Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የአድቬንቲስት ቤት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ምዕራፍ ስምንት—የተለመዱ የመጠናናት ተግባራት

    ስለመጠናናትና ጋብቻ የተሳሳቱ አስተሳሰቦች፦ ስለመጠናናት ያለው አስተሳሰብ ስለጋብቻ ባለው የተሳሳተ አመለካከት ላይ መሠረት ያደረገ ነው። የልብ ትርታንና ጭፍን ፍላጎትን የሚከተል ነው። መጠናናት ቀልድ በተሞላበት መንፈስ የሚተገበር ሆኗል። ሁለቱም ወገኖች ብዙ ጊዜ የመጠንንና የቁጥብነትን መርህ ይጥሳሉ። የእግዚአብሔርን ሕግ ባይተላለፉም እንኳ የችኩልነት ጥፋተኞች ናቸው። ታላቁ፣ የከበረውና ግዙፉ የእግዚአብሔር የትዳር አመሠራረት ንድፍ በውል አይታወቅም። በመሆኑም ንጹህ የሆነ ልባዊ ፍቅርና የከበረ የባህርይ ልምድ አይጎለብትም።AHAmh 31.1

    በላይ በሰማይ ካለው መዝገባችሁ ውስጥ መላእክት እንዲመዘግቡት የማትፈልጉትን አንድም ቃል አትናገሩ፤ ምንም ሥራ አትሥሩ። ለእግዚአብሔር ክብር ብቸኛ የሆነ አይን ይኑራችሁ። ልባችሁ ንጹህና የተቀደሰ ፍቅር የሚሰጥ ከምድራዊ ይልቅ ሰማያዊ ይሁን። የሱስን ለመከተል ብቁ የሚያደርጋችሁና በባህርይውም ከፍ ከፍ ያለ ይሁን። ማንኛውም ከዚህ ውጪ የሆነ መንገድ ሁሉ መጠናናትን የረከሰና የዘቀጠ ያደርገዋል። በከበረው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የተመሠረተ ካልሆነ እንከን-የለሽና ቅዱስ አምላክ ፊት፣ ትዳር ቅዱስና ክቡር ሊሆን አይችልም።1Manuscript 4a, 1885.AHAmh 31.2

    ወጣቱ ከሚገባው በላይ ቅጽበታዊ በሆነ ስሜት ያምናል። እራሳቸውን በቀላሉ አሳልፈው መስጠትና በአፍቃሪያቸው ውጫዊ ውበት መሸነፍ የለባቸውም። የዚህ ዘመን መጠናናት መመጻደቅንና ማታለልን ስውር ዓላማው አድርጎ የያዘ፣ ከእግዚአብሔር ይልቅ የነፍሳቸው ጠላት ዲያብሎስ እንዲጠቀምባቸው የሚዳርግ ነው። ጥልቅ ማስተዋል አስፈላጊ ሆኖ ሳለ በመጠናናት ጉዳይ ላይ ግን እምብዛም ቦታ አይሰጠውም።2Fundamentals of Christian Education, p. 105.AHAmh 31.3

    በውድቅት መገናኘት፦ ከመሸ በኋላ (በጨለማ) አብሮ መቀመጥ የተለመደ ነው። ሁለቱም ክርስቲያን ቢሆኑም እንኳ ይህ እግዚአብሔርን አያስደስተውም። እነዚህ ጊዜን ያልጠበቁ ሰዓታት ጤናን ያውካሉ፤ ለሚቀጥለው ቀን ሥራችን ዝግጁ እንዳንሆን ያደርጋሉ፤ የጥፋትም መልክ የያዙ ናቸው። ወንድሜ ሆይ ከእንደዚህ ዓይነቱ መጠናናት እራስህን ለማግለል የሚያስችልህ ለራስህ በቂ ክብር እንደምትሰጥ ተስፋ አደርጋለሁ። ለእግዚአብሔር ክብር የሚሆን ዐይን ብቻ ካለህ፣ ግንዛቤ በተሞላበት ጥንቃቄ ትንቀሳቀሳለህ። እንደ ክርስቲያን እግዚአብሔር በአንተ ላይ ያለውን መጠይቅ እንዳታውቅ በማድረግ እይታህን ከሚያጨልም ከፍቅር ገመምተኛነት ስሜት ትጠበቃለህ።3Testimonies for the Church, Vol. 3, pp. 44, 45.AHAmh 31.4

    በጨለማ ለመጠናናት ሰፋ ያለ ጊዜ የሚወስዱትን የሰይጣን መላእክት በአንክሮ ይከታተሏቸዋል። ዐይናቸው ቢከፈትና ቢያዩ ንግግራቸውንና እንቅስቃሴአቸውን የሚመዘግበውን መልአክ ይመለከቱ ነበር። የጤናና የቁጥብነት ሕጎች ተጥሰዋል። ከእንዲህ ዓይነቱ ተግባር ይልቅ የተወሰነውን የመጠናናት ጊዜ ከጋብቻ በኋላ ማድረግይሻላል። እንደ ተለምዶ ሆኖ ግን በመጠናናት የታየው ትኩረትና ጥረት ጋብቻ ሲፈፀም ያቆማል። እነዚህ በውድቅት የሚባክኑ ሰዓታት በዚህ በዘቀጠ ዘመን በአብዛኛው ሁለቱንም ወደ ጥፋት የሚመሩ ናቸው። ሴቶችና ወንዶች ራሳቸውን ሲያረክሱ ሰይጣን ከፍ ከፍ ሲል፣ እግዚአብሔር ይዋረዳል። የክብር መልካም ስም በስሜታዊ ፍቅር ሥር ስለሚሰዋ፣ የእንደዚህ ዓይነት ሰዎች ጋብቻ በእግዚአብሔር ዘንድ ጸድቆ እውቅና አይሰጠውም። በስሜት ተነሳስተው ነው የተጋቡት። ከጊዜ በኋላ ይህ ስሜታዊ ፍቅራቸው ሲቀዘቅዝ ምን እንዳደረጉ ይገባቸዋል።4Review and Herald, sept. 25, 1888.AHAmh 31.5

    ምን ምን ነገሮችን መጠቀም እንዳለበት ሰይጣን ጠንቅቆ ያውቃል። የተለያዩ መሣሪያዎቹን በመጠቀም ዲያብሎሳዊ ጥበቡን ይገልጻል። በማታለል ስልቱም ወደ ጥፋታቸው ይመራቸዋል። ሰዎች የሚወስዱትን እያንዳንዱን እንቅስቃሴ ይመለከታል፤ ብዙ አማራጮችን ይጠቁማል፤ ብዙ ጊዜ የእግዚአብሔርን ቃል ምክር ከመስማት ይልቅ ሰይጣን የጠቆማቸው አማራጮች በመፍትሄነት ይወሰዳሉ።AHAmh 32.1

    ይህ በቀጭኑ የተሸመነ አደገኛ መረብ በብልሃት ተዘጋጅቶ ወጣቱንናያልተጠረጠረውን ያጠምዳል። እራሱን ደብቆ በብርሃን ተጀቡኖ ይመጣል፤ የዚህ ረቂቅና እኩይ ሥራ ተጠቂዎች ግን ዘልቆ በሚገባ የሐዘን በትር ራሳቸውን ይገርፋሉ። የሰው ዘር ፍርስራሽ በሁሉም ቦታ ተበታትኖ የምናየውም ለዚህ ነው።5Fundamentals of Christian Education, pp. 103,104.AHAmh 32.2

    በሰው ልብ ማላገጥ፦ በሰው ልብ ማላገጥ በእግዚአብሔር ዕይታ ቀላል የሚባል ወንጀል አይደለም። ሆኖም አንዳንድ ወጣቶች ሴቶችን ከመረጡና እንደሚያፈቅሩአቸው ከነገሯቸው በኋላ ያሉትን ሁሉ ረስተው፣ የተናገሩት በሴትዋ ላይ ያመጣውን ተጽዕኖ ችላ ብለው የራሳቸውን መንገድ ይሄዳሉ። አዲስ ፊት ይማርካቸዋል፤ እነዚያን ለፊተኛዋ የተናገሩትን ቃላት ለአዲስዋም ይደግሙታል፤ ተመሳሳይ ትኩረት ለኋለኛዋም ይለግሳሉ። ይህ ዝንባሌ በጋብቻ ሕይወትም ይገለፃል። ወደ ትዳር ሕይወት መግባቱ ከዳተኛ የነበረውን ህሊና ጽኑ፤ ያቅማማ የነበረውን ሰው የማያወላውል ለመርህም ታማኝ አያደርገውም። ሁልጊዜ ተመሳሳይ በሆነው ነገር ይሰላቻሉ፤ የረከሰ አስተሳሰባቸውም በረከሰ ተግባራቸው ይገለጻል። ወጣቶች የአስተሳሰባቸውን መቀነት አጥብቀው ጠባያቸውንም ተቆጣጥረው ቀጥተኛ ከሆነው መንገድ ሰይጣን እንዳያስታቸው መትጋ እንዴት አስፈላጊ ነው!6Review and Herald, Nov. 4, 1884.AHAmh 32.3

    በመጠናናት ጊዜ አሳሳች የሆኑ ተግባራት፦ እናትና አባትዋ ሳያውቁ የአንዲትን ወጣት አብሮነትና ጓደኝነት የሚካፈል ወጣት፣ ለእርስዋም ሆነ ለቤተሰቦችዋ ክርስቲያናዊ ጨዋነትን እያሳየ አይደለም። በምሥጢራዊ ግንኙነትና ንግግር በአስተሳሰቧ ላይ ተጽዕኖ ሊያተርፍ ይችላል። እንዲህ ሲያደርግ ግን የእግዚአብሔር ልጆች የሆኑ ሁሉ ሊኖራቸው የሚገባውን የነፍስን ጨዋነትና ሐቀኝነት ማሳየት ይሳነዋል። ፍላጎታቸውንም ለማርካት የመጽሐፍ ቅዱስ ደረጃን ያልጠበቀ፣ ሐቀኛና ግልፅ ያልሆነ ድርጊት ይፈጽማሉ፤ ለሚወዷቸው ታማኝ ጠባቂያቸው ለመሆን በሚጥሩት ወላጆቻቸው ላይ ውሸታሞችመሆናቸውን ያረጋግጣሉ። በእንደዚህ ዓይነቱ ተጽዕኖ የሚፈጸሙ ጋብቻዎች እንደ እግዚአብሔር ቃል የሆኑ አይደሉም። የተሰጧትን ግዴታዎች የሚያስተዋት፤ እናትና አባትዋን እንድትታዘዝና እንድታከብር እግዚአብሔር የሰጠውን ግልጽና ቁርጥ ያለ ትዕዛዝ ስለመከተል ያላትን ዓላማ የሚያምታታባት ወንድ እርሱ ለጋብቻ ኃላፊነቶች ታማኝ የሚሆን አይደለም…..AHAmh 32.4

    ‘‘አትስረቅ’’ የሚለው ትዕዛዝ በእግዚአብሔር ጣት በጽላት ላይ የተጻፈ ነው። ሆኖም ምን ያህል እጅ ከፍንጅ የሚያዝ የፍቅር ስርቆት ይፈፀማል፤ ይሸፋፈናል! አሳሳች መጠናናቶች ባሉበት ይጠበቃሉ፤ የተደበቁ ግንኙነቶች ይቀጥላሉ።AHAmh 33.1

    ልምድ የሌላትም ወጣት እነዚህ ነገሮች ወደ የት አቅጣጫ እያደጉ እንደሆነ ሳታውቅ፣ ለቤተሰቦችዋ ያላት ፍቅር ቀስ በቀስ ቀዝቅዞ በሚጠቀመው የማታለያ መንገድ ምክንያት ልታፈቅረው ባልተገባው ሰው ላይ ያርፋል። መጽሐፍ ቅዱስ ማንኛውንም ዓይነት ሸፍጥ ያወግዛል። እነዚህ የተደበቁና እምነት የጎደላቸው መጠናናቶችና ጋብቻዎች የጥልቀቱ ዲካ በእግዚአብሔር ብቻ ሊታወቅ የሚችል የከባድ መከራና ስቃይ ምክንያቶች ናቸው። ቁጥር ስፍር የሌላቸው ሰዎች ከድንጋይ ጋር እንደ ተጋጨች መርከብ ከትዳር ቋጥኝ ጋር ተላትመው ሕይወታቸው የተንኮተኮተባቸው ነፍሳት ሆነዋል። ሕይወታቸው በሐቀኝነት የተሞላ፣ በሌላው መስክ ሁሉ አስተዋይ የሆኑ፣ የተዋጣላቸው ክርስቲያኖች ጭምር እዚህ ላይ አስፈሪ ስህተት ይሠራሉ። ውሳኔያቸውን አሳማኝ ምክንያት ሊቀይረው የማይችል ዓይነት አቋም ይይዛሉ። በሰውኛ ስሜትና የልብ ትርታ ሰክረው፣ መጽሐፍ ቅዱስን ለመመርመርና ከእግዚአብሔር ጋር የጠበቀ ጓደኝነት ለመመሥረት ፈጽሞ ፍላጎት የላቸውም።7Fundamentals of Christian Education, pp. 101-103. AHAmh 33.2

    ቁልቁል የሚያወርዳችሁን የመጀመሪያውን እርምጃ አስወግዱ፦ ከአሥርቱ ትዕዛዛት አንዱን መተላለፍ ከተጀመረ የውድቀት እርምጃ ተጀመረ ማለት ነው። የሴት ልጅ የቁጥብናዋ መከለያ ከተወገደ በኋላ ወራዳና ፀያፍ የሆነውን ሥራ የመሥራት ፈቃደኝነትዋ እንኳ ፈጽሞ ኃጢአት መስሎ አይታያትም። ወይኔ! እንዴት አሰቃቂ የሆነ የሴት ልጅ የጥፋት ተጽዕኖ ውጤት ዛሬ በምድራችን በዝቶ ይታያል! “በእንግዳ ሴቶች” ተታልለው በሺዎች የሚቆጠሩ በእስር ቤት እየማቀቁ ነው፤ ብዙዎች ራሳቸውን አጥፍተዋል፤ ብዙዎች የሌሎችን ሕይወት በአጭር አስቀርተዋል። የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት እንዴት እውነት አላቸው፤ እንዲህ ይላሉና:- “እግሮችዋ ወደ ሞት ይወርዳሉ አረማመድዋም ወደ ሲኦል ነው።”AHAmh 33.3

    ወንዶች ወደ አደገኛና የተከለከለ ምድር መዳረሻ እንዳይቀርቡ በሁሉም የሕይወት ጎዳና ዙሪያ የማስጠንቀቂያ መብራቶች ተቀምጠዋል። ሆኖም ብዙዎች ምክንያት የሚያስተምረውን የእግዚአብሔርን ቃል በመፃረር፤ ለእግዚአብሔር ሕግ ጆሮ ባለመስጠት፤ የእርሱንም በቀል በመገዳደር፤ የጥፋትን መንገድ ይመርጣሉ። ጤንነታቸውን የሚጠብቁ፣ ጥልቅ የማሰብ ችሎታና መልካም ግብረ-ገብነት ያላቸው እነርሱ “ከወጣትነት ዝሙት…. መሸሽ” አለባቸው። ዐይን ያወጣ ርኩሰትን ለማስቆም በቀናኢነትና በቆራጥ ውሳኔ ጥረት የሚያደርጉ በመካከላችን ያሉ ልበ-ሙሉ ሰዎች በአጥፊዎች አፍ ቢታሙና ቢጠሉ እንኳ እግዚአብሔር ያከብራቸዋል።8Signs of the Times, July 1, 1903.AHAmh 34.1

    ስናር(wild oats) ዝሩ መራር ሰብልን ትሰበስባላችሁ፦ ስናር በመዝራት ኑሮአችሁንና ነፍሳችሁን አደጋ ላይ አትጣሉ። የሕይወት አጋራችሁን ለመምረጥ ዋዘኛ ትሆኑ ዘንድ አይቻላችሁም።9Messages to Young People, p. 164. ስናር በመዝራት የምታጠፉት የአጭር ጊዜ ደስታችሁ ሕይወታችሁን ሙሉ መራራ የሚያደርግ ሰብልን ያመርታል። የአንድ ሰዓት ግድ-የለሽነት የሕይወታችሁ ሞገድ በተሳሳተ አቅጣጫ እንዲንቀሳቀስ ይመራል።የሚኖራችሁ አንድ ወጣትነት ጊዜ ብቻ ነው፤ የሚጠቅም አድርጉት። አንድ ጊዜ ፈጽማችሁት ካለፋችሁ በኋላ ተመልሳችሁ ስህተታችሁን ልታስተካክሉ አትችሉም። ከእግዚአብሔር ጋር ለመቆራኘት እምቢ የሚል፣ ራሱንም በፈተና መንገድ የሚያኖር፣ እርሱ በእርግጥ ይወድቃል። እግዚአብሔር እያንዳንዱን ወጣት ይፈትናል። ብዙዎቹ የግድ-የለሽነታቸውና የእርባና-ቢስነታቸው ምክንያት በልምድ ከነርሱ በተሻሉ ክርስቲያን ነን ባዮች የተሳሳተ ምሳሌነት እንደሆነ አድርገው ያሳብባሉ። ይህ ግን ማንንም መልካም ከማድረግ ሊገድበው አይገባም። በመጨረሻው ቀን ስትጠየቁ አሁን የምታቀርቡትን ማስተባበያ ያንጊዜ ልታቀርቡ አትችሉም ።10Testimonies for the Church, Vol. 4, pp. 622, 623.AHAmh 34.2