Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የአድቬንቲስት ቤት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ምዕራፍ ሰማንያ ስድስት—ሕይወት በኤደን ቤት

    ኤደን ትታደሳለች፡- አዳም ከአስደሳች ጎዳናዎችዋ ወጥቶ ከተጣለ በኋላ ለብዙ ጊዜ ኤደን-ገነት በምድር ቆይታለች። ተመልሶ እንዳይገባባት በሮችዋ በመላእክት ሲጠበቅ የነበረ ቢሆንም የወደቀው ዘር የፃድቃንን ቤት ከሩቅ እንዲመለከታት ተፈቅዶለት ነበር። በኪሩቤል በምትጠበቀው የገነት ደጃፍ መለኮታዊ ክብር ይገለጽ ነበር። አዳምና ልጆቹም እግዚአብሔርን ለማምለክ ወደዚህ ሥፍራ ይመጡ ነበር። በአመፃቸው ከኤደን ገነት እንዲባረሩ ምክንያት የሆነውን የሕጉን ታዛዥነታቸውን ቃልኪዳን እዚህ ሥፍራ ያድሱ ነበር። የጥፋት ማዕበል ምድርን በሞላት ጊዜ፣ የሰዎችም ርኩሰት በውኃ ሙላት እንዲጠፉ ባደረገ ጊዜ፣ በምድር የተከላት እጅ ኤደንን ከምድር ወሰዳት። ነገር ግን በመጨረሻው እድሳት “አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር” ሲመጡ ኤደን መጀመሪያ ከነበረችው በበለጠ አም ራና ተጊጣ ትታደ ሳለች።AHAmh 395.1

    ከዚያም የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት የጠበቁ ሁሉ በማይደክም ብርታት በሕይወት ዛፍ ሥር ያርፋሉ። መጨረሻ በሌላቸውም ዘመናት ኃጢአት ያላወቃቸው ዓለማት በዚያች የደስታ ገነት በኃጢአት ርግመት ያልተነካውን ነቁጥ የሌለውን የእግዚአብሔርን የእጅ ሥራ ምሣሌ ያያሉ። ይህ ኤደን ሰው የፈጣሪን ግሩም ዕቅድ ቢያሳካ ኖሮ ምድር ሁሉ ትሆን የነበረውን ናሙና ነው።1Patriarchs and Prophets, p. 62.AHAmh 395.2

    ታላቁ የማዳን ዕቅድ ዓለም እንደገና ሙሉ በሙሉ የእግዚአብሔርን ሞገስ ያገኝ ዘንድ የሚያደርግ ነው። በኃጢአት ምክንያት ጠፍቶ የነበረው ይታደሳል። ሰው ብቻ ሳይሆን የታዛዦች የዘለዓለም መኖሪያ ትሆን ዘንድ ምድር ጭምር ትዋጃለች። ለስድስት ሽህ ዓመታት ሰይጣን ምድርን የራሱ ለማድረግ ሲታገል ኖሯል፤ አሁን እግዚአብሔር ለፍጥረት የነበረው የፊተኛው ዕቅድ ተግባራዊ ይሆናል። “የልዑል አምላክ ቅዱሳን መንግሥቱን ይወስዳሉ፤ በመንግሥቱም ለዘለዓለም ይነግሳሉ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም።” 2d., p. 342.AHAmh 395.3

    “የተገዙት የእግዚአብሔር ንብረቶች መዋጀት”፡- ምድር የተዋጁት የዘለዓለም መኖሪያ ስትሆን እግዚአብሔር ለምድር መፈጠር ምክንያት የነበረው የመጀመሪያው ዕቅድ ይፈጸማል። “ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ በእርስዋም ለዘለዓለም ይኖራሉ።” የሚንቀለቀለው ሰይፍ የመጀመሪያዎቹ ጥንዶች ወደ ኤደን እንዳይገቡ ከከለከለበት ጊዜ አንሥቶ ቅዱሳን ሲመኙት የኖሩት ሰዓት፣ “የተገዙት የእግዚአብሔር ንብረቶች መዋጀት” ጊዜ አሁን መጥቷል። በመንግሥትነት ለሰው ልጅ የተሰጠችው ኤደን በክህደቱ ለሰይጣን አሳልፎ ሰጥቷት እስካሁን በኃይለኛው ጠላት ተይዛ ኖራ በታላቁ የማዳን ዕቅድ ተመልሳለች።3Signs of the Times, Dec,. 29, 1909.AHAmh 395.4

    በመጀመሪያው አዳም የታጣው በሁለተኛው [አዳም] ተመልሶ ይታደሳል። ነቢዩም አለ፡- “አንተም የመንጋ ግምብ የጽዮን ልጅ አምባ ወዳንት ትመጣለች ትደርስማለች የቀደመችው ግዛት።” ጳውሎስም ስለ “የተገዛው የእግዚአብሔር ንብረት መዋጀት” ያወሳል። የቅዱስና ደስተኛ ፍጡራን መኖሪያ ትሆን ዘንድ እግዚአብሔር ምድርን ፈጠራት። በእግዚአብሔር ኃይል ስትታደስና ከኃጢአትና ከሐዘን ነፃ ስትሆን የተዋጁት የዘለዓለም መኖሪያ ስትሆን ያኔ ያ ዕቅዱ ይፈጸማል።4Review and Herald, Oct, 22, 1908.AHAmh 396.1

    አዳም ወደ ኤደን ቤቱ ይመለሳል፡- ከኤደን ከተባረረ በኋላ የአዳም ሕይወት በሐዘን የተሞላ ነበር። እያንዳንዱ የሚረግፍ ቅጠል፤ እያንዳንዱ የመስዋዕት ተጠቂ [እንስሳ]፤ በምድር መልካም ገጽታ ላይ የወረደው እያንዳንዱ ዋግ፤ በሰው ንጽህና ላይ የመጣው እያንዳንዱ እንከን፤ አዳም የሠራውን ኃጢአት ሁልጊዜ አዲስ አድርጎ ያስታውሰው ነበር። ኃጢአት ሲበዛ ሲያይ ማስጠንቀቂያ ሲሰነዝር የዚህ ሁሉ ችግር መንስኤ እራሱ እንደሆነ ወቀሳ ሲወርድበት የፀፀት ስቃዩ እጅግ ከባድ ነበር። ትዕግሥት በተሞላበት ደግነት የመተላለፍን ቅጣት ለአንድ ሺህ ዓመት የተቃረበ ዘመን ተሸከመ። በእምነት ኃጢአቱን ተናዘዘ፤ ቃል-ኪዳን በተገባለት አዳኝ ሥጦታ አምኖና ከጥፋቱ ተመልሶ ከሞት እንደሚነሣ ተስፋ አድርጎ አንቀላፋ። የእግዚአብሔር ልጅ የሰውን ግድፈትና ውድቀት አስወገደ። ስለዚህ አሁን በመዋጀት ሥራ ምክንያት አዳም ወደ ቀድሞው ግዛቱ ይመለሳል።AHAmh 396.2

    በደስታ ስሜት ተውጦ በአንድ ወቅት የተድላው ምንጭ የነበሩትን ዛፎች ይመለከታቸዋል -በንጽህናውና በደስታው ዘመን ፍሬ ሲለቅምባቸው የነበሩትን ዛፎች ራሳቸውን ያገኛቸዋል። የራሱ እጆች ያሰለጠናቸውን የወይን ግንዶች ሲንከባከባቸው የነበሩትን አበቦች ያያቸዋል። የክስተቱን እውንነት አእምሮው ያስተውላል። እርሱ ከመባረሩ በፊት ከነበረችው በላይ አምራና ደምቃ የሚያያት የቀድሞዋ ኤድን እንደሆነች ይገባዋል። አዳኙ ወደ የሕይወት ዛፍ ይመራውና ከፍሬዋ ቀጥፎ ይበላ ዘንድ ይሰጠዋል። በዙሪያውም ሲመለከት የተዋጁት ቤተሰቦቹ በእግዚአብሔር ገነት ቁመው ያያቸዋል። ከዚያም የሚያብረቀርቀውን ዘውዱን አውርዶ በየሱስ እግር ሥር ያኖራል፤ በየሱስ ደረት ላይም ወድቆ አዳኙን ያቅፈዋል። በገናውንም ሲጫወት የሰማይ ጣሪያ በድል መዝሙር ማሚቶ ያስገመግማል። “ለታረደው በግ እንደገናም ለሚኖረው ይገባዋል ይገባዋል ይገባዋል” እያሉ የአዳም ቤተሰቦች ዘውዳቸውን አንስተው በአዳኙ እግር ሥር በማኖር ለአምልኮ በፊቱ ይሰግዳሉ።AHAmh 396.3

    አዳም በወደቀ ጊዜ ያለቀሱ፣ በስሙ ያመኑ ሁሉ ይድኑ ዘንድ መቃብር ከፍቶ ከሞት በመነሳት ወደ ሰማይ ሲያርግ የፈነጠዙት መላእክት ይህንን ቅልቅል በዓይናቸው ያዩታል። አሁን የማዳን ሥራ ሲፈጸም ያያሉ፤ በሕብረትም የምሥጋና መዝሙር ያሰማሉ።5Great Controversy, pp. 647, 648.AHAmh 397.1

    ለምድር የእምነት መንገደኞች እልፍኞች ተዘጋጅተዋል፡- የወደፊቱ ውርስ ከሚገባው በላይ ቁሳዊ ሆኖ እንዳይታይ በመስጋት የራሳችን ቤት እንደሆነ አድርገን እንድንናፍቀው ከሚያደርጉን እውነታዎች ብዙዎች ሸሽተዋል። በአባቱ ቤት እልፍኞችን ሊያዘጋጅላቸው እንደሄደ ደቀ-መዛሙርቱ እርግጠኞች እንዲሆኑ ክርስቶስ ነግሯቸዋል። የእግዚአብሔርን ቃል አስተምህሮት የሚቀበሉ ሁሉ በሰማይ ስላለው ቤት ሙሉ በሙሉ እውቀት የሌላቸው አይሆኑም… ፃድቃን የሚወርሱትን ሽልማት የሰው ቋንቋ ይገልጸው ዘንድ ይሳነዋል። የሚያዩት ብቻ የሚያስተውሉት ይሆናል። ይህ ውስን የሆነ አዕምሮ የእግዚአብሔርን ገነት ክብርና ግርማ ሞገስ ይረዳው ዘንድ አይችልም።AHAmh 397.2

    መጽሐፍ ቅዱስ የዳኑት ውርስ አገር ተብሎ ይጠራዋል። በዚያ ቦታ ሰማያዊው እረኛ መንጋውን ሕያው ምንጮች ወዳሉበት ይመራቸዋል። የሕይወት ዛፍ በየወሩ ፍሬ ትሰጣለች፤ ቅጠሎችዋም ለአሕዛብ አገልግሎት ይውላሉ። ሳያቋርጡ የሚፈሱ፣ እንደ መስታወት ድንጋይ ኩልል ጅረቶች፣ ባጠገባቸው ቅጠላቸውን የሚያውለበልቡ፣ ጥላቸውን ለዳኑት ባዘጋጀው መንገድ ላይ የሚያሳርፉ ዛፎችም አሉ። ወደ ውብ ኮረብታማ ሥፍራዎች የሚለወጡ የተነጣጠሉ ሜዳዎች አሉበት፤ የእግዚአብሔር ተራራዎችም ግዙፍ ቁንደዶአቸውን አምጥቀው ገዝፈው ይታያሉ። በነዚያ ፀጥታ በሰፈነባቸው ሜዳዎች በሕያው ምንጮች አፋፍ ለረዥም ጊዜ ተጓዥና ተቅበዝባዥ የነበሩት የእግዚአብሔር ሕዝቦች ቤታቸውን ያገኛሉ።6Review and Herald, Oct. 22, 1908.AHAmh 397.3

    ለምድር የእምነት ተጓዦች ቤቶች አሉ። ከክብር ዘውዶችና ከድል ዘንባባዎች ጋር ለፃድቃን ልብሶች በዚያ አሉ። አሁን ግራ የሚያጋቡን የእግዚአብሔር ሥጦታዎች በሚመጣው ዓለም ቁልጭ ይሉልናል። የፀጋ ምሥጢራት ሁሉ ይገለጹልናል። ውስን አዕምሮአችን፣ ድንግርግርና ሳይፈጸሙ የቀሩ የሚመስሉ ተስፋዎችን ብቻ ያስተዋለበትን ያህል ያኔ እንከን የለሽና እጅግ ውብ መስማማትን እናያለን። እጅግ ፈታኝ የመሰሉትን ገጠመኞች በዘለዓለማዊ ፍቅር እንዳቀናጃቸው እናውቃለን። ሁሉም ነገር ለበጎ ይሆንልን ዘንድ በለሰለሰ ፍቅሩ እንደሚንከባከበን ሲገባን ያኔ ሊነገር በማይችል በምልዓተ-ክብር በደስታ እንፈነጫለን….AHAmh 397.4

    ወደ ቤቱ እንሄድ ዘንድ ግድ ይለናል። እስከሞት ድረስ የወደደን እርሱ ከተማ ሠርቶልናል። አዲሲትዋ ኢየሩሳሌም የማረፊያችን ቦታ ናት። በእግዚአብሔር ከተማ ምንም ዓይነት ሐዘን የለም፤ የሰቆቃ ድምፅ የለም፤ የተደቆሱ ተስፋዎችና የተቀበሩ ፍላጎቶች ሙሾ የለም፤ ከአሁን በኋላ ፈጽሞ የለም። ብዙም ሳንቆይ የጭቆና ልብሶች ተለውጠው በሠርጉ ልብስ ይተካሉ። በቅርቡ የንጉሣችንን ሥርዓተዘውድ እናያለን። ሕይወታቸው በክርስቶስ የተሸፈነላቸው በምድር መልካሙን የእምነት ተጋድሎ የተጋደሉ እነርሱ በእግዚአብሔር ከተማ በመድኃኒታቸው ክብር ያንፀባርቃሉ።7Testimonies for the Church, Vol. 9, pp. 286, 287.AHAmh 397.5

    የተዋጁት ልዩ ጥቅም፡- ሰማይ መልካም ሥፍራ ነው። እዚያ ለመሆንና ወደርሱ የከበረ አምሣልነት በመለወጥ ሕይወቱን የሰጠኝን ተወዳጁን የሱስን ለማየት እናፍቃለሁ። ኦ የሚመጣውን የብርሃን ዓለም ግርማ ሞገስ ቋንቋ እንዴት ይገልፀዋል! የእግዚአብሔር ከተማ ውስጥ ከሚገኙት ሕያው ምንጮች ለመጠጣት ተጠምቻለሁ። AHAmh 398.1

    የሌሎች ዓለማት እይታ እንዲኖረኝ ጌታ አድርጓል። ክንፎች ተሰጥተውኝ አንድ መላክ ከከተማዋ ወደ ከበረና በብርሃን የተሞላ ቦታ ወሰደኝ። የዚያ ቦታ ሣር ሁሌም አረንጓዴ ነበረ፤ ወፎችም ጣፋጭ መዝሙር ያዜሙ ነበር። ነዋሪዎቹ የተለያየ መጠን ያላቸው ነበሩ፡ የከበሩ ግርማ ሞገስ ያላቸውና ውብ ነበሩ። የየሱስን አምሣል የያዙ ፊታቸው በተቀደሰ ደስታ የሚፈካ በቦታው ነፃነትና ፍጹም ተድላ ሐሴት የሚያደርጉ ነበሩ። በምድር ከሚኖሩት በልጠው እጅግ የተዋቡ ለምን እንደሆኑ አንደኛውን ጠየቅሁት። መልሱም፡- “እኛ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት በፍጹም መታዘዝ እንከተላለን፤ በምድር እንዳሉት በአመጽ የወደቅን አይደለንም” የሚል ነበር…. እዚያ ሥፍራ እኖር ዘንድ እንዲተወኝ የወሰደኝን መልአክ ለመንኩት። ወደዚህ ጨለማ ዓለም እንደገና እመጣ ዘንድ ማሰብ አቃተኝ፤ መልአኩም “ተመልሰሽ መሄድ አለብሽ፤ ታማኝ ከሆንሽ ከ144 ሺዎቹ ጋር ሌሎችን ዓለማት የመጎብኘትና የእግዚአብሔርን የእጅ ሥራዎች የማየት ዕድል ይኖርሻል” አለኝ።8Early Writings, pp. 39, 40.AHAmh 398.2

    የሰማይና የምድር ጥምር ቤተሰብ፡- እዚያ የዳኑት “ያውቃሉ እነርሱ ደግሞ እንደታወቁት” እግዚአብሔር እራሱ የተከለው በነፍስ ውስጥ ያለው ፍቅርና ርኅራኄ እዚያ ፍጹም እውነተኛና ጣፋጭ ልምምድ ያገኛል። ከቅዱስ ፍጡራን ጋር ያለው አብሮነት፤ ልብሳቸውን በበጉ ደም አጥበው ነጭ ካደረጉ፤ ለዘመናት ከነበሩ ታማኞችና ከተባረኩ መላእክት ጋር ያለው ማህበራዊ ኑሮ “የሰማይና የምድር ጥምር ቤተሰብ”ን ሁሉ የሚያቆራኘው ቅዱስ ትስስር…. እነዚህ ሁሉ የተዋጁትን ደስታ ለመጨመር የሚያግዙ ናቸው።9Great Controversy, p. 677.AHAmh 398.3

    የዳኑት ሕዝቦች ከሰማይ ሕግ ሌላ የሚያውቁት ሕግ አይኖርም። ሁሉም አንድ ደስተኛ ቤተሰብ ይሆናሉ። የምሥጋናና የውዳሴን ልብስ የለበሱ በዚያ ሥፍራ የማለዳ አጥቢያ ከዋከብት በአንድነት ይዘምራሉ፤ የእግዚአብሔር ልጆችም በደስታ ይጮሃሉ፤ አብና ወልድም በአንድ ላይ “ኃጢአት ከእንግዲህ ወዲህ የለም ሞትም ከእንግዲህ አይሆንም” በማለት ያውጃሉ።10Prophets and Kings, pp. 732, 733.AHAmh 398.4

    ከሰማያዊ የደስታ ትዕይንት [የክርስቶስ እርገት] ወደ ምድር ተመልሰው ያስተጋቡት የክርስቶስ የራሱ ቃላት እንዲህ ይላሉ “እወጣለሁ ወዳ አባቴ አባታችሁም። ወደ አምላኬ አምላካችሁም።” የሰማይ ቤተሰብና የምድር ቤተሰብ አንድ ናቸው። ጌታችን ለእኛ አረገ ለእኛም ይኖራል። “ወደ እግዚአብሔር በእርሱ የሚመጡትን ፈጽሞ ያድን ዘንድ። ሁልጊዜ ሕያው ነውና። ፀሎት ስለራሳቸው ያሳርግ ዘንድ።” 11Desire of Ages, p. 835.AHAmh 399.1

    ቢዘገይም እንኳ ተስፋው እርግጥ ነው፡- የአዳኛችንን መመለስ ለረዥም ጊዜ ጠብቀናል፤ ነገር ግን ተስፋው እርግጥ ነው። በቅርቡ ቃል በተገባልን ቤት እንሆናለን። እዚያ ከእግዚአብሔር ፀባኦት ከሚወጣው የሕይወት ጅረት አጠገብ የሱስ እየመራን ሳለ በምድር ላይ ባህርያችንን ወደ ፍጽምና ለማምጣት ይሰጠን ስለነበረው ምሥጢራዊ ምሪት ይገልጽልናል። እዚያ የታደሰችውን የኤደንን ውበት ባልደበዘዘ ዕይታ እንመለከታለን። በራሳችን ላይ የጫነውን ዘውድ አውርደን በአዳኙ እግር ሥር በማስቀመጥና በገናችንን አንሥተን በመደርደር በዙፋን ለተቀመጠው ሰማይን ሁሉ በምሥጋና እንሞ ላለን።12Testimonies for the Church, Vol. 8, p. 254.AHAmh 399.2

    በዚህ ዓለማዊ ቤታችን ያለው ውብ ነገር ሁሉ የብርጭቆ ወንዙንና አረንጓዴ መስኩን፤ የሚወዛወዙትን ዛፎችና የሕይወት ምንጮች አንፀባራቂዋን ከተማና ነጭ የለበሱ መዘምራኖችዋን - ማንም ሰዓሊ ሊስለው የሟች ምላስ ሊገልጸው የማይችለውን ሰማያዊ ቤታችንን ያስታውሰን። “ዐይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰው ልብም ያልታሰበ እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው ነው።” 13Review and Herald, July 11, 1882.AHAmh 399.3