Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የአድቬንቲስት ቤት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ ዘጠኝ—የተከለከሉ ጋብቻዎች

    የክርስቲያኖች ጋብቻ ከማያምኑ ጋር፦ አማኞች ከማያምኑ ጋር ስለሚፈጽሙት ጋብቻ እግዚአብሔር የሚያስተምረውን ትምህርት ቸል ማለት በሚያስገርምና በሚያሳስብ ሁኔታ በክርስቲያኑ ዓለም አለ። እግዚአብሔርን እንደሚወዱና እንደሚፈሩት የሚናገሩ ሁሉ፣ የማያልቀውን የጥበብ ባለቤት እግዚአብሔርን እንደማማከር የራሳቸውን የጎበጠ ዝንባሌ መከተልን ይመርጣሉ። በዚህና በሚመጣው ዓለም የሁለቱንም ወገኖች ደስታና ደህንነት በሚገዳደር ሁኔታ ግንዛቤ፣ አስተዋይነትና ፈሪሐ-እግዚአብሔር ወደ ጎን ይገፈተራሉ። ጭፍን የስሜት ግፊትና መንቻካነት እንዲቆጣጠሩን ይፈቀድላቸዋል። ጥንቁቅና አስተዋይ መሆን ይችሉ የነበሩ ሰዎች ለምክር ጆሮአቸውን ይደፍናሉ። ከጓደኛ፣ ከዘመድ አዝማድና ከእግዚአብሔር አገልጋዮች ለሚቀርብላቸው ማግባባትና ልመና ደንቆሮ ይሆናሉ። ማስጠንቀቂያው ሁሉ እንደ ዋጋ-ቢስ ጣልቃ-ገብነት ይቆጠራል፤ ለወዳጅነቱም ታማኝ የሆነና ተቃውሞውን በግልጽ ለመናገር የደፈረ ጓደኛ እንደ ጠላት ይታያል። ይህ ሁሉ እንደ ሰይጣን ሐሳብ ነው። በነፍሳቸው ዙሪያ አስማት ይሠራል። የነሆለሉና በዐይን ፍቅር የፈዘዙ ይሆናሉ። ምክንያታዊነትና ራስን-የመግዛት ልጓም በዝሙት አንገት ላይ ይጠመጠማሉ። መመለስ እስከማይቻልበት ደረጃ ድረስ ያልተቀደሰ ፍላጎት እየወተወተ ሥራውን ይሠራል። ተጠቂው ሲነቃም እራሱን በሰቆቃና በባርነት ሕይወት ውስጥ ያገኘዋል። ይህ ሁኔታ በምናብ የተሳለ ሥዕል እንዳይመስላችሁ፤ በእርግጥ የተፈጠሩ ነገሮች ድግግሞሽ ነው። በግልጽ ለከለከለው የትዳር ጥምረት እግዚአብሔር ፈቃዱን አይሰጥም፤ ይህ ዓይነቱን ጋብቻ እርሱ አያጸድቀውም።1Testimonies for the Church, Vol. 5, pp. 356, 366.AHAmh 35.1

    የእግዚአብሔር ትዕዛዛት ግልጽ ናቸው፦ እግዚአብሔር ጥንታዊ እስራኤላዊያንን በአካባቢያቸው ካሉ ጣኦትን ከሚያመልኩ ሕዝቦች ጋር እንዳይጋቡ አዟቸው ነበር፤ “ከርሳቸው ጋር አትጋባ ሴት ልጅህን ለወንድ ልጁ አትስጥ ሴት ልጁንም ለወንድ ልጅህ አትውሰድ” ምክንያቱም ተሰጥቷል። ወሰን የለሽ ጥበብ በእንደዚህ ዓይነቱ ጋብቻ ወደፊት የሚከተለውን በማየት “ልጅህን ያስታሉና እንዳይከተለኝ ሌሎችንም አማልክት ያመልካሉ። የእግዚአብሔርም ቁጣ ይበረታባችኋል ፈጥኖም ያጠፋኻል” “አንተ ለእግዚአብሔር ለአምላክኽ የተቀደሰ ሕዝብ ነህና። አንተንም መረጠ እግዚአብሔር አምላክኽ የተወደደ ሕዝብ ትሆንለት ዘንድ በምድር ፊት ከሚኖሩ”….AHAmh 35.2

    በአዲስ ኪዳንም ክርስቲያኖች ከማያምኑ ጋር ስለሚያደርጉት ጋብቻ ተመሳሳይ መከላከያዎች ተቀምጠዋል። ሐዋርያው ጳውሎስ በመጀመሪያው የቆሮንቶስ ሰዎች መልእክት እንዲህ ይላል “ሴት በህግ ለባልዋ ታስራ ትኖራለችና ባለበቱ ዘመን። ባልዋ ግን ከሞተ በኋላ አርነት ትወጣለች ከባልዋ ህግ፤ በጌታ ብቻ” በሁለተኛው መልእክቱም እንዲህ ይላል “ከማያምኑ ሰዎች ጋር የምትስማሙ አትሁኑ። ምን አንድነት አለ በጽድቅና በኃጢአት መካከል። ወይስ ምን መገናኘት አለው ለብርሃን ከጨለማ ጋራ። ወይስ ምን ፈንታ ለሚያምን ከማያምን ጋራ። ወይስ ምን መዋደድ አለው ለእግዚአብሔር መቅደስ ከጣዖታት ጋራ። እላንት የሕያው እግዚአብሔር መቅደስ ናችሁና እግዚአብሔር እንዳለ እኔ አድርባቸዋለሁ ከእርሳቸውም ጋራ እሄዳለሁ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ እርሳቸውም ወገኖቼ ይሆናሉ። ስለዚህ ከመካከላቸው ውጡ ከእርሳቸውም ተለዩ እግዚአብሔር ይላል። ወደ ርኩስም ሁሉ አትቅረቡ እኔም እቀበላችኋለሁ እኔም አባት እሆናችኋለሁ እላንትም ልጆች ትሆኑልኛላችሁ ይላል እግዚአብሔር ሁሉን የሚችል።” 2Id., pp. 363, 364.AHAmh 36.1

    በዚህ ዘመን በዓለም ያለጊዜያቸው የሚፈፀሙና ተገቢ ያልሆኑ ግንኙነቶች የእግዚአብሔር ርግማን የሚወርድባቸው ሆነዋል። መጽሐፍ ቅዱስ ለነዚህ ጥያቄዎች የሚሰጠው መልስ የደበዘዘ ብርሃንና የሚያጠራጥር ቢሆን ኖሮ የዘመኑ ወጣቶች የሚከተሏቸው የተሳሳቱ የግንኙነት መንገዶች የበለጠ ይቅርታ ሊደረግላቸው ይችሉ ነበር። ነገር ግን የመጽሐፍ ቅዱስ ድንጋጌዎች የከፊል ትዕዛዛት አይደሉም፤ ፍጹም የሆነ የአስተሳሰብና የሥራ ንጽህናን የሚሹ ናቸው። ቃሉ ለእግራችን መብራት ስለሆነ፤ ማንም የጥፋትን መንገድ መከተል ስለማይገባው እግዚአብሔርን እናመሠግናለን። ወጣቶች ገጾቹን ማንበብ ተግባራቸው በማድረግ ምክሩን ያስተውሉ፤ ሁልጊዜ አሳዛኝ ጥፋቶች የሚሠሩት ከመመሪያው ፈቀቅ ስንል ነውና።3Fundamentals of Christian Education, pp. 102, 103.AHAmh 36.2

    የሚያምኑ ከማያምኑ ጋር እንዳይጋቡ እግዚአብሔር ይከለክላል፦ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ወደ ተከለከለ ምድር ይገቡ ዘንድ በጭራሽ አይገባም።በሚያምኑና በማያምኑ መካከል የሚፈፀም ጋብቻ በእግዚአብሔር ዘንድ የተከለከለ ነው። ብዙ ጊዜ ግን ያልተለወጠው ልብ የራሱን ፈቃድ በመከተል እግዚአብሔር የማያጸድቃቸው ጋብቻዎች ይመሠረታሉ። በዚህም ምክንያት ብዙ ሴቶችና ወንዶች በዚህ ምድር ያለ ተስፋና ያለ እግዚአብሔር ቀርተዋል። በተለያዩ ሁኔታዎቻቸው በሰይጣን መረብ ተይዘው የከበረ ምኞታቸው ሞቷል። ለስሜታዊ ፍላጎትና ግፊት የሚገዙ ሁሉ በዚህ ዓለም ሕይወታቸው መራራ መከርን የሚሰበስቡ ናቸው። ይህ አካሄዳቸው በሚመጣው ዓለምም የነፍሳቸው ጥፋት ሊሆን ይችላል።4Id., pp. 500, 501.AHAmh 36.3

    እውነትን የሚመሰክሩ ሁሉ፣ ያን እውነት የማያምኑትን በማግባታቸው በእግዚአብሔር ፈቃድ ላይ የሚረማመዱ ናቸው። አማኝ ያልሆነው አካል በጣም ጥሩ የሆነ የግብረ-ገብነት ባህርይ ይኖረው ይሆናል፤ ነገር ግን ለእግዚአብሔር የይገባኛል ጥያቄ መልስ አለመስጠቱ፣ ታላቁንም ማዳኑን ቸል ማለቱ ጋብቻውን ላለመፈጸም በቂ ምክንያት ነው። የማያምነው ሰው ባህርይ ክርስቶስ እንዲህ እንዳለው፣ እንደዚያ ወጣት ነው “አንድ ነገር ብቻ ጎደለህ” አንድ ነገር - ግን እጅግ አስፈላጊ የሆነ ነገር።5Testimonies for the Church, Vol. 4, p. 505.AHAmh 37.1

    የሰለሞን ምሣሌነት፦ እግዚአብሔር ሊቀበላቸውና በምድር እጅግ ጠቃሚዎች፣ የሰማይም ደስታ ሊያደርጋቸው የሚፈልጋቸው [እውነት] ተጋርዶባቸው በብዙዎች ሳይታወቁ በድህነት የሚኖሩ ሰዎች አሉ። ይህን የአምላክን እቅድ ግን ለማኮላሸት ሰይጣን እጅግ ተግቶ ይሠራል፤ ራሳቸውን ከሕይወት መንገድ በማራቅ ነፍሳቸውን ወደ ሞት ለመወርወር ግድ የማይላቸው ዓይነት ባህርይ ያላቸው ሰዎች ጋር በጋብቻ እንዲጣመሩ በማድረግ ወደ ሲኦል ያወርዳቸዋል። ከዚህ ዓይነቱ ድንብርብር በአሸናፊነት የሚወጡ በጣም ጥቂቶች ናቸው።6Id., Vol. 5, p.124.AHAmh 37.2

    መታዘዝ የሚያስከትለውን ውጤት ሰይጣን ጠንቅቆ ያውቀዋል። በመጀመሪያዎቹ የሰለሞን የንግሥና ዓመታት - በንጉሡ ጥበብ ችሮታና ንጽህና ምክንያት የተገኙ እነዚያን ወርቃማ ዓመታት - ያሳለፈ ቢሆንም እንኳ ለመርህ ታማኝነቱን ቀስ በቀስ ውስጥ ውስጡን እየሸረሸረ ከእግዚአብሔር ሊለየው የሚችለውን ተጽዕኖ ዲያብሎስ በንጉሡ ላይ ለማምጣት ጣረ። በዚህ ረገድ ጠላት ውጤታማ እንደነበረ ከተጻፈው እናውቃለን፡- “ሰለሞንም ለፈርዖን ለምስር ንጉሥ አማች ሆነ ልጁንም አገባ ወደ ዳዊት ከተማም ይዝዋት መጣ።”AHAmh 37.3

    ከከሃዲ ሕዝብ ጋር ወዳጅነት የመመሥረት ግንኙነቱን ጣዖት አምላኪ ንግሥት በማግባት በማጠናከሩ የእርሱን ሕዝብ ንጽህና ይጠብቅ ዘንድ እግዚአብሔር የሰጠውን ጥበብ የተሞላበት ስጦታ ፈጥኖ ችላ አለ። ያቺ ግብጻዊ ሚስቱ ትለወጣለች የሚለው ተስፋ ለተሠራው ኃጢአት ማስተባበያ የቀረበ ደካማ ምክንያት ነበረ። ከሌሎች ሕዝቦች ጋር እንዳይቀላቀሉ የተቀመጠውን ቀጥተኛ ትዕዛዝ በመተላለፍ ንጉሡ የተሰጠውን መለኮታዊ ኃይል ከሥጋ ክንድ ጋር አጎዳኘው። ለተወሰነ ጊዜ እግዚአብሔር በሩኅሩኅ ምህረቱ ከባድ ጥፋቱን ሽሮት ነበር። የሰለሞን ሚስት ተለወጠች፤ ንጉሡም በብልህ አካሄዱ በብልግናው ምክንያት ሥራ የጀመረውን የርኩሰት ኃይል ለማስቆም ብዙ ሳይለፋ አልቀረም። ነገር ግን ሰለሞን የኃይሉና የክብሩን ምንጭ ማየት እየተሳነው መጣ። የራሱ ዝንባሌ በምክንያታዊነት ላይ ድል እየተቀዳጀ ሄደ። በራስ መተማመኑ እየጨመረ ሄዶ የእግዚአብሔርን እቅድ በራሱ መንገድ ማሳካት ፈለገ….AHAmh 37.4

    ብዙ ኃይማኖተኛ ክርስቲያኖች ልክ እንደ ሰለሞን ያስባሉ፤ ከከሐዲዎች ጋር መጎዳኘታቸው የእነርሱ ተጽዕኖ ለማያምኑት እጅግ ጠቃሚ እንደሆነ ያምናሉ፤ በአብዛኛው ግን የማያምነውን ወገን በመለወጥ ፈንታ እራሳቸው ታጥረውና ተሸንፈው፣ ቅዱሱን እምነታቸውን ትተው፣ መመሪያቸውን ሰውተው፣ እራሳቸውን ከእግዚአብሔር ይነጥላሉ። አንድ የተሳሳተ እርምጃ ወደ ሌላው እየመራ መጨራሻ የተበተባቸውን ሰንሰለት እንበጥሳለን ብለው ተስፋ ማድረግ በማይችሉበት ሁኔታ እራሳቸውን ያስቀምጣሉ።7Fundamentals of Christian Education, pp. 48-500.AHAmh 38.1

    ለኃይማኖቴ ምቹ ነው” የሚባለው አቤቱታ፦ አንዳንድ ጊዜ የሚሰጡ ምክንያቶች አሉ፤ አማኝ ያልሆነው የሚጎድለው አንድ ነገር ብቻ ነው - ክርስቲያን አይደለም - ሆኖም በእምነቴ ላይ ችግር የሚፈጥር አይደለም ይባላል። ከማያምኑ ጋር ዕድሜአቸውን ሙሉ በጋብቻ ለመቆራኘት የሚመርጡት ምርጫ አግባብነት የሌለው እንደሆነ ሕሊናቸው ቢነግራቸውም፣ ከአሥር ዘጠኝ የሚሆኑት አማኞች ግን በጋብቻቸው የመግፋቱ ዝንባሌ እንዲያሸንፋቸው ይፈቅዱለታል። የጋብቻ ቃል-ኪዳን በተፈፀመበት ቅጽበት መንፈሳዊ ዝቅጠት ይጀምራል። ለኃይማኖት ያለው አድናቆት ይቀዘቅዛል፤ አንዱ መመከቻ ሌላውን ተከትሎ እየተሰበረ መጨረሻ ሁለቱም ጎን ለጎን በጥቁሩ የሰይጣን ሰንደቅ ዓላማ ሥር ይቆማሉ። በጋብቻው ሥነ-ሥርዓት ጊዜ እንኳን የዚህ የዓለም መንፈስ፣ በሕሊና በእምነትና በእውነት ላይ ድል መቀዳጀቱ ይታያል። በአዲሱ ቤታቸው የፀሎት ሰዓት አይከበርም፤ ሙሽሪትና ሙሽራው እርስ በእርስ ተመራርጠው የሱስን አሰናብተውታል።8Testimonies for the Church, Vol.4 p. 505.AHAmh 38.2

    መለወጥ በአማኙ ላይ ይከሰታል፦ መጀመሪያ አካባቢ የማታምነው/የማያምነው ለእንደዚህ ዓይነቱ ዝምድና ተቃውሞዋን/ውን አታሳይ/አያሳይ ይሆናል፤ ነገር ግን ስለ መጽሐፍ ቅዱስ እውነት ማሰብና ትኩረት መስጠት በሚያሻት/ው ጊዜ ሐሳቧ/ቡ ግንፍል ይልና “ምን ዓይነት ሰው እንደሆንሁ እያወቅህ/ሽ ነው ያገባኸኝ/ሽኝ እንድረበሽ አልፈልግም፤ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ስለዚህ እንግዳ ስለሆነው አስተሳሰብህ/ሽ መነጋገር የተከለከለ መሆኑን እንድታውቅልኝ/ቂልኝ እፈልጋለሁ” ይላሉ። አማኙ ወገን በእምነቱ ረገድ ጠንካራ አቋም የያዘ እንደሆነ ለማያምነውና የክርስትናን ሕይወት ላልተለማመደው ወገን ደግነት አለማሳየት መስሎ ይሰማዋል። አማኙ ከመረጠው አጋር ጋር ስላለው አብሮነት ሲል ነገሮችን መተው እንዳለበት ይሰማዋል። ማህበራዊና ዓለማዊ የሆኑ መደሰቻዎች መበረታታት ይጀምራሉ። መጀመርያ ለእንደዚህ ዓይነቱ አካሄድ ፈቃደኛ ያለመሆን ነገር አለ፤ ሆኖም ለዕውነት ያለው ፍላጎት እየቀዘቀዘ እየቀዘቀዘ ይሄድና እምነት በጥርጣሬና ባለማመን ይተካል። ያ ጠንካራና ጥንቁቅ አማኝ፣ የክርስቶስ ታማኝ ተከታይ፣ እንደዚህ የሚጠራጠርና የሚዋዥቅ ይሆናል ብሎ ማንም ሊገምት አይችልም። ኦ! ብልሃት በጎደለው ጋብቻ ምክንያት የመጣው ለውጥ!9Id., pp. 505, 506.AHAmh 38.3

    ዓለማዊ ህብረት መፍጠር በጣም አደገኛ ነው። የብዙዎቹ ወጣት ሴቶችና ወንዶች ጋብቻ፣ የኃይማኖት ልምምዳቸውና የጠቃሚነታቸው ታሪክ የሚዘጋበት(የሚያበቃበት) ሰዓት እንደሆነ ሰይጣን ጠንቅቆ ያውቃል፤ ከክርስቶስ ተማርከው ተወስደዋልና። ለተወሰነ ጊዜ ክርስቲያናዊ ሕይወት ለመኖር ይሞክራሉ፤ ነገር ግን ጥረታቸው በማያቋርጥ ተጽዕኖ ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ ይመራል። በአንድ ወቅት ስለ እምነታቸውና ስለ ተስፋቸው መናገር እንደመታደል ይቆጥሩት እንዳልነበር፣ አብሮአቸው ያለው ሰው ምንም ፍላጎት እንደሌለው ስለሚያውቁ ስለዚያ ነገር እንኳ መጥቀስ ፈቃደኛ አይሆኑም። የከበረው እውነትና እምነት ከልብ ውልቅ ብሎ ይወጣና ውስጥ ውስጡን ሰይጣን የመጠራጠርን ድር ያደራባቸዋል።10Id., pp. 504, 505.AHAmh 39.1

    የሰማይን ደስታ አደጋ ላይ መጣል፦ “በውኑ ሁለት ሰዎች ያለ ስምም ባንድ ይሔዳሉን?” “ደግሞም እላችኋለሁ። ከላንት ሁለቱ በምድር አንድ ቢሆኑ በልመናቸው የለመኑት ሁሉ ይሆንላቸዋል ከሰማዩ አባቴ ዘንድ።” ነገር ግን አንደኛው በታማኝነትና በፍቅር የተጠመደ ሆኖ ሌላኛው ቸልተኛና ግድ-የለሽ ሲሆን፤ እንደኛው ዘለዓለማዊ ሕይወት ሲሻ ሌላኛው ወደ ሞት በሚወስደው በሰፊው መንገድ ላይ ሲራመድ እንዴት እንግዳ ትዕይንት ነው!AHAmh 39.2

    ብዙዎች ያልተለወጡ ሰዎችን በማግባታቸው ሰማይንና የሱስን ሰውተዋል፤ የሱስና ሰማይ ቀርተውባቸዋል። የምስኪን ጠፊ ሰዎችን አብሮነት መምረጣቸው የክርስቶስን ጓደኝነትና ፍቅር ምን ያህል ዝቅተኛ ዋጋ ቢሰጡት ይሆን? በውስጡ የሚገኘውን ሃሴት አደጋ ላይ ጥለው ለውዱ አዳኝ ፍቅር የሌለውን ሰው መምረጣቸው ሰማይን እንዴት የተዋረደ ቦታ አድርገው ቢያስቡት ነው?11Id., p. 507.AHAmh 39.3

    ከማያምን ጋር መቆራኘት በሰይጣን ግዛት ውስጥ እራስን ማስቀመጥ ነው። የእግዚአብሔርን መንፈስ ታሳዝናላችሁ፤ ጥበቃውንም ታጣላችሁ። ለዘለዓለማዊ ሕይወት ለምትዋጉት ውጊያ እንዲህ ዓይነት አሳዛኝ ዕድል እንዲገጥማችሁ ልትፈቅዱ ይቻላችኋልን?12Id., Vol. 5, p. 364.AHAmh 39.4

    እራሳችሁን ጠይቁ “የማያምን ባል ለየሱስ ካለኝ ሐሳብ አያርቀኝም? እግዚአብሔርን በመውደድ ፈንታ የራሱን ደስታ የሚያፈቅር ነው፤ እርሱን የሚያስደስቱትን ነገሮች እኔም እንድወዳቸው አይገፋፋኝም?” ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት የሚወስደው መንገድ ገደል የመሰለ አቀበትና ወጣ ገባ የበዛበት ጎዳና ነው፤ ወደ ኋላ የሚጎትታችሁን ተጨማሪ ክብደት አትሸከሙ።13Id., p. 363.AHAmh 39.5

    ያንዣበበበት ጥላ ፈጽሞ የማይለቀው ቤት(ትዳር)፦ ልብ የሰውኛን ፍቅር ይናፍቃል። ይህ ዓለማዊ ፍቅር ግን የክርስቶስን የፍቅር ቦታ ሊተካ የሚችል ብቁ ጥንካሬ፣ ንጽህናና ክቡርነት ይጎለዋል። አንዲት ሚስት ሕይወት የሚያመጣውን ሰቆቃ፣ የሚያስፈልገውን ጥንቃቄና ኃላፊነት ለመሸከም የሚያስችላት ጥበብ፣ ጥንካሬና ፀጋ የምታገኘው ከአዳኙ ብቻ ነው። የሱስን ጥንካሬዋና መሪዋ ልታደርገው ይገባል። አንዲት ሴት ለምድራዊ ጓደኛዋ እራስዋን አሳልፋ ከመስጠትዋ በፊት ለክርስቶስ እራስዋን አሳልፋ መስጠት አለባት፤ ይህንን ከሚጻረር ወደ ማንኛውም ግንኙነት መግባት የለባትም። እውነተኛ ደስታ ሊያገኙ የሚፈልጉ ሁሉ በሥራቸውና በንብረታቸው ላይ የእግዚአብሔር በረከት ሊኖርበት ግድ ይላል። ለእግዚአብሔር አለመታዘዝ ብዙ ልቦችንና ቤቶችን በስቃይ የተሞሉ ያደርጋቸዋል። እህቴ ሆይ ጥላ ያጠላበት ቤት እንዲኖርሽ ካልፈለግሽ በስተቀር የእግዚአብሔር ጠላት ከሆነ ጋር ራስሽን አታዛምጂ።14Id., pp. 362, 363.AHAmh 39.6

    ክርስቲያኑ ማቅረብ ያለበት ምክንያት፦ የኃይማኖት መመሪያዎችን ትክክለኛነት ጥያቄ ውስጥ የሚከት ፈታኝ ሁኔታ ሲገጥማቸው ክርስቲያኖች ምን ማድረግ አለባቸው? እርግጠኛ እንደሆነ በሚያስታውቅ ሁኔታ በዕውነት እንዲህ ይበል:- “እኔ ሕሌና ያለኝ ክርስቲያን ነኝ፤ የሣምንቱ ሰባተኛው ቀን የመጽሐፍ ቅዱስ ሰንበት እንደሆነ አምናለሁ፤ የሁለታችን እምነትና መመሪያዎች በተቃራኒ አቅጣጫዎች የሚመሩን በመሆናቸው ደስተኞች ልንሆን አንችልም፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማድረግ የተሻለና ፍጹም እውቀት ለማግኘት ስጥር ከዓለም ጋር ያለኝ ልዩነት እየሰፋ ክርስቶስን ወደ መምሰል እየተጠጋሁ እሄዳለሁ። ክርስቶስ ፍቅር መሆኑ የማይታይሽ ከሆነ፤ እውነት የማይማርክሽ ከሆነ፣ ዓለምን አፍቃሪ ትሆኛለሽ፤ እኔ ግን ዓለምን ልወድ አልችልም። እኔ የእግዚአብሔርን ነገሮች ሁሉ ስወድ ሳለ አንቺ ግን ልትወጃቸው አትችይም። የመንፈስ ነገሮች በመንፈሳዊነት ነው የሚታወቁት፤ ያለ መንፈስ እውቀት እግዚአብሔር በእኔ ላይ ያለውን የባለቤትነት መብት ማየት ወይም ለጌታዬ ያለብኝን የማገልገል ግዴታዎች ማስተዋል ይሳንሻል። በመሆኑም ለኃይማኖታዊ ግዴታዎች ስል አንቺን ቸል ያልሁሽ ይመስልሻል፤ ደስተኛ አትሆኝም። ለእግዚአብሔር ባለኝ ፍቅር የተነሣ ቅናተኛ ትሆኛለሽ፤ እኔም በእምነቴ ብቸኛ እሆናለሁ። ልብሽ ለእግዚአብሔር የይገባኛል ጥያቄ አወንታዊ መልስ ሲሰጥና አዳኙን መውደድ ስትማሪ ያኔ ግንኙነታችን ሊታደስ ይችላል።”AHAmh 40.1

    ጠንካራው አማኝ ህሌናው የሚቀበለውን በመከተል ለክርስቶስ ሲል መስዋዕት ይከፍላል፤ ይህም ለዘለዓለማዊ ሕይወት ምን ያህል ከፍተኛ ዋጋ እንደሚሰጥና ይህን አደጋ ላይ ከሚጥሉ ነገሮች እንደሚሸሽ ያሳያል። ከየሱስ ይልቅ ዓለምን ከወደደች፤ ከክርስቶስ መስቀል ከምታርቀው ሴት ጋር ዕድሜውን ሙሉ ከመኖር አለማግባት የተሻለ እንደሆነ ይሰማዋል።15Id., Vol. 4, pp. 506, 507.AHAmh 40.2

    አደጋ የሌለው ጥምረት፦ አደጋ የሌለው ትዳር ሊመሠረት የሚቻለው በክርስቶስ ብቻ ነው። የሰው ፍቅር ከመለኮታዊ ፍቅር ጋር መተሳሰር አለበት። ጥልቅ፣ እውነተኛና ራስ-ወዳድነት የማይታይበት ፍቅር የሚኖረው ክርስቶስ ሲገኝበት ብቻ ነው።16Ministry of Healing, p. 358.AHAmh 41.1

    ከጋብቻ በኋላ አንደኛው ወገን አማኝ ሲሆን፦ ሳያምን ወደ ጋብቻ ገብቶ ከዚያ በኋላ የተለወጠና አማኝ የሆነ ሰው በመለወጡ ለአጋሩ የበለጠ ታማኝ መሆን ይጠበቅበታል። በእምነታቸው ልዩነት ቢኖርም እንኳ የእግዚአብሔርን ጥያቄ ከማንኛውም ዓለማዊ ግንኙነት ማስበለጥ ይገባቸዋል። ውጤቱ ፈተናና ስደት ቢሆንም እንኳ በፍቅር መንፈስና በየዋህነት የተመሠረተ ይህ ታማኝነት የማያምነውንየማሸነፍ ተጽዕኖ ይኖረዋል።17Patriarchs and Prophets, p. 175.AHAmh 41.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents