል አልሰጠሃትም፤ ሚስት መያዝ ያለባትን ደረጃ በውል ማስተዋል አልቻልህም። ሚስትህ ግሩምና አመዛዛኝ ጭንቅላት ያላት ናት። 22Letter 47, 1904.AHAmh 274.7

    ከምታገኘው ገንዘብ ለሚስትህ አካፍል፤ የምትሰጣት ገንዘብ የወደደችውን የምታደርግበት የራስዋ ይሁን። ሠርታ የምታገኘውን ገንዘብ እንደማስተዋልዋ ትጠቀምበት ዘንድ ይፈቀድላት እንደነበረው ይሁን። ነቀፋ ሳይደርስባት የምትጠቀምበት የራስዋ የሆነ ገንዘብ ቢኖራት ኖሮ ከባድ ጫና ከአዕምሮዋ በተነሳላት ነበር። 23Letter 157, 1903.AHAmh 274.8

    የምቾትና የጤና መሻት ይኑር፦ ወንድም ፒ(P) ገንዘቡን በብልሃት እየተጠቀመ አይደለም። የልጆቹ ውትወታና ፍላጎት ያሳደረበትን ተጽዕኖ ያህል ጥበብ የተሞላበት ማመዛዘን ተጽዕኖ አላደረገበትም። በእጁ ላይ ካለው ገንዘብ ምን ያህሉን መጠቀም እንዳለበት ግምት የለውም፤ ምቾትንና ጤናን ለመጠበቅ በጣም አስፈላጊ ለሆኑት ነገሮች ብቻ ገንዘብ ማውጣት እንዳለበት አያስተውልም። በዚህ ረገድ ሁሉም ቤተሰብ መሻሻል ያስፈልገዋል። ቤተሰቡ ሕይወትን ቀለል የሚያደርጉና ምቾት የሚፈጥሩ ብዙ ነገሮች ያስፈልጉታል። በቤተሰብ ጉዳዮች አደረጃጀት ለሥርዓትና ደንብ ዋጋ አለመስጠት ወደ ጥፋት የሚመራና ታላቅ ጉዳት የሚያመጣ ነው። 24Testimonies for the Church, Vol. 2, p. 699.AHAmh 275.1

    ሰውነታችንን በድሪቶ በመሸፈናችን ወይም ሕይወትን ቀላል የሚያደርጉ ምቾትንና ምርጫን የሚጠብቁ ነገሮችን ከቤት በማጥፋታችን ልባችን የተሻለ ንጽህና ወይም ቅድስና እንዲኖረው ማድረግ አንችልም። 25Review and Herald, May 16, 1882.AHAmh 275.2

    ሕዝቦች ለምቾታቸውና ለጤናቸው በእርግጥ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች እራሳቸውን ይነፍጉ ዘንድ እግዚአብሔር አይፈልግም፤ ታይታን፣ አባካኝነትንና ልቅነትን ግን እርሱ አይወድም። 26Review and Herald, Dec. 19, 1893.AHAmh 275.3

    መቼ መቆጠብና መቼ መጠቀም እንዳለባችሁ ተማሩ፦ መቼ መቆጠብና መቼ መጠቀም እንዳለባችሁ ተማሩ። ራሳችንን ክደን መስቀሉን ካላነሳን የክርስቶስ ተከታዮች ልንሆን አንችልም። የህይወትን መንገድ ስንጓዝ ሳለ መክፈል ያለብንን በሐቀኝነት እንክፈል። የተንዘላዘሉትን ስፌቶች ሸክፉ፤ የተለያየውን ጠርዝ አያይዙ፤ የኔ ብላችሁ ልትጠሩት የምትችሉትን እወቁ። እራስን ለማስደሰት የወጡትን ሁሉንም ጥቃቅን ወጪዎች አስቧቸው። እንዲሁ ምርጫን ለማሳካት የሚወጣውንና የተጣመመ የመንደላቀቅ ፍላጎትን ለማርካት የምታወጡትን ልብ በሉ። እርባና-ቢስ ለሆኑ ነገሮች የምታወጡት ገንዘብ ኑሮአችሁን ለሚያቀልሉና ምቾታችሁን ለሚጨምሩ ለቤታችሁ አስፈላጊ በሆኑ ነገሮች ላይ ማጥፋት የነበረባችሁን ነው። ገብጋባ እንድትሆኑ አይደለም፤ ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ ግን ታማኞች ሁኑ። ገብጋባነት የእግዚአብሔርን ለጋስነት መሳደብ ነው፤ ከመጠን በላይ [እንዳገኙ] ገንዘብን መዝራትም እንዲሁ። ልትዘረዝሯቸው አስፈላጊ የማይመስሏችሁ ጥቃቅን የምትሏቸው ወጪዎች በመጨረሻ ሲጠራቀሙ ብዙ ገንዘብ የወጣባቸው ይሆናሉ። 27.Letter 11, 1888.AHAmh 275.4

    እራሱን ያስረከበ ልብ ምሪትን ያገኛል፦ ቁጠባ በእያንዳንዱ ነገር ላይ እንዴት እንደሚተገበር እዚህ ላይ መግለጽ አላስፈላጊ ሊሆን ይችላል። ሙሉ ልባቸውን ለእግዚአብሔር የሰጡ ቃሉን በመሪነቱ የተቀበሉ እነርሱ በሁሉም የኑሮ ኃላፊነቶች እራሳቸውን እንዴት መምራት እንዳለባቸው ያውቃሉ። የዋህና እራስን ዝቅ ያደረገ ልብ ካለው ከየሱስ ይማራሉ። የየሱስንም የዋህነት በማጎልበት ቁጥር ስፍር የሌላቸውን የፈተና በሮች ሊዘጉ ይቻላቸዋል። 28Christian temperance and Bible Hygiene, p. 63AHAmh 275.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents