Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የአድቬንቲስት ቤት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ምዕራፍ ሠላሳ ሁለት—የልብን የአትክልት ቦታ ቀድማችሁ ያዙ

    ወላጆች አትክልተኞች ናቸው፦ እግዚአብሔር ለወላጆች ክቡርና ቅዱስ ሥራ ሰጥቷቸዋል። የልብን ማሳ በጥንቃቄ ያዘጋጁ ዘንድ ከእግዚአብሔር ጋር ሠራተኞች እንዲሆኑ ተጠርተዋል። በልጆቻቸው የልብ የአትክልት ሥፍራ በመገኘት ሊንከባከቡትና በጥንቃቄ ሊጠብቁት ይገባል። መልካሙን ዘር ዝሩ፤ መልከ-ጥፉውን አረም ንቀሉ። እያንዳንዱ የባህርይ ግድፈት፣ እያንዳንዱ የጠባይ ጉድለት ሊቆረጥ ይገባዋል፤ እንዲቀጥል ከተፈቀደለት የባህርይን ውበት ያበላሻልና። 1Manuscript 138, 1898.AHAmh 137.1

    ወላጆች! ቤታችሁ እንድትለፉበት የተሰጣችሁ የመጀመሪያው የሥራ መስክ ነው። በቤታችሁ የአትክልት ሥፍራ ያሉት ወርቃማዎቹ ዕፀዋት የእናንተን ተቀዳሚ እንክብካቤ ይሻሉ። እንደ እነርሱ ያሉትን ነፍሳት ትጠብቁ ዘንድ ከተጠያቂነት ጋር ሃላፊነት ተሰጥቷችኋል። የሥራችሁን ጠባይ ዛላና ግብአቱን(ውጤቱን) በጥንቃቄ አጢኑ። 2Signs of the Times, July 1, 1886.AHAmh 137.2

    በቤታችሁ ውስጥ ልትንከባከቡት የሚገባ ትንሽ ቁራጭ መሬት ተሰጥቷችኋል። በእጃችሁ ለተሰጠው ለዚህ ሥራ እግዚአብሔር በኃላፊነት ይጠይቃችኋል። 3Review and Herald, Sept. 15, 1891.AHAmh 137.3

    የአትክልት ቦታውን መንከባከብ፦ በዓለም ላይ የተንሰራፋው ተጽዕኖ ወጣቱ የራሱን ተፈጥሮአዊ ዝንባሌ እንዲከተል የሚያስገድድ ነው። በወጣትነታቸው ልቅ ባህርይ ሲያሳዩ ወላጆች “ግድ የለም ስላልበሰሉ ነው፤ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ይስተካከላሉ፤ አሥራ ስድስት አሥራ ስምንት ዓመት ሲሞላቸው ለራሳቸው ያመዛዝናሉ፤ መጥፎ ባህርያቸውን አራግፈው በመጨረሻ ጠቃሚ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ይሆናሉ” ይላሉ። ምን ዓይነት ሥህተት ነው! የልብን የአትክልት ሥፍራ ለዓመታት ጠላት እንዲዘራበት ይፈቅዱለታል። መጥፎ መመሪያዎች እንዲጎለምሱ ወላጆቻቸው ይተውአቸዋል። ብዙውን ጊዜ በዚያ ማሳ ላይ ወደ ፊት የሚፈስሰው ጉልበት ኪሣራ ሆኖ ይቀራል….AHAmh 137.4

    አንዳንድ ወላጆች ልጆቻቸው መጥፎ ልማዶችን ተላብሰው እንዲያድጉ በመተው የዕድሜ-ልክ ጠባሳ ተሸክመው እንዲኖሩ አድርገዋቸዋል። ይህ ኃጢአት የሚያርፈው በወላጆች ላይ ነው፤ በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ የሚያድጉ ልጆች ክርስቲያን ነን ይሉ ይሆናል፤ ሆኖም የተለየ የፀጋ ሥራ በልባቸውና በሕይወታቸው ፍጹም ለውጥ ካላመጣ በስተቀር ቀድሞ የነበረው ልማዳቸው ይቀጥላል። ወላጆቻቸው ይዘውት እንዲያድጉ የፈቀዱላቸውን ባህርይ ያንፀባርቃሉ። 4Testimonies for the Church, Vol.1 p. 403AHAmh 137.5

    ወደ ፊት “መልካሙ እያሸነፈ መጥፎው ተጽዕኖ ደግሞ እየመነመነ ይሄዳል” በሚል አስተሳሰብ እጅ እንዳመጣ መልካሙንና ክፉውን ሳይለያዩ ቀላቅለው ማስተማር የለባቸውም። ክፉው ከመልካሙ በበለጠ ፍጥነት ያድጋል። ከብዙ ዓመታት በኋላ ሲማሩት የኖሩት ክፋት ሊወገድ ይችል ይሆናል፤ ግን ይህን ለማድረግ(ይህንን መንገድ ለመሞከር) የሚደፍር ማን ነው? ጊዜው አጭር ነው፤ በኋላ አረሙን ለማረም ከመንደፋደፍ ከአሁኑ መልካምና ንፁህ ዘር በልጆቻችሁ ብትዘሩ እጅግ ቀላልና አደጋም የሌለበት ይሆናል። በወጣቶች ጭንቅላት ያረፉ አሻራዎችን ቆይቶ መፋቅ እጅግ ከባድ ነው። ታዲያ እነዚህ እጥፍ-ዘርጋ የሚሉት የልጆች የተፈጥሮ ተሰጥኦዎች ወደ እውነት አቅጣጫ ቢያዘሙና መልካሙ አሻራ ቢያርፍባቸው እንዴት መልካም ነው። 5Christian Temperance and Bible Hygiene, pp. 138, 139.AHAmh 137.6

    ዘር መዝራትና ማረም፦ ገና በሕፃንነት ጊዜው፣ የልጁ የልብ እርሻ ለእግዚአብሔር የፀጋ ዝናብ በጥንቃቄ መዘጋጀት አለበት። ከዚያም የእውነት ዘር በተገቢው መንገድ መዘራት በትጋትም መጠበቅ አለበት። በስሙ ለተደረጉ ጥረቶች ሁሉ፣ ዋጋ የሚሸልመው እግዚአብሔር ለተዘራው ዘር ሕይወትን ይሰጣል። ከዚያም በመጀመሪያ ቡቃያ፣ ኋላም ዛላ፣ ኋላም በዛላው ፍጹም ሰብሉ ይታያል። በአብዛኛው የወላጆችን የቸልተኝነት ግፍ ተንተርሶ ሰይጣን በልጆች ልብ ዘሩን ይዘራል። የሐፍረትና የሃዘን ምርትም ይሰበሰባል። ዛሬ ዓለም የእውነተኛ መልካምነት ድሀ የሆነችው፣ ወላጆች ልጆቻቸውን በቤት ውስጥ ወደ እራሳቸው ማስጠጋት ስለተሳናቸው ነው። ከዋዘኞችና ከግድ-የለሾች ህብረት አይጠብቋቸውም። በመሆኑም ልጆቻቸው የሞትን ዘር ለመዝራት ወደ ዓለም ይገሰግሳሉ። 6Manuscript 49, 1901.AHAmh 138.1

    ታላቁ የማስተዳደር ሥራ - እርባና-ቢስና መርዛማ የሆኑ አረሞችን መንቀል፣ ከሁሉም የበለጠ አስፈላጊ ተግባር ነው። ሳይነቀሉ ከተተዉ እነዚህ አረሞች የግብረገብነት መርህና እውነት የሆኑትን ወርቃማ ተክሎች አንቀው ያስቀሯቸዋል። 7Review and Herald, April 14, 1885.AHAmh 138.2

    አንድ እርሻ ሳይታረስ ከተተወ በኋላ ለማጥፋት አስቸጋሪ የሆኑ አረሞች እንደሚበቅሉበት እርግጥ ነው። ወርቃማዎቹ ዕፀዋት ከመተከላቸውና ከማደጋቸው በፊት ማሳው መለስለስና አረሞቹ መወገድ ለባቸው። እነዚህ ውድ ዋጋ ያላቸው ዕፀዋት ከማደጋቸው በፊት ዘሩ በሥነ-ሥርዓት መዘራት አለበት። እናቶች ወርቃማውን ዘር ለመዝራት ችላ ብለው ነገር ግን መልካም ምርት ለመሰብሰብ የሚያስቡ ከሆነ የጠበቁት ስለማይሆን ቅር መሰኘታቸው አይቀሬ ነው፤ እሾህና አሜኬላ ይሰበስባሉና። የራሱን ዲያብሎሳዊ ባህርይ ያዘለ የተትረፈረፈ ምርት የሚያስገኝ ዘር ሊዘራ ሰይጣን ምን ጊዜም በተጠንቀቅ ላይ ነው። 8Manuscript 43, 1900.AHAmh 138.3

    በልጆቻችን ጉዳይ ያላሰለሰ ጥንቁቅነት ማሳየት ግድ ይለናል። ሰይጣን ዘርፈ-ብዙ መሣሪያዎቹን ተጠቅሞ ገና እንደተወለዱ በጠባያቸውና በፍላጎታቸው ላይ መሥራት ይጀምራል። በዚህ ጊዜ ደህንነታቸው በወላጆቻቸው ንቁ እንክብካቤና ጥበብ የሚወሰን ይሆናል። ወላጆች በፈሪሃ-እግዚአብሔርና በፍቅር ሆነው የልጆቻቸውን የልብ አትክልት ሥፍራ ለመልካም በመጥመድ፣ በልጆቻቸው ልብ ትክክለኛ መንፈስና ትክክለኛ ልማድ እንዲሁም ፍርሃትና ፍቅር ለእግዚአብሔር የሚያጎለብት መልካም ዘርን በመዝራት ሊተጉ ይገባቸዋል። 9Manuscript 7, 1899.AHAmh 138.4

    ተፈጥሮአዊ ውበትን መግለጥ፦ ክርስቶስ ሁል ጊዜም ሊሰጥ የተዘጋጀውን ጥበብ ወላጆችና መምህራን በዕውነት ሊሹት ይገባል። ልጆች እጅግ ደስ በሚያሰኘው በሰው አእምሮ ላይ አሻራ ማሳረፍ በሚቻልበት የሕይወት ምዕራፍ ላይ ናቸው። ልክ በአትክልት ቦታው እንዳሉት ተክሎችና አበቦች ቀስ በቀስ እየፈኩ በእያንዳንዱ የእድገት ደረጃቸው የዚያ፣ ዕድሜ ክልል የሚጠይቀውን ውበት ማሳየት ይችሉ ዘንድ የወጣቶችን ዝንባሌ በእውነተኛው መንገድ ለማጎልበት ማቀድ ይገባቸዋል። 10Testimonies for the Church Vol. 6, pp. 204, 205.AHAmh 139.1