Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የአድቬንቲስት ቤት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ምዕራፍ ሰማንያ ሁለት—ክርስቲያን የአዕምሮ ማደሻዎቹን እንዴት ይመርጣል?

    የክርስቲያናዊ አዕምሮ ማደሻና የዓለማዊ ፈንጠዝያ ንጽጽር፡- በመታደስና በመፈንጠዝ መካከል ልዩነት አለ። መታደስ እንደ ስሙ በትክክል ሲተገበር - እንደገና መፈጠር ማለት ሲሆን የሚያጠነክርና የሚገነባ ነው። ከተለመደው ጭንቀታችንና መዋከባችን ገለል በማድረግ የአዕምሮና የአካል መታደስ በመለገስ ለከባዱ የሕይወት ተግባር በአዲስ ጉልበት እንድንመለስ ያስችለናል። በሌላ በኩል ፈንጠዝያ የሚፈለገው ለ[ጊዜያዊ] ደስታ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜም ከመጠን ባለፈ መልኩ ይተገበራል። ለጠቃሚ ሥራ የሚያስፈልገውን ጉልበት ያሟጥጣል፤ በመሆኑም ለሕይወት ትክክለኛ ስኬት መሰናክል መሆኑ በእርግጠኝነት ይታያል።1Education, p. 207.AHAmh 377.1

    ለክርስቲያናዊ መታደስ በሚሰበሰቡ የክርስቶስ ተከታዮችና ለደስታና ጨዋታ በሚደረጉ ዓለማዊ ስብሰባዎች ግልጽ ልዩነት አለ። በመፀለይ የክርስቶስን ስምና የተቀደሱ ነገሮችን በማንሣት ፈንታ ከዓለማውያን የሚሰማው የመጃጃል ሳቅና እርባናቢስ ጭውውት ነው። የሚያስቡት አስደሳች ጊዜን ማሳለፍ ነው። ፈንጠዝያቸው በጅልነት ተጀምሮ በከንቱነት ይደመደማል።2Review and Herald, May 25, 1886.AHAmh 377.2

    በሌሎች ነገሮቻችን ሁሉ ማድረግ እንዳለብን ሁሉ በምንዝናናበትም ጊዜ መሻትን መግዛት እጅግ አስፈላጊ ነው። የመዝናኛዎቹ ባህርይ በጥሞና ሊጤን ይገባዋል። እያንዳንዱ ወጣት እራሱን ይጠይቅ፤ እነኚህ ፈንጠዝያዎች በአካል በአዕምሮና በግብረ-ገብነት ሕልውና ላይ የሚያደርሱት ተጽዕኖ ምንድን ነው? አዕምሮዬ በስሜት ሰክሮ እግዚአብሔርን ይረሳል? በፊቴ ይሆን ዘንድ ያለው ክብሩ ከአሁን በኋላ ይቁም? ብሎ እያንዳንዱ ወጣት ይጠይቅ።3Counsels to Teachers, Parents, and Students, pp. 333, 334.AHAmh 377.3

    ሕገ-ወጥ ያልሆኑ መደሰቻዎች ሊለዩ የሚችሉበት አካሄድ፡- የሱስ የደስታ ሁሉ ምንጭ የመሆኑ እውነት ከእኛ ፈጽሞ ሊሠወር አይገባውም። በሰው ልጅ ስቃይ ሐሴት አያደርግም፤ ደስ ብሏቸው ሊያያቸው ይወዳል እንጂ። ክርስቲያኖች ብዙ የደስታ ምንጮች አሏቸው፤ የትኞቹ ሕጋዊና ትክክል እንደሆኑ እቅጩን መናገር ይችላሉ። አዕምሮአቸውን የማያራቁቱትን፣ ነፍስንም የማያረክሱትን መታደሻዎች ይደሰቱባቸዋል። ለራስ የሚገባውን ክብር በመደምሰስና ወደ ጠቃሚነት የሚወስደውን ጎዳና በመዝጋት ቅር የሚያሰኝና የሚያሳዝን ቅሪት ትተው አያልፉም። የሱስን ይዘውት ቢሄዱና በጸሎት መንፈስ ውስጥ ቢሆኑ አንድም አደጋ ፈጽሞ አይደርስባቸውም።4Review and Herald, August 19, 1884.AHAmh 377.4

    በእምነት የእግዚአብሔር በረከት እንዲጨመርበት ልትጠይቁበት የምትችሉበት [ፈንጠዝያ ብለን የጠራነው] መደሰቻ ሁሉ አደገኛ አይሆንም። ነገር ግን የድብቅ ጸሎት ታደርጉ ዘንድ የማያስችላችሁ፤ በፀሎት መሠውያ የመሰጠትን ዕድል የማይቸራችሁ፤ ወይም የፀሎት ስብስባን እንዳትካፈሉ የሚያደርጋችሁ ፈንጠዝያ መልካም አይደለም፤ አደገኛም ነው።5Counsels to Teachers, Parents, and Students, p. 337.AHAmh 377.5

    ለዕለት ተዕለት ኃላፊነቶቻችን እንዳንወጣ የሚያደርጉን ፈንጠዝያዎች፡- እግዚአብሔርን በምድር ከፍ ከፍ ያደርጉ ዘንድ በሚሰጧቸው እያንዳንዱ ቀናት ዕድለኞች እንደሆኑ ከሚያምኑት ወገን ነን፤ በዚህ ዓለም የምንኖረው ለራሳችን ጥቅምና ለራሳችን ደስታ አይደለም፤ እዚህ ያለነው ለሰው ዘር ጥቅም፣ ለህብረተሰብ በረከት ልንሆን ነው። በዚያ በተዋረደ መንገድ አዕምሮአችን እንዲጓዝ ከፈቀድንለት፣ ከንቱነትንና ሞኝነትን ያግበሰብስ ዘንድ አዕምሮአቸውን በሚሰጡ ሰዎች መንገድ ከተራመድን ለትውልዳችንና ለዘር-ሐረጋችን እንዴት ጥቅም ልንሆን አንችላለን? በዙሪያችን ላለው ማህበረሰብ እንዴት በረከት ልንሆን እንችላለን? የዕለት ተዕለት ኃላፊነቶቻችንን በታማኝነት እንፈጽም ዘንድ የማያስችሉንን ፈንጠዝያዎች እያወቅን ልንረካባቸው አይቻለንም።6Id., p. 336.AHAmh 378.1

    የነፍስ ደህንነት ራስ-ወዳድ ፍላጎትን ለማርካት ሲባል አደጋ ላይ መውደቅ የለበትም። አዕምሮአችንን ለአልባሌ ስሜት በማስገዛት የተለመዱት የኑሮ ኃላፊነቶች፣ ተራና ደስ የማያሰኙ እንዲመስሉ የሚያደርገውን አዕምሮአችንን የሚያቅበጠብጠውን የፈንጠዝያ አይነት ልንሸሽ ይገባናል። በእንደዚህ ዓይነቶቹ መደሰቻዎች መርካት አዕምሮ ለተሳሳተ መንገድ የተሰጠ እንዲሆን ያደርገዋል፤ ሰይጣንም አስተሳሰብን በማጣመም ስህተቱ ትክክል እንዲመስል ያደርጋል፤ ከዚያም ወጣቶች እንዳያደርጉት መከልከላቸውና ለወላጆቻቸው መገዛታቸው- ልክ ክርስቶስ ለወላጆቹ ያደረገው ዓይነት መታዘዝ- ሊሸከሙት የማይችሉት ቀንበር ይመስላቸዋል።7The Youth’s Instructor, July 27, 1893.AHAmh 378.2

    የተወገዙ ማህበራዊ ስብሰባዎች፡- በራሳቸው ትክክል የሆኑ ነገር ግን ሰይጣን ስለሚያጣምማቸው ላልጠረጠረው ወጥመድ የሚሆኑ ብዙ ነገሮች አሉ።8Letter 144, 1906.AHAmh 378.3

    የመደሰቻ ፓርቲዎች (ድግሶች) በተለምዶ ሲካሄዱ የአዕምሮ ወይም የባህርይ ዕድገት ማነቆ ናቸው። እርባና-ቢስ ጓደኝነቶች የማባከን ልምድ፣ የደስታ ጥማትና ከንቱነት ሕይወትን ሙሉ ለሙሉ ለጥፋት ያዘጋጁታል። በእነዚህ ዓይነት መዝናኛዎችፈንታ ወላጆችና መምህራን የተመጣጠኑና ሕይወት ሰጪ የሆኑ የጊዜ ማሳለፊያዎችን በመዘርጋት ብዙ ሥራ ሊያከናውኑ ይችላሉ።9Education, p. 211.AHAmh 378.4

    ለተቋሞቻችንና ለቤተ-ክርስቲያኒቱ አሳፋሪ የሆኑ የስሜት ማርኪያ ድግሶች ለማካሄድ የሚጠቀሙባቸው ማህበራዊ ስብሰባዎች አሉ። እነዚህ ስብሰባዎች የአለባበስ መኮፈስን፣ በዕይታ መምቦጥረርን፣ ራስን ማርካትን፣ በከንቱ ሳቅ መንከትከትንና ስንፍናን የሚያበረታቱ ናቸው። ሰይጣን እንደ የክብር እንግዳ በሐሴት ይስተናገዳል። እንደነዚህ ዓይነቶቹን ስብሰባዎች የሚያዘወትሩትን ሰዎች ዲያብሎስ በንብረትነት ይረከባቸዋል።AHAmh 378.5

    እውነትን እንደሚያምኑ የሚናገሩ ሆኖም እንደነዚህ ዓይነት ተግባር የሚያራምዱ ስብሰባዎች በፊቴ በራዕይ ቀርበውልኝ ነበር። አንደኛው ከሙዚቃ መሣሪያው አጠገብ ተቀምጦ ነበር። ዜማዎቹ ሲደመጡ መላእክት እያለቀሱ ይመለከቱ ነበር። ማሽካካትና የሚያንቧርቅ ሳቅ ነበር፤ የጋለ ስሜትና መነቃቃት በገፍ ነበር፤ ይህ ዓይነት ደስታ ግን ሰይጣን ብቻ ሊፈጥረው የሚችለው ነበር። ይህ የገነፈለ ስሜትና መነሁለል እግዚአብሔርን የሚወዱ ሁሉ የሚያፍሩበት ነው። ተሳታፊዎችንም ቅዱስ ላልሆነ ሐሳብና ድርጊት የሚያዘጋጃቸው ነው። እንደዚያ ዓይነቱ ትዕይንት ላይ የተሳተፉ አንዳንዶቹ በአሳፋሪ ድርጊታቸው ልባዊ ፀፀት እንዳደረጉ ለማመን በቂ ምክንያት አለኝ። AHAmh 379.1

    እንደዚህ ዓይነቶቹን ብዙ ስብሰባዎች እንዳይ ሆኛለሁ። ድምቀቱን፣ የአለባበስ ትዕይንቱንና መሽቀርቀሩን አይቻለሁ፤ ሁሉም ተሳታፊዎች ሊቆች እንደሆኑ ሌሎች እንዲያስቡ ይጥራሉ። በሳቅ በመንፈቅፈቅ እራሳቸውን ይረሳሉ፤ የጅል ቀልድ ይቀልዳሉ። ርካሽና የተጋነነ ሙገሳ ያሞግሳሉ። ሁካታ በሚፈጥር ሳቅ ያሽካካሉ። ዐይን ይቁለጨለጫል፤ ጉንጭ ደም ይመስላል፤ ንቃተ-ህሊና(አዕምሮ) ግን ይተኛል። በመብላት፣ በመጠጣትና በመደሰት እግዚአብሔርን ለመርሳት የተቻላቸውን ሁሉ ያደርጋሉ። የሚያዩት ደስታ ለእነርሱ ገነታቸው ነው። ሰማይ ግን ይመለከታል፤ ሁሉንም ነገር ይሰማል፤ ይታዘባልም።10Counsels to Teachers, Parents, and Students, pp. 339, 340.AHAmh 379.2

    ለመጫወት የሚደረጉ ስብሰባዎች እምነትን ግራ ያጋባሉ፤ የተደበላለቀና እርግጠኛ ያልሆነ ስሜትን ይፈጥራሉ። ጌታ የተከፋፈለ ልብ አይቀበልም፤ የሰውየውን ሁለመና ይፈልጋል።11Id., p. 345.AHAmh 379.3

    አደጋ የሌለባቸው ፈንጠዝያዎች የሉም ቢባል ይቀላል፡- አሁን በዓለም ተወዳጅ የሆኑት ፈንጠዝያዎች በክርስቲያኖች መካከል ጭምር ያሉት እንኳን መጨረሻቸው እምነት የሌላቸው እንደሚያደርጉት ነው። እንዲያውም ሰይጣን ነፍሳትን ለማጥፋት የማይጠቀምባቸው ፈንጠዝያዎች የሉም ቢባል ይሻላል። ድራማን በመጠቀም ፍላጎትን በማነሳሳት ዝሙት ክቡር ተግባር እንደሆነ ለማሳየት ለዘመናት ሠርቷል። በሙዚቃዊ ተውኔቱ መደነቅን በሚፈጥረው ትዕይንቱና በሚያሰክረው የዘፈን ጫጫታው እውነት በሚመስሉ ማታለያዎችና በካርታ ጨዋታ(game) ጠረጴዛዎቹ ሰይጣን የመርህን ግድግዳ በመስበር ለስሜት እርካታ በር እንዲከፈት ያደርጋል። ኩራት የሚፋፋምበትና ሆዳምነት የሚገንበት እግዚአብሔር የሚረሳበትና ዘለዓለማዊ ጥቅሞች ከዕይታ የሚሠውሩበት ይህ የፈንጠዝያ ስብሰባ ሰይጣን በነፍስ ዙሪያ ሰንሰለቱን የሚጠመጥምበት ሥፍራ ነው።12Patriarchs and Prophets, pp. 459, 460.AHAmh 379.4

    የእግዚአብሔር ባርኮት ሊጠየቅበት ወደማይችል ፈንጠዝያ ወይም ማንኛውም የጊዜ ማጥፊያ ቦታ እውነተኛ ክርስቲያን አይገባም። በቲያትር ቤት፣ በጠረጴዛ ቁማር አዳራሽ ወይም በቦውሊንግ ሳሎን አይገኝም። ከግብረ-ሰዶማዊያን የዋልትዝ (waltz) ተወዛዋዦች ጋር ወይም በማንኛውም የሚያነሆልል ደስታና ክርስቶስን ከአዕምሮ አሟጦ በሚያጠፋ ጨዋታ ላይ ክርስቲያኖች አይሳተፉም።AHAmh 379.5

    ለእንደነዚህ ዓይነቶቹ የጊዜ ማሳለፊያዎች ግብዣ ለሚጠይቁን ሁሉ የምንመልሰው የናዝሬቱ የሱስን ስም ጠርተን ልንሳተፍባቸው አንችልም በማለት ነው። በቲያትር ወይም በዳንስ ቤት ውስጥ እያለን በምናጠፋው ሰዓት መካከል የእግዚአብሔርን በረከት ልንጠይቅ አንችልም። ማንም ክርስቲያን ሞትን በእንደዚህ ዓይነት ቦታ ለመገናኘት አይመኝም፤ የሱስ ሲመጣ ማንም እዚያ ቦታ ሆኖ መገኘት አይፈልግም።13Review and Herald, Feb. 28, 1882.AHAmh 380.1

    ትያትር ቤት ምግባረ-ብልሹነትን ለማጎልበት ዓይነተኛ ቦታ ነው፡ - ከመደሰቻ ቦታዎች መካከል እጅግ አደገኛ ከሚባሉት አንዱ ቲያትር ቤት ነው። የግብረ-ገብነት ባህርይ ትምህርት ቤት በመሆን ሁሌም አስተማሪ ነው እንደሚባለው ሳይሆን ይልቅም የምግባረ-ቢስነት መፈልፈያ ነው። የረከሱ ልማዶችና የኃጢአት ዝንባሌዎች ተበረታትተው በእንደዚህ ዓይነቶቹ መደሰቻዎች ይጠናከራሉ። የረከሱ ዘፈኖች፤ ወሲብ ቀስቃሽ ውዝዋዜዎች፤ ንግግሮችና ባህርያት አስተሳሰብን ያራቁታሉ፤ ግብረ-ገብነትን ያላሽቃሉ። እንደነዚህ ዓይነቶችን ሥፍራዎች በተለምዶ የሚሄድባቸው እያንዳንዱ ወጣት የተበላሸ መርህ የሚቀረጽበት ይሆናል። አስተሳሰባችን በመመረዝ ኃይማኖታዊ ዕይታዎቻችን በማጥፋት ፀጥታ ለሰፈነባቸው መደሰቻዎችና ለተረጋጉት የኑሮ እውነታዎች ያለውን ፍቅር የዶለዶመ በማድረግ ረገድ እንደ ትያትር ያለ ክፉ ነገር የለም። የመጠጥ አጠቃቀም እየጨመረ ሲሄድ የአስካሪነቱ ፍላጎት እየተጠናከረ እንደሚሄድ ሁሉ የእነዚህም መዝናኛዎች ፍላጎት በእያንዳንዱ ትዕይንት ይጨምራል። አደጋ የሌለበት አካሄድ ማለት ትያትርን ሰርከስን ወይም ማንኛውንም ጥያቄ ውስጥ የሚገባ ፈንጠዝያን መተው ነው።14Counsels to Teachers, Parents, and Students, p. 334, 335.AHAmh 380.2

    ዳንስ - የነውረኛነት ትምህርት ቤት፡- በብዙ ኃይማኖተኛ ቤተሰቦች የካርታ ጨዋታና ዳንስ በማረፊያ ክፍል የሚደጋገሙ የጊዜ ማሳለፊያዎች ናቸው። እነዚህ በእርጋታና በጸጥታ ቤት ውስጥ የሚጫወቱት ጨዋታ በወላጆች ዕይታ ሥር ስለሆኑ መዝናኛው አደጋ የሌለው ነው ይባላል። ነግር ግን ለነዚህ የሚያፍነከንኩ መጫዎቻዎች ያለው ፍቅር ይጎለብትና በቤት ውስጥ መልካም ነው የተባለው በውጭም አደገኛነቱ ብዙም ሳይቆይ ይደበዝዛል። ከእንደዚህ ዓይነቶቹ መዝናኛዎች አንዳች መልካም ነገር ይገኝ አይገኝ ገና የሚረጋገጥ ነው። ለሰውነት ጥንካሬ ለአዕምሮም ዕረፍት አይሰጡም። የደግነትም ሆነ የቅድስና ስሜት በነፍስ ላይ አይተክሉም። በተቃራኒው ቁም-ነገር ላለው አስተሳሰብና ኃይማኖታዊ አገልግሎት ያለውን ፍላጎት ያጠፋሉ። የተሻሉ በተባሉ መደቦች በሚካሄዱ ፓርቲዎችና የተዋረዱና ዝሙታዊ የርኩሰት ዳንስ በሚካሄድባቸው ስብስቦች መካከል ትልቅ ልዩነት አለ። ሆኖም ሁሉም ወደማይረባ አቅጣጫ የሚያስገቡ እርምጃዎች ናቸው።15Review and Herald, Feb. 28, 1882.AHAmh 380.3

    የዳዊት ዳንስ እንደ ምክንያት ሲቀርብ፡- በእግዚአብሔር ፊት ዳዊት የደነሰው ክብር የተሞላበት የደስታ ዳንስ፣ ፋሽንን የሚከተልና ዘመናዊ ዳንስ ለመደነስ በሚፈልጉ የሐሴት አፍቃሪያን ዘንድ እንደ ምክንያት ይጠቀሳል። ለዚህ ክርክር ግን ምንም መሠረት የለም። የዚህ ዘመን ዳንስ ከመጃጃልና በውድቅት ከሚፈፀም ፈንጠዝያ ጋር የተያያዘ ነው። ጤናና ግብረ-ገብነት ለደስታ ሲባል ተሰውተዋል። ወደ ዳንስ አዳራሾች በተደጋጋሚ ለሚሄዱት ሁሉ እግዚአብሔር የሐሳባቸው ወይም የውዳሴአቸው አካል አይደለም። ፀሎት ወይም የምሥጋና መዝሙር ለቦታውና ለመስብሰባቸው የማይገጥም ይሆናል። ይህ ፈተና በቀላሉ መታየት የለበትም። ለተቀደሱ ነገሮች ያለንን ፍቅር የማዳከምና በእግዚአብሔር አገልግሎት የምናገኘውን ፍስሐ የመቀነስ ዝንባሌ ያላቸው ጊዜ ማሳለፊያዎች በክርስቲያኖች ሊፈለጉ አይገባም። ታቦቱ በተነሣ ጊዜ የነበረው ለእግዚአብሔር የደስታ ምሥጋና የቀረበበት ሙዚቃና ዳንስ ከአሁኑ የብኩንነት ዘመናዊ ዳንስ ጋር ቅንጣት ታክል ተመሣሳይነት የለውም። አንደኛው የእስራኤላውያን ውዝዋዜ እግዚአብሔርን በማስታወስ ቅዱስ ስሙን ከፍ ከፍ ያደረገ ነበር፤ ሌላኛው ሰዎች እግዚአብሔርን እንዲረሱና እንዲያዋርዱት የሚያደርግ የሰይጣን መሣርያ ነው።16Patriarchs and Prophets, p. 707.AHAmh 380.4