Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የአድቬንቲስት ቤት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ ሃምሳ አንድ—ምክር ለልጆች

    እግዚአብሔርን ቀድማችሁ በልጅነታችሁ ፈልጉት፦ ልጆችና ወጣቶች ቀደም ብለው እግዚአብሔርን መፈለግ ይጀምሩ፤ የልጅነት ልምድ አሻራዎች በሕይወትና በባህርይ ላይ ጠንካራ ተጽዕኖ ማሳደር ይችላሉና። ሳሙኤልን፣ ዮሐንስን በተለይም ደግሞ ክርስቶስን የሚመስሉ ልጆች ዝቅተኛና ተራ ለሚባሉት ነገሮች ሁሉ ታማኝ በመሆን በዚህ ዓለም የሚኖሩት፣ የራስን ፍላጎት ለማሟላትና ለመደሰት እንደሆነ ከሚያስቡ፣ ክፋትን ከሚያልሙ፣ ጉድኝቶችና ጥምረቶች መራቅ ይጠበቅባቸዋል። ብዙ ጥቃቅን የቤት ውስጥ ሥራዎች አለመሥራት ምንም ችግር እንደማያስከትሉ ተደርገው በቸልታ ይታለፋሉ፤ ሆኖም ጥቃቅኖቹ በቸልታ ከታለፉ፣ ትልልቆቹም እንዲሁ ይተዋሉ። ንጹህ ትክክለኛና ክቡር ባህርያት ያላችሁ ሙሉ ወንዶችና ሴቶች መሆን ትፈልጋላችሁ? በቤት ውስጥ ሥራ መሥራት ጀምሩ፤ ልቅምና ጥርት ባለ ሁኔታ አከናውኗቸው። በጥቃቅኖቹ ነገሮች ታማኝ እንደሆናችሁ ጌታ ሲያይ በታላላቅ ኃላፊነቶች እንድትቀመጡ ያደርጋችኋል። እንዴት እንደምትገነቡ፣ ለሕንፃውም ምን ዓይነት ቁሳቁስ እንደምትጠቀሙ ተጠንቀቁ። አሁን የምትገነቧቸው ባህርያት ዘለዓለማዊ ይዘት ያላቸው ናቸው።AHAmh 210.1

    ፍላጎታችሁን ልባችሁንና አዕምሮአችሁን ጌታ ይረከበው፤ የቤት ግዴታዎቻችሁን በንቃት እየፈጸማችሁ፣ ራስን የመካድንና የቸርነትን ሥራ እየሠራችሁ፤ ጊዜያችሁን በትጋት እየተጠቀማችሁ፤ ሊስተዋሉ ለሚከብዱ ትንንሽ ስህተቶች እየተጠነቀቃችሁ፤ ለጥቃቅን ባርኮቶች አመሥጋኝ ሆናችሁ ክርስቶስ ይሠራ በነበረው አኳኋን እናንተም ሥሩ። በመጨረሻም እንደ ዮሐንስና ሳሙኤል በተለይም እንደ ክርስቶስ ለራሳችሁ የምሥክርነት ቃል ታተርፋላችሁ። “የሱስም በጥበብና በቁመት ያድግ ነበረ፣ በፀጋም በእግዚአብሔር በሰውም ዘንድ።” 1The Youth’s Insturctor, Nov. 3, 1886.AHAmh 210.2

    “ልብህን ስጠኝ”፦ ጌታ ለወጣቶች እንዲህ ይላል፡- “ልጄ ሆይ ልብህን ስጠኝ።” የዓለም ሁሉ አዳኝ ልጆችና ወጣቶች ልባቸውን ቢሰጡት ይወድዳል። ክርስቶስ በብርሃን እንደሆነ፣ በብርሃን በመራመዳቸው ምክንያት ለእግዚአብሔር ታማኝ የሆነ ታላቅ የልጆች ጭፍራ ሊመሠረት ይችላል። ጌታ የሱስን የሚወዱ፣ በመደሰቱም ሃሴት የሚያደርጉ ይሆናሉ። ሲገሰጹም ትዕግሥት-የለሽ አይሆኑም፤ እንዲያውም በደግነታቸውና በትዕግሥታቸው የዕለት ተዕለት ኑሮ ይዞ የሚመጣውን ሸክም በደስታ ለመጋራት ፈቃደኛ በመሆን የወላጆቻቸውን ልብ በደስታ የሚያስፈነድቁ ይሆናሉ። በልጅነታቸውና በወጣትነታቸው ጊዜያት ሁሉ ለጌታችን ታማኝ ደቀ-መዛሙርት ሆነው ይገኛሉ። 2 Messages to Young People, p. 333.AHAmh 210.3

    ግላዊ ምርጫ መምረጥ ያስፈልጋል፦ በእግዚአብሔር ነገሮች ላይ ግላዊ ልምምድ (ተሞክሮ) ይኖራችሁ ዘንድ ጥንቃቄ አድርጉ፤ ፀልዩም። ወላጆቻችሁ ያስተምሯችኋል፤ እግሮቻችሁ በማይሰናከሉበት መንገድ ላይ እንድትራመዱ ሊመሯችሁ ይሞክራሉ፤ ሆኖም ልባችሁን ለመቀየር ለእነርሱ ፈጽሞ የማይቻል ነው። ልባችሁን ለየሱስ ልታስረክቡና እርሱ በሰጣችሁ ክቡር የእውነት ብርሃን ልትራመዱ ግዴታ አለባችሁ። የቤት ውስጥ ሕይወት ኃላፊነቶችን በታማኝነት በመተግበር፣ በእግዚአብሔር ፀጋ ክርስቶስ በእርሱ ሥር ያለ ልጁን ሊያሳድገው እንደሚፈልገው ዓይነት ወደ ሙሉ ጉልምስና እደጉ። ወላጆቻችሁ ሰንበትን መጠበቃቸውና እውነትን መታዘዛቸው ለናንተ ድነት ዋስትና አይሆንም (መዳናችሁን አያረጋግጥም)። ኖህ፣ ኢዮብና ዳንኤል በምድር ቢገኙባትም “እኔ ሕያው ነኝ ይላል እግዚአብሔር አምላክ ወንድ ልጅም ሆነ ሴት ልጅም ሆነች እንዳያድኑ እርሳቸው ነፍሳቸውን ያድናሉ እንጂ በጽድቃቸው።” ብሏል።AHAmh 211.1

    በልጅነታችሁና በወጣትነታችሁ እግዚአብሔርን ማገልገል ልትለማመዱ ትችላላችሁ። እውነት እንደሆነ የምታውቁትን አድርጉ። ለወላጆቻችሁ ታዘዙ። ምክራቸውን አድምጡ፤ ምክንያቱም ወላጆቻችሁ እግዚአብሔርን የሚወድዱና የሚፈሩ ከሆኑ ለማይሞተው ሕይወት ሊያስተምሯችሁ፣ ሥርዓት ሊያስይዟችሁና ሊያሰለጥኗችሁ ኃላፊነት የተጣለባቸው ናቸውና። ሊለግሷችሁ የሚፈልጉትን እርዳታ ጎንበስ ብላችሁ በፀጋ ተቀበሉ፤ ጥበብ ለተሞላበት ፍርዳቸው በፈገግታ እጅ በመስጠት የወላጆቻችሁን ልብ በደስታ ሙሉ። እንዲህም ሲሆን ወላጆቻችሁን ታከብራላችሁ፤ እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ ታደርጋላችሁ፤ ለምትጎዳኟቸው ሁሉ በረከት ትሆናላችሁ። 3The Youth’s Insturctor, Aug. 17, 1893.AHAmh 211.2

    ልጆች! ውጊያውን ተጋደሉ፤ አስታውሱ እያንዳንዱ ድል ከጠላት በላይ ያስቀምጣችኋል። 4Manuscript 19, 1887.AHAmh 211.3

    ልጆች ለእርዳታ ይፀልዩ፦ የራሳቸውን መንገድ እንዲከተሉና ራስ-ወዳድ የሆነውን ፍላጎታቸውን እንዲያረኩ፣ የሚኮተኩታቸውን ወደ እነርሱ የሚመጣውን ፈተና መቋቋም ይችሉ ዘንድ ፀጋን እንዲቀበሉ መፀለይ አለባቸው። በሕይወታቸው አገልግሎት ውስጥ ሐቀኛ፣ ቸርና ታዛዥ ይሆኑ ዘንድ በቤተሰብ ዙሪያ የተጣለባቸውን ኃላፊነት መሸከም ይችሉ ዘንድ ክርስቶስን እርዳታ ሲጠይቁት በልጅነት አዕምሮአቸው የፀለዩትን ፀሎት ይሠማል። 5Review and Herald, Nov. 17, 1896.AHAmh 211.4

    ጌታ ልጆችና ወጣቶች ልክ ወደ ወላጆቻቸው በሚቀርቡበት መተማመን ወደርሱ እንዲጠጉ ይፈልጋል። ልጅ ሲርበው እናቱን ወይም አባቱን እንጀራ ስጪኝ/ስጠኝ እንደሚለው ጌታም የምትፈልጓቸውን ነገሮች እንድትጠይቁት ይፈልጋል….AHAmh 211.5

    የሱስ ልጆች የሚፈልጉትን ያውቃል፤ ፀሎታቸውንም ማዳመጥ ይወድዳል። ዓለምን እንዲሁም ሐሳባቸው ከእግዚአብሔር እንዲለይ የሚገፋፋቸውን ማንኛውንም ነገር ሁሉ ልጆች ጥርቅም አድርገው ይዝጉበት። ከእግዚአብሔር ጋር ብቻቸውን እንደሆኑ፣ የእርሱም ዓይን የልብን ጓዳ እንደሚመለከት፣ የነፍስንም መሻት እንደሚያነብብናከጌታ ጋር ማውራት እንደሚችሉ ይሰማቸው....AHAmh 212.1

    ልጆች ለራሳችሁ ማድረግ የማትችሏቸውን ነገሮች እግዚአብሔር እንዲፈጽምላችሁ ጠይቁት። ምንም ሳታስቀሩ ሁሉንም ለየሱስ ንገሩት። የልባችሁን ምስጢራት በፊቱ ፍንትው አድርጋችሁ አቅርቡ፤ አይኑ የነፍስን አጣብቂኝ ስፍራዎች ሁሉ ያስሳል፤ ሃሳባችሁን እንደተገለጠ መጽሐፍ ማንበብ ይችላል። ለነፍሳችሁ መልካምነት አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ሁሉ ስትጠይቁ እንደተቀበላችኋቸው እመኑ፤ በእርግጥ ይሰጣችኋል። 6The Youth’s Insturctor, July 7, 1892.AHAmh 212.2

    የቤት ኃላፊነቶችን በደስታ አከናውኑ፦ ከቤተሰቡ መካከል የግድ አንድ ሰው ሊሠራቸው የተገባውን የቤት ሥራዎች በመሥራት ልጆችና ወጣቶች የቤት ውስጥ ሚሲዮናዊያን ይሁኑ…. ጠቃሚ የማይመስሏችሁን ጥቃቅን የቤት ሥራዎች በታማኝነት በመፈፀም እውነተኛ የአገልጋይነት መንፈስ እንዳላችሁ ልታረጋግጡ ትችላላችሁ። በመንገዳችሁ የምታገኟቸውን ኃላፊነቶች ለመወጣት ፈቃደኛ ስትሆኑ ሸክም የከበደባትን እናታችሁን ስታሳርፏት ነው ለበለጠ ኃላፊነት ብቁ መሆናችሁንና እምነት ሊጣልባችሁ የተገባችሁ እንደሆናችሁ የምታረጋግጡት። የምግብ ዕቃዎችን ማጠብ ደስ የሚል ሥራ ነው ብላችሁ መቸም አታስቡም፤ በነዚያ የምግብ ማቅረቢያ ዕቃዎች የተቀመጠውን መብል የመብላት ዕድል እንዲነፈጋችሁ ግን በጭራሽ አትፈልጉም። እነዚያን ተግባራት ስታከናውን መሠራት ስላለባቸው እንጂ [እቃዎችን ማጠብ] ከእናንተ የበለጠ ለእናታችሁ አስደሳች የሆኑ ይመስላችኋል?AHAmh 212.3

    ሴት መስላችሁ እየተንቀሳቀሳችሁ፣ የማይስማማችሁን የሥራ አይነት እናንተን በመንከባከብ ያለቀችው እናታችሁ እንድትሠራው ልትፈቅዱ ይቻላችኋል? የመጥረግ ሥራ አለ፤ የወለሉ ምንጣፍ መራገፍ አለበት፤ ክፍሎች መስተካከል አለባቸው፤ ለእነዚህ ነገሮች ግድ-የለሽ ሆናችሁ ሳለ ከባድ ሃላፊነት ላይ ለመቀመጥ መጠየቃችሁ ራሳችሁን እንድትቃረኑ አያደርጋችሁምን? እናንተ ስትዝናኑና ትምህርት ቤት ስትሄዱ እናታችሁ እነዚህን ሥራዎች ምን ያህል ጊዜ ደጋግማ እንደምትሠራቸው አስባችሁ ታውቃላችሁ? 7The Youth’s Insturctor, March 2, 1893.AHAmh 212.4

    ብዙ ልጆች የቤት ውስጥ ሃላፊነቶችን ማከናወን ደስ የማያሰኝ ተግባር እንደሆነ አድርገው በዘፈቀደ ለመሥራት ይሞክራሉ፤ እንደሚጠሏቸውም ፊታቸው ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። እንከን ሲፈልጉና ሲያጉረመርሙ ይታያሉ እንጂ በፈቃዳቸው ምንም ሥራ አይሠሩም። ይህ ክርስቶስን መምሰል አይደለም፤ የሰይጣን መንፈስ ነው፤ ይህንን መንፈስ ካበረታታችሁት እንደ እርሱ ትሆናላችሁ። ራሳችሁ ተሰቃይታችሁ በዙሪያችሁም ያሉትን ታሰቃያላችሁ። ምን ያህል መሥራት እንዳለባችሁና ምን ያህል አጭር የመዝናኛ ጊዜ እንዳላችሁ ሲነገራችሁ አታማርሩ፤ ነገር ግን አሳቢና የምትንከባከቡ ሁኑ። ጊዜያችሁን ጠቃሚ ሥራ ላይ ስታውሉት የሰይጣንን የፈተና በሮች ትዘጋላችሁ። የሱስ ራሱን ለማስደሰት እንዳልኖረ እርሱንም መምሰል እንዳለባችሁ አስታውሱ። ይህንን ከሃይማኖታችሁ መርሆዎች አንዱ አድርጉት፤ የሱስንም እርዳታ ጠይቁት። በዚህ ረገድ አዕምሮአችሁን ካለማመዳችሁት በቤት ክበብ እንደሆናችሁት ሁሉ በእግዚአብሔር ጉዳይም ቀንበር ለመሸከም የተዘጋጃችሁ ትሆናላችሁ። በሌሎች ላይ መልካም ተጽዕኖ በማሳደር እንዲያገለግሉ ልትማርኳቸው ትችላላችሁ። 8The Youth’s Insturctor, Jan. 30, 1884.AHAmh 212.5

    ለእናቶች ለውጥና ፋታ ስጡ፦ የማይወዱትን ሥራ ላለመሥራት ሲሉ ማናቸውንም ምክንያት ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆኑ፣ ለሥራው ምንም ፍላጎት የሌላቸውን ልጆችዋን እንዲሠሩ ማስገደድ ለአፍቃሪዋ እናታቸው ከባድ ነው። ልጆችና ወጣቶች ሆይ ክርስቶስ እየተመለከታችሁ ነው፤ በእጃችሁ ያስቀመጠውን አደራ ቸል ስትሉ እንዲያያችሁ ትፈልጋላችሁ? ጠቃሚ መሆን ከፈለጋችሁ ዕድሉ የእናንተ ነው። የመጀመሪያው ሃላፊነታችሁ ብዙ የደከመችላችሁን (የዋለችላችሁን) እናታችሁን መርዳት ነው። በሕይወትዋ በጣም ጥቂት የበዓል ቀናት ነው የነበራት፤ ለውጥም አይታ አታውቅም፤ ስለዚህ ሸክምዋን አንሱ፤ አስደሳች የዕረፍት ቀናት ለግስዋት። ሁሉም መዝናናትና ደስታ ይገባኛል ስትሉ ኖራችኋል፤ አሁን ለቤቱ የፀሐይ ብርሃን ትሆኑ ዘንድ ሠዓቱ ነው። ሃላፊነታችሁን ተረከቡ፤ ቀጥታ ወደ ሥራችሁ ግቡ። ራሳችሁን ክዳችሁ ደስታና ዕረፍት አበርክቱላት። 9The Youth’s Insturctor, March 2, 1893.AHAmh 213.1

    የእግዚአብሔር ሽልማት ለዛሬዎቹ ዳንኤሎች፦ እንደ ዳንኤል ደፋር ሠራተኛ የሆኑ ወንዶች ዛሬ ያስፈልጋሉ። ንፁህ ልቦና ያለው፣ ጠንካራና ፍራትን የማያውቅ ትውልድ ዓለም ዛሬ ትፈልጋለች። ሰው በእውቀት እርከን ከፍተኛ ደረጃ እንዲደርስና ሁሌም እንዲሻሻል የእግዚአብሔር እቅድ ነው። ራሳችን ልንረዳ ጥረት ካደረግን እርሱም ይረዳናል። በሁለቱም ዓለማት እውን ይሆን ዘንድ ተስፋ የምናደርገው ደስታ በዚህኛው ዓለም በምናሳየው መሻሻል ይወሰናል….AHAmh 213.2

    ውድ ወጣቶች ሆይ በፀጋው ልትሠሩት የምትችሉትን ሥራ እንድትሠሩ እግዚአብሔር ይጠራችኋል። “ሥጋችሁን ታቀርቡ ዘንድ ሕያው መሥዋዕት አድርጋችሁ የተቀደሰች እግዚአብሔርን ደስ የምታሰኝ። እርስዋም በአዕምሮ ያለች ማገልገላችሁ ናት።” እግዚአብሔር በሰጣችሁ ወንድነታችሁና ሴትነታችሁ ተነሡ። ከዳንኤል ጋር ሊወዳደር የሚችል የምርጫ የፍላጎትና የልምድ ንጽህና አሳዩ። እንዲህ ካደረጋችሁ በተረጋጋ አዕምሮ፣ በንጹህ ጭንቅላት፣ ባልተጋረደ ሚዛናዊነት፣ ባልተሸፈነ አመለካከትና በፈጣን አስተዋይነት እግዚአብሔር ዋጋችሁን ይከፍላችኋል። መመሪያቸው ጠንካራና የማይዋዥቅ የሆኑ የዛሬዎቹ ወጣቶች በጤናማ አካል፣ አዕምሮና ሕይወት ይባረካሉ። 10The Youth’s Insturctor, July 9, 1903.AHAmh 213.3

    ያለፈውን ለመለወጥ አሁን ጀምሩ፦ ወጣቱ የራሱን ዘለዓለማዊ ዕጣ ፈንታ እየወሰነ ነው፤ እግዚአብሔር ተስፋ የቀጠለበትን ትዕዛዝ በቁም ነገር እንድትመለከቱት እለምናችኋለሁ። “ዕድሜህ ይረዝም ዘንድ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር።” ልጆች! የዘለዓለም ሕይወት ምኞታችሁ ነው? ከሆነ እናትና አባታችሁን አክብሩ። ልባቸውን አቁስላችሁና አሳዝናችሁ በእናንተው ጉዳይ በስቃይና በጭንቀት እንቅልፍ-የለሽ ሌሊቶች እንዲያሳልፉ አታድርጓቸው። ፍቅርና መታዘዝን ባለማሳየታችሁ ኃጢአት ሠርታችሁ ከሆነ ያለፈውን ለመቀየር አሁን ጀምሩ። የዘለዓለም ሕይወትን የሚሰጣችሁ እርሱ ነውና ሌላ መንገድ ልትመርጡ አይቻላችሁም። 11The Youth’s Insturctor, June 22, 1893AHAmh 214.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents