Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የአድቬንቲስት ቤት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ክፍል ፲፮—ቤትና ማህበራዊ ግንኙነቶቹ

    ምዕራፍ ሰባ ሦስት—የማህበራዊ ፍላጎቶቻችን

    እግዚአብሔር ለማህበራዊ ፍላጎቶቻችን የወደፊት ዕቅድ አውጥቷል፡- የተመረጡትን ሕዝቦች ለማስተማር በተደረጉ ቅድመ ዝግጅቶች እንደተረጋገጠው እግዚአብሔርን ማዕከል ያደረገ ሕይወት የሙሉነት ሕይወት ነው። በውስጣችን ያስቀመጠውን እያንዳንዱን ፍላጎት ለማርካት አቅርቦት አለው። ያካፈለንን እያንዳንዱን ክህሎት የማሳደግ ፍላጎት አለው።AHAmh 333.1

    የውበት ደራሲው የሚያምረውን ሁሉ የሚወድ እግዚአብሔር ልጆቹ ለውበት ያላቸውን ጥማት ለማርካት ሁሉን አቀረበ። ርኅራኄን ለማጎልበት ሕይወትን ብሩህና ጣፋጭ ለማድረግ እጅግ የሚረዱትን አጋዥና በቅን መንፈስ የሚደረጉ ጉድኝቶችን በመፍጠር ለማህበራዊ ፍላጎቶቻቸው የሚያስፈልጋቸውን አቅርቧል።1Education p. 41AHAmh 333.2

    የማህበራዊ ጉድኝት ተጽዕኖ፡- እያንዳንዱ ሰው ጓደኞችን ይገናኛል ወይም ይመሠርታቸዋል። ጓደኞች ለእርስ በእርሳቸው የሚያሳርፉት የመልካም ወይም የክፋት ተጽዕኖ ክብደት በጓደኝነቱ ጥንካሬ የሚወሰን ነው። ሁሉም ሰው ጓደኞች አሉት፤ በእነዚህ ጉድኝቶች ተጽዕኖ ያደርጋል፤ ይደረግበታልም።2Testimonies for the Church, Vol. 4, p. 587.AHAmh 333.3

    የጓደኝነት ተጽዕኖን በተመለከተ የእግዚአብሔር ቃል ጥልቅና ለየት ያለ ትኩረት ይሰጣል፤ ይህም ትኩረት በዕድሜ በጎለመሱ ወንዶችና ሴቶች የሚደረጉ ግንኙነቶችን ጭምር ያጠቃልላል ። የጉድኝት ተጽዕኖ እያደጉ ባሉ ልጆችና ወጣቶች አዕምሮና ባህርይ ላይ ምን ያህል ኃይል ያሳርፋል! የሚመሠረቱት ጓደኝነት በሥራ ላይ የሚያውሏቸው መርሆዎችና የሚገነቡአቸው ልማዶች የአሁኑ ጠቃሚነታቸውን እንዲሁም የወደፊት ዕጣ ፈንታቸውን ጥያቄ የሚመልሱ ናቸው….AHAmh 333.4

    ወጣቶች፣ ጓደኞች እንደሚኖራቸው ተጽዕኖአቸውም እንደሚደርሳቸው ምንም ጥርጥር የለውም። የአንደኛው ልብ ለሌላኛው ልብ መልስ መስጠት እስኪችል ድረስ ነፍሳትን በጥብቅ ቁርኝት የሚያጣብቁ ምሥጢራዊ ትስስሮች አሉ። አንዱ የሌላውን ሐሳቦች ስሜቶችና መንፈሱን ጭምር ይጋራል። ይህ ጉድኝት በረከትም መርገምም ሊሆን ይችላል። አንዱ የሌላውን እውቀት ፍላጎትና ጠባይ በማሻሻል ሊበረታቱና ሊተጋገዙ ይችላሉ። በአንፃሩ ደግሞ ግድ-የለሽና እምነተ-ቢስ በመሆን የሌሎች ሥነምግባር እንዲበላሽ ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ።3Counsels to Teachers, Parents, and Students, p. 220.AHAmh 333.5

    “ጓደኛህን አሳየኝና ባህርይህን እነግርሃለሁ” የተባለው እውነት ነው። በሚመርጧቸው ጓደኝነቶች ባህርያቸውና ስማቸው ምን ያህል እንደሚጎዳ ወጣቶች በቅጡ አልተገነዘቡትም። አንድ ሰው ጓደኝነት መመሥረት የሚፈልገው ምርጫዎቹ፣ ልማዶቹና እንቅስቃሴዎቹ ከራሱ ከሚመሳሰል ሰው ጋር ነው። ከመልካሞቹና ከብልሆቹ ይልቅ የጭፍኖችንና የክፉዎችን አብሮነት የሚመርጥ እርሱ የራሱ ባህርይ ግድፈት እንዳለበት ያሳያል። መጀመሪያ ላይ ምርጫዎቹና ልማዶቹ ለጓደኝነት ከሚመርጣቸው ሰዎች ምርጫና ልማድ የማይመሳሰል ሊሆን ይችላል። ሆኖም ከዚህ መደብ ጋር እየተቀላቀለ ሲሄድ አስተሳሰቡና ስሜቱ ይቀየራል። ትክክለኛ መርሆዎቹን በመሰዋት በቅጡ ሳያስተውለው ሊያመልጠው በማይችል ሁኔታ ጓደኞቹ ወዳሉበት ደረጃ ይዘቅጣል። አንድ ጅረት የሚያልፍበትን አፈር መልክ እንደሚጋራ ሁሉ የወጣቶች መመሪያዎችና ልማዶችም ከሚቀላቀሏቸው ጓደኞቻቸው ባህርያት ጋር መቀየጡ የሁል ጊዜ ሐቅ ነው።4Id., p. 221.AHAmh 333.6

    ተፈጥሮአዊ ዝንባሌዎች ቁልቁል የሚያወርዱ ናቸው፡- ወጣቶች ከንጹሆች፣ ከአሳቢዎችና ተወዳጅ ባህርይ ካላቸው ጋር ጓደኝነት እንዲመሠርቱ ቢበረታቱ ውጤቱ እጅግ ጠቃሚና የሚስማማ ነው። ጌታን ከሚፈሩ ጋር ለመወዳጀት ከተወሰነ ተጽዕኖአቸው ወደ እውነት ወደ ሥራና ወደ ቅድስና የሚመራ ይሆናል። የእውነተኛ ክርስቲያን ሕይወት የመልካም ነገር ኃይለኛ ተጽዕኖ ነው። ነገር ግን በተቃራኒው መጥፎ መመሪያዎችና ተግባራት እንዲሁም ጥያቄ ውስጥ የሚገቡ ግብረ-ገብነቶች ካሏቸው ጋር ጓደኝነት የሚመሠርቱ ሳይውሉ ሳያድሩ እነርሱም በዚያው መንገድ መራመድ ይጀምራሉ። የተፈጥሮአዊ ልብ ዝንባሌዎች ቁልቁል የሚያወርዱ ናቸው። ከሚጠራጠር ሰው ጋር ጓደኝነት የጀመረ እራሱ ተጠራጣሪ ይሆናል። የሚናቅ ባህርይ ካላቸው ጋር የሚቀላቀል እራሱም ብልሹ እንደሚሆን ቅንጣት ታክል ጥርጥር የለም። በከሃዲዎች ሸንጎ መመላለስ በኃጢአተኞች መንገድ የመቆምና በናቂዎች ወንበር የመቀመጥ የመጀመሪያው እርምጃ ነው።5Testimonies for the Church, Vol. 4, p. 587.AHAmh 334.1

    ጓደኝነት የመመሥረት ምኞትና የደስታ ፍቅር የዓለማዊ ወጣቶችን ስሜት የተቆጣጠረ ጠንካራ ፍላጎት ሆኗል። ለመልበስ ለመጎብኘት ሆድንና ፍላጎትን ለማርካት በማይረባ የማህበራዊ ሕይወት ውስጥ መመላለስ የመኖር ዋና ትርጉም እንደሆነ ተቆጥሯል፤ በብቸኝነት ከተተዉ ደስተኞች አይሆኑም። ዋና ምኞታቸው አድናቆትን ማትረፍ መሸንገልና በማህበረሰቡ ውስጥ ልዩ ስሜት መፍጠር መቻል ነው። ይህ ምኞታቸው ካልተሟላ ሕይወት ሊሸከሙት የማይችሉት ጭነት ይሆንባቸዋል።6Id., Vol. 5, p. 112.AHAmh 334.2

    ሕብረት የሚወድዱ ብዙውን ጊዜ ይህንን ጠባያቸውን ሲከተሉ መጨረሻ የሚቆጣጠራቸው ባህርይ ይሆንባቸዋል…. መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ ወይም ሰማያዊ ነገሮችን ለማሰላሰል ትዕግሥት የላቸውም። የሚያስፈነድቃቸው ነገር ከሌለ በስተቀር ብስጩዎች ናቸው። ደስተኛ የመሆን ኃይል በውስጣቸው የለም፤ ደስታቸው የሚወሰነውም እንደ እነርሱ ከማያስቡና ግድ-የለሾች ጋር በሚመሠርቱት ጓደኝነት ነው። ለከበረ ዓላማ ሊጠቀሙበት የሚችሉትን ጉልበት ለከንቱነትና ለአዕምሮ ብኩንነት አሳልፈው ይሰጣሉ።7Id., Vol. 4, p. 624.AHAmh 334.3

    የክርስቲያናዊ ማህበራዊነት በረከቶች፡- ክርስቲያናዊ ማህበራዊነት በእግዚአብሔር ህዘብ ዘንድ ገና በእንጭጩ ያለ ጉዳይ ነው… እራሳቸውን በራሳቸው የለጎሙ በመልካም አብሮነት ሌሎችን ለመባረክ ፍቃደኞች ያልሆኑ ብዙ በረከቶችን ያጣሉ። በጋራ ቅርርብ አዕምሮዎች ይቦረሻሉ፤ ይጠራሉ፤ በማህበራዊ ቅልቅሎች ትውውቆች ይመሠረታሉ፤ ጓደኝነቶች ይፈጠራሉ። የእነዚህ ግንኙነቶች ውጤትደግሞ ልብን አንድ የሚያደርግና የፍቅር ከባቢ አየርን የሚፈጥር ሰማይ ይመለከተው ዘንድ የሚያስደስት ነው።AHAmh 335.1

    በተለይ ደግሞ የክርስቶስን ፍቅር የቀመሱ የማህበራዊ ግኙነት ኃይላቸውን ማጎልበት አለባቸው፤ ነፍሳትን ለአዳኙ ሊማርኩ ይችላሉና። በመሆኑም ቅዱስና ጣፋጭ ከመሆኑ የተነሣ እንደ ብርቅዬ ቅርስ ተቆልፎበት ለብቻቸው ሊደሰቱበት የተገባ ይመስል ክርስቶስ በልባቸው ተደብቆ መቀመጥ የለበትም። የክርስቶስ ፍቅር የሚገለጸው ለራሳቸው ፍላጎት ለተገዙት ብቻም መሆን የለበትም። እነዚህ ሰዎች እነርሱ ለራሳቸው የሚመርጧቸው ዓይነት ጓደኞች ባይሆኑም እንኳን አብሮነት በእጅጉ ለሚያስፈልጋቻው ሁሉ ቸርነት የተላበሰ ፍላጎትና ማህራዊ ባህርይ ያሳዩ ዘንድ ተማሪዎች ክርስቶስን መምሰል ሊማሩ ይገባቸዋል። በሁሉም ጊዜና ቦታ ክርስቶስ ለሰው ዘር አፍቃሪ ዝንባሌውን በማሳየት በዙሪያው ላሉ ሁሉ በደስታ የተሞላ ርኅራኄ አንፀባርቋል።8Id., Vol. 6, pp. 172, 173.AHAmh 335.2