Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የአድቬንቲስት ቤት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ አሥራ ስድስት—ደስተኛና ውጤታማ ሽርክና

    እውነተኛ ጥምረት የዕድሜ ልክ ልምምድ ነው፦ የጋብቻን ግንኙነት ትክክለኛ ዕውቀት ማግኘት የዕድሜ-ልክ ሥራ ነው። ጋብቻ የሚፈጽሙ ሁሉ በዚህ ዓለም ሕይወታቸው ተምረው ወደማይመረቁበት ትምህርት ቤት ይገባሉ።1Testimonies for the Church, Vol. 7, p. 45.AHAmh 66.1

    ወደ ትዳር የተገባው ምኑንም ያህል ጥንቃቄና ጥበብ በተሞላበት ሁኔታ ቢሆንም እንኳ የጋብቻ ሥርዓቱ ሲፈፀም ሙሉ በሙሉ የተዋሐዱ ጥንዶች የሉም ማለት ይቀልላል። የጋብቻቸው ትክክለኛ ጥምረት እውን መሆን የወደፊት ዓመታት ሥራ ነው።2Ministry of Healing, pp. 359,360.AHAmh 66.2

    የሕይወት ግራ መጋባትና የጭንቀት ሸክም አዲስ ባለትዳሮችን ሲገጥማቸው ስለ ጋብቻ ያስቡት የነበረው ምናባዊ የፍቅር ታሪክ ይጠፋል። በጓደኝነታቸው ጊዜ ሊያውቋቸው ያልቻሏቸውን ባህርያት ባልና ሚስት አሁን መማር ይጀምራሉ። ይህ የልምምዳቸው አስፈላጊው ወቅት ነው። አሁን የሚጀምሩት ትክክለኛ አካሄድ የወደፊቱን ደስታቸውንና አስፈላጊነታቸውን ይወስናል። ሁልጊዜ ሁለቱም ያልጠረጠሩትን ድክመትና ያልጠበቁትን ግድፈት ያገኛሉ። ፍቅር ያጣመራቸው ልቦች ግን በፊት ያላወቋቸውን ግሩም ባህርያት ጭምር ወደ ማወቅ ይመጣሉ። ሁላችንም ጉድለትን ከመፈለግ ይልቅ መልካም የሆኑትን ባህርያት እናበረታታ። ብዙ ጊዜ የራሳችን አስተሳሰብና አመለካከት እንዲሁም በዙሪያችን የከበቡን ሁኔታዎች ስለሌላው ሰው ሊገለጥልን ካለው መልካም ነገር ይከልሉናል።3Id., p. 360.AHAmh 66.3

    ፍቅር ሊመረመርና ሊፈተሽ ይገባዋል፦ ፍቅር እንደ መስታወት ድንጋይ(crystal) ጥርት ያለ በንጽህናውም ውብ ሊሆን ይችላል፤ በአንጻሩ ደግሞ ሥር ያልሰደደና ጥልቀት የሌለው ሊሆንም ይችላል፤ ምክንያቱም በችግር አልተፈተነምና። ክርስቶስን በሁሉም ነገር የመጀመሪያ፣ የመጨረሻና ከሁሉም የሚበልጥ አድርጉት፤ ሁልጊዜ ጌታን ተመልከቱት፤ ፍቅራችሁ በተፈተነ ጊዜ ለእርሱ ያላችሁ ፍቅር በየቀኑ ጥልቅና ጠንካራ እየሆነ ይሄዳል። ለእርሱ ያላችሁ ፍቅርም እየጨመረ ሲሄድ ለእርስ በእርስ ያላችሁ ፍቅር እየጠለቀና እየጎለበተ ይሄዳል።4Testimonies for the Church, Vol. 7, p. 46AHAmh 66.4

    ችግር፣ ግራ መጋባትና ተስፋ መቁረጥ ቢኖርም ጥምረታቸው ስህተት ወይም ቅር የሚያሰኝ እንደሆነ የሚሰማቸውን ስሜት ባልም ሆነ ሚስት አጠገባቸው ሊያስደርሱት አይገባም። አንዳችሁ ለአንዳችሁ ልትሆኑላቸው የምትችሉትን ሁሉ ለመሆን ወስኑ። መጀመሪያ የነበራችሁን ትኩረት ቀጥሉበት፤ የሕይወትን የአድቬንቲስት ሰልፍ በጋራ በመዋጋት በሁሉም አቅጣጫ እርስ በእርሳችሁ ተበረታቱ። የእርስ በእርሳችሁን ደስታ እንዴት እንደምታስቀድሙ ጥናት አድርጉ፤ የጋራ ፍቅር፣ የጋራ መቻቻል ይኑር። እንዲህም ሲሆን ትዳር የፍቅር መጨረሻ መሆኑ ቀርቶ የፍቅራችሁ መጀመሪያ ይሆንላችኋል። የዕውነተኛ ጓደኝነት ሙቀትና ልብን ከልብ የሚያስተሳስረው ፍቅር በሰማይ የሚጠብቃችሁ ደስታ ቅምሻ ነው።5Ministry of Healing, p. 360.AHAmh 66.5

    ሁለቱም ትዕግስትን በመለማመድ መቻቻልን ያዳብሩ። ቸርና ታጋሽ በመሆን እውነተኛ ፍቅር በልብ ውስጥ ሁልጊዜ ትኩስ እንደሆነ እንዲቆይ ማድረግ ይቻላል። ሰማይ የሚያፀድቃቸውን ባህርያት ማዳበር ይቻላል።6Review and Herald, Feb. 2, 1886.AHAmh 67.1

    ጠላት ሊያለያያችሁ ይወዳል፦ የሚያቃቅር ነገር በሚገጥም ጊዜ ሰይጣን ይህንን ዕድል ለመጠቀም ምንጊዜም የተዘጋጀ ነው። ባል ወይም ሚስት በሚያሳዩት ከዘር የተላለፈ ደካማ ባህርያቸው ላይ በመሠልጠን በእግዚአብሔር ፊት በተቀደሰ ቃል-ኪዳን የተሳሰሩትን ሁሉ እንዲራራቁ ያደርጋል። በጋብቻ መሐላቸው አንድ ሊሆኑ ቃል ተጋብተዋል፤ ሚስት ባልዋን ልታፈቅረውና ልትታዘዘው ቃል ገብታለች፤ ባል ደግሞ ሚስቱን ሊያፈቅራትና ሊንከባከባት ቃል ገብቷል። የእግዚአብሔር ሕግ ከተከበረ የጥል መንፈስ ወደ ቤተሰቡ እንዳይገባ ይከለከላል። የፍላጎት ልዩነትም አይፈጠርም፤ ፍቅርም እንዲቀዘቅዝ አይሆንም።7Letter 18a, 1891.AHAmh 67.2

    ምክር ግትር ባህርይ ላላቸው ጥንዶች፦ ባልም ሆነ ሚስት የገዥነት ጥያቄ ማቅረብ የለባቸውም። በዚህ ጉዳይ ላይ እግዚአብሔር መመሪያ አስቀምጧል። ክርስቶስ ቤተ-ክርስቲያንን እንደሚንከባከብ ሁሉ ባል ሚስቱን ሊንከባከባት ይገባል። ሚስት በበኩልዋ ባልዋን ልታከብርና ልታፈቅረው ይገባታል። በፍጹም ቁርጠኝነት አንዳቸው ሌላኛውን ፈጽሞ ላለማሳዘንና ላለመጉዳት የሚችሉትን ሁሉ የደግነት መንፈስ ማጎልበት አለባቸው....AHAmh 67.3

    እንደራሳችሁ ፍላጎት ብቻ ሌላኛው እንዲያደርግ አታስገድዱ፤ ይህንን እያደረጋችሁ ለእርስ በእርስ ያላችሁን ፍቅር ልትጠብቁ አትችሉም። የራስን ፍላጎት ማንፀባረቅ የቤትን ሠላምና ደስታ የሚደመስስ ነው። የትዳር ሕይወታችሁ የዝብራት(የፉክክር) አይሁን። እንዲህ የምታደርጉ ከሆነ ሁለታችሁም የተከፋችሁ ትሆናላችሁ። የራሳችሁን ፍላጎት በመተው በንግግር ደግ፣ በተግባር ጨዋ ሁኑ። ስለምትናገሩት በጣም ተጠንቀቁ፤ ለመልካም ወይም ለክፋት ከባድ ተጽዕኖ ያደርጋልና። ድምፃችሁ የሚሰብቅ እንዲሆን አትፍቀዱ። ክርስቶስን የመምሰል መዓዛ ወደ ጥምር ሕይወታችሁ አምጡ።8Testimonies for the Church, Vol. 7, p. 47.AHAmh 67.4

    ፍቅርን መግለጽ እንደደካማነት የሚቆጥሩ ብዙዎች ናቸው፤ ሌሎችን ሊያስከፋ የሚችል የአትቅረቡኝ ዓይነት ባህርይ ያሳያሉ። ይህ የርኅራኄን ጅረት የሚያደርቅ ነው። የማህበራዊ ፍላጎቶቻችን ሲጨቆኑ እየመነመኑና እየጠወለጉ ይሄዱና ልባችንን ባይተዋርና የቀዘቀዘ ያደርጉታል። ከዚህ ስህተት እንጠንቀቅ። ፍቅር ካልተገለፀ ለረዥም ጊዜ አይቆይም። ከእናንተ ጋር የተጣመረው የሌላኛው ልብ ቸርነትንና ርኅራኄን እንዲራብ አታድርጉ....AHAmh 67.5

    እያንዳንዱ ሰው ፍቅርን በኃይል ለማግኘት ከመሞከር ይልቅ ፍቅርን ይስጥ፤ በውስጣችሁ ክቡር የሆነውን ባህርያችሁን አዳብሩ። እርስ በእርሳችሁ ላላችሁ መልካም ባህርያት እውቅና ለመስጠት አትዘግዩ። የማድነቅ ንቃተ-ሕሊና ግሩም መነቃቃትና እርካታ የሚፈጥር ነው። ርኅራኄና አክብሮት ወደ ላቀ ደረጃ ለመድረስ የሚደረገውን ጥረት ያበረታታሉ፤ ወደ ተሻለ ዓላማ እያነሣሱ ፍቅርም በዚያው መጠን ይጨምራል።9Ministry of Healing, pp. 360, 361.AHAmh 68.1

    በዓለማችን እጅግ ብዙ ወንዶችና ሴቶች ልበ-ደንዳና የሆኑበት ምክንያት እውነተኛ ፍቅር እንደ ደካማነት እየታየ ስለሚጣጣልና ስለሚገታ ነው። እንደዚህ ዓይነት ሰዎች መልካሙ ተፈጥሮአቸው በልጅነታቸው ተጣሞና ቆርቁዞ ያደጉ ናቸው። ቀዝቃዛነታቸውን ልበ-ደንዳና የሆነ ራስ-ወዳድነታቸውን የመለኮታዊ የብርሃን ጮራ አቅልጦ ካላጠፋው በስተቀር ደስታቸው ለዘለዓለም የተቀበረ ነው። ክርስቶስ በዚህ ምድር እንደነበረው ዓይነት የለዘበ ልብና መላእክት ሟች ለሆነው ኃጢያተኛ የሚያሳዩት የተቀደሰ ርኅራኄ እንዲኖረን ከፈለግን የልጅነታችን መልካም ባህርያት የሆኑትን የዋህነትንና ቀናነትን እናጎልብት። እንዲህ ሲሆን ነጽተንና ከፍ ከፍ ብለን በሰማያዊ መመሪያወች እንተዳደራለን።10Testimonies for the Church, Vol. 3, p. 539.AHAmh 68.2

    እጅግ ብዙ ጭንቀቶችና ሸክሞች ወደ ቤተሰቡ እንዲገቡ ይፈቀድላቸዋል፤ ተፈጥሮአዊ ቀናነት፣ ሠላምና ደስታ ግን አይበረታቱም። የውጪው ዓለም ምን ይል ይሆን ብሎ ከመጨነቅ ይልቅ የላቀ አሳቢነት የተሞላበት ትኩረት በቤተሰብ አባላት ዙሪያ መጠንከር አለበት። የዓለማዊ ትዕይንትና ደግነትን ቀንሶ የበለጠ ገራምነትና ፍቅር፣ ደስታና ክርስቲያናዊ ይሉኝታ በቤተሰቡ መካከል ይብዛ። ብዙዎች ቤትን እንዴት ማራኪና የደስታ ቦታ እንደሚያደርጉት መማር የሚያስፈልጋቸው ናቸው። አመሥጋኝ ልቦችና ቸርነት የተላበሱ ገጽታወች ከሀብትና ከድሎት የበለጠ ዋጋ አላቸው፤ ባሉንና ተራ በሆኑ ነገሮች የምንረካ ከሆነ ፍቅር እስካለ ድረስ ቤታችንን ደስተኛ ያደርጉታል።11Id., Vol. 4, pp. 621, 622.AHAmh 68.3

    ለጥቃቅን ነገሮች ትኩረት መስጠት በጣም አስፈላጊ ነው፦ እግዚአብሔር የሚፈትነንና ሆነን መገኘታችንን የሚያረጋግጠው በሕይወታችን ሁልጊዜ በሚያጋጥሙን ቀላልና ጥቃቅን ነገሮች ላይ ነው። ጥቃቅን ነገሮች ናቸው የልብን ምዕራፍ የሚገልጡት። ለትንንሽ ነገሮች የምንሰጠው ትኩረትና የምንለግሰው ትህትና ተጠራቅመው ሕይወትን በደስታ ይሞላሉ። ለትንንሽ ነገሮች ጭምር ትህትና አለማሳየት፣ የፍቅር ንግግርን አለማበረታታትና ደግነትን ቸል ማለት ደግሞ የሕይወትን መንኮታኮት የሚያቀናብር ነው። በሰማይ ባለው የሕይወት መጽሐፍ ውስጥ ብዙውን ቦታ ይዞ የሚገኘው በዙሪያችን ላሉ ሰዎች ደስታና ጥቅም ስንል እራሳችንን ክደን የምናገለግልበት መዝገብ እንደሆነ በመጨረሻ የሚታይ ይሆናል። ለሌሎች ደስታና ጥቅም ግድ ሳይኖረን ለራሳችን ብቻ የምንሮጥ ከሆነም ይህ ሐቅ ከሰማያዊ አባታችን የተደበቀ እንዳልሆነ በመጨረሻ የሚገለጥ ይሆናል።12Id., Vol. 2, pp. 133, 134.AHAmh 68.4

    ፍቅርን መግለጽ ያቃተው ባል፦ ፍቅር የሞላበትን ቤት - ፍቅር በቃልና በፊት ገጽታ እንዲሁም በተግባር የሚገለጽበትን ቤት - መላእክት በቦታው መገኘታቸውን ማሳወቅ የሚጓጉበትና ከክብሩ በሚመጣው የብርሃን ጮራ ቤተሰቡን የሚቀድሱበት ሥፍራ ነው። በዚህ ቦታ ተራ የሚባሉ የቤተሰብ ኃላፊነቶች እንኳ ውበት የተላበሱ ናቸው። በዚህ ሁኔታ ማናቸውም የኑሮ ኃላፊነቶች ለሚስትህ አሰልቺ አይሆኑም። ደስታ በሞላበት መንፈስ ታከናውናቸዋለች፤ በዙሪያዋ ላሉት ሁሉ እንደ ፀሐይ ጨረር ትሆናለች፤ በልብዋም ለእግዚአብሔር ጥዑመ-ዜማ ታቀርባለች። ሆኖም አሁን ከልቡ ያፈቅረኛል የሚል ሐሳብ የላትም፤ እንደዚህ እንድታስብ ዕድል የከፈትከው አንተ ነህ። እንደ ቤተሰብ እራስነትህ የተጣሉብህን አስፈላጊ ግዴታዎች ሁሉ በብቃት እየተወጣህ ነው፤ ሆኖም ጉድለት አለህ፤ ቸር ወደ ሆነው፣ ለእርስዋ ሊኖርህ ወደሚገባው ትኩረት የሚመራው የፍቅር ግሩም ተጽዕኖ በአስጊ ሁኔታ ይጎድልሃል። የፍቅር ፊቱም ፍትፍቱም፣ ድምጹና ቃናውም ጭምር መታየት አለበት።13Id., pp. 417, 418.AHAmh 69.1

    ቅር የምታሰኝ፣ ራስ-ወዳድ ሚስት፦ የሚጋቡ ሰዎች በመጣመራቸው ምክንያት ግብረ-ገብነታቸው ይሻሻላል ወይም ይቀንሳል። የዝቅጠት ሥራ በርካሽ፣ በአሳሳች በራስ-ወዳድና ከቁጥጥር ወጭ በሆነ ተፈጥሮ እየታገዘ የጋብቻው ሥነሥርዓት እንዳለቀ ይጀምራል። ወጣቱ ብልህ ምርጫ አድርጎ ከሆነ ከጎኑ በመቆም በምትችለው ሁሉ የፈንታዋን የሕይወት ሸክም የምትሸከም፣ የምታስከብረውና የምታነጥረው፣ ከግድፈት የምታጠራውና የምትሞርደው በፍቅርዋም ደስ የምታሰኘው ሚስት ትሆንለታለች። ባህርይዋ የሚለዋወጥ፣ ራስዋን አሞካሽ፣ በቃኝ የማትል፣ ኮናኝ፣ ከራስዋ የተበላሸ ወፈፍተኛነት በመነጨ ስሜትና ተነሳሽነት ባልዋን የምትወነጅል ከሆነች፤ የባልዋን ፍቅር ለይታ ለማየትና ለማድነቅ የሚያስችል እውቀት ከሌላት፤ እያንዳንዱን አምሮትዋን በነቂስ ማሟላት ሳይችል ሲቀር ቸል እንዳላትና ለእርስዋ ፍቅር እንደሌለው የምታወራ ሴት፤ እንደዚህ ተጎዳሁ ብላ የምታለቃቅስባቸው ሁኔታዎችና የምታማርርባቸው ነገሮች ጠባይዋን ካላስተካከለች በስተቀር በእርግጥ በሕይወትዋ እውን ከመሆን አይዘሉም። እነዚህ ውንጀላዎችዋ በሙሉ የትዳራቸው የዘወትር ነባራዊ ክስተቶች ይሆናሉ።14Letter 10, 1889AHAmh 69.2

    ጥሩ ጓደኛ የምትሆን ሚስትና እናት መለያ ባህርያት፦ በቤተሰብ ኃላፊነት ባርያ ከመሆን ይልቅ ሚስትና እናት ለማንበብ፣ ጠለቅ ያለ ግንዛቤ ለመውሰድ፣ ለባልዋ ጓደኛ ለመሆንና የሚሰፋውን የልጆችዋን አዕምሮ ለመከታተል ጊዜ መውሰድ አለባት። ውድ ልጆችዋን ከፍ ወዳለው ሕይወት ለመምራት የምትችልበት ዕድልዋ አሁን ነውና ተጽዕኖዋን በብልሃት ትጠቀምበት። ውድ አዳኝዋን የዘወትር ጓደኛዋ ለማድረግና ቃሉን ለማጥናት ጊዜ ትውሰድ፤ ከልጆችዋ ጋር ወደ መስክ በመውጣት ውብ ከሆነው የእጅ ሥራዎቹ ለመማር ጊዜ ይኑራት። AHAmh 70.1

    ፍልቅልቅና ደስተኛ ትሁን። ማለቂያ በሌለው ስፌት (የጓዳ ሥራ) ሰዓትዋን ከምትጨርስ ከቀኑ ድካም የሚያሳርፍ ይሆን ዘንድ ምሽቱን የሚያስደስት የቤተሰብ የአንድነት ጊዜ ታድርገው። ይህም ሲሆን ብዙ ወንዶች ጊዜያቸውን በመሸታ ቤት ከማጥፋት ይልቅ ቤታቸው ውስጥ ከቤተሰባቸው ጋር መሆንን ይመርጣሉ። ብዙ ወንዶች ልጆች በአካባቢው የምግብ መደብር ወይም መንገድ ላይ ከመጎለት ይቆጠባሉ፤ ብዙ ሴቶች ልጆች ከከንቱ፣ ከርካሽና አታላይ ግንኙነቶች ይተርፋሉ። የቤት ውስጥ ተጽዕኖ ለወላጆችና ለልጆች እግዚአብሔር እንዳቀደው የዕድሜ-ልክ በረከት ይሆንላቸዋል።15Ministry of Healing, p. 294.AHAmh 70.2

    የጋብቻ ሕይወት ፍቅር ብቻ አይደለም፤ ያፈጠጡ ችግሮችና የቤት ጣጣዎችም አሉበት። ሚስት ራስዋን አሻንጉሊት አድርጋ በመቁጠር እንክብካቤ ብቻ የምትፈልግ ሳትሆን፤ ትክሻዋን በምናብ ጭነት ሳይሆን በትክክል የሕይወት ሸክም ሥር በማድረግ ከራስዋ ውጪ ሌሎች ሊታሰብባቸው የሚገቡ ነገሮች እንዳሉ በመረዳት ብልህና አስተዋይ ሕይወት መምራት ይኖርባታል....AHAmh 70.3

    የገሃዱ ሕይወት የራሱ ጽልመትና ሐዘን ያለው ነው። እያንዳንዱን ነፍስ ችግር ይገጥመው ዘንድ ግድ ነው። ሰይጣን የእያንዳንዳችሁን ብርታትና ተስፋ ሊያጠፋ፣ እምነታችሁን ሊሸረሽር፣ ልባችሁን ሊያሸብር ሳያሰልስ እየሠራ ነው።16Letter 34, 1890.AHAmh 70.4

    ምክር ደስታ ለሌላቸው ጥንዶች፦ የትዳር ሕይወታችሁ ምድረ-በዳ ይመስላል፤ በመልካም ልታስታውሷቸው የምትችሏቸው አረንጓዴ ነጠብጣቦች በመንገዳችሁ እምብዛም አይታዩም። እንደዚህ መሆን አልነበረበትም። እሳት ያለ ነዳጅ መቀጣጠልና መንደድ እንደማይችል ሁሉ፣ ፍቅርም በሚታይ አድራጎት ራሱን ካልገለጸ ሊኖር አይችልም። አንተ ወንድም ሲ(C) በለሰለሰ አነጋገርና ቅን መንፈስ በተላበሰ አክብሮት፣ ለሚስትህ ፍቅርህን ለመግለጽ አጋጣሚዎችን ሁሉ በመጠቀም ርኅራኄና መልካም አድራጎት ማሳየት ክብርህን የሚነካ ተግባር ሆኖ አግኝተኸዋል። ጠባይህ የሚቀያየርና በዙሪያህ በሚፈጠሩ ክስተቶች ምክንያት የሚቃወስ ነው....AHAmh 70.5

    የሥራህን ጭንቀት፣ ድንግርግርና ብስጭት እዚያው በሥራ ቦታህ ተወው። በርኅራኄ በለዘብታና በፍቅር ሆነህ ደስተኛ ፊት ይዘህ ወደ ቤተሰብህ ና። ይህ ለሚስትህ መድኃኒት ለመግዛት ወይም የጤና ባለሞያዎችን እንድታማክር ከምታወጣው ገንዘብ የተሻለ ሥራ ይሠራል። ለአካል ጤንነትና ለነፍስ ብርታት ይሆናል። ሕይወታችሁ በጣም የፈራረሰ ሆኗል። እንዲህ እንዲሆን ሁለታችሁም የየበኩላችሁን ሚና ተጫውታችኋል። እግዚአብሔር በስቃያችሁ ደስ አይለውም። እራሳችሁን መቆጣጠር ስላልቻላችሁ ይህንን ፍዳ በራሳችሁ ላይ አምጥታችኋል። AHAmh 71.1

    ፍላጎቶቻችሁ መረን እንዲለቀቁ ፈቀዳችሁላቸው። ወንድም ሲ በፍቅርና በቸርነት መናገርና ፍቅርህን መግለጽ ክብርህን የሚያጎድል ሆኖ አገኘኸው። እነዚህ የለዘቡ ቃላት ሁሉ የወኔ-ቢስነትና የደካማነት መልክ የሚታይባቸው አላስፈላጊ የሆኑ ድርጊቶች መስለውሃል። የእነርሱን ቦታ የሚተኩት ግን ጭንቀትና የብጥብጥ ቃላት፣ ጥልና ነቀፌታ ናቸው....AHAmh 71.2

    እርካታ ያገኘ የመንፈስ ገጽታ አይታይብህም፤ በችግሮችህ ውስጥ ነው የምትኖረው፤ ሐሳብ የወለደው እጦትና ድህነት ፊትህ ላይ አፍጥጦብሃል። የተጎዳህ፣ የተጨነቅህና የተሰቃየህ ሆኖ ይሰማሃል፤ ጭንቅላትህ እየተቃጠለ ያለ ይመስልሃል፤ መንፈስህ አዝኗል። ቸሩ ሰማያዊ አባትህ ለሰጠህ በረከት ልባዊ ምሥጋና አላቀረብህም፤ ለእግዚአብሔር ላለህ ፍቅር ዋጋ አልሰጠኸውም። የሕይወት ጉስቁልናው ብቻ ነው የሚታይህ። ዓለማዊ እብደት ልክ እንደ ጥቁር ከባድ ደመና ጭንቅላትህን ዘግቶታል። ሠላምና ደስታ በእጅህ ሥር ሊታዘዙልህ ሲችሉ የምትሰቃይ ሆነሃልና ሰይጣን ይፈነድቃል።17Testimonies for the Church, Vol. 1, pp. 695-697.AHAmh 71.3

    የጋራ ፍቅርና መቻቻል ሽልማት አላቸው፦ ያለ የጋራ ፍቅርና ትዕግሥት የትኛውም ምድራዊ ኃይል አንቺንና ባለቤትሽን በክርስቲያናዊ ህብረት ሊያቆያችሁ አይችልም። ጓደኝነታችሁ የለመለመና የጠበቀ፣ ቅዱስና ከፍ ከፍ ያለ የእግዚአብሔር ቃል እንደሚጠይቀው ለእርስ በእርሳችሁ ሁሉንም ነገር ትሆኑ ዘንድ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል በሕይወታችሁ የሚተነፈስ ይሁን። ጌታ የሚፈልግባችሁን ደረጃ ስትደርሱ ሰማይን በምድር እግዚአብሔርን ደግሞ በሕይወታችሁ ታገኟቸዋላችሁ።18Letter 18a, 1891.AHAmh 71.4

    ውድ እህቴና ወንድሜ ሆይ፣ አስታውሱ እግዚአብሔር ፍቅር ነው፤ አንዳችሁ ለሌላችሁ ደስታ ትሆኑ ዘንድ ስትጋቡ ለመፈጸም ቃል እንደገባችሁት ታደርጉ ዘንድ ፀጋው ያስችላችኋል። ክርስቶስን ረዳታቸው አድርገው የሚቀበሉ ወንዶችና ሴቶች እግዚአብሔር ለእነርሱ ወደ አቀደው ደረጃ መድረስ ይችላሉ። እራሳቸውን በእምነትና በፍቅር ለእርሱ አሳልፈው ለሚሰጡ፣ የሰው ጥበብ የማይችለውን ፀጋ ያከናውንላቸዋል። የእርሱ መለኮታዊ ምሪት የሰማይ መሠረት ባለው ጥምረት ልባቸውን ያስተሳስረዋል። ፍቅር የሚያባብል የቃላት ድርደራና የሽርደዳ ንግግር ልውውጥ አይሆንም። የሰማይ የሸማ-እቃ የሚሸምነው ድርና ማግ፣ ቀጭን ግን ጠንካራ ሲሆን በምድር ከሚሠሩት ሁሉ እጅግ የላቀ ነው። ውጤቱም ብጭቅ ብጭቅ የሚል ጨርቅ ሳይሆን ደንደን ያለ ሲለበስ እንግልት የሚችልና የማያልቅ ነው። ልብ ከልብ በማይቆረጥ ወርቃማ የፍቅር ሰንሰለት ይተሳሰራል።20Ministry of Healing, p. 362.AHAmh 71.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents