Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የአድቬንቲስት ቤት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ ሰማንያ ሰባት—የአዲሲቱ ምድር ሥዕላዊ መግለጫ

    የወደፊቱ ክብር ራዕይ፡- ክርስቶስ በላያችን ሆኖ ከከተማይቱ ወደዚህ ምድር ወረድን፤ በታላቅና ግዙፍ ተራራ ላይም አረፍን። ተራራውም ክርስቶስን ይሸከም ዘንድ ስላልቻለ ሸሸ፤ እነሆም በፊታችን ሰፊ ሜዳ ሆነ። ዓይናችንንም አንሥተን ታላቋን ከተማ በአሥራ ሁለት መሠረቶችና በአሥራ ሁለት በሮች ሦስት በአንድ ረድፍ በእያንዳንዱም በሮችዋ መልአክ ቆሞ ዐየን። ሁላችንም እየጮህን “ከተማይቱ ታላቋ ከተማ ወጣች ከእግዚአብሔር ዘንድ ከሰማይ ወጣች!” አልን። መጥታም በቆምንበት ሥፍራ አረፈች። ከዚያም ከከተማዋ ውጭ ያሉትን የከበሩ ነገሮች መመልከት ጀመርን። በዚያ ለዓይን እጅግ በከበረ ሉል የተጌጡ አራት ምሰሶዎች የቆሙባቸው እጅግ የሚያማምሩ ቤቶችን አየሁ። እነዚህ ቅዱሳን እንዲኖሩባቸው የተዘጋጁ ነበሩ። በእያንዳንዱ ቤት ከወርቅ የተሠራ መደርደሪያ ነበር። ብዙዎቹ ቅዱሳን ወደ ቤታቸው ሄደው የሚያንፀባርቀውን ዘውዳቸውን በመደርደሪያው ላይ አስቀምጠው ወደ መስኩ ወጡ፤ መሬት ላይም አንዳንድ ነገር ይሠሩ ጀመሩ። እኛ እዚህ ምድር ላይ መሥራት እንደሚጠበቅብን አይደለም፣ አይደለም፤ አይደለም። የክብር ነፀብራቅ በራሳቸው ዙሪያ ያበራ ነበር፤ ያለማቋረጥም በታላቅ ድምፅ ለእግዚአብሔር ምሥጋና ያቀርቡ ነበር።AHAmh 400.1

    ሁሉም ዓይነት አበቦች ያሉበት ሌላ መስክ አየሁ፤ በምቀጥፋቸውም ጊዜ ጮኹና “ፈጽሞ አይጠወልጉም” አልሁ። ቀጥሎም ለዓይን እጅግ የከበረ ረዥም ሣር ያለበት መስክ አየሁ። ሁሌም አረንጓዴ ነበረ፤ በግርማም ለንጉሡ የሱስ ክብር ሲወዛወዝ የብርና ወርቅ ነፀብራቅ ይፈነጥቅ ነበረ። ከዚያም ሁሉም ዓይነት አራዊት ወዳሉበት መስክ ገባን - አንበሣው፣ የበግ ጠቦቱ፣ ነብሩ፣ ተኩላው፣ ሁሉም በፍጹም መስማማት የሚኖሩበት። በመሐላቸውም አለፍን፤ ሰላማዊ ሆነውም ተከተሉን። ከዚያም ወደ ደን ገባን፤ ዛፎቹ እንደዚህ ዓለም የደበዘዘ ገፅታ ያላቸው አይደሉም፤ የለም አይደሉም፤ የሚያንፀባርቁና ግርማ ሞገስ የተላበሱ ነበሩ፤ ቅርንጫፎቻቸው ወደፊትና ወደ ኋላ ይወዛወዙ ነበር፤ ሁላችንም ጮኽን “በዱር በሠላም እንኖራለን በዛፎችም መካከል እንተኛለን” አልን።1Early Writings, pp. 17, 18.AHAmh 400.2

    የድህረ-ምረቃ ሥራ በሚመጣው ዓለም፡- እዚያ ምንም የማንማር ይመስላችኋል? በፊታችን ምን እንደሚጠብቀን ቅንጣት ታክል መረዳቱ የለንም። ከክርስቶስ ጋር በሕይወት ውኃዎች አጠገብ አንራመዳለን። የተፈጥሮን ውበትና ግርማ ይገልጽልናል። እርሱ ለእኛ እኛ ደግሞ ለእርሱ ምን እንደሆንን ያብራራልናል። አሁን በውስን አዕምሮአችን የማንረዳውን እውነት ያኔ እናውቀዋለን።2Counsels to Teachers, Parents, and Students, p. 162.AHAmh 400.3

    የክርስቲያን ቤተሰብ ልጆች በእግዚአብሔር እልፍኞች ውስጥ ለመማር ወደ ከፍተኛ ትምህርት ያልፉ ዘንድ የሚመረቁበት የማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ነው።3Review and Herald, March 30, 1897.AHAmh 401.1

    ሰማይ ትምህርት ቤት ነው፤ የጥናት መስኩ ዩኒቨርስ ነው፤ መምህሩ ደግሞ መለኮት ነው። የዚህ ትምህርት ቤት ቅርንጫፍ በኤደን ተከፍቶ ነበር። የማዳን እቅድ ከተፈፀመ በኋላ ትምህርቱ እንደገና በኤደን ትምህርት ቤት ይቀጥላል….AHAmh 401.2

    በመጀመሪያው የኤደን ትምህርት ቤትና ለወደፊት በሚመጣው ትምህረት ቤት መካከል የዓለምን ታሪክ በሙሉ የሚገልጽ ጠቋሚ ተቀምጧል፡- የሰውን መተላለፍና ስቃዩን፤ በመለኮታዊ መስዋዕትነት በሞትና በኃጢአት ላይ የተገኘው ድል…. ሰው ወደ እግዚአብሔር መገኘት እንደገና ታድሶ ልክ መጀመሪያ እንደነበረው ከአምላክ ይማራል፡- “ሕዝቤ ስሜን ያውቃል። ስለዚህ በዚያ ቀን ያውቃል እኔ እንደሆንሁ የምናገር እኔ አልሁ።”….AHAmh 401.3

    እዚያ ዕይታችን አጨልሞት የነበረው ግርዶሽ ይወገዳል፤ ዓይናችንም አሁን በሚያጎላ መነጽር በጨረፍታ የምናየውን ውበት ማየት ይችላል፤ አሁን አቅርቦ በሚያሳየው መነጽር የምናየውን የሰማይ ግርማ ያኔ በዓይናችን እንመለከታለን። የኃጢአት መቅሰፍት ሲወገድ መሬት “በእግዚአብሔር በአምላካችን ውበት” መልክ ሲይዝ ምን ዓይነት የጥናት መስክ ይከፈትልናል!4Education, pp. 301-303.AHAmh 401.4

    ሰማያዊ ዕውቀት እያደገ የሚሄድ ነው፡- በሥነ-ፍጥረት ውስጥ በዩኒቨርስ ያሉት እምቅ መዛግብት ሁሉ የተዋጁት ያጠኑዋቸው ዘንድ የተከፈቱ ይሆናሉ። በሞት እግር-ብረት ሳይገደቡ በሰው ልጅ መከራ የተነሣ በሐዘን ይሸበሩ፣ እዳዋ በተከፈለላት ነፍስ ምክንያት ደግሞ የደስታ መዝሙር ይዘምሩ ወደ ነበሩ ወደ እነዚያ ሩቅ ዓለማት በማይደክመው ክንፋቸው ይበርራሉ። ሊነገር በማይችል ደስታ የምድር ልጆች ወዳልወደቁት ተድላና ጥበብ ይገባሉ። ለዘመን ለዘመናትም በእግዚአብሔር የእጅ ሥራ ላይ ሲደረግ ከነበረው ጥናት የተከማቸ ዕውቀትና መረዳት ተካፋይ ይሆናሉ። ባልደበዘዘ ዕይታ የፍጥረትን ክብር ያያሉ፤ ፀሐዮችና ከዋከብት በግሩም የአሠራር ቅንጅታቸው ሁሉም በተሰጣቸው የኃላፊነት ሥነሥርዓት የመለኮትን ዙፋን ከብበው ሲዞሩ ይመለከታሉ። በጥቃቅንና ታላላቅ ነገሮች ሁሉ ላይ የፈጣሪ ስም ተጽፎባቸዋል፤ በሁሉም ላይ የኃይሉ ጥልቀት ይገለጽባቸዋል።AHAmh 401.5

    ዲካ የማይገኝላቸው ዓመታትም ባለፉ ቁጥር ስለ እግዚአብሔርና ስለ ክርስቶስ ሰፊና የከበረ ከበፊቱም የተሻለ መገለጽ ይሆናል። ዕውቀትም ሲጨምር ፍቅርም፣ ውዳሴም፣ ደስታም እንዲሁ ይጨምራሉ። ሰዎች ስለ እግዚአብሔር የበለጠ በተማሩ ቁጥር ስለ ባህርይው ያላቸው ግርምትና መደነቅ እየጨመረ ይሄዳል።5Great Controversy, pp. 677, 678.AHAmh 401.6

    ማህበራዊ ኑሮ፡- እዚያ የምንታወቀውን ያህል እኛም እናውቃለን። እግዚአብሔር በነፍስ የተከለው ፍቅርና ርኅራኄ ወደር የሌለው እውነተኛና ጣፋጭ ተግባራዊነትን እዚያ ያገኛል። ከቅዱስ ፍጡራን ጋር ያለው ንጹህ አንድነት፤ ከተባረኩት መላእክትና በዘመናት ሁሉ ታማኝ ከነበሩት ጋር ያለው ማህበራዊ ሕይወት፤ “በሰማይና በምድር ያለው ቤተሰብ ሁሉ” የሚያስተሳስረውም የተቀደሰው ስብሰባ ሁሉ በሚመጣው ዓለም የምናገኛቸው የሥራ ልምምዶች ናቸው።66. Education, p. 307.AHAmh 402.1

    ሥራ በአዲሲቱ ምድር፡- አዲስ በሆነችው ምድር የዳኑት በመጀመሪያ ለአዳምና ለሔዋን ደስታ ያመጡላቸው ዘንድ በተሰጡአቸው ሥራዎችና የደስታ ምንጮች ላይ ይሰማራሉ። የአትክልት ሥፍራና የመስክ ሕይወት፤ ያ በኤደን የነበረው ኑሮ ይቀጥላል። “ቤትን ይሠራሉ ይቀመጡበታልም፤ ወይንም ይተክላሉ ፍሬውንም ይበላሉ። ሌላ እንዲቀመጥበት አይሠሩም ሌላም እንዲበላው አይተክሉም የሕዝቤ ዕድሜ እንደ ዛፍ ዕድሜ ይሆናልና እኔም የመረጥኋቸው የእጃቸውን ሥራ ረጅም ዘመን ደስ ይላቸዋልና።” 7Prophets and Kings, pp. 730, 731.AHAmh 402.2

    እዚያ ሁሉም ጉልበት ይጠነክራል፤ እያንዳንዱ ችሎታ ይጨምራል። ታላላቅ የሥራ እቅዶች ይተገበራሉ፤ የገዘፉ ምኞቶች ወደ ፍፃሜ ይመጣሉ፤ የመጠቁት ጉጉቶች እውን ይሆናሉ። ሆኖም አሁንም እንደገና መወጣት ያለበት አዲስ ከፍታ ይኖራል፤ የሚያስገርሙ አዳዲስ ድንቃድንቆች ማስተዋል የሚጠይቁ አዳዲስ እውነቶች የአካልን፣ የአዕምሮንና የነፍስን ኃይላት የሚጋብዙ አዳዲስ ነገሮች ይነሣሉ።8. Education, p. 307.AHAmh 402.3

    ከፍፃሜ አፋፍ ላይ፡- ዓለም ካለፈበት ታሪክ ውስጥ እጅግ ጨለማና ተስፋ በሚያስቆርጥ ዘመን ነው የምንኖረው። ኃጢአት ለመሥራት ጊዜ የለም፤ በአመጽ ለመቀጠል እንደፍር ዘንድ አይቻለንም፣ ሁልጊዜም አደገኛ ነውና። ነግር ግን በተለየ ሁኔታ ይህ ዕውነታ አሁን ተግባራዊ እየሆነ ነው። አሁን እኛ በዘለዓለማዊ ዓለም ጠርዝ ላይ ነን። ከማንኛውም ጊዜ ይልቅ ከዘመንና ከዘለዓለም ጋር ባለን ከባድ ግንኙነት ላይ ቆመናል። እያንዳንዱ ሰው አሁን ልቡን ይመርምር፤ ከርኩሰትና ከመንፈሳዊ ጽልመት ይላቀቅ ዘንድ ደማቁን የብርሃን ጮራ ከጽድቅ ፀሐይ [የሱስ] ይለምን።9Testimonies to Ministers, p. 147.AHAmh 402.4

    በፍፃሜአቸው አፋፍ ላይ ለቆምን ለእኛ እነዚህ ሊሆኑ ያላቸው ነገሮች የድንበር መከለያዎች እንዴት የሚመስጡ ጊዜያት ናቸው! ምን ዓይነት ሕያው ፍላጎት የሚጭሩ ናቸው! እነዚህ ክስተቶች የመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን እግራቸውን ከኤደን ፈቀቅ ካደረጉ ጊዜ አንሥቶ የእግዚአብሔር ልጆች በናፍቆትና በልመና ዓይን ሲያዩና ሲጠብቋቸው የኖሩት ጊዜያት ናቸው!AHAmh 402.5

    መንገደኛው ሰው ሆይ አሁንም በዓለማዊ ግርግር ጥላ ሥር ነን፤ ነገር ግን አዳኛችን መታደግንና ዕረፍትን ይዞ በቅርቡ ብቅ ይላል። በእግዚአብሔር እጅ የተሣለውንና የተባረከውን የወደፊቱን ዓለም በእምነት እንመልከት።10Prophets and Kings, pp. 731, 732.AHAmh 402.6

    ለግል መዘጋጀት የቀረበ ልመና፡- በሰማይ ደመና ለሚመጣው ክርስቶስ ትዘጋጁ ዘንድ እለምናችኋለሁ። ቀን በቀን ለዓለም ያላችሁን ፍቅር ከልባችሁ መንጥቃችሁ አስወጡት። ከክርስቶስ ጋር የአንድነት ጊዜ ማለት ምን ማለት እንደሆነ በልምምድ ተረዱ። በሚያምኑት ሁሉ ፊት ደስታ ይሆን ዘንድ ክርስቶስ ሲመጣ በሠላም ትገናኙት ዘንድ ለፍርዱ ተዘጋጁ። በዚያን ቀን ከአብና ከወልድ ክብር የተነሣ የዳኑት ያበራሉ። መላእክት በገናቸውን እየደረደሩ ንጉሡንና ለእርሱ የክብር ዘውድ የሚሆኑለትን በበጉ ደም ልብሳቸው የታጠበላቸውንና ነጭ የሆነላቸውን እንኳን ደህና መጣችሁ ይሏቸዋል። ታላቅ የድል ጩኸት ሰማይን እስኪሞላ ድረስ ወደ ላይ ይወጣል። ክርስቶስ ድል ነስቷል። የስቃይና የመሥዋዕትነት ተልዕኮው በከንቱ እንዳልነበረ ምሥክር የሚሆኑትን የተዋጁትን በዙሪያው ይዞ ወደ ሰማያዊ መንግሥቱ ይገባል።11Testimonies for the Church, Vol. 9, pp. 285, 286.AHAmh 403.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents