Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የአድቬንቲስት ቤት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ክፍል ፲፯—መንፈስን ማደስና መዝናናት

    ምዕራፍ ሰባ ዘጠኝ—መታደስ አስፈላጊ ነው

    መታደስን በተመለከተ የሚቀርቡ ጽንፈ-ኃሳቦች፡- ኃይማኖት አምባ-ገነን ሆኖ በብረት በትር እንደሚገዛቸው የሚሰማቸው ሐሳበ-በሽተኛ ሰዎች አሉ። እነዚህ ሰዎች ሁልጊዜ በችግራቸው የሚያለቃቅሱና እራሳቸው በፈጠሩት ምናባዊ ክፋት የሚያቃስቱ ናቸው። ፍቅር በልባቸው ውስጥ የለም፤ ሁሌም የተጨማደደ ፊት አላቸው። በወጣቶችም ሆነ በማንም ሰው የሚሳቅ የቅን ሳቅ ያቀዘቅዛቸዋል። ሁሉንም ዓይነት መታደስና መጫወት እንደ ኃጢአት ስለሚቆጥሩት፣ አዕምሮ በተደጋጋሚ ወደ ጥብቅ ከባድና አጣብቂኝ ሁኔታ ውስጥ መምጣት አለበት ብለው ያስባሉ። ይህ አንዱ ጽንፍ ነው። ሌሎች ደግሞ ጤናማ ይሆን ዘንድ አእምሮ አዳዲስ መጫዎቻዎችንና ጊዜ ማሳለፊያዎችን በመፈለግ መቦረቅ አለበት ይላሉ። ፈንጠዝያ ሱስ ይሆንባቸውና ያለ እርሱ የማይመቻቸው ይሆናሉ። እነዚህ እውነተኛ ክርስቲያኖች አይደሉም፤ የሁለተኛው ጽንፈ-ሐሳብ አራማጆች ናቸው። የእውነተኛ ክርስትና መርሆዎች ቁመቱና ጥልቀቱ፣ ርዝመቱና ወርዱ ሊለካ የማይችል የደስታ ምንጭ ለሁሉም ሰው የሚከፍቱ ናቸው።1Testimonies for the Church, Vol. 1, p. 565.AHAmh 362.1

    መንፈስን ለማደስና አካልን ለማነቃቃት፡- የአካላዊና አዕምሮአዊ ኃይላቸውን ለእግዚአብሔር ክብር የማዋል ዓላማ አንግበው ንጹህ በሆነ መታደስ መንፈሳቸውን ማደስና አካላቸውን ማነቃቃት የክርስቲያኖች መብትና ግዴታ ነው። የመታደሻ ጊዜዎቻችን ትርጉመ-ቢስ የሆነ ሳቅ የሞላባቸው የመጃጃል መልክ የያዙ መሆን የለባቸውም። አብረውን ያሉትን ሰዎች የሚጠቅሙና ከፍ ከፍ የሚያደርጉ እንዲሆኑ ማድረግ እንችላለን። እኛም ሆንን እነርሱ እንደ ክርስቲያንነታችን የተጣለብንን ኃላፊነት በተሻለ ብቃት እንወጣ ዘንድ የሚያግዙን ልናደርጋቸው እንችላለን።2Health Reformer, July, 1871.AHAmh 362.2

    የዕረፍት ጊዜ ሳይወስዱና ለውጥ ሳያደርጉ ሰንበት ጠባቂ ሕዝቦች ከሚገባው በላይ እንደሚሠፉ በራዕይ አይቻለሁ። መታደስ የጉልበት ሥራ ለሚሠሩ አስፈላጊ ነው። የአዕምሮ ሥራ ለሚሠሩ ደግሞ የበለጠ አስፈላጊ ነው። በኃይማኖታዊ ጉዳዮች ላይ እንኳ ቢሆን አዕምሮን ያለ ዕረፍትና ከሚገባው በላይ ማሠራት ለመዳናችንም ሆነ ለእግዚአብሔር ክብር አስፈላጊ አይደለም።3Testimonies for the Church, Vol. 1, p. 514.AHAmh 362.3

    መታደስን በተመለከተ የቤታችንና የትምህርት-ቤታችን ዙሪያዎች ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ። የቤታችንም ሆነ የትምህርት-ቤታችን ቦታ ስንመርጥ እነዚህን ነገሮች በማሰብ መሆን አለበት። አዕምሮአዊና አካላዊ ደህንነታቸው ከገንዘብ ወይም ከማህበረሰቡ መጠይቅና ልማድ የሚበልጥባቸው እነርሱ የተፈጥሮን ትምህርትና እርስዋ የምትለግሰውን መታደስ ለልጆቻቸው ይምረጡ።4Education, pp. 211, 212.AHAmh 362.4

    ሥራን በጥሞና ለማከናወን መታደስ አስፈላጊ ነው፡- በአካላዊ እንቅስቃሴ የጠፋው ሰዓት የባከነ ጊዜ አይደለም…. የአካል ክፍሎቻችን የየፊናቸውን ሥራ በብቃት ያከናውኑ ዘንድ ተመጣጣኝ የሆነ ለእያንዳንዱ የአካል ክፍል የተገባው የሰውነት እንቅስቃሴ ያስፈልጋቸዋል። የህያው መሣሪያ [የሰውነት] ሌሎች ክፍሎች አርፈው ሳለ ጭንቅላት ብቻውን በሥራ መጠመዱ የአካልና የአዕምሮ ኃይል እጦት ያመጣል። አካል የጤናማነቱን ቃና ይነፈጋል፤ አእምሮ ትኩስነቱንና ኃይሉን ያጣል፤ ውጤቱም ጤናማ ያልሆነ የመንፈስ ሲቃ ይሆናል።5Fundamentals of Christian Education, p. 418.AHAmh 363.1

    የሥራና የመኝታ ሰዓታት ቁጥጥር ላይ ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ ነው። የማረፊያ፣ የመዝናኛና የማሰላሰያ ጊዜ መውሰድ አለብን…. የቁጥብነት መርሆዎች ብዙዎች ከሚያስቡት የበለጠ ሰፊ ወሰን ይሸፍናሉ።6Manuscript 60, 1894.AHAmh 363.2

    ተማሪዎች ዘና ማለት ያስፈልጋቸዋል፡- በጥናት የተጠመዱ ሁሉ የመዝናኛ ጊዜ ያስፈልጋቸዋል። አእምሮ ሁልጊዜ ትኩረት በሚያሻው ሐሳብ ውስጥ የሚሆን ከሆነ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ጭንቅላት እያረጀና እየተዳከመ ይሄዳል። አካልም ሆነ አዕምሮ እንቅስቃሴ ያስፈልጋቸዋል።7Counsels to Teachers, Parents, and Students, p. 333.AHAmh 363.3

    ለመታደስና ለአካል እንቅስቃሴ የሚሰጠው ጊዜ የተለመደውን የትምህርት ቤት የሥራ ሂደት ሊያቋርጠው ይችል ይሆናል፤ ማቋረጡ ግን ለመልካም እንደሆነ ቆይቶ ይታያል። አዕምሮና ሰውነት በመፍታታቱ ምክንያት ራስ-ወዳድነት የሌለበት መንፈስ ማደጉ፣ በጋራ ጥቅምና ጓደኛዊ ዝምድና፣ ተማሪና መምህር መጣመራቸው ጊዜውንና ድካሙን መቶ እጥፍ አድርጎ ይመልሰዋል። ብዙውን ጊዜ ወጣቱን አደጋ ላይ የሚጥለው የታመቀና ዕረፍት-የለሽ ጉልበት የተባረከ መተንፈሻ ቀዳዳ ያገኛል። አዕምሮን በመልካም ነገር መጥመድ ወጣቱን ከክፉ ነገር ከመጠበቅ አኳያ ያለው ጠቀሜታ ቁጥር ስፍር የሌላቸው የህግና የሥነ-ሥርዓት ደንቦች ከሚሰጡት ከለላ የበለጠ ዋጋ አለው።8Education, p. 213.AHAmh 363.4

    የመታደሻ ቀናት የሚያስፈልጋቸው የቢሮ ሠራተኞች፡- የቢሮ ሥራን የኃላፊነት ሸክም የሚሸከሙ ምን ያህል አድካሚ ሥራ እንደሚሠሩ የሚገነዘቡ በጣም ጥቂቶች ናቸው። ቀን በቀን፣ ሣምንት በሣምንት ቢሮ ውስጥ ታቁረው በአዕምሮ ላይ ያላሰለሰ ዝለት በማምጣት አካላቸውን በመጉዳት ሕይወታቸውን የሚመሩበት ኃይላቸው የቀነሰ ይሆናል። እነዚህ ወንድሞች/እህቶች በድንገት የመሰበር አደጋ ውስጥ ናቸው። ዘለዓለማዊ አይደሉም፤ ካልተተኩ በስተቀር ያልቃሉ፤ ይጠፋሉም።AHAmh 363.5

    ወንድሞች ኤ(A) ቢ(B)ና ሲ(C) የከበሩ ሥጦታዎች አሏቸው፤ እራሳቸውን አግልለው በማያቋርጥ ልፋት ውስጥ ሆነው ጤናቸውን ያጡ ዘንድ ልንተዋቸው አይቻለንም.…ከትኩሳትና ከህመም በስተቀር ሌላ ተለዋዋጭ ነገሮች በሕይወታቸው አላዩም። በየጊዜው ለውጥ ያስፈልጋቸው ነበር፤ አብሮነታቸው ከተነፈጋቸው ቤተሰቦቻቸው ጋር ሙሉ ቀን ወስደው መታደስ ነበረባቸው። ሁሉም ሠራተኞች በአንድ ጊዜ ሥራ መልቀቅ አይችሉ ይሆናል። ነገር ግን ተነጋግሮ እቅድ በማውጣት አንድ ወይም ሁለት ሆኖ ለዕረፍት በመውጣትና ሌሎች ቦታውን እንዲተኩት በማድረግ ያልወጡት ደግሞ በተራቸው ሌላ ጊዜ እንዲያርፉ ማመቻቸት ይቻላል። እንደ ኃይማኖታዊ ተግባርም እነዚህ ወንድሞች ኤ ቢ ና ሲ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ጤናቸውን በማጠናከር ባግባቡ የመጠበቅ ኃላፊነት እንደተጣለባቸው አይቻለሁ። እግዚአብሔር አሁን ለእርሱ ሥራ ሰማዕታት እንዲሆኑ አይፈልግም። ይህንን መሥዋዕትነት በመክፈላቸው ሽልማት የላቸውም፤ እግዚአብሔር በሕይወት እንዲኖሩ ይፈልጋልና።9Testimonies for the Church, Vol. 1, pp. 515, 516.AHAmh 363.6

    ጨዋና ትምህርታዊ መታደሻ ፈልጉ፡- ለአዕምሮና ለአካል በጣም ጠቃሚ የሆኑ የመታደሻ ዘዴዎች አሉ። በእውቀት የበሰለና መለየት የሚችል አዕምሮ በርካታ የጊዜ ማሳለፊያ መንገዶችን ከመልካምና አስተማሪ ከሆኑ ምንጮች ያገኛል። የእግዚአብሔርን ተፈጥሮአዊ ሥራዎች እያሰላሰሉ በንጹህ አየር መታደስ ወደር የሌለው ጥቅም አለው።10Id., Vol. 4, p. 653.AHAmh 364.1

    መንፈሳችንን ለማደስና ሰውነታችንን ለማነቃቃት በምንጥርበት ጊዜ ያለንን ኃይል ሁሉ ለመልካም ዓላማ እንድናውለው እግዚአብሔር እንደሚፈልግብን አምናለሁ። ዛሬ እዚህ እንደተሰበሰብን*ማስታወሻ፡- በጎጉዋክ ሃይቅ ባትል ክሪክ ሚችጋን አጠገብ በግንቦት 1870 የመታደሻዎችን ወቅት እያጣጣሙ ለነበሩ ሁለት መቶ ያህል ሰዎች ከተሰጠው መልእክት ከፊሉ የተወሰደ፡፡ ሁሉ በሌላውም ጊዜ ሁሉንም ነገር ለጌታ ክብር ልናደርገው እንችላለን። መታደስ ያለብን የተጣሉብንን ኃላፊነቶች በውጤታማነት ለማካሄድ ብቁ በሚያደርገን አኳኋን ነው። ለሚጎዳኙንም ሁሉ ተጽዕኖአችን የበለጠ ጠቃሚ የሚሆንላቸው ሊሆን ይገባል። በተለይ በእንደዚህ ዓይነት አጋጣሚዎች ደግሞ ለሁሉም መልካም ሊሆን ይገባል። በአስተሳሰብ ተሸለን አካላችን ታድሶ እንደ አዲስ በተሻለ ተስፋና በተሻለ ብርታት ሥራችን ለመሥራት ተዘጋጅተን ወደ ቤታችን እንመለሳለን።11Id., Vol. 2, p. 586.AHAmh 364.2

    የእግዚአብሔር ጥሪ ለእያንዳንዱ ወጣት፡- የእግዚአብሔር ጥሪ ለእያንዳንዱ ወጣት ይመጣል፤ “ልጄ ሆይ ልብህን ስጠኝ በንጽሕና እጠብቃታለሁ ጥማትዋንም በእውነተኛ ደስታ አረካዋለሁ” እርሱ ይጠብቀው ዘንድ ልባቸውን እንዲሰጡት የጠየቃቸው እግዚአብሔር ደስ እያለው የሰጣቸው ክህሎቶችም ብርቱና ጤናማ ሆነው ማየት ስለሚፈልግ ነው። የእግዚአብሔርን የሕይወት ስጦታ ይዘዋል፤ ልብ እንዲመታ የሚያደርግ እርሱ ነው፤ ለእያንዳንዱ የአካል ክፍል ብርታት ይሰጣል። በንጽህና ኃሴት ማድረግ የእግዚአብሔን ሥጦታዎች አያረክስም።12The Youth’s Instructor, Jan. 5, 1887.AHAmh 364.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents