Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የአድቬንቲስት ቤት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ምዕራፍ አሥራ ሁለት—መጣጣም ወይም መገጣጠም

    አንዱ ለሌላው እንዲስማማ ይሁን፦ በብዙ ቤት ውስጥ የቤተሰቡን አባላት የሚያዘጋጅና አግብተው የራሳቸውን ደስተኛ ቤተሰብ እንዲመሠርቱ የሚያግዝ ክርስቲያናዊ ገርነት፣ እውነተኛ ደግነት፣ ፈቃደኝነትና የእርስ በእርስ መከባበር የለም። በትዕግስት፣ በደግነት፣ በሩኅሩኅነት፣ በክርስቲያናዊ አዛኝነትና በፍቅር ፈንታ የሚነቁሩ ቃላት፣ የሚጋጩ ሐሳቦች፣ የውግዘትና የአምባ-ገነንነት መንፈስ በቤት ውስጥ ይበዛል።1Review and Herald, Feb, 2, 1886.AHAmh 50.1

    በአብዛኛው ሰዎች ከመጋባታቸው በፊት የእያንዳንዳቸውን ፈቃድና ልምድ በቅጡ የማወቅ ወይም የመለማመድ ዕድል አያገኙም። የዕለት ተዕለት ሕይወታቸውን ስናስብ፣ በሚገባ ያልተዋወቁ ለእርስ በእርሳቸው እንግዳ ሆነው ሳለ፣ ኑሮአቸውን በመሠውያው ሥር አንድ ለማድረግ ይጋባሉ። ብዙዎች የሚስማሙ እንዳልሆኑ የሚነቁት ነገር ካለቀ በኋላ፣ ውሳኔአቸውን መቀልበስ በማይችሉበት ጊዜ ነው። በዚህም ምክንያት ሕይወታቸው ሙሉ የተንኮታኮተ ይሆናል። ሁልጊዜ ሚስቶችና ልጆች በባሎችና በአባቶች ስንፍናና ጉድለት ወይም የአረመኔነት ጠባይ የተነሣ የሚሰቃዩ ይሆናሉ።2Patriarchs and Prophets, p. 189.AHAmh 50.2

    በማይጣጣሙ ጋብቻዎች ምክንያት ዛሬ ዓለማችን በስቃይና በኃጢአት የተሞላች ሆናለች። ባልና ሚስት ጠባያቸው ወደ አንድነት ሊመጣ (ሊኳኋን) እንደማይችል ለማወቅ ከጥቂት ወራት በላይ አይወስድባቸውም። በመሆኑም ሰማያዊ መስማማትና ፍቅር መንገሥ ሲገባው ንትርክ ቤታቸውን ይሞላዋል። በጥቃቅንና አላስፈላጊ ነገሮች ላይ የሚነሣው ጭቅጭቅ መራራ መንፈስን ያጎለብታል። ይፋ የሆነ ልዩነታቸውና በማይረባ ነገር ላይ ንዝንዛቸው ሊነገር የማይችል ሰቆቃ ወደ ቤታቸው በማምጣት በፍቅር ሰንሰለት ተሳስረው መኖር የነበረባቸውን ጥንዶች ይለያያቸዋል። በመሆኑም በሺዎች የሚቆጠሩ ብልሃት ባልተጨመረበት ጋብቻ ምክንያት እራሳቸውን፣ ነፍሳቸውንና አካላቸውን ሰውተዋል፤ የጥፋትንም መንገድ ይዘው ቁልቁል ወርደዋል።3Messages to Young People, p. 453.AHAmh 50.3

    ዘላቂ የሆነ ልዩነት በተከፋፈለ ትዳር ውስጥ፦ የትዳር ኑሮ ደስታና ብልጽግና ሁለቱ ባላቸው ህብረት ይወሰናል። የአንደኛው የሥጋ ሐሳብ ከክርስቶስ መስማማት ካለው ከሌላኛው ሐሳብ ጋር እንዴት ሊጣጣም ይችላል? አንደኛው ልቡ እንደሚመራው የሚያስብና የሚንቀሳቀስ፣ ለሥጋ የሚያከማች ሲሆን ሌላኛው ወገን ለመንፈስ የሚያዘምር፤ ራስ-ወዳድነቱን ለመግታትና ምኞቱን ለማሸነፍ የሚጥር፣ አገልጋይነቱን ላወጀለት ለጌታ የሚኖርና የሚታዘዝ ነው። ስለዚህ ዘላቂ የጣዕም፣ የዝንባሌና የዓላማ ልዩነት ይኖራቸዋል። አማኙ ወገን የዓላማ ጽናት በማሳየት ንስሐ ያልገባውን አካል ማሸነፍ ካልቻለ በቀር፣ ብዙ ጊዜ እንደሚሆነው ሁሉ እርሱ እራሱ ተስፋ ቆርጦ፣ የኃይማኖቱን መመሪያ ከሰማይ ጋር ምንም ግንኙነት ለሌለውና ለደካማው ትዳሩ ይሸጠዋል።4Testimonies for the Church, Vol. 4, pp. 507, 508.AHAmh 50.4

    ባለመጣጣም የፈረሰ ትዳር፦ ብዙ ትዳሮች ሰቆቃ የተሞሉ እንደሚሆኑ ግልጽ ነው፤ ሆኖም ግን የወጣቶች አስተሳሰብ ይህንን የሚረዳ አልሆነም። ወደዚያ የተሳሳተ ዝንባሌ የሚመራቸው ደግሞ ሰይጣን ነው። እራሳቸውን መቆጣጠር ወይም ቤተሰብ ማስተዳደር የማይችሉ ሆነው ሳለ ደስተኛ መሆን ከፈለጉ ማግባት እንዳለባቸው ዲያብሎስ ያሳምናቸዋል። አንዳቸው ከሌላኛው ባህርይ ጋር እራሳቸውን ለማጣጣም ፈቃደኛ ካልሆኑ በስተቀር ከትዳር በኋላ የሚመጡ፣ የማይመቹ ልዩነቶችንና ንትርኮችን ለማስወገድ ሲባል እነዚህ ወገኖች ጋብቻ መፈፀም የለባቸውም። ይህ ዓይነቱ አካሄድ የመጨረሻዎቹ ቀናት መማረኪያ ወጥመዶች ውስጥ አንዱ ነው፤ በሺዎች የሚቆጠሩ የዚህና የሚመጣው ሕይወታቸው ተበላሽቶ ይቀራል።5Id., Vol. 5, pp. 122, 123.AHAmh 51.1

    የጭፍን ፍቅር መጨረሻው፦ በዚህ ተላላፊ በሽታ - በእውር ፍቅር - የተለከፉ ሰዎች ሁሉ በቁጥጥሩ ሥር ይሆናሉ። መልካም አስተሳሰባቸው የጠፋባቸው ይመስላል፤ ለሚመለከታቸው ሁሉ አካሄዳቸው የማይጥም ይሆናል…. ይህ በሽታ ያለ ጊዜው በተፈፀመ ጋብቻ ይከሰታል። የሙሽርነት ጊዜያቸው ሲያልቅ፤ የግብረሥጋ ግንኙነት የውለሽ ኃይል (የጋለ ስሜቱ) ሲቀዘቅዝ፤ አንደኛው ወይም ሁለቱም ወገኖች ለነባራዊ ሁኔታቸው ይነቃሉ። ከዚያም የማይገጥሙ ግን ለዘለዓለም የተሳሰሩ መሆናቸውን ይደርሱበታል። ከምንም በላይ ከባድ በሆነው ቃል-ኪዳን ተጠፍረው መምራት ያለባቸውን የሰቆቃ ሕይወት ሐዘን በተሞላ ልብ ይመለከቱታል። ሁኔታዎቻቸውን በፀጋ ተቀብለው ለማሻሻል ቢጥሩ መልካም በሆነ ነበር፤ ግን ብዙዎች እንዲህ አያደርጉም። ለገቡት የጋብቻ ቃል-ኪዳን ታማኝ ሳይሆኑ ይቀራሉ። በራሳችን ላይ ካልጫንን ብለው አንቢ ያሉትን የጋብቻ ቀንበር የባሰ አሰቃቂ በማድረግ ጥቂት የማይባሉ ወኔ የሌላቸው አጋሮቻቸው እራሳቸውን እንዲያጠፉ ምክንያት ሆነዋል።6Id., pp. 110, 11.AHAmh 51.2

    ስለዚህ ጭቅጭቅ የሚያመጣውን ነገር ሁሉ በማስወገድ የጋብቻ ቃል-ኪዳናቸው ሳይጣስ ለማቆየት ሲባል ትዳር የባልና የሚስት፣ የሁለቱም፣ የዕድሜ ልክ ጥናት ሊሆን ይገዋባል።7Id., p. 122AHAmh 51.3

    የሌሎች ተሞክሮ እንደማስጠንቀቂያ፦ አቶ ኤ (Mr.A) ሰይጣን ሊጠቀምበትና ግሩም ውጤት ሊያገኝበት የሚችል ዓይነት ጠባይ ያለው ነው። ይህ የአቶ ኤ ገጽታ ወጣቶችን ሊያስተምር ያስፈልጋል። የአቶ ኤ ሚስት ሐሳቧንና የልብ ትርታዋን ተከትላ እንጂ ምክንያትንና ህሊናን ያማከረ ውሳኔ ሳታደርግ ነው አጋርዋን የመረጠችው። ጋብቻቸው የእውነተኛ ፍቅር ውጤት ነው? አይ! አይደለም፤ የስሜት ውጤት ነው - እውር፣ ያልተቀደሰ ፍላጎት። ሁለቱም የጋብቻ ሕይወት ለሚጠይቀው ኃላፊነት ብቁ አልነበሩም። የአዲስ ሙሽራነታቸው ሆይ ሆይታ ሲያረጅና ሁለቱም በደንብ እየተዋወቁ ሲመጡ ፍቅራቸው ጠነከረ? መውደዳቸው ጥልቅ ሆነ? በሚማርክ መስማማት ሕይወታቸው አንድ ሆነ? ፈጽሞ ተቃራኒው ነው የሆነው። መልካም ያልሆነው የባህርይ ገጽታቸው የባሰ በልምድ እየዳበረና እየጠለቀ ሄደ። የጋብቻ ሕይወታቸው ደስተኛ መሆን ሲገባው ችግራቸውን የሚያባብስ ሆነ።8Id., pp. 121, 122.AHAmh 51.4

    ልብ የሚያሳምም የአመጽ ታሪክ የተሞላባቸው፣ ደስታ የሌላቸው ትዳሮች ውስጥ ከተዘፈቁ ከተለያዩ ሰዎች ለዓመታት ደብዳቤዎች ደርሰውኛል። ለእነዚህ እድለ-ቢስ ሰዎች መራራ ዕጣቸው እንዴት ሊቀልላቸው እንደሚችል ምን ዓይነት ምክር መስጠት እንደሚቻል መወሰን ቀላል አይደለም፤ ነገር ግን ይህ አሳዛኝ ገጠመኝ ለሌሎች ማስጠንቀቂያ ይሁን።9Id., p. 366.AHAmh 52.1