Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የአድቬንቲስት ቤት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ምዕራፍ አርባ አራት—ሕፃናትን መንከባከብ

    ትክክለኛ አመለካከት ለምታጠባ እናት፦ ለሕፃኑ ወደር የማይገኝለት ምግብ ተፈጥሮ የሚያቀርበው ነው። ይህ ምግብ ተገቢ ባልሆነ ምክንያት ሊነፈግ አይገባውም። ለምቾትዋ ወይም ለማህበራዊ ደስታዋ ስትል ልጅዋን ከማጥባት መልካም የሥራ ገበታዋ እራስዋን ነፃ ማድረጓ ለእናት የአረመኔነትዋ መገለጫ ነው። 1Ministry of Healing, p. 383.AHAmh 182.1

    ሕፃን የእናቱን ጡት የሚጠባበት ጊዜ በጣም አስፈላጊው ወቅት ነው። ብዙ እናቶች በሚያጠቡበት ጊዜ በከባድ ሥራ ስለሚጠመዱና ምግብም ስለሚያበስሉ ደማቸው ይሞቃል፤ ትኩሳት ባለው የእናት ጡት ብቻ ሳይሆን በእናቱ ጤናማ ባልሆነ አመጋገብ ምክንያት አካልዋ በሙሉ ወተቱን በሚመርዝ መልኩ ስለሚሞቅ፣ ጡት ያልጣለው ሕፃን ክፉኛ ይጎዳል። ሕፃኑ በእናቱ አዕምሮአዊ ሁኔታም ይጎዳል። ደስታ-ቢስ፣ ቶሎ የምትረበሽ፣ የምትቆጣና ግንፍል ለሚሉት ስሜቶችዋ ቦታ የምትሰጥ ከሆነ ሕፃኑ ከእናቱ የሚያገኘው ምግብ የተቃጠለና የተመረዘ ስለሚሆን ብዙ ጊዜ የአንጀት በሽታ፣ የጡንቻ መኮማተር በአንዳንድ ሁኔታዎችም የመንቀጥቀጥ፣ የመዝለፍለፍና ድንገተኛ ስሜታዊ የመሆን በሽታን ሊያስከትልበት ይችላል።AHAmh 182.2

    የሕፃኑ ባህርይም ከእናቱ ከሚያገኘው ምግብ ሁኔታ አንፃር ከሞላ ጎደል ሊጎዳ ይችላል። በመሆኑም እመጫትዋ የአዕምሮዋን ደስታ ልትጠብቅ፣ መንፈስዋንም ሙሉ በሙሉ ልትቆጣጠር እጅግ አስፈላጊ ነው። እንዲህም ሲሆን የሕፃኑ ምግብ የተበላሸ አይሆንም፤ በሕፃኑ እንክብካቤ ረገድም የተረጋጋና ራስን የገዛ አካሄዷ በልጅዋ ባህርይ አቀራረጽ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያደርጋል። የሚደነግጥና በቀላሉ የሚረበሽ ከሆነ የእናቱ ጥንቁቅና የሰከነ ጠባይ፣ የሚያረጋጋና የሚያስተካክል ተጽዕኖ ይኖረዋል፤ የሕፃኑ ጤናም በእጅጉ ሊሻሻል ይችላል። 2Counsels on Diet and Food, p. 228.AHAmh 182.3

    ሕፃኑ ፀጥታ የሰፈነበትና ቀለል ያለ ሕይወት ያለው ከሆነ ለአካሉና ለአዕምሮው እድገት በጣም ተስማሚ ሁኔታን ይፈጥርለታል። በማንኛውም ጊዜ እመጫትዋ ፀጥታ የተላበሰች፣ የተረጋጋችና እራስዋን የገዛች እንድትሆን ትጣር። 3Ministry of Healing, p. 381.AHAmh 182.4

    ምግብ ለልጆች የሚገባውን ትኩረት አይተካም፦ ሕፃናት ተገቢ ባልሆነ አያያዝ ይጎሳቆላሉ። የብስጭታቸው ምክንያት ከመጠን በላይ መመገባቸው ወይም በሚጎዳ የእናት ባህርይ ምክንያት ሆኖ ሳለ፣ ሲነጫነጩ ዝም እንዲሉ ምግብ ይሰጣቸዋል። ሆዳቸውን በምግብ ስለሚያጨናንቁት ሁኔታውን የበለጠ ያባብሰዋል። AHAmh 182.5

    በተለምዶ ሕፃናት ለሆዳቸው እንዲገዙ ሆነው ስለሚያድጉ የሚኖሩት ለመብላት እንደሆነ ይማራሉ። እናት በሕፃንነታቸው የልጆችዋን ባህርይ በመቅረፅ ረገድ ትልቅ ሥራ ልትሠራ ትችላለች። ፍላጎታቸውን እንዲቆጣጠሩ ልታስተምራቸው ወይም ስግብግብ እንዲሆኑ ልታደርጋቸው ትችላለች። እናት ብዙ ጊዜ በቀን ውስጥ ልታከናውነው የምትፈልገውን ሥራ እቅድ ታወጣለች፤ ልጆችዋ ሲረብሹዋትም ከጥቃቅን እንጉርጉሯቸው ልትመልሳቸው ጊዜ መውሰድ ሲገባት ከክልፍልፍነታቸው እርፍ እንዲሉ ምግብ ትሰጣቸዋለች፤ ለጊዜው መፍትሄ ቢሆንም ቆይቶ ግን ነገሮችን ያባብሳል። በዚያን ጊዜም የማይፈልጉት ነገር ቢኖር መብላት ሆኖ እያለ ሆዳቸው በተጨማሪ ምግብ ይጠቀጠቃል። ፈልገውት የነበረው የእናታቸውን ትንሽ የአብሮነት ጊዜና ተኩረት ነበር። እናት ግን ወርቃማ ጊዜዋን ልጆችዋን በማጫወት ማባከን አትፈልግም። ምን አልባትም ቤትዋን ባማረ ሁኔታ በማስተካከል፣ እንግዶች እንዲያደንቋት በማሰብ ቄንጠኛ በሆነ መንገድ ምግብ በማዘጋጀትና በማቅረብ ጊዜዋን መጨረስ፣ ከልጆችዋ ደስታና ጤና አብል ጣ የምታየው ጉዳይ ሆኖባት ይሆናል ። 4Solemn Appeal, pp. 125, 126.AHAmh 182.6

    ምግብ የተመጣጠነና የሚያስጎመዥ ግን ቀለል ያለ መሆን አለበት፦ የምግብ ዝግጅት የእናትን ሁሉንም ጊዜዋን የማይጨርስ ቀለል ያለ መሆን አለበት። እርግጥ ነው የምግቡ ጠረጴዛ ጤናማ የተመጣጠነና ሊበሉት በሚጋብዝ ምግብ መሞላት አለበት። እናት ሆይ ማንኛውንም ነገር በግድ-የለሽነት ጨማምረሽ የምታቀርቢው ምግብ ለልጆች በቂ ነው ብለሽ እንዳታስቢ። ነገር ግን የተዛባ ፍላጎትን ለማርካት ጤናማ ያልሆኑ ምግቦቸን በማዘጋጀት የሚጠፋው ጊዜ ተቀንሶ ልጆችን ለማሠልጠንና ለማስተማር የበለጠ ሰዓት መውሰድ ተገቢ ነው። 5Christian Temperance and Bible Hygiene, p. 141.AHAmh 183.1

    የሕፃኑን የተሟላ ልብስ ማዘጋጀት፦ የልጅ የልብስ ቁም ሳጥን ሲዘጋጅ፣ ከፋሽንና አድናቆትን ከማትረፍ ይልቅ ከምቾት፣ ሕይወትን ቀላል ከማድረግና ከጤና አኳያ መታየት አለበት። እናት የልጆችዋን ትንንሽ ልብሶች፣ በጌጠኛ ጥልፍ በማሸብረቅ በአላስፈላጊ ሥራ ራስዋን በማድከም የራስዋንም ሆነ የልጆችዋን ጤና ሊጎዱ ከሚችሉ እንግልቶች መጠበቅ አለባት። ደስታ የሚሰጥ እንቅስቃሴና ዕረፍት በሚያስፈልጋት ጊዜ ነርቯንና ዐይንዋን በሚጎዳ ስፌት መጉበጥ የለባትም። የሚጠበቅባትን ኃላፊነት በብቃት መወጣት ትችል ዘንድ ኃይልዋን የመቆጠብ ግዴታዋን ማስተዋል ይኖርባታል። 6Ministry of Healing, pp. 381, 382.AHAmh 183.2

    ንጽህና፣ ሙቀትና ንጹህ አየር መኖሩን አረጋግጡ፦ ልጆች ሙቀት ይፈልጋሉ፤ ሆኖም ከመጠን በላይ በጋሉ ንጹህ አየር በማይዘዋወርባቸው በታፈኑ ክፍሎች በማስቀመጥ ከባድ ስህተት ይሠራል….AHAmh 183.3

    ሕፃኑ አካሉን ከሚያዳክም ወይም ከሚመርዝ ማንኛውም ነገር ነፃ መሆን አለበት። በዙሪያው ያለ ነገር ሁሉ ደስ የሚል፣ የሚማርክና ንፁህ እንዲሆን ከፍ ያለ ጥንቃቄ መውሰድ ተገቢ ነው። ከድንገተኛ ወይም ከፍተኛ የአየር ሙቀት መለዋወጥ፣ ልጆች የመጠበቃቸው አስፈላጊነት እንዳለ ሆኖ ተኝተውም ሆነ ነቅተው፣ በቀንም ሆነ በሌሊት ንጹህና የሚያነቃቃ አየር መተንፈስ እንዲችሉ መደረግ አለበት። 7Id., p. 381.AHAmh 183.4

    በሚታመሙ ጊዜ ልጆችን መንከባከብ፦ ብዙውን ጊዜ የልጆች መታመም ምክንያቱ የአስተዳደር ወይም የ[እን]ክብካቤ ጉድለት ነው። ቋሚ ያልሆነ የአመጋገብ ሥርዓትና በቀዝቃዛ ምሽት የሚሞቅ ልብስ አለማልበስ፤ ደም በጤናማ ሁኔታ እንዲዘዋወር የሚያደርግ በቂ እንቅስቃሴ አለማድረግና ለደም መጥራት የሚያስፈልገውን ንፁህ አየር አለማግኘት የችግሩ መንሥኤ ሊሆኑ ይችላሉ። ወላጆች የህመሙ መንሥኤ ምን እንደሆነ በመመርመር በአፋጣኝ መፍትሔ መፈለግ ይኖርባቸዋል።AHAmh 184.1

    ሁሉም ወላጆች በሽታን ለመከላከል ለማስታመም ብሎም ለመፈወስ እንዴት እንደሚችሉ የማወቅ ችሎታው አላቸው። በተለይም እናት ለሚደጋገሙ ሕመሞች ምን ማድረግ እንዳለባት ማወቅ ግድ ይላታል። የታመመ ልጅን እንዴት መርዳትና መንከባከብ እንዳለባት ትወቅ። ኃ ላፊነቱን ለእንግዳ እጆች አሳልፎ ከመስጠት፣ ለልጅዋ ያላት ፍቅርና መረዳት እነዚህን እርዳታዎች ለመለገስ ብቁ ሊያደርጋት ይገባል። 8Id., p. 385.AHAmh 184.2