Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የአድቬንቲስት ቤት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ምዕራፍ ሦስት—የቤተ-ኤደን ምሣሌነት

    እግዚአብሔር የሰውን ልጅ የመጀመሪያ ቤት አዘጋጀ፦ በኤደን የነበረውን የመጀመርያ ወላጆቻችንን ቤት እግዚአብሔር እራሱ አዘጋጀው። የሰው ልጅ ሊያስፈልገው የሚችለውን ነገር ሁሉ ካሟላለት በኋላ እንዲህ አለ “ሰውን እንፍጠር በመልካችን እንደ ምሳሌአችን’’…. እግዚአብሔር መጨረሻ በፈጠረውና ከሁሉም በላይ ባከበረው ፍጥረቱ ደስተኛ ነበረ፤ እንከን የለሽ ነዋሪ ሆኖ በፍጹም ዓለም ላይ እንዲኖርም አቀደ። ሰው ብቻውን ይኖር ዘንድ ግን የእርሱ ዓላማ (ፈቃድ) አልነበረም። እግዚአብሔርም አለ “ሰው ብቻውን ይኖር ዘንድ መልካም አይደለም የምትረዳውን በአጠገቡም የምትሆን የምትስማማውን ልፍጠርለት’’ 1The Youth’s Instructor, Aug. 10, 1899.AHAmh 10.1

    እግዚአብሔር እራሱ ለአዳም አጋር ፈጠረለት። “የምትረዳውን፣ የምትስማማውን”፣ የምትመስለውን ረዳት፣ ገጣሚው የሆነችውን ጓደኛ ሰጠው። በፍቅርና በርኅራኄ ከእርሱ ጋር አንድ የምትሆነውን አበረከተለት። ሔዋን ከአዳም የጎን አጥንት ተፈጠረች፤ አመላካችነቱም እራስ ሆና እንዳትቆጣጠረው መናኛም ሆና ከእግሩ ሥር እንዳትረገጥ ነገር ግን ከጎኑ በእኩልነት የምትቆም ሊያፈቅራትና ሊንከባከባት የተገባው እንደሆነች ነው። በዚህ ግንኙነት ሊኖር የሚገባውን የጠበቀ አንድነትና አፍቃሪ ጥምረት በሚያሳይ መልኩ የአካሉ ክፋይ፣ የአጥንቱ አጥንት፣ የሥጋውም ሥጋ እርስዋ ሁለተኛው ራሱ[አዳም] ነበረች። “ሰው የራሱን ሥጋ ይጠላት ዘንድ ከቶ አይቻለውም ይመግባታል ከፍ ከፍ ያደርጋታል እንጂ’’ ስለዚህ ‘‘ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል በሚሽቱም[በሚስቱም] ይጣበቃል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።’’ 2Patriarchs and Prophets, p. 46.AHAmh 10.2

    የመጀመሪያው ጋብቻ በእግዚአብሔር ተፈፀመ፦ እግዚአብሔር የመጀመሪያውን ጋብቻ አከበረ፤ ይህ ተቋም ለጀመረውና የዓለም ፈጣሪ ለሆነው ለእርሱ ነው። “ጋብቻ ክቡር ነው” እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ከሰጣቸው የመጀመሪያ ሥጦታዎች አንዱ ሲሆን ከውድቀት በኋላ አዳም ከገነት በሮች ሲወጣ ከወሰዳቸው ከሁለቱ ተቋማት አንዱ ነበር። በዚህ ግንኙነት ለመለኮታዊ መርህ እውቅና ስንሰጥና ስንታዘዝ ጋብቻ የሚባርክ ይሆናል። የትውልድን ንጽህናና ደስታ ይጠብቃል። የሰውን ማህበራዊ ፍላጎት ያሟላል፤ አካላዊ አዕምሮአዊና ግብረ-ገባዊነት የሞላበት ተፈጥሮን ያበለጽጋል።3Ibid.AHAmh 10.3

    ሔዋንን ለአዳም ረዳት ትሆን ዘንድ የሰጠ እርሱ፣ የመጀመሪያውን ታምሩን በሥርዓተ-ጋብቻ አደረገ። ጓደኛና ዘመድ አዝማድ በተሰበሰቡበትና ሐሴት በሚያደርጉበት የበዓል አዳራሽ ውስጥ ሕዝባዊ አገልግሎቱን ጀመረ። ስለዚህ እርሱ የመሠረተው ተቋም እንደሆነ እውቅና በመስጠት ጋብቻን አፀደቀው። ክርስቶስ የጋብቻን ግንኙነት በእርሱና በዳኑት መካከል ካለው ጥምረት ጋር በማመሳሰል አክብሮታል። ሙሽራው እርሱ ራሱ ነው፤ ሙሽራዋም ቤተ-ክርስቲያን። ሙሽራዪቱም በእርሱ የተመረጠች ስለሆነች እንዲህ ይላታል “ሁለንተናሽ ውብ ነው ወዳጄ ሆይ ነውርም የለብሽም።” 4Ministry of Healing, p. 356.AHAmh 11.1

    የሚያስፈልገው ሁሉ ተሟልቶ ነበር፦ አዳም ልቡ ሊመኘው በሚችለው ነገር ሁሉ ተከብቦ ነበር፤ ሁሉም ፍላጎቱ ተሟልቶ ነበር። ግርማ ሞገስ በነበራት ኤደን የኃጢአት ወይም የመበስበስ ምልክት ፈጽሞ አልነበረም። እግዚአብሔር በነፃነትና በፍቅር ቅዱስ ከሆኑት ጥንዶች ጋር ይወያይ ነበር። ደስተኞቹ ዘማሪዎች ነፃና ሐሴት የሞላባቸው ሆነው የምሥጋና ጥዑመ-ዜማቸውን ለፈጣሪያቸው ያቀርቡ ነበር። ለአዳምና ሔዋን ትዕዛዝ ፍጹም ተገዢ ሆነው፤ ደስተኛ፣ የዋህና የማይተናኮሉ የምድር አራዊት በዙሪያቸው ይጫወቱ ነበር። አዳም ፍጹም ዕፁብ ድንቅና ወደር የማይገኝለት የፈጣሪ የእጅ ሥራ ነበር።5Signs of the Times, June 11, 1874.AHAmh 11.2

    የጥላ ግርዶሽ እንኳን በእነርሱና በፈጣሪያቸው መካከል አይገባም ነበር። እግዚአብሔር በጎ የሚያደርግላቸው አባታቸው እንደሆነ ያውቁ ነበር፤ በሁሉም ነገር ፈቃዳቸው ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር የተስማማ ነበር። የእግዚአብሔር ባህርይ በአዳም ባህርይ ላይ ይንፀባረቅ ነበር። የእግዚአብሔር ክብር በፍጥረት ሁሉ ላይ ይታይ ነበር።6The Youth’s Instructor, June2, 1898.AHAmh 11.3

    ሥራ ለሰው ልጅ ደስታ ሲባል የተሰጠ ነበር፦ እግዚአብሔር የውበት አፍቃሪ ነው። ይህንንም የማያምታታ መረጃ በሆኑት የእጅ ሥራዎቹ አረጋግጦልናል። ለመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን የሚያምር የአትክልት ሥፍራ በኤደን አዘጋጀ። ግርማ ሞገስ የተላበሱ ዛፎች በየወገናቸው ለጥቅምና ለጌጥ እንዲያገለግሉ ሆነው ከመሬት እንዲያድጉ አደረገ። በሁሉም ዓይነትና ቀለማት ብርቅዬ ውበት የተላበሱና አየሩን የሚያውዱ የደመቁ አበባዎች ተፈጠሩ…. የፈጠረውን ነገር ሁሉ ለመንከባከብ በመወከሉ ምክንያት ሰው ደስታን ሊያገኝና የሚፈልገው ነገር ሁሉ በአትክልት ቦታው ባሉ ዛፎች ፍሬ ይሟላ ዘንድ የእግዚአብሔር ሐሳብ ነበር።7The Health Reformer, July, 1871.AHAmh 11.4

    የአትክልት ሥፍራውን የመንከባከብ ኃላፊነት ለአዳም ተሰጥቶት ነበር። ያለ ሥራ አዳም ደስተኛ ሊሆን እንደማይችል እግዚአብሔር ያውቅ ነበር። የአትክልት ሥፍራው ውበት ያስደስተው ነበር፤ ይህ ግን በቂ አልነበረም። ግሩም የሆኑት የአካሉ ብልቶች እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ሥራ መሥራት ነበረበት። ደስታ ምንም ነገር ባለማድረግ የሚገኝ ቢሆን ኖሮ፣ ሰው በነበረው የተቀደሰ ማንነቱ ኃላፊነት ሳይሰጠው ይቀጥል ነበር። ሰውን የፈጠረ እርሱ ግን ለደስታው የሚያስፈልገውን ያውቅ ነበር። በአዳም መፈጠርና የሥራ ኃላፊነት በመሰጠቱ መሐል ምንም የጊዜ ክፍተት አልነበረም። ቃል የተገባለት የወደፊቱ ክብርና የሰው ልጅ ለዕለት እንጀራው መልፋት እንዳለበት የተነገረው አዋጅም የወጣው ከዚሁ ዙፋን ነበር።8The Youth’s Instructor, Feb, 271902.AHAmh 11.5

    እግዚአብሔር በክርስቲያን ቤት ይከብራል፦ በቤተሰባቸው እግዚአብሔርን ተቀዳሚ የሚያደርጉ፤ የጥበብ መጀመሪያ እርሱን መፍራት እንደሆነ ለልጆቻቸው የሚያስተምሩ እናቶችና አባቶች በአመፅ ፈንታ አምላክን የሚወድና የሚታዘዝ፤ ሥርዓት ያለው፣ በጥሩ ሥነ-ምግባር የታነፀ ቤተሰብ ለዓለም በማበርከት በመላእክትና በሰው ፊት ፈጣሪን ያከብሩታል። ክርስቶስ በቤታቸው እንግዳ አይደለም፤ ስሙ የተከበረና የተወደሰ የቤተሰብ ስም ነው። የእግዚአብሔር ልዕልና በነገሠበት ቤት መላእክት ሐሴት ያደርጋሉ፤ ልጆችም ኃይማኖታቸውን፣ መጽሐፍ ቅዱስንና ፈጣሪያቸውን የሚያከብሩ ይሆናሉ። እንደነዚህ ዓይነት ቤተሰቦች “የሚያከብሩኝን አከብራለሁ” የሚለውን የተስፋውን ቃል ለመረከብ የተገባቸው ናቸው። በማለዳ ከእግዚአብሔር ጋር ከሚያደርገው ንግግር የተነሣ ከእንደዚህ ዓይነቱ ቤት አባት ጥዋት ወደ ዕለት ተግባሩ ሲወጣ በትህትናና እራስን ዝቅ ባደረገ መንፈስ ነው።9Testimonies for the Church, Vol. 5, p. 424.AHAmh 12.1

    ወንዶችና ሴቶች ደስታ ያገኙ ዘንድ የክርስቶስ መገኘት ብቻ በቂያቸው ነው። ጣዕም አልባና ተራ የሆኑትን የኑሮ ውኃዎች ሁሉ ክርስቶስ ወደ ሰማያዊ ወይን ጠጅ ሊቀይራቸው ይችላል። ከዚያም ቤታቸው የተድላ ገነት ይሆንላቸዋል - ውብ የሰማይ ቤተሰብ ምሣሌ።10Manuscript 43, 1900.AHAmh 12.2