Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የአድቬንቲስት ቤት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ምዕራፍ ሰባ አራት—አደጋ ያለባቸውና የሌለባቸው ጉድኝቶች

    በእኛና በልጆቻችን ላይ ተጽዕኖ የሚያደርሱ ነገሮች፡- እያንዳንዱ የምንመሠርተው ጉድኝት ውስን እንኳ ቢሆን ተጽዕኖ ማሳደሩ አይቀሬ ነው። ለተጽዕኖው እጅ አሰጣጣችን ደግሞ እንደ ቅርብ ግንኙነታችን፤ ድግግሞሽና ለጓደኛችን ባለን ፍቅርና አክብሮት ይወሰናል።1Testimonies for the Church, Vol. 5, pp. 222, 223AHAmh 336.1

    ተጽዕኖአቸው ጌታ በእኛ ላይ ያለውን መጠይቅ ሊያስረሳን የሚችል ዝንባሌ ካለው ሰዎች መካከል እራሳችንን ካስቀመጥን ፈተናን እንጋብዛለን፤ ለመቋቋም ያለን የግብረ-ገብነት ኃይል እጅግ ደካማ ይሆናል። የጓደኞቻችንን መንፈስና ሐሳብ ወደ መጋራት እንመጣለን፤ በዚህም ምክንያት የተቀደሱና ዘለዓለማዊ የሆኑ ነገሮቻችንን ከጓደኞቻችን ሐሳቦች ዝቅ አድርገን እናያቸዋለን። በአጭሩ ልክ የጽድቅ ሁሉ ጠላት እንዳቀደው፤ እርሱ እንደሚፈልገው ተሞልተናል ማለት ነው [እርሱ በሚፈልገው እርሾ ተቦክተናል ማለት ነው።] በእንደዚህ ዓይነት ተጽዕኖ ሥር ከሆኑ በዕድሜ ከፍ ካሉት ይልቅ ወጣቶች በቀላሉ ተጠቂ ይሆናሉ። የሚመለከቱት ፊት፣ የሚሰሙት ድምፅ፣ የሚጎበኟቸው ቦታዎች፣ የሚመሠርቱት ጓደኝነትና የሚያነብቧቸው መጻሕፍት ሁሉ በአዕምሮአቸው አሻራ ጥለው ያልፋሉ። ለእኛ በተለይም ደግሞ ለልጆቻችን የምንመርጠው ጓደኝነት ለዚህም ሆነ ለሚመጣው ዓለም ካለው ጠቀሜታ አንፃር ምንም ያህል ሰፊ ትኩረት ብንሰጠው ፈጽሞ ተጋነነ ሊባል አይችልም።2Id., p. 543.AHAmh 336.2

    ከከሐዲዎች ጋር የመጎዳኘት አደጋዎች፡- መመዘኛችን ዓለም ሊሆን አይገባውም። የሐሰት አማልክትን ያመልክ ዘንድ ልብን ከእግዚብሔር ያርቁታልና ከከሐዲዎች ጋር ጓደኝነት ልንመሠርት ከመንፈሳቸውም ልንካፈል አይገባንም። በእምነቱ ጠንካራ የሆነ የማይለዋወጥ ነፍስ ብዙ መልካም ማድረግ ይችላል። ከሁሉም በላይ ከፍ ያለውን በረከት ለጓደኞቹ ያካፍላል፤ የእግዚአብሔር ሕግ በልቡ ውስጥ ነውና። ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ላይ ከሚረማመዱ ሰዎች ጋር በፈቃዳችን ጓደኝነት መስርተን እምነታችን ንጹህ እንደሆነ ሳይወይብ ጠብቀን ማቆየት አንችልም። መንፈሳቸውን እንወርሳለን፤ ካልተለየናቸው በስተቀር ጥፋታቸውን ለመጋራት ከእነርሱ ጋር እንተሳሰራለን።3Manuscript 6, 1892.AHAmh 336.3

    ዕብራውያን የእግዚአብሔርን ሕግ የተላለፉት፣ ፍርዱም በህዝቡ ላይ እንዲመጣ ምክንያት የሆኑት ከጣኦት አምላኪዎች ጋር ግንኙነት ስለጀመሩና በበዓላቶቻቸው አከባበርም ስለተሳተፉ ነበር። አሁን ሰይጣን ሰዎችን በማታለል ወደ ኃጢአት በመምራት እጅግ የተዋጣለት የሆነው፣ የክርስቶስ ተከታዮች ከከሐዲዎች ጋር እንዲጎዳኙና መዝናኛቸውም አንድ ዓይነት እንዲሆን በመገፋፋት ነው። “ከመካከላቸው ውጡ ከእርሳቸውም ተለዩ እግዚአብሔር ይላል። ወደ ርኩስም ሁሉ አትቅረቡ።” በጥንት ዘመን ከእስራኤሎች እንደፈለገባቸው ሁሉ ዛሬም በባህላቸው፣ በልማዳቸውና በመርሆዎቻቸው ፍጹም ከዓለም የተለዩ ይሆኑ ዘንድ እግዚአብሔር ከሕዝቦቹ ይፈልግባቸዋል።4Patriarchs and Prophets, p. 458.AHAmh 336.4

    ሳምሶን በፈቃደኝነት የመረጠው ምርጫ፡- የተጠራበትን ሥራ ለመፈጸም ይዘጋጅ ዘንድ የእግዚአብሔር ግሩም ጥበቃ በሳምሶን ላይ ነበር። ገና ከሕፃንነቱ ጀምሮ ለአካል ጥንካሬ፣ ለአዕምሮ ብርታትና ለግብረ-ገብነት ንጽህና በሚመቹ ሁኔታዎች ተከብቦ ነበር። ሆኖም የክፋት ተጽዕኖ የሰው ልጅ ብቸኛ መተማመኛ የሆነውን እግዚአብሔርን እንዲለቅቀው አደረገው፤ በጥፋት ማዕበልም ተጠርጎ ተወሰደ። በሥራ ላይ ያሉ ወደ ፈተናም የሚገቡ እግዚአብሔር እንደሚጠብቃቸው እርግጠኛ ይሆኑ ይሆናል። ነገር ግን ሰዎች በምርጫቸው እራሳቸውን በፈተና ኃይል ሥር ማስቀመጥ ከፈቀዱ ሊፈጥንም ሊዘገይም ይችላል፤ ሆኖም መውደቃቸው ግን አይቀርም።5Id., p. 568.AHAmh 337.1

    የእርጉምነትና የተንኮል እርሾ፡- ውድ ተማሪዎች ሆይ፣ ሌትም ቀንም የወላጆቻችሁ ፀሎት ይከተላችኋል። ልመናቸውን አድምጡ፣ ማስጠንቀቂያቸውን ስሙ፤ ግድ-የለሽ ጓደኞችን ለራሳችሁ አትምረጡ። ክፋትን እንድትሠሩ በመምራትና መጥፎ ባህርያትን እንድታጎለብቱ በማበረታታት፣ የርኩሰትና የተንኮል እርሾ አዕምሮአችሁን እንዴት እንደሚበርዘው፣ ልማዳችሁን እንዴት እንደሚያደበዝዘው ልታውቁ አትችሉም። መጀመሪያ ላይ ምንም አደጋ ላይታያችሁ፣ መልካም ነገርን እንደ በፊቱ ያለ ችግር እንፈጽማለን ብላችሁ ታስቡ ይሆናል፤ ይህ ግን ስህተት ነው። እግዚአብሔርን የሚወዱና የሚፈሩ ወላጆቻችሁና መምህሮቻችሁ ሊያስጠነቅቋችሁ፣ ሊለምኗችሁና ሊመክሯችሁ ይችላሉ። ሆኖም እናንተ እራሳችሁን ለእግዚአብሔር ካላስረከባችሁ፣ የሰጣችሁን ክህሎት ለእርሱ ክብር ልታውሉት ካልመረጣችሁ በስተቀር የወላጆቻችሁና የአስተማሪዎቻችሁ ልፋት ከንቱ ነው።6The Youth’s Instructor, Jan. 18, 1894.AHAmh 337.2

    ለኃይማኖት ግድ ከሌላቸው ተጠንቀቁ¬፡- ልጆች ንግግራቸው ጠቀሜታ ከሌለውና ዓለማዊ ከሆኑ ጓደኞች ጋር ጊዜ የሚያጠፉ ከሆነ እነርሱም ወደ ተመሳሳይ ደረጃ ይመጣሉ። የኃይማኖት መመሪያዎች ሲሰደቡ፣ እምነታችን ሲንቋሸሽና ተንኮል ያዘለ ተቃውሞ በእውነት ላይ ሲቀርብ ወደ ጆሮአቸው ከደረሰ እነዚህ ነገሮች በአዕምሮአቸው ይጣበቁና ባህርያቸውን ይቀርጹታል።7Testimonies for the Church, Vol. 5, p. 543AHAmh 337.3

    ከንቱ፣ ግድ-የለሽና የተበላሸ አስተሳሰብ እንዳላቸው ሰዎች ጠቃሚ ገጽታዎችንና መልካም ዝንባሌዎችን በተሳካ ሁኔታ የሚገድብ ወይም የሚያጠፋ የለም። በቀልዳቸው በአሽሙራቸውና በጨዋታቸው ምኑንም ያህል ማራኪ ቢሆኑም ኃይማኖትን እንደ ቀላልና አላስፈላጊ ነገር ማየታቸው ብቻ ከእነዚህ ሰዎች ጋር ጓደኝነት ላለመመሥረት በቂ ምክንያት ነው። መንፈሳዊ ባልሆኑ ጉዳዮች የበለጠ የሚስቡ ሲሆኑ ተጽዕኖአቸው የበለጠ ሊፈራ ይገባዋል። ምክንያቱም ኃይማኖት በሌለበት ሕይወትና በብዙ አደገኛ ማራኪ ነገሮች ስለሚከቡን ነው።8Id., Vol. 3, p. 126.AHAmh 337.4

    ዓለማዊ ጓደኝነቶች የስሜት ሕዋሳቶቻችን በመማረክና በማስደመም ሰዎች በጥንካሬ መቆም ይችሉ ዘንድ ርኅራኄ፣ ፈሪሐ-እግዚአብሔር፣ እምነትና ታማኝነት በቂ ጉልበት የማይለግሷቸው ይሆናሉ። ተራና ትሁት የነበረው የክርስቶስ ሕይወት ምኑም የሚስብ አይመስልም ነበር። የእግዚአብሔር ወንዶችና ሴቶች ልጆች ነን ለሚሉ ለብዙዎች የሰማይ ልዑል የሱስ “እንደቡቃያ ይወጣልና እንደ ሳርም ከተጸማች ምድር። መልክ የለውም፤ ውበትም” የሌለው ነው።9Manuscript 6, 1892.AHAmh 338.1

    ፍላጎታችሁ ዓለማዊ ዘመዶቻችሁን ማዕከል ያደረገ አይሁን፡- ዓለምንና እግዚአብሔርን በአንድ ጊዜ ልናገለግል አይቻለንም። ቅርርቦቻችን እውነትን ለመማር ፍላጎት በሌላቸው ዘመዶቻችን ዙሪያ ሊሆን አይገባውም። ብርሃናችን ይበራላቸው ዘንድ ጓደኞቻቸው በመሆን በሁሉም አቅጣጫ ጥረት ማድረግ እንችላለን። ነገር ግን ንግግራችን፣ ጠባያችን፣ ባህሎቻችንና እንቅስቃሴዎቻችን በምንም ዓይነት በእነርሱ አሳተሳሰብና ልማድ ሊቀረጹ አይገባቸውም። ከእነርሱ ጋር ባለን ግንኙነቶች ሁሉ እውነትን ማሳየት አለብን። ይህንን ማድረግ የማንችል ከሆነ ቅርርባችንን ብንቀንስ ለመንፈሳዊ ሕይወታችን የተሻለ ይሆንልናል።10Testimonies for the Church, Vol. 5, p. 543.AHAmh 338.2

    ዝቅተኛ ደረጃ እንዲሁም ልል ግብረ-ገብነት ካላቸው ሽሹ፡- ልቅ ሥነ-ምግባር ካላቸው ጋር ግንኙነት መመሥረት ለክርስቲያኖች ስህተት ነው። ለአዕምሮ ወይም ለግብረ-ገብነት ጥንካሬ ምንም አስተዋጽኦ የማያደርግ፣ በከንቱ ጊዜን የሚያጠፋ፣ ቀን በቀን የሚደረግ የቀረበ ግንኙነት አደገኛ ነው። ሰዎችን የከበበው የሥነ-ምግባር ከባቢ አየር ንፁህና የተቀደሰ ካልሆነ በብልሽት የጎደፈና የተመረዘ ከሆነ ይህንን አየር የሚተነፍሱ ሁሉ ሊታወቅ በሚከብድ ሁኔታ ለመመረዝና ለማጥፋት አዕምሮአቸውና ልባቸው ላይ ሲሠራ ያገኙታል። አዕምሮአቸው የተዋረደ ደረጃ ከያዘ፣ ሰዎች ጋር ውይይት ማድረግ አደገኛ ነው። በተፈጥሮአቸው ንቁና ንጽህናን የሚወዱ እነርሱ ቀስ በቀስ ሳይታወቃቸው ወደ ተዋረደው ደረጃ ዝቅ በማለት ሁል ጊዜ ከሚያገኟቸው ሰዎች ጅልነትና ግብረ-ገባዊ ድርቀት ተሳታፊ ይሆናሉ።11Id., Vol. 3, p. 125.AHAmh 338.3

    መልካም ስም ከከበረ ወርቅ ይበልጣል። ወጣቱ አስተሳሰባቸውና ሞራላቸው ከወደቀ ሰዎች ጋር የመጎዳኘት ዝንባሌ ይታይበታል። አንድ ወጣት የወረደ አስተሳሰብ፣ ስሜትና ባህርያት ካላቸው ሰዎች ጋር በፈቃደኝነት ግንኙነት መፍጠሩ ምን ዓይነት እውነተኛ ደስታ ሊያስገኝለት ይችላል? አንዳንዶች ምርጫቸው የረከሰ ልምዳቸውም ነውረኛ ነው፤ የእነዚህን ጓደኝነት የሚመርጡ ሁሉ እንደ እነርሱ ይሆናሉ። የምንኖረው የሁላችንንም ልቦች በፍርሃት ሊያንቀጠቅጥ በሚገባ የጥፋት ዘመን ነው።12Testimonies for the Church, Vol. 4, p. 588.AHAmh 338.4

    ብዙዎች እንዳይቀለድባቸው በመስጋት ለፈተና እጅ ይሰጣሉ፡- ልጆች…. ሊኖራቸው የሚገባቸው ጓደኞች ንጹህና ዋጋ ባለው ነገር ላይ የሚቀልዱ ሳይሆን እንዲያውም ለእውነት የሚከራከሩትን ነው። መሳለቂያ እንሆናለን የሚለው ፍራቻ ብዙ ወጣቶች ለፈተና እጅ እንዲሰጡና ከከሐዲዎች ጋር አብረው እንዲጓዙ መርቷቸዋል። በንቀትና ቀልድ መሐል ልጆቻቸው እውነትን ይዘው መቆም ይችሉ ዘንድ በምሣሌነትና በምክር እናቶች ብዙ ማድረግ ይችላሉ።13Review and Herald, March 31, 1891.AHAmh 339.1

    ሌሎችን ወደ ተከለከሉ መንገዶች ለመምራት የተነሡ ሁሉ በፈተና በቀላሉ የሚሸነፉ፤ ሥርዓት አልበኝነትን የሚያበረታቱ፤ ንቁና የባህርይ ቅንነታቸውን ጠብቀው በሚቆሙ ላይ የሚስቁ የሰይጣን ሥራ አስፈፃሚዎች እንደሆኑ ወጣቱ የማያጤነው ለምንድን ነው?14The Youth’s Instructor, Jan. 18, 1894.AHAmh 339.2

    በእግዚአብሔር ፊት እንደምትኖሩ ሁሉ በእንግዶችም ፊት ተመላለሱ፡- ወጣት ወዳጆች ሆይ ለንጹሁና ለተቀደሰው የእግዚአብሔር ሥራ ገጣሚ ከማይሆኗችሁ ሰዎች ጋር አንድ ሰዓት እንኳን አታጥፉ። በወላጆቻችሁ ፊት ልትሠሩት የማትደፍሩትን ወይም በክርስቶስና በመላእክቱ ፊት የሚያሳፍራችሁን አንድም ነገር በወዘ-ልውጦች ፊት አታድርጉ።AHAmh 339.3

    እነዚህ ማስጠንቀቂያዎች ሰንበትን ለሚጠብቁ የሚያስፈልጉ አይደሉም ብለው አንዳንዶች ያስቡ ይሆናል፤ እንደሚያስፈልጓቸው የሚያውቁ ግን ምን እያልኩ እንደሆነ ይገባቸዋል። እነግራችኋለሁ ወጣቶች ሆይ ተጠንቀቁ፤ ከመላእክትና ከእግዚአብሔር ዐይን የተሰወረ ምንም ነገር ማድረግ አትችሉም። የጥፋት ሥራ ልትሠሩና ሌሎች ላይጎዱበት የሚችሉበት አጋጣሚ ፈጽሞ የለም። አካሄዳችሁና ባህርያችሁ የተገነባው በምን ዓይነት ቁሳቁሶች እንደሆነ ከመግለጹም በተጨማሪ በሌሎች ላይ ከባድ ተጽዕኖ ያሳድራል። የእግዚአብሔር እንደሆናችሁ፣ በዋጋ እንደገዛችሁ በአደራ የሰጣችሁን ክህሎቶች እንዴት እንደተጠቀማችሁባቸው እንደምትጠየቁባቸው ፈጽሞ ለአፍታ እንዳትዘነጉ።15Testimonies for the Church, Vol. 5, pp. 398, 399.AHAmh 339.4

    በሚፈለግበት ጊዜ የተለየ እርዳታ አለ፡- ከተበላሹና ዝቅ ካሉት ጋር ጓደኝነት መመሥረት ግድ በሚላቸው ሥፍራ ልጆቻችንን ማስቀመጥ የለብንም። ከእርሱ ጋር ሊተባበሩ ፈቃደኛ እስከሆኑ ድረስ ልክ በዳንኤልና በጓደኞቹ እንዳደረገው ሁሉ አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር በጥበቃው ወጣቶችን ንጹህ ካልሆኑና ካልተገቱ ጋር እንዲገናኙ ሊፈቅድ ይችላል። ሁል ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር የሚተባበሩ መሆን አለባቸው። እግዚአብሔርን ከሚያዋርድ ማንኛውም ነገር ተጠብቀው ለእርሱ ክብር ብቻ በሚሆን ዐይን ሁል ጊዜ በማየት እራሳቸውን በንጽህና ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል። የእግዚአብሔርን ማንነት ላበላሹት፣ ከልብ በመሥራት፣ ነፍሳትን ለሚያድስ ከፍ ከፍ ለሚያደርግና ለሚያስከብር ተጋድሎ ተዋጉ።16Manuscript 18, 1892.AHAmh 339.5

    አሳቢና ኮስታራ ጓደኞችን ምረጡ፡- ከክርስቶስ ጋር የተስማሙ ወጣቶች መልካም ለመሥራት የሚያግዟቸውን በጓደኝነት ይመርጣሉ፤ ትክክለኛ መርሆዎችንና የከበሩ ዓላማዎችን ለማጎልበት ከማያግዟቸው ይሸሻሉ። አስተሳሰባቸው ዝቅተኛ የሆኑ ወጣቶች በየትም ቦታ ይገኛሉ። ሳይለግሙ እራሳቸውን በክርስቶስ ጎን ያሰለፉ እነርሱ ሚዛናዊነታቸውና ሕሊናቸው የሚነግራቸውን ትክክለኛ ነገር በማድረግ በዓላማቸው ፀንተው ይቆማሉ።17.Counsels to Teachers, Parents, and Students, p. 226.AHAmh 339.6

    ትክክለኛ ባህርይ መመሥረት የሚፈልጉ ሁሉ አሳቢ ትጉህና ለእምነት እውነተኛ ዝንባሌ ካላቸው ጋር ይጎዳኙ። ወጭውን ያሰሉና ለዘለዓለም መገንባት የፈለጉ ሁሉ ጥራት ያላቸው የህንጻ እቃዎችን ይጠቀሙ። የበሰበሱ ግንዶችን ከተቀበሉ፤ ጎደሎ ባለባቸው ባሕርያት ከረኩ ህንፃው ከመፍረስ አይድንም። እንዴት እንደሚገነቡ ሁሌም ጥንቃቄ ያድርጉ። የፈተናው ማዕበል በህንፃው ላይ ያልፋል፤ በጥንካሬና በእምነት ያልተገነባ ከሆነ ፈተናውን አይቋቋመውም።18Testimonies for the Church, Vol. 4, p. 588AHAmh 340.1

    እንደ መልካም መመሪያቸው ከሚራመዱ ጋር ጓደኝነት በመፍጠር ግድ-የለሾች እንኳ ጽድቅን መውደድ ይማራሉ። እውነት የሆነውን በሥራ በመለማመድ ተራና መናኛ ለሆነው ነገር እንዲሁም የእግዚአብሔርን ቃል ለሚፃረረው መርህ ልብ ጣዕም ያጣል።19Counsels to Teachers, Parents and Students, p. 222.AHAmh 340.2