Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የአድቬንቲስት ቤት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ አሥራ አራት—እውነተኛ መለወጥ አስፈላጊ ነው

    ኃይማኖት የቤተሰቡን ደስታ ያረጋግጣል፦ የቤተሰብ ኃይማኖት ግሩም ኃይል ነው። በቤት ውስጥ ባልየው ለሚስቱ ሚስቱም ደግሞ ለባልዋ የሚያሳዩት ጠባይ በላይ በሰማይ ወዳለው ቤተሰብ እንዲገቡ የሚያዘጋጃቸው ነው።1Letter 57, 1902.AHAmh 58.1

    በክርስቶስ ፍቅር የተሞሉ ልቦች ፈጽሞ ተራርቀው ሊቀሩ አይችሉም። ኃይማኖት ፍቅር ነው፤ የክርስቲያን ቤት ፍቅር የነገሠበት ነው። ፍቅሩንም በቃልና በተግባር መግለጽ የሚችል ጥልቅ ደግነትና ርኅራኄ ያለው ነው።2Testimonies for the Church, Vol. 5, p. 335.AHAmh 58.2

    ኃይማኖት በቤት ውስጥ ተፈላጊ ነው፤ ምክንያቱም ብዙ ጊዜ የትዳርን ሕይወት መራራ የሚያደርገው አሳዛኝ ስህተት እንዳይሠራ ስለሚከለክል ነው። ክርስቶስ የነገሠበት ቤት ብቻ ነው ጥልቅ እውነተኛና እራስ-ወዳድ ያልሆነ ፍቅር የሚኖረው። ክርስቶስ ሲኖር ነፍስ ከነፍስ ጋር ይሸረባል፤ ሁለቱም በመስማማት ይዋሐዳሉ። የእግዚአብሔር መላእክት የቤቱ እንግዶች ይሆናሉ፤ ቅዱስ ጥበቃቸው የትዳሩን አዳራሽ ይቀድሰዋል፤ የሚያረክስ የአካላዊ እርካታ ይወገዳል። ሐሳብ ሁሉ ወደ ላይ ወደ እግዚአብሔር ይመራል። ልባዊ አገልግሎት ወደ እርሱ ይወጣል።3Id., p. 362.AHAmh 58.3

    እያንዳንዱ ክርስቶስ የሚኖርበት ቤተሰብ አንዱ ለሌላው መልካም ፍላጎትና ፍቅር መግለጽ የሚችልበት ነው። ፍቅራቸው የአካል መነካካት በሚኖርበት ጊዜ የሚገለጽ፤ ድንገት ሰውነትን የሚወር ፍቅር አይደለም፤ ጥልቅና ዘላቂ እንጂ።4Review and Herald, Feb. 2, 1886AHAmh 58.4

    ክርስትና የመቆጣጠር ተጽዕኖ ሊኖረው ይገባል፦ ክርስትና የጋብቻን ግንኙነት ሊቆጣጠር የሚገባ ቢሆንም ብዙ ጊዜ ግን ወደዚህ ጥምረት የሚመሩት ግፊቶች የክርስቲያን መርሆዎችን የጠበቁ አይደሉም። ሰይጣን በእግዚአብሔር ህዝቦች ላይ ኃይሉን ማጠናከር ይችል ዘንድ በቁጥጥሩ ሥር ካሉ ሰዎች ጋር ህብረት እንዲፈጥሩ ያግባባቸዋል፤ ይህንንም ለማሳካት ያልተቀደሰ ፍላጎት በልባቸው እንዲነሣሳ ይጥራል። ጌታ ግን ግልጽ በሆነ ቃሉ ሕዝቦቹ የእርሱ ፍቅር በውስጣቸው ከሌለባቸው ሰዎች ጋር እንዳይጣመሩ አዟል።5Patriarchs and Prophets, p. 563.AHAmh 58.5

    ምክር ለአዲስ ሙሽሮች፦ ጋብቻ የዕድሜ ልክ ጥምረት ሆኖ በክርስቶስና በቤተ-ክርስቲያን ያለው ግንኙነት ምሣሌ ነው። ክርስቶስ ለቤተ-ክርስቲያን የሚያሳየው መንፈስ ባልና ሚስት ለእርስ በእርሳቸው ሊያሳዩት የሚገባ መንፈስ ነው። እግዚአብሔርን ከሁሉም በላይ ከወደዱት ወደ አንድነት በመምጣት እርስ በእርሳቸው በጌታ ይፋቀራሉ፤ ይከባበራሉም። በእራስ መካዳቸውና በእራስ መስዋዕትነታቸው አንዱ ለሌላው በረከት ይሆናል….AHAmh 58.6

    ሁለታችሁም ልትለወጡ ይገባል፤ ለክርስቶስ መታዘዝ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ሁለታችሁም በቅጡ አልተረዳችሁትም፤ ቃሉን አጥኑ፤ “ከኔ ጋር ያይደለ እርሱ በላየ ላይ ነው [ይቃወመኛል]። ከኔም ጋር የማይሰበስብ እርሱ ይበትናል።” ጌታ ኃላፊነት ሊሰጣችሁ የምትችሉ አገልጋዮችና እውነተኛ የእግዚአብሔር ልጆች ትሆኑ ዘንድ ምኞቴ ነው። ከዚያም ሠላም፣ ልበ-ሙሉነትና እምነት ወደ እናንተ ይመጣሉ፤ አዎ ሁለታችሁም ደስተኛና የማትዋዥቁ ክርስቲያኖች ትሆናላችሁ። መልካሙን እንዴት መምረጥ ክፉውን ደግሞ እንዴት መቃወም እንድታውቁ የአስተሳሰብ ብልጥነትን አዳብሩ። የእግዚአብሔርን ቃል ጥናታችሁ አድርጉ፤ የሱስ እንድትድኑ ይፈልጋል። ወንድሜ ሆይ ሕይወትህ ጠቃሚ ይሆን ዘንድ የሱስ በግሩም ሁኔታ ጠብቆ አቆይቶሃል፤ መልካሙን ሁሉ በሕይወትህ ተግብር። የእግዚአብሔር ልጆች የመሆን እውነተኛ ፍላጎት ከሌላችሁ እርስ በእርሳችሁ እንዴት ልትረዳዱ እንደምትችሉ ዕውቀቱ አይኖራችሁም። ለእርስ በእርሳችሁ ገራምና አሳቢ ሁኑ፤ የራሳችሁን ምኞትና እቅድ ሌላኛውን ለማስደሰት ስትሉ ተዉት። ቀን በቀን እራሳችሁን የበለጠ እያወቃችሁት ትሄዳላችሁ። ቀን በቀን ያለባችሁን የባህርይ ድክመት እንዴት እንደምታሻሽሉ ትማራላችሁ። የራሳችሁን ፈቃድ ለእርሱ ፈቃድ አስረክባችኋልና ጌታ የሱስ ብርሃናችሁ፣ ጉልበታችሁና የሐሴታችሁ ዘውድ ይሆንላችኋል….AHAmh 59.1

    የሚያሸንፈው የእግዚአብሔር ፀጋ በልባችሁ ሊኖር ያስፈልጋችኋል። ከእግዚአብሔር ሥራ ጋር የተቆራኙ ሰዎች ራስ-ወዳድነትን ለማስወገድ ዘወትር ንቁ መሆን ይኖርባቸዋል። ፋኖሳችሁ ክሩ የተከረከመና የተቀጣጠለ ይሁን። ይህም ሲሆን ለምትሠሩትና ለምትናገሩት ግድ-የለሽ አትሆኑም። አንደኛው ሌላውን ለማስደሰት የሚጥር ከሆነ ሁለታችሁም ደስተኞች ትሆናላችሁ። የነፍሳችሁን መስኮት ወደ ምድር የተዘጋ፤ ወደ ሰማይ አቅጣጫ የተከፈተ አድርጉት። ክርስቶስን የግል አዳኛቸው አድርገው ሲቀበሉ ብቻ ነው ሴቶችና ወንዶች ከፍተኛ ደረጃ የሚደርሱት። ሁሉንም ነገር ለእግዚአብሔር አስረክባችሁ ነቅታችሁ ፀልዩ። ለዘለዓለማዊው ሕይወት እየለፋችሁ እንደሆነ ማወቃችሁ ሁለታችሁንም ያበረታታችኋል፤ ያጽናናችኋልም። በሐሳብ በንግግርና በሥራ የዓለም ብርሃን ልትሆኑ የተገባችሁ ናችሁ፤ በጌታ የተቀጣችሁ ሁኑ። በክርስቶስ በማመናችሁ እራሳችሁን ብቻ እንድታድኑ ሳይሆን በመመሪያነትና በምሣሌነት ሌሎች ነፍሳትን ታተርፉ ዘንድ ይጠበቅባችኋል። ክርስቶስን ምሣሌአችሁ አድርጉት። የማሸነፍ ኃይል እንደሚሰጣችሁ ተማምናችሁ ጥብቅ አድርጋችሁ ያዙት። ራስ-ወዳድነትን ከሥሩ መንግላችሁ ጣሉት፤ የራሱ ልጆች ናችሁና እግዚአብሔርን አግንኑት፤ መድኃኒታችሁን አክብሩት፤ በግዛቱ ውስጥ ቦታ 60 የአድቬንቲስት ቤት ይሰጣችኋል።6Letter 57, 1902.AHAmh 59.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents