Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የአድቬንቲስት ቤት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ምዕራፍ ሰማንያ ሦስት—የእርካታ ፍቅር አሳሳችነት

    ተፈጥሮአዊው ልብ እርካታ ይፈልጋል፡- አዕምሮ ወደ እርካታ ፍቅርና እራስን ወደ ማስደሰት የማዘንበል ተፈጥሮ አለው። ይህንን በገፍ ማቅረብ ደግሞ የሰይጣን መርሀ-ግብር ነው። #ነፍሴ በምን ሁኔታ ላይ ናት?; የሚለውን ጥያቄ ራሳቸውን ይጠይቁ ዘንድ ጊዜ እንዳይኖራቸው በዓለማዊ መደሰቻዎች የሰዎች አዕምሮ ይሞላ ዘንድ ሰይጣን ይፈልጋል። የእርካታ ፍቅር እንደ ተላላፊ በሽታ ነው። ለዚህ የተሰጠ አዕምሮ ደስታ ፍለጋ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ሁል ጊዜ ይኳትናል።1Counsels to Teachers, Parents, and Students, p. 337.AHAmh 382.1

    ዓለማዊው መደሰቻዎች የሚያነሆልሉ ናቸው፤ ለጥቂት ደቂቃዎች ዓለማዊ ደስታ ሲሉ ብዙዎች የሰማይን ጓደኝነት ከነሙሉ ሠላሙ ፍቅሩና ደስታው ጋር ይሰዋሉ። ነገር ግን እነዚያ በደስታ ምንጭነት የተመረጡት ነገሮች ሳይቆዩ ቀፋፊና እርካታ የማይሰጡ ሆነው ይገኛሉ።2Review and Herald, Jan. 29, 1884.AHAmh 382.2

    ወደ መዝናኛ ቦታዎች ሚሊዮኖች ይጎርፋሉ፡- ለእርካታ ያለው የጦፈ ፍላጎት ታይቶ የማይታወቅ ነው፤ ጤናንና ገንዘብን ጨምሮ የሚሰዋ ቅጥ ያጣ አባካኝነት በሁሉም ቦታ ተንሰራፍቷል። ቁጥር ሥፍር የሌላቸው ለመፈንጠዝ የቋመጡ ናቸው። በጥልቀት ማሰብ ወይም ማጥናት ስለማይለማመድ አእምሮ ውጥንና እርባና ቢስ ይሆናል። ድንቁርናን የተላበሰ ስሜታዊነት በሁሉም ሥፍራ አለ። እያንዳንዱ ነፍስ እንዲያድግ፣ እንዲነጥር፣ ከፍ ከፍ እንዲልና እንዲከብር እግዚአብሔር ይጠይቃል። ነገር ግን ብዙውን ጊዜ እያንዳንዱ ዋጋ ያለው ስኬት ፋሽንን በሚከተል ታይታና ጊዜያዊ እርካታ ምክንያት ቸል ይባላል።3Review and Herald, Dec. 6, 1881.AHAmh 382.3

    የሚያቅበጠብጡት የዚህ የዘመናችን መፈንጠዣዎች የሴቶችንና የወንዶችን በተለይም የወጣቶችን አዕምሮ በደስታ ትኩሳት በማቃጠል ሁሉም ዓይነት ጥናቶቻቸውና የጉልበት ሥራዎቻቸው ከሚያደክሟቸው በላይ ኃይላቸውን ያሟጥጡባቸዋል። አዕምሮን የማቆርቆዝ ግብረ-ገብነትንም የማበላሸት ዝንባሌ አላቸው።4Health Reformer, Dec., 1872.AHAmh 382.4

    በዚህ አጥፊ የሆነ ግን የሙጥኝ በተባለ ተወዳጅ ማዕበል ወጣቱ ተጠርጎ እየተወሰደ ነው። ከፈንጠዝያ ለሚያገኙት እርካታ ብቻ ሲሉ ይህንን ደስታ የሚያሳድዱ ሁሉ የፈተና ጎርፍ በር እየከፈቱ ነው። ለማህበራዊ ድምቀትና ትርጉም ለሌለው ሳቅ እራሳቸውን አሳልፈው ይሰጣሉ። ለጠቃሚ ሕይወት ያላቸውን ፍላጎትም ሆነ ችሎታ እስኪያሟጥጡ ድረስ ከአንድ ዓይነት መራቆት ወደ ሌላው ይመራሉ። የነበራቸው ኃይማኖታዊ ምኞት ይቀዘቅዛል፤ መንፈሳዊ ሕይወታቸውም ይጨልማል። ሰውን ከመንፈሳዊ ዓለም ጋር የሚያቆራኙት የከበሩት የነፍስ ክፍሎች ሁሉ ይረክሳሉ።5Testimonies for the Church, Vol. 9, p. 90.AHAmh 382.5

    ከእርካታ አፍቃሪዎች መካከል ብዙ የቤተ-ክርስቲያን አባላት ይገኛሉ፡- ዓለማዊ በሆኑና ግብረ-ገብነትን በሚገድሉ፣ የእግዚአብሔር ቃል በሚከለክላቸው መፈንጠዣዎች ብዙዎች በጉጉት እየተሳተፉ ነው። ከዚህም የተነሣ ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸውን ግንኙነት እያቋረጡ ከዓለም ደስታ አፍቃርያን ጋር እየተሰለፉ ናቸው። ከውኃ ጥፋት በፊት የነበሩትን እንዲሁም በሰዶምና ጎሞራ የኖሩትን ሰዎች ያጠፋው ኃጢአት ዛሬም አለ። እምነት በሌለባቸው ሀገራትና እውቅና ባተረፉ የክርስትና እምነት ተከታዮች መካከል ብቻ አይደለም ይህ ስህተት የሚታየው፤ የክስቶስን ዳግም ምጽአት በሚጠባበቁትም መካከል ይህ ኃጢአት አለ። እነዚህን ኃጢአቶች እግዚአብሔር በሚያያቸው ዕይታ በፊታችሁ ቢያቀርባቸው ኖሮ በሐፍረትና በሽብር በተሞላችሁ ነበር።6Id., Vol. 5, p. 218.AHAmh 383.1

    ለሚያዝናና ለሚያስደስት ትዕይንት ያለው ፍላጎት ፈተና ነው፤ ለእግዚአብሔር ህዝቦች በተለይም ለወጣቶች ወጥመድ ነው። በቅርብ ለሚሆኑት የወደፊት ሁኔታዎች ያሉባቸውን ከባድ የመዘጋጀት ሥራ ይዘነጉ ዘንድ አዕምሮአቸውን የሚስብና የሚቀሰቅስ ነገር በማዘጋጀት ሰይጣን ሁልጊዜም እየሠራ ነው። በዓለማውያን ሥራ አስፈጻሚዎች በመታገዝ፣ ዓለማዊ እርካታዎችን ይቀላቀሉ ዘንድ ያልጠረጠሩትን በማያቋርጥ ምድራዊ ፌሽታ ሥር እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል። ዓለምን ወደ መውደድ እንዲመሩ ተደርገው የተዘጋጁ ትርኢቶች መግለጫዎችና ሥፍር ቁጥር የሌላቸው የተለያዩ መቦረቂያዎች አሉ። በዚህም ምክንያት የሚመጣው ከዓለም ጋር ያለው አንድነት እምነትን ያዳክማል።7Counsels to Teachers, Parents, and Students, p. 325.AHAmh 383.2

    ሰይጣን የታወቀው አዝናኝ፡- የምህረት ደጅ ከመዘጋቱ በፊት ያሉት ወርቃማ የሙከራ ዘመናት(የምህረት ጊዜያት) እንደ አንድ ትልቅ የበዓል ጊዜያት ተቆጥረው፣ የራሳቸውን እርካታና ፈንጠዝያ ለማጣጣም ይጠቀሙባቸው ዘንድ እንደተሰጣቸው አድርገው ወጣቶች በዘፈቀደ ሲንቀሳቀሱ ይታያሉ። በዓለማዊ ፈንጠዝያዎች ደስታን ያገኙ ዘንድ በመምራት፤ መፈንጠዣዎቹ ንጹህና ጉዳት የሌላቸው እንደሆኑ እንዲያውም ለጤና አስፈላጊ መሆናቸውን ለማስመስከር እንዲጥሩ በማሳመን ሰይጣን የተለየ ጥረት እያደረገ ነው።8Testimonies for the Church, Vol. 1, p. 501.AHAmh 383.3

    የቅድስና መንገድ እጅግ አስቸጋሪ በአንጻሩ ደግሞ ዓለማዊ እርካታዎች አበባ የተነሰነሰባቸው እንደሆኑ ለማሳየት ሰይጣን ይጥራል። በሀሰትና በመሸንገያ ቀለሞች ዓለምን ከነብልጭልጯ በወጣቶች ፊት ያቀርባል። የዓለም ደስታ ሁሉ ግን ወደ ፍጻሜ ይመጣል፤ የተዘራው መታጨድ ይኖርበታልና።9 [The] Youth’s Instructor, Jan 1, 1907.AHAmh 383.4

    ቃሎች እንደሚገልጹት ሁሉ አታላይና በብልሀት የተሞላ አስማት ያለው ነው። በቀጭኑ የተሸመኑ ብዙ መረቦች አሉት። የዋሆችና ጉዳት የማያደርሱ ይመስላሉ ነገር ግን በጥበብ ወጣቶችንና ያልጠረጠሩትን ለመተብተብ የተዘጋጁ ናቸው።10Counsels to Teachers, Parents, and Students, p. 325.AHAmh 383.5

    በእርካታ ፍቅር ምክንያት ትምህርት ዘቅጧል፡- በስሜት ማርኪያ ድግሶች ላይ ካልተሳተፉ፤ የእርካታ ፍቅር ካለባቸው ጋርም ካልተቀራረቡ፣ ልጆቹ ምንም ሳያውቁ ያድጋሉ የሚለው ፍራቻ ስለሚይዛቸው ገና በለጋ ዕድሜያቸው ልጆቻቸው ጉዋደኝነትን እንዲጀምሩ ወላጆች በማበረታታት ስህተት ይሠራሉ። ይህ እጅግ ከባድ ስህተት ነው። በዚህ አካሄድ ልጆች ሳይንስ ከሚማሩት እጅግ በፈጠነ ሁኔታ ክፋትን ይሰማሉ፤ አዕምሮአቸው በእርባና ቢስ ነገሮች ይሞላና ለፈንጠዝያ ያላቸው ፍላጎት እየጎለበተ ሄዶ የተለመዱትን የትምህርት ዘርፎች ዕውቀት እንኳ ማግኘት ፈጽሞ ይሳናቸዋል። ትኩረታቸው በትምህርትና በእርካታ ፍቅር ይከፋፈልና የእርካታ ፍቅር አይሎ የአዕምሮ ዕድገታቸው ዘገምተኛ ይሆናል።11The Youth’s Instructor, July 27, 1893.AHAmh 384.1

    እንደ ቀድሞዋ እስራኤል ሁሉ ዛሬም እርካታ አፍቃሪያን ይበላሉ፤ ይጠጣሉ፤ ለጭፈራም ይነሣሉ። ትርጉመ-ቢስ ሳቅ፣ የስካር ሞቅታ፣ ውካታና ፍንደቃ ይበዛል። በዚህ ሁሉ ወጣቶች በእጃቸው የያዙዋቸውን የሚያጠኑዋቸውን መጽሐፎችና የጻፏቸውን ሰዎች ምሣሌ ይከተላሉ። ከሁሉም የሚበልጠው ክፋት ደግሞ እነዚህ ነገሮች በባህርይ ላይ የሚያመጡት የዕድሜ ልክ ጠንቅ ነው።12Testimonies for the Church, Vol. 8, p. 66.AHAmh 384.2

    የእግዚአብሔር የመጨረሻው መልዕክት ቸል ተብሏል፡- የምህረት ጊዜያቸው እየተዘጋ ባለበት ወቅት በኖህ ዘመን ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ለሚያቅበጠብጡ ፈንጠዝያዎችና በዓላት እራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተው ነበር። ተጽዕኖ የማሳደር ጉልበት የነበራቸው ሰዎች እንኳ ሌሎች የመጨረሻውን ማስጠንቀቂያ ሰምተው እንዳይመለሱ አዕምሮአቸውን በከንቱ ሳቅና በከንቱ እርካታ በመዘፈቅ ተግባር ላይ የተሰማሩ ነበሩ። በእኛ ዘመን እራሱ እየተደገመ እንዳለ አይታየንምን? የእግዚአብሔር ባርያዎች የሁሉም ነገር መቋጫ በደጅ እንዳለ መልእክቱን እያስተላለፉ ሳለ ዓለም ቅጥ ያጣ ደስታንና ፈንጠዝያን ፍለጋ እየተፍገመገመ ነው። ማብቂያ የሌለው የደስታ አዝዋሪት እግዚአብሔርን ቸል እንዲሉ በማድረግ ከሚመጣው ጥፋት የሚያተርፋቸውን ብቸኛውን የእውነት ማህተም ገሸሽ እንዲሉ ያደርጋቸዋል።13Patriarchs and Prophets, p. 103.AHAmh 384.3

    ሰንበትን ጠባቂዎች ይፈተናሉ፤ ብቁ መሆናቸውም ይረጋገጣል፡-ለዓለም ተጽዕኖ እጃቸውን የሰጡ ወጣት ሰንበት ጠባቂዎች ሊፈተኑና ሊያስመሠክሩ ይጠበቅባቸዋል። የመጨረሻዎቹ ቀናት ውድመቶች በላያችን ናቸው፤ ብዙዎች ያልጠበቁት ፈተና በወጣቶች ላይ ተጋርጧል። በሚያስጨንቅ ግራ መጋባት ሥር ይወድቃሉ፤ የእምነታቸው እውነተኛነትም ይመዘናል፤ ይረጋገጣልም። የሰውን ልጅ መመለስ በናፍቆት እንደሚጠባበቁ ይናገራሉ፤ ሆኖም አንዳንዶቹ ለማያምኑት እጅግ አሳዛኝ ምሣሌዎች ሆነዋል። ዓለምን ለመተው ፈቃደኞች አይደሉም፤ ነገር ግን በሽርሽሮችና *ማስታወሻ፡- እዚህ ላይ እየተጠቀሰ ያለው የተለመደው የቤተሰብ ወይም የቤተ-ክርስቲያን አባላት ከቤት ውጪ የሚያደርጉት መሰባሰብ አይደለም፤ ነገር ግን በዚያን ጊዜ የተለመደ የነበረውን የቤተ-ክርስቲያን አባላት “ከዓለም ጋር ተባብረው” ያካሂዱት የነበረውን ሕብረተሰቡ የሚሰበሰብበትን ክብረ-በዓል (ካርኒቫል) ነው።. በሌሎች ስብሰባዎች ለርካታቸው ሲሉ በመተባበር ከዓለም ጋር ቢቆራኙም ንጽህናቸው ባልተጓደለ መደሰቻዎች ብቻ ሲዝናኑ እንደነበር በማሰብ እራሳቸውን ይደልላሉ። ሆኖም እንደነዚህ ያሉት እርካታዎች ናቸው ከእግዚአብሔር ለይተው የዓለም ልጆች የሚያደርጓቸው…. ሐሴት ፈላጊውን እግዚአብሔር በተከታይነት አይቀበለውም። ራሳቸውን የካዱ ሕይወታቸው የቁጥብነት፣ የደግነትና የቅድስና ተምሣሌት የሆኑት ብቻ ናቸው የየሱስ እውነተኛ ተከታዮች። እነዚህ ሰዎች የዓለም አፍቃርያን የሚያወሩት ከንቱና ባዶ ጭውውት ሊያስደስታቸው አይችልም።14Counsels to Teachers, Parents, and Students, pp. 327, 328.AHAmh 384.4

    ሊታሰብበት የሚገባው ከሁሉም በላይ አስፈላጊው ነገር፡- ፈንጠዝያዎች አስፈላጊ እንደሆኑ ማንም አይመን፤ በነዚህ ራስ-ወዳድ የሐሴት ጊዜያት የሚደረገው ግድ-የለሽ መንፈስ ቅዱስን የማቃለል ተግባር ቀላል ነገር አድርጎ ማንም እንዳይቆጥረው፤ እግዚአብሔር አይላገጥበትም። እያንዳንዱ ጎረምሳ ያጢን፣ እያንዳንዷ ኮረዳም ታጢን፡- “ዛሬ የሕይወቴ መጨረሻ ቢሆን ዝግጁ ነኝ? ጌታ የሰጠኝን ሥራ እፈጽም ዘንድ ብቁ የሚያደርገኝ የልብ መዘጋጀት አለኝ?” በማለት ይጠይቁ።15The Youth’s Instructor, Aug. 14, 1906.AHAmh 385.1