Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የአድቬንቲስት ቤት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ ሃያ ዘጠኝ—ወደ ሌሎች ሊተላለፍ የማይችለው ሥራ

    ማንም ሊሸከማቸው የማይችላቸው የልጆች ኃላፊነቶች፦ ወላጆች ሆይ ሌላ ማንም ሊሸከማቸው የማይችል ኃላፊነቶች ተጥለውባችኋል። በሕይወት እስካላችሁ ድረስ መንገዱን ትጠብቁ ዘንድ በእግዚአብሔር ተጠያቂዎች ናችሁ…. የእግዚአብሔርን ቃል መመርያቸው ያደረጉ ወላጆች ልጆቻቸው ወርሰውት ለሚያድጉት ባህርይ ምን ያህል እንደሚያስፈልጓቸው ግንዛቤው ስለሚኖራቸው መልካም ምሣሌ በፊታቸው በማስቀመጥ ቢከተሉት አደጋ የሌለበት ፈር መቅደድ ይችላሉ።1Letter 356, 1907.AHAmh 126.1

    እናቶችና አባቶች ለልጆቻቸው ጤና አደረጃጀትና የባህርይ መጎልመስ ኃላፊነት አለባቸው። ይህንን ሥራ ለመሥራት ሌላ ሰው ሊተካ አይችልም። በመልካም አስተዳደር ከእግዚአብሔር ጋር በመተባበር እራሳችሁ ታሳድጓቸው ዘንድ ወላጆቻቸው ሆናችኋል።2Manuscript 126, 1897.AHAmh 126.2

    ከእግዚአብሔር የሆነውን ኃላፊነት አሽቀንጥረው ጥለው ልጆቻቸው እንግዳ በሆኑ ሰዎች እጅ እንዲያድጉ ወላጆች ሲፈቅዱ እንዴት ያሳዝናል! ለእነርሱ ልጆች ሌሎች እንዲለፉ እራሳቸውን ከኃላፊነት ነፃ ለማድረግ ፈቃደኞች ሆነዋል።3Review and Herald, Oct. 25, 1892.AHAmh 126.3

    ዛሬ በልጆቻቸው የባህርይ አስቸጋሪነት እርር ትክን የሚሉ ሁሉ ሊኮንኑት የሚችሉት እራሳቸውን ብቻ ነው። እነዚህ ሰዎች እንደ ወላጆችና እንደ ጠባቂዎች እግዚአብሔር የጣለባቸውን አደራ መጽሐፍ ቅዱሳቸውን ከፍተው ያንብቡ። ለረዥም ጊዜ ቸል ብለውት የነበረውን ግዴታቸውን ይሸከሙት። ልጆቻቸውን በማሠልጠን ረገድ ሊከተሉት የሚገባቸውን አቅጣጫ ቸል ብለው ቆይተዋልና በእግዚአብሔር ፊት ራሳቸውን አዋርደው ይቅርታ ይጠይቁት። የራሳቸውን መንገድ ትተው ዝንፍ ሳይሉ በጥንቃቄ መጽሐፍ ቅዱስን መካሪና መሪ አድርገው ይከተሉት።4Manuscript 57, 1897.AHAmh 126.4

    ቤተ-ክርስቲያን ብቻዋን ይህንን ኃላፊነት መሸከም አትችልም፦ ኦ ወጣቶችና ልጆች ልባቸውን ለክርስቶስ ምነው ቢሰጡ! ሌሎችን ለጽድቅ የሚያሸንፍ ምን ዓይነት ጭፍራ ማስነሣት ይቻል ነበር! ወላጆች ይህን ሥራ ቤተ-ክርስቲያን ብቻዋን እንድትወጣው ሊተዋት አይገባም።5Signs of the Times, Aug. 13, 1896.AHAmh 126.5

    አገልጋዩም ብቻውን አይችልም፦ ከባድ ሸክም ጠቅልላችሁ በአገልጋዩ ላይ ትጭናላችሁ፤ ይባስ ብሎም የልጆቻችሁን ነፍስ ከእጁ ትሻላችሁ። እንደ ወላጅና አሠልጣኝ ያለባችሁን የራሳችሁን ግዴታ ግን አታስተውሉትም…. ሴቶችና ወንዶች ልጆቻችሁ በእናንተው የዘቀጠ መመሪያ ምሣሌነት ብልሹ ሆነዋል። የቤት ውስጥ ሥልጠናችሁን ማጓደላችሁ ሳያንስ የእናንተን የዕለት ተዕለት ጉድለት [የቤተ ክርስቲያን] አገልጋዩ እንዲሞላላችሁ ትፈልጋላችሁ። ልባቸውንና ሕይወታቸውን ወደ ቅድስናና ፍጽምና የሚያመጣውን የመልካም አስተዳደር ውጤት የሆነውን ግሩም ስኬት እናንተ በተዋችሁት ሥልጠና አማካይነት እንዲያስገኝላችሁ ትጠብቁበታላችሁ። በታማኝነት፣ ፍቅር በተሞላበት ተግሳጽ፣ በታጋሽ ሥነሥርዓትና በትጉህ ፀሎት አገልጋዩ ለቤተ-ክርስቲያን ማድረግ የሚችለውን ሁሉ ካደረገ በኋላ እንዲመለሱና እንዲያድጉ ቢጥርም ውጤታማ ካልሆነ ምን ጊዜም አባቶችና እናቶች ልጆቻቸው ባለመለወጣቸው ጣታቸውን የሚቀስሩት ወደ አገልጋዩ ነው። ሆኖም የልጆቻቸው ነፍስ መጥፋት የራሳቸው ዋዘኝነት ሊሆን ይችላል። ሸክሙ ማረፍ ያለበት በወላጆች ላይ ነው። እግዚአብሔር እንዲሠሩ በአደራ የሰጣቸውን ሥራ ለመሥራት ቆርጠው ይነሣሉ? በታማኝነትስ ይተገብሩት ይሆን? ከፍ ከፍ ወዳለው ደረጃ እራሳቸውን ብሎም ልጆቻቸውን እነርሱ ከደረሱበት ከፍታ ለማውጣት በተዋረደ አኳኋን ወደ ፊትና ወደ ላይ መራመድ ይችሉ ይሆን?6Testimonies for the Church, Vol. 5, pp. 494, 495.AHAmh 126.6

    ብዙ እናቶችና አባቶች የራሳቻውን ኃላፊነት በሌሎች ላይ እየጣሉ አይደለምን? ልጆቻቸው እንዲለወጡ፤ የእግዚአብሔርም ማህተም እንዲያርፍባቸው የማድረግ ሸክም የአገልጋዩ እንደሆነ ክትትልም ማድረግ የሚገባው እርሱ እንደሆነ የሚያስቡ ወላጆች ብዙ አይደሉም?7Review and Herald, May 21, 1895.AHAmh 127.1

    የሰንበት ትምህርት ክፍልም አይችልም፦ ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት ይዘውት ሊገቡ የሚችሉትን ዕውቀት ልጆቻቸውን ማስተማር ለወላጆች የተሰጠ እድል ነው። ነገር ግን በሆነ ምክንያት ወላጆች ለልጆቻቸው መንፈሳዊ ትምህርት መስጠት ይጠላሉ። ለእግዚአብሔር ያለባቸውን የኃላፊነት ድርሻ እንዲያውቁ ለሰንበት ትምህርት ክፍል ይተዋቸዋል። እንደዚህ ዓይነት ወላጆች ሊያውቁት የሚገባ ነገር ቢኖር የሚቀርጹት ባህርይ ለዚህና ለወዲያኛው ሕይወት የሚጠቅማቸው መሆኑን በግልጽ በማስረዳት፣ ልጆቻቸውን እንዲያስተምሩ እንዲያስተካክሉና እንዲያሠለጥኑ እግዚአብሔር የሚፈለግባቸው መሆኑን ነው።8Review and Herald, June 6, 1899.AHAmh 127.2

    በምትፈልጉት መንገድ እንዲሄዱ አድርገው እንዲያሠለጥኑላችሁ በሰንበት ትምህርት ክፍል መምህራን ሐሳባችሁን አትጣሉ። አዎን የሰንበት ትምህርት ታላቅ በረከት አለው፤ በሥራችሁም ያግዛችኋል፤ እናንተን ግን ፈጽሞ ሊተካ አይችልም። ልጆቻቸውን ይዘው ወደ ጌታ በመቅረብ እንዴት መፀለይ ያውቁ ዘንድ በቃሉም እምነት ይኖራቸው ዘንድ እንዲያስተምሯቸው ለሁሉም እናቶችና አባቶች ሃላፊነት ተሰጥቷል። የሰንበት ትምህርት ክፍልና አገልጋዩ እናንተየተዋችሁትን ሥራ ይሠሩልናል በማለት ልጆቻችሁ ሊማሩት የሚገባቸውን ታላቁን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ወደ ጎን አትግፉ። ልትከፍቱትና በየቀኑ በትጋት ልታነብቡት፣ ልትነኩትና ልትገልጡት የተከበረ ግርማው የሚያስፈራ አይደለም። የእግዚአብሔርን ቃል እውነታዎች በሕይወታችን ከሚያጋጥሙን እጅግ ጥቃቅንና ተራ ከምንላቸው ነገሮች ጋር ልናመሳክራቸው ይገባናል። በትክክል ከተጠበቁም ተራውን ሕይወት ያፈካሉ፤ የመታዘዝንና መርህን የመከተል ዝንባሌን በመለገስ ትክክለኛ ባህርይ እንዲመሠረት ይረዳሉ።9Manuscript 5, 1896.AHAmh 127.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents