Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የአድቬንቲስት ቤት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ ሰባ—የደስታ ነፀብራቅ

    እውነተኛ ክርስቲያን ደስተኛ ነው፦ የዕለት ተዕለት ድንግርግሮሾችና ጭንቀቶች ነጭናጮችና ግንባራችሁ የተቋጠረ እንዲያደርጓችሁ አትፍቀዱላቸው። እንደዚህ ካደረጋችሁ ሁልጊዜም የምትበሳጩበትና የምትናደዱበት ነገር አታጡም። ኑሮን ኑሮ የምናደርገው እኛው ነን፤ የፈለግነውንም ሳናገኝ አንቀርም። ሐዘንና ችግር የምንፈልግ ከሆነ፤ ጥቃቅን ችግሮችን የማግዘፍ ነገር ከተጠናወተን፤ ንግግራችንና አስተሳሰባችን እስኪመሰጥ ድረስ በገፍ እናገኛቸዋለን። የነገሮችን መልካም ጎን የምንመለከት ከሆነ ግን ፍልቅልቅና ደስተኛ የምንሆንባቸው በቂ ምክንያቶች እናገኛለን። ፈገግ የምንል ከሆነ በዚያው ልክ ይመለስልናል፤ መልካምና የሚያስደስቱ ቃላትን ብንናገር እነርሱ እራሳቸው ተመልሰው ለእኛ ይነገራሉ።AHAmh 314.1

    ክርስቲያኖች ጓደኛ እንደሌላቸው ሁሉ የቆዘሙና የተጨነቁ ሲመስሉ የእምነታቸውን የተሳሳተ ገጽታ ያንፀባርቃሉ። ደስተኛነት ከክርስቲያን ባህርይ ጋር ተራማጅነት የለውም የሚለው አባባል በአንዳንዶች ዘንድ አለ፤ ይህ ግን ስህተት ነው። ሰማይ ደስታ ነው። የሰማይን ደስታዎች ሁሉ ለነፍሳችን ብንሰበስብ በቻልነውም መጠን በንግግራችንና በጠባያችን ብንገልጻቸው ደብዛዛና ሐዘንተኛ ከምንሆን ይልቅ ለሰማይ አባታችን የበለጠ ደስ የምናሰኘው እንሆናለን።AHAmh 314.2

    በሐዘንና በችግር ከመተከዝ ይልቅ እያንዳንዱ ሰው ደስተኛ ይሆን ዘንድ ኃላፊነት አለበት። ብዙዎች በዚህ አካሄዳቸው የተንኮታኮቱ ብቻም ሳይሆኑ በታመመው አስተሳሰባቸው ጤናንና ደስታን ሰውተዋል። በዙሪያቸው የማይስማሟቸው ነገሮች አሉ፤ ፊታቸው ሁሌም የተቋጠረ ግንባር ለብሶ ከንግግራቸው በተሻለ ቅሬታቸውን አጉልቶ ያሳያል። እነዚህ የሚያስጨንቁ ስሜቶቻቸው ለጤናቸው እጅግ ጎጅዎች ናቸው፤ የምግብ መፈጨት ሂደትን በማደናቀፍ ከሰውነት ጋር ያለውን ውሕደት ያውካሉ። ሐዘንና ጭንቀት አንድን ጥፋት እንኳ ማረም አይችሉም፤ ትልቅ ጉዳት ያደርሳሉ እንጂ። ነገር ግን ደስታና ተስፋ የሌሎችን መንገድ በብርሃን ትሞላለች፤ “ለሚያገኝዋት ሕይወት ለሥጋቸውም ሁሉ ፈውስ ናትና።” 1Signs of the Times, Feb. 12, 1885.AHAmh 314.3

    ሚስስ ዋይት በመከራዋ ጊዜ ሁሉ ደስተኛ ነበረች*ማስታወሻ፦ በ1867 ኤልደር ጀምስ ዋይት ሽባ ያደረገውን ድንገተኛ የልብ ምት ችግር (Stroke) ምክንያት በአደገኛ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ በኒዮርክ ዳንስቭል(Dansville New York) በሚገኘው “Our Home” ታማሚ ነበር፡፡ የተቋሙ ሃላፊ የነበረው ዶክተር ሃይማኖት የሃዘን ተጽዕኖ እንዳለው ገልፆ በሽተኞቹ በተለያዩ መዝናኛዎች እንዲሳተፉና ደስተኛ እንዲሆኑ ያበረታታ ነበር፡፡ ሚስስ ዋይትም የዳንስ ቡድን አባል እንድትሆንና በዚህ ተግባርም ያሉባትን ሃዘኖች ሁሉ እንድትቀብር ከታሳታፊዎቹ በአንዱ ተጋብዛ ነበር፡፡ ከላይ የተጠቀሰው ለዚያ ለቀረበላት ሃሳብ መልስ የሰጠችበት ነው፡፡ የተከዝሁ ተስፋ የቆረጥሁና የማማርር ሆኜ አይታችሁኝ ታውቃላችሁ? ይህን የሚከለክል እምነት አለኝ። ወደ እንዲህ ዓይነቱ መጨረሻ የሚያደርሰው ትክክለኛውን የክርስቶስን ባህርይና የክርስቲያን አገልግሎት አለማወቅ ነው። ትካዜ፣ ተስፋ መቁረጥና ሐዘን የእውነተኛ ኃይማኖት እጥረት ውጤቶች ናቸው። ክርስቲያን ማለት ክርስቶስን መምሰል ስለሆነ ሐቀኛ ክርስቲያኖች የሱስን ለመምሰል ይጥራሉ። ክርስቶስን መምሰል በሚያስፈልገን በእኛ ውስጥ የእርሱ መመሪያዎች እንደገና ይታዩ ዘንድ ትክክለኛውን የክርስቶስን ሕይወትና ልማድ መረዳት እጅግ አስፈላጊ ነው። AHAmh 314.4

    የከፊል አገልግሎት፣ የዓለም ፍቅር፣ የራስ መውደድና የከንቱ መዝናኛዎች ፍቅር ድንጉጥና ፈሪ አገልጋይ ያደርጋል። ይህ የሱስን ከመከተል ፈጽሞ የራቀ ነው። ልባዊና በፍላጎት ላይ የተመሠረተ ለየሱስ የሚደረግ አገልግሎት አንፀባራቂና አስደሳች እምነትን ይፈጥራል፤ ክርስቶስን በፍጹም ቅርበት የሚከተሉ የሚተክዙ አይደሉም። በክርስቶስ ዘንድ ብርሃን ሠላምና ደስታ ለዘለዓለም አሉ። የሚያስፈልገን የበለጠ ክርስቶሳዊነት - ያነሰ ዓለማዊነት፤ የበዛ ክርስቶስ ያነሰ ራስ-ወዳድነት ነው።2Manuscript 1, 1867.AHAmh 315.1

    እንደ ብርሃን ልጅነታችሁ ተራመዱ፦ ሚዛነ-ቀላልና መናኛዎች ተካዦችና ትዕግስተ-ቢሶች እንድንሆን የእግዚአብሔር ፈቃድ አይደለም። ከአንድ ጫፍ ወደ ሌላ ጫፍ ሰዎችን ማወዛወዝ የሰይጣን የተጠና እቅድ ነው። እንደ ብርሃን ልጅነታችን ፍልቅልቅና ደስተኛ መንፈስ ያለን እንድንሆን እግዚአብሔር ይፈልጋል፤ ውዳሴዎቹን እናቀርብ ዘንድ ከጨለማ ወደ ግሩም ብርሃን የጠራን እርሱ ነውና።3Australasian Union Conference Record, Nov. 1, 1904.AHAmh 315.2

    የልጆችን ፍቅር ማግኘት፦ ወላጆች ሆይ ፈገግ በሉ፤ መምህራን ሆይ ፈገግ በሉ። ልባችሁ አዝኖ ከሆነ ፊታችሁ አያስታውቅበት። አፍቃሪና አመሥጋኝ ከሆነው ልብ የሚወጣው የፀሐይ ብርሃን ፊታችሁን ፈካ ያድርገው። እንደ ብረት ከተገተረው ክብራችሁ ጎንበስ ብላችሁ የልጆችን ፍላጎት መሠረት አድርጋችሁ እራሳችሁን አስተካክሉ፤ እንዲያፈቅሯችሁ አድርጓቸው። ኃይማኖታዊ እውነት በልባቸው ማተም ከፈለጋችሁ በፍቅር አሸንፏቸው።4Fundamentals of Christian Education, p. 68.AHAmh 315.3

    አስደሳች ፊትና ለዛ ያለው ድምፅ ይኑራችሁ፦ ወላጆች ሆይ ደስተኞች፤ ለሰማይ አባታችሁ አመሥጋኞች ታዛዥና ተገዥዎች እንጅ ተራና ዋጋ-ቢሶች አትሁኑ። የሚያበሳጩ ነገሮች በሚገጥሟችሁ ጊዜ ስሜታችሁ ጥሷችሁ ንዴታችሁ ገንፍሎ እንዲወጣ ነፃነት አልተሰጣችሁም። በልጆቻችሁ አስተዳደር ረገድ የሚያሸንፍ ፍቅር ማለት ሁልጊዜ የሚፈስ ጥልቅ ውኃ ማለት ነው። የእግዚአብሔር መንጋ ጠቦቶች ናቸው፤ ታናናሽ ልጆቻችሁን ወደ ክርስቶስ አምጡ። ልጆቻቸው አስደሳች እንዲሆኑ ማስተማር ከፈለጉ ወላጆቸ ኮናኝ በሆነ አኳኋን ፈጽሞ ሊናገሯቸው አይገባም። ፊታችሁ የፈካ እንዲሆን ተማሩ፤ የምትችሉትን ያህል ድምጻችሁን ግሩም ቃና አላብሱት። የእግዚአብሔር መላእክት ሁልጊዜ ከታናናሽ ልጆቻችሁ አጠገብ ናቸው፤ የሻከረው የሚያንቧርቀውና የሚነጫነጨው ድምፃችሁ ለጆሮአቸው የሚሰቀጥጥ ነው።5Manuscript 126, 1897.AHAmh 315.4

    እናት እርካታ የሚታይበት ፈገግተኛና ደስተኛ ጠባይ ማዳበር ይገባታል። በዚህ ረገድ የሚደረግ እያንዳንዱ ጥረት በልጆችዋ የአካል ደህንነትም ሆነ በመልካም ባህርይ ተትረፍርፎ ይመለስላታል። የደስተኛነት ስሜትዋ የቤተሰቧን ደስታ ያፋፋል፤ የራስዋንም ጤንነት በእጅጉ ያሻሽላል።6Ministry of Healing, p. 374.AHAmh 316.1

    ጽልመቱን አንሱ ሥራውን አቅልሉ፦ ነገሮችን በደስታ ብርሃን ተመልከቷቸው፤ ካልተቀጨ በስተቀር የሚሰፋውን፤ ነፍስን የሚሸፍነውን ጥላ ከላያችሁ ግፈፉ። ለሌሎች ርኅራኄ ማሳየትን አዳብሩ። ደስተኛነት ቸርነትና ፍቅር ቤታችሁን ይሙሉት። ይህ ለኃይማኖታዊ ተግባር ያለውን ፍቅር ይጨምራል፤ ትናንሽም ሆኑ ትላልቅ ኃላፊነቶች ለልብ ሳይከብድ ይፈጸማሉ።7Signs of the Times, Sept 1, 1898.AHAmh 316.2

    የማይዋዥቅና የማይለዋወጥ ደስታ የክርስቲያን ፀጋ ነው፦ እውነተኛ ክርስቲያናዊ ክብር እንዲሁም ደስተኛና መልካም ጠባይ ሊኖረን ይችላል። የማይለዋወጥ ደስተኛነት ከክርስቲያን ፀጋዎች አንዱ ነው።8Testimonies for the Church, Vol. 4, p. 62.AHAmh 316.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents