Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የአድቬንቲስት ቤት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ምዕራፍ ሃምሳ—ስምንት የአገልጋይ ቤተሰብ

    የአገልጋዩ የቤት ሕይወት የመልእክቱ ተምሣሌት ይሁን፦ የመጽሐፍ ቅዱስ መምህሩ በትዳር ሕይወቱ የሚያስተምራቸው እውነታዎች ተምሣሌት እንዲሆን የእግዚአብሔር ዓላማ ነው። በተግባር የሚገለጸው የሰው ማንነቱ እርሱ ከሚናገረው የተሻለ ተጽዕኖ አለው። የዕለት ተዕለት የኑሮ ቅድስና የህዝባዊ ምስክርነት ኃይል ሰጪ ነው። ስብከቶች ሊደርሷቸው ያልቻሉትን ልቦች ትዕግሥት የማይለዋወጥ ማንነትና ፍቅር ይነኳቸዋል። 1Gospel Workers, p. 204AHAmh 255.1

    የአገልጋዩ ልጆች ሥልጠና በሥነ-ሥርዓት ከተተገበረ፣ በመድረክ ላይ ቆሞ የሚሰጠውን ትምህርት በተግባር የሚያሳይ ይሆናል። የተሳሳተ ትምህርት ልጆቹን የሚያስተምር ከሆነ ግን አገልጋዩ ለማስተዳደርና ለመቆጣጠር ያለውን የችሎታ ማነስ ያሳያል። የእግዚአብሔር መንጋ እረኛ በመሆን ኃላፊነቱን ከመወጣቱ በፊት፣ ልጆቹን ሥነ-ሥርዓት ማስያዝ ጌታ የሚፈልግበት መሆኑንም ሊማር ይገባዋል። 2Letter 1, 1877.AHAmh 255.2

    ተቀዳሚ ኃላፊነቱ ለልጆቹ ነው፡- የአገልጋዩ ኃላፊነቶች ከቅርብም ሆነ ከሩቅ ሊኖሩ ይችላሉ፤ የመጀመሪያ ግዴታዎቹ ግን ልጆቹ ናቸው። በውጪ ሥራ እጁ ተጠምዶ ልጆቹ የሚያስፈልጋቸውን ትምህርት ቸል ማለት አይገባውም። በቤት ሕይወት ውስጥ ያሉበትን ኃላፊነቶች አስፈላጊነት ዝቅ አድርጎ ሊመለከታቸው ይችል ይሆናል፤ እውነታው ግን እነዚህ ኃላፊነቶች በግለሰብና በማህበረሰብ የደህንነት መሠረት ላይ የተቀመጡ ናቸው። የሴቶችና የወንዶች ደስታ እንዲሁም የቤተ-ክርስቲያን ውጤታማነት በስፋት የሚወሰነው ቤት ውስጥ ባለው ተጽዕኖ ነው….AHAmh 255.3

    አገልጋዩ፣ ውስጠኛውን ክበብ ለሰፊውና ውጫዊዉ ክበብ ሲል ቸል የሚልበት ምንም ምክንያት የለውም። የቤተሰቡ መንፈሳዊ ደህንነት ተቀዳሚ ነው። በመጨረሻው የፍርድ ስሌት ቀን ኃላፊነቱን ወስዶ ወደ ዓለም ያመጣቸውን እነርሱን የክርስቶስ ይሆኑ ዘንድ ምን እንዳደረገ እግዚአብሔር ይጠይቀዋል። ለሌሎች ያደረገው ታላቅ መልካምነት የራሱን ልጆች ይንከባከብ ዘንድ ከእግዚአብሔር የወሰደውን ዕዳ አይከፍልለትም። 3Gospel Workers, p. 204.AHAmh 255.4

    የአገልጋዩ ተጽዕኖ ወሰን ስፋት፦ በዓለም ፈጽሞ ቸል የተባሉት የአገልጋዮች ልጆች የሚሆኑበት አንዳንድ ሁኔታዎች አሉ። ምክንያቱ ደግሞ አባት ለእነርሱ ጊዜ የሌለው መሆኑ ነው። የሚሠሩትንና የሚጫወቱበትን ነገር እንኳ ያለ ዕድሜያቸው እራሳቸው እንዲመርጡ ይገደዳሉ። 4 Id., p. 206.AHAmh 255.5

    ወላጃዊ እምነተ-ቢስነቶች በማንኛውም ሁኔታ ታላቅ ጥፋቶች እንደሆኑ ሁሉ፣ እነዚህ ጥፋቶች ሕዝቡን እንዲያስተምሩ በተወከሉት ቤተሰቦች ሲታዩ ደግሞ ኃጢአቱ አሥር ዕጥፍ ይሆናል። እነዚህ ሰዎች የራሳቸውን ቤተሰብ መቆጣጠር ሲሳናቸው በጥፋት ምሣሌነታቸው ብዙዎችን ወደ ስህተት የሚመሩ ናቸው። የኃላፊነታቸው ደረጃ ከፍተኛ እንደሆነ ሁሉ ጥፋታቸውም ከሌሎች ይልቅ መጠነ-ሰፊ ነው። 5Patriarchs and Prophets, p. 579.AHAmh 256.1

    ሚስቱና ልጆቹ ስለእርሱ መንፈሳዊነት ከሌሎች የተሻሉ ፈራጆች(መስካሪዎች) ናቸው፦ የባህርያችንን ትክክለኛ መልክ ከሚገልጠው ከቤተሰባዊ ኃይማኖት ጋር ሲነፃጸር መድረክ ላይ የምናሳየው አምልኮ ጠቀሜታው ብዙም አይደለም። የአገልጋዩ ሚስት ልጆቹ እንዲሁም በረዳትነት በቤት የተቀጠሩት ከሁሉም በተሻለ ስለቅድስናው መፍረድና አስተያየት መስጠት ይችላሉ። መልካም ሰው ለቤተሰቡ በረከት ነው። እምነቱን ተግባራዊ እንዲያደርግ ሚስቱ፣ ልጆቹና ሌሎች ረዳቶቹ የተሻለ የሚጠቅሙት ይሆናሉ።AHAmh 256.2

    ወንድሞች ሆይ ወደ ቤተሰባችሁ የሱስን ይዛችሁት ሂዱ፤ ወደ መድረክ ውሰዱት፤ የትም ስትሄዱ ተሸክማችሁት ሂዱ። እንዲህም ስታደርጉ ሌሎቹ አገልግሎታቸው ዋጋ ያለው እንደሆነ እንዲያውቁ መገፋፋት አያስፈልጋችሁም። ምክንያቱም የክርስቶስ አገልጋዮች እንደሆናችሁ የሚያረጋግጥ ሰማያዊ መረጃ ስለምትይዙ ነው። 6Testimonies for the Church, Vol. 5, p. 161.AHAmh 256.3

    የአገልጋዩ ባለቤት ረዳት ነች ወይስ እንቅፋት?፦ አንድ ሰው አገልጋይ ለመሆን ኃላፊነቱን በእሽታ ሲቀበል የእግዚአብሔር ቃል-አቀባይ፤ ከእግዚአብሔር አፍ ቃሉን ወስዶ ለሕዝቡ የሚሰጥ እንደሆነ ያረጋግጣል። ታዲያ ወደ ታላቁ እረኛ ጉያ ምን ያህል መጠጋት ይኖርበታል? ክርስቶስን ከፍ ከፍ በማድረግ እራሱን ከእይታ ውጪ፣ ዝቅም አደርጎ እንዴት በእግዚአብሔር ፊት መራመድ አለበት! ልጆቹ በሙሉ ኃይላቸው ሊታዘዙ የሚስቱ ባህርይ የመጽሐፍ ቅዱሱን ምሣሌነት ሊከተል እንዴት አስፈላጊ ነው!AHAmh 256.4

    የወንጌላዊው ባለቤት ወደር የሌላት ውጤታማ ረዳትና በረከት፣ ወይም ደግሞ ለሥራው እንቅፋት ልትሆን ትችላለች። የአገልጋዩ የጠቃሚነት ወሰን የዕለት ተዕለት እድገቱ ወይም ተራ ወደ ሆነ ደረጃ መስመጡ በአብዛኛው በሚስቱ የሚወሰን ይሆናል። 7Letter 1, 1877.AHAmh 256.5

    የአገልጋዮች ሚስቶች ባሎቻቸውን ሊረዷቸውና በሚፈጥሩት ተጽዕኖ ትክክል ብሎም ጥንቁቅ መሆን ይገባቸዋል። በሰዎች እይታ ውስጥ ናቸው፤ ከሌሎች የተሻለ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ቀሚሳቸው ምሣሌ ይሁን፤ የኑሮአቸውና የንግግራቸው ምሣሌ የሕይወት መልክ ያለው እንጂ የሞት ገጽታ የያዘ አይሁን። ትሁትና የዋህ ነገር ግን ከፍ ከፍ ያለ አቋም መያዝ እንዳለባቸው በነገሮች ላይ የሚያደርጉት ውይይት አዕምሮን ወደ ሰማይ የማይመራውን ዓይነት መሆን እንደሌለበት አይቻለሁ። መጠየቅ ያለበት ታላቁ ጥያቄ፡- “የራሴን ሕይወት አትርፌ ለሌሎች ነፍሳት ደግሞ የመዳን ምክንያት እንዴት እሆናለሁ?” የሚለው ነው። በግማሽ ልብ የሚሠራ ምንም ዓይነት ሥራ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት እንደሌለው አይቻለሁ። እርሱ የሚፈልገው ሙሉ ልብና ፍላጎትን፣ ይህ ካልሆነ ደግሞ ምንም ነው። በማያወላውልና በማያሳስት ሁኔታ ተጽዕኗቸው እውነትን በመደገፍ ወይም በመቃወም ይናገራል። ከየሱስ ጋር ይሰበስባሉ፤ ወይም ወደ ውጪ ይበትናሉ። ያልተቀደሰች ሚስት ማለት አንድ አገልጋይ በሕይወቱ ሊያጋጥመው ከሚችለው ፈተና ሁሉ በላይ አቻ የሌለውና እጅግ ከባዱ መርገም ነው። 8Testimonies for the Church, Vol. 1, p. 139.AHAmh 256.6

    እግዚአብሔር እውነትን እንዲሰብኩ የመረጣቸውን አገልጋዮች ሰይጣን ተስፋ ሊያስቆርጥና ወደ ተሳሳተ መንገድ ሊመራቸው ምን ጊዜም በሥራ ላይ ነው። [ሰይጣን] ሊጠቀምባቸው የሚችሉ እጅግ ውጤታማ የሆኑ መንገዶች የቤት ውስጥ ተጽዕኖዎችናያልተቀደሱ የትዳር አጋሮች ናቸው። የሚስቶቻቸውን አዕምሮ መቆጣጠር ከቻለ በእነርሱ አማካይነት ለቃሉና ለአስተምህሮው የሚለፋውን ባል በቀላሉ ማግኘት ይችላል….በራስ-ወዳድነትና የነገሮች አልጋ በአልጋ መሆንን በሚወዱ አጋሮቻቸው አማካይነት የአገልጋዮቹን ሥራ የሚቆጣጠረው ሰይጣን ነው። 9Id., pp. 149, 451.AHAmh 257.1

    ስለ ቤተሰብ አስተዳደር ለአገልጋዮች የተሰጠ ምክር፦ ለእግዚአብሔርና እርሱ ለሰጣችሁ አደራ ታማኝ መሆናችሁ እንደ ተጠበቀ ሆኖ ልታመልጡት የማትችሉት የቤት ኃላፊነት አለባችሁ…. የወንጌሉ መስክ ዓለም ነው። በሰላውን በወንጌል እውነት ልትዘሩት እግዚአብሔርም ውኃ እንዲያጠጣውና ፍሬ እንዲያፈራ ትመኛላችሁ። የምትንከባከቡት ለራሳችሁ ቁራጭ መሬት ወስዳችኋል፤ የሌሎችን የአትክልት ሥፍራ አረም ስትነቅሉ የራሳችሁ ታዛ እሾህና ቁጥቋጦ ውጦታል። ይህ ቀላል የሚባል ሥራ አይደለም፤ ግሩም እድል እንጂ። ወንጌሉን ለሌሎች እየሰበካችሁ ነው፤ እራሳችሁ በቤታችሁ ተግብሩት። 10Testimonies for the Church, Vol. 4, p. 381.AHAmh 257.2

    ልጆቻችሁን በተገቢው ሥነ-ሥርዓት የመቅረጽ ሥራ ላይ መተባበር እስክትችሉ ድረስ እናት ያልተቀጣ ልጅዋን ይዛ ባል ከሚሠራበት አካባቢ ገለል ትበል፤ ምክንያቱም ልቅና የተሞላቀቀ ሥነ-ምግባር ለእግዚአብሔር ቤተ-ክርስቲያን እንደ ምሣሌነት መቅረብ ስለሌለበት ነው።AHAmh 257.3

    ያልተገራ ልጃቸውን ይዘው የሚዞሩ ብዙ አገልጋዮችን አውቃለሁ። መድረክ ላይ የሚያደርጉት ጥረት መልካም ያልሆነ ጠባይ በሚያንፀባርቁት ልጆቻቸው ምክንያት መና ይሆናል። 11Letter 1, 1877.AHAmh 258.1

    የሌሎች ሰዎች ልጆች ጉዳይ ይመልከታችሁ፦ ትኩረታችሁ በሙሉ በራሳችሁ ቤተሰብ ተውጦ ለሌሎች የማትተርፉ አትሁኑ። ከባልንጀሮቻችሁ ለተደረገላችሁ በጎነት አጽፋውን ትመልሱ ዘንድ ሊጠብቁባችሁ ይችላሉ። ከእነዚህ ሰዎችና ልጆቻቸው የኑሮ ደረጃ ጋር እራሳችሁን በማመሳሰል ለማስተማርና ለመባረክ ጣሩ። እራሳችሁን ለእግዚአብሔር ሥራ ቀድሳችሁ ልጆቻቸውን በምንም ዓይነት ሁኔታ ትኩረት ሳትነፍጓቸው ከወላጆቻቸው ጋር በመወያየት ለሚያስተናግዷችሁ ሁሉ በረከት ሁኑ። የራሳችሁ ትንሽ ፍጡር በእግዚአብሔር እይታ ከሌሎች ልጆች ይልቅ የበለጠ ዋጋ ያለው ሆኖ እንዳይሰማችሁ። 12Testimonies for the Church, Vol. 4, p. 382.AHAmh 258.2

    ከቁጥጥር ውጭ ለሆነ የአገልጋይ ወንድ ልጅ የቀረበ ልመና፦ አባትህ የወንጌል አገልጋይ ነው። የአገልጋዮች ልጆች ወላጆቻቸውን የማያከብሩ እንዲሆኑ ሰይጣን በተለየ ትጋት ይሠራል። ቢችልስ የፍላጎቱ እስረኞች አድርጎ በራሱ የክፋት ዝንባሌዎች ሊሞላቸው ይጥራል። ሰይጣን አንተን ተጠቅሞ ቤተሰብህ ተስፋና እርካታ እንዲያጣ ያደርግ ዘንድ ትፈቅድለታለህ? ራስህን ለሰይጣን ቁጥጥር አሳልፈህ ስለሰጠህ ወላጆችህ ሁልጊዜ በሐዘን እንዲመለከቱህ ይገደዱ? የመጣው ቢመጣ የራሳቸውን ፈቃድ ከመከተል ፈቀቅ የማይሉና ትዕዛዛታቸውን አሻፈረኝ የሚሉ ልጆች እንዳሳደጉ በማሰብ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ እንዲሆኑ ትተዋቸዋለህ?....AHAmh 258.3

    ሙከራዎችህ ጥሩ ናቸው፤ መልካም ነገርን እንዲጠብቁ በወላጆችህ አዕምሮ ተስፋን ትጭራለህ፤ ነገር ግን እስካሁን የሰይጣንን ሽንገላ ለመቋቋም አቅመ-ቢስ ሆነሃል፤ ልክ እርሱ እንደሚፈልገው ልትሆንለት የተዘጋጀህ ስለሆንህ ሰይጣን ሐሴት እያደረገ ነው። ሁልጊዜ ቤተሰቦችህን በተስፋ የሚያነሳሳ ንግግር ትናገራለህ፤ በዚያው ልክ ደግሞ ትመክናለህ፤ ጠላትን መቋቋም አልቻልህም። በሰይጣን ጎን ስትገኝ እናትና አባትህ ምን ያህል እንደሚያዝኑ ማወቅ ያዳግትሃል። ማድረግ አልችልም የምትላቸው ነገሮች ልትፈጽማቸው የተገቡህ እንደሆኑ ልብህ እያወቀው ብዙ ጊዜ “ይህን ማድረግ አልችልም” “ያንን ማድረግ አልችልም” ትላለህ። ጠላትን መዋጋት ትችላለህ፤ በራስህ ኃይል ግን አይደለም። ሁልጊዜም ድልን ሊሰጥህ ዝግጁ በሆነው በእግዚአብሔር ጉልበት ትችላለህ። ቃሉን በመተማመን “አልችልም” የሚለውን ቃል ፈጽሞ አትናገረው…. ጊዜ ሳለ እንድትመለስ በጌታ ስም እማፀንሃለሁ። ጥሩ ስነ-ምግባር ያለህ ልጅ መሆን አለብህ፤ ምክንያቱም አንተ የእግዚአብሔር የሥራ ባልደረባ የሆኑ ሰዎች ልጅ ነህ። ብዙ ጊዜ ግን ባፈንጋጭነትህ አባትህንና እናትህን ታዋርዳቸዋለህ። ሊሠሩት የሚፈልጉትንም ሥራ ታበላሽባቸዋለህ። ከአንተ ሥርዓት-አልበኝነት ውጪ እናትህ መንፈስዋን የሚጨቁንና የሚሰብር ሌላ ብዙ ነገር የሌላት ይመስልሃልን? የአባትህ ልብ በሐዘን ሸክም እንዲዝል ይህንን መንገድህን አሁንም ትቀጥልበታለህን? ሰማይ ሁሉ በሐዘን ሲመለከትህ ደስ ይልሃልን? በጠላት እዝና ቁጥጥር ሥር እራስህን ማስቀመጥህ እርካታ ይሰጥሃልን?AHAmh 258.4

    ኦ! አሁን ዛሬ ተብሎ እየተጠራህ ሳለ ወደ ጌታ ብትመለስ! እያንዳንዷ ተግባርህ ለተሻለ ወይም ለባሰ ነገር እየዳረገችህ ነው። እንቅስቃሴዎችህ በሰይጣን ጎራ ከሆኑ የክፋት መዘዛቸውን እውን የማድረግ ተጽዕኖ ትተው ያልፋሉ። ወደ እግዚአብሔር ከተማ መግባት የሚችለው ንጹሁ የጠራውና ቅዱሱ ብቻ ነው። የተጓዝህበት መንገድ ውድመት ትቶ የሚያልፍ እንዳይሆን ወደ ጌታ ተመለስ። 13Letter 15a, 1896.AHAmh 259.1

    አገልጋዮች፣ ልጆችን በደግነትና በቸርነት እንክብካቤ ይያዟቸው፦ የአገልጋዩ ደግነትና ቸርነት ከልጆች ጋር ባለው ግንኙነት ሊታይ ይገባዋል። በአካል ያነሱ ወንዶችና ሴቶች ታዳጊ የእግዚአብሔር ቤተሰብ አባላት እንደሆኑ ሁልጊዜም በአዕምሮው ያስቀምጥ። እነዚህ ለጌታ በጣም የቀረቡና ውድ የሆኑ በትክክል ቢሠለጥኑና ሥነ-ሥርዓት ይዘው ቢያድጉ፣ በወጣትነታቸው እንኳ የእርሱ አገልጋይ ሊሆኑ ይችላሉ። እያንዳንዱ በልጆች ላይ የሚሰነዘር ሸካራ፣ ጠንካራና ርኅራኄ የጎደለው አነጋገር የሱስን ያሳዝነዋል። መብታቸው ሁልጊዜ አይከበርም። ብዙ ጊዜ የእግዚአብሔር ዓላማ በሕይወታቸውሳይተገበር እንዳይቀርና ጠባያቸው ቅርጽ እንዳያጣ በጥንቃቄ ሊጎለብት የሚገባው ግላዊ ባህርይ እንዳላቸው ተደርጎ አይታይም። 14Testimonies for the Church, Vol. 4, pp. 397, 398.AHAmh 259.2

    ቤተ-ክርስቲያን ለመንጋው ጠቦቶች የተለየ ጥንቃቄ ታድርግ፤ በተቻላቸው ሁሉ የልጆችን ፍቅር ለማትረፍ ተጽዕኖአቸውን በማሳረፍ ከእውነት ጋር እንዲቆራኙ ይሁኑ። አገልጋዮችና የቤተ-ክርስቲያን ምዕመናን፣ ወላጆች ልጆቻቸው በመልካሙ መንገድ ይራመዱ ዘንድ የሚያደርጉትን ጥረት ማገዝ አለባቸው። በእርሱ ሰንደቅ ዓላማ ሥር የመልካም አገልግሎት ረዳቶች ይሆኑ ዘንድ ጌታ ወጣቶችን እየጠራ ነው። 15Review and Herald, Oct. 25, 1892.AHAmh 259.3

    እግዚአብሔርን ስለመምሰል ውጤታማ ስብከት፦ አገልጋዩ ስለ ልጆች አስተዳደር ሕዝቡን ያስተምር፤ የራሱም ልጆች የትክክለኛ ስነ-ሥርዓት ምሣሌ ይሁኑ። 16Letter 1, 1877.AHAmh 259.4

    እግዚአብሔርን ስለመምሰል ሲሰብክ ሳለ፣ ተግባራዊና ውጤታማ የሆነ አንድነት በአገልጋዩ ቤተሰብ መካከል ሊታይ ይገባል። በመገደብ፣ በማስተካከል፣ በመምከር፣ በማሳየትና በመምራት አገልጋዩና ባለቤቱ በቤት ውስጥ ያለውን ኃላፊነታቸውን በታማኝነት ሲወጡ፣ በቤተ-ክርስቲያን ለመሥራት የተሻለ ብቃት ያላቸውና ከቤት ውጪ ሊከናወን የሚገባውን የእግዚአብሔር ሥራ የሚፈጽሙ ወኪሎቹን ያበራክታሉ። የቤተሰቡ አባላት የሰማይ ቤተሰብ አካል ይሆናሉ፤ የመልካምነት ኃይል በመሆን ተጽዕኖአቸው ወሰነ-ሰፊ ይሆናል። 17Gospel Workers, pp. 204, 205.AHAmh 259.5