Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የአድቬንቲስት ቤት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ክፍል ፲፭—የቤተሰብን ሕይወት የሚያፈኩ ፀጋዎች

    ምዕራፍ ስድሳ ዘጠኝ—ደግነትና ቸርነት

    ደግነትና ቸርነት የሕይወትን መከራ በግማሽ ይቀንሰዋል፦ “እርስ በእርሳችሁ ተዋደዱ” የሚለው ትዕዛዝ የሚያሰርጸው መርህ የቤት ውስጥ ደስታ መሠረት ነው። ክርሰቲያናዊ ደግነት በእያንዳንዱ ቤት ውስጥ መንገስ አለበት። ብዙ ዋጋ ሳይከፈል የሚገኝ ነው፤ ሆኖም የእርሱ መገኘት ግትርና ሸካራ ይሆን የነበረውን ተፈጥሮ የማለስለስ ኃይል አለው። ወጥነት ያለው በጎነት ማጎልበት ለራሳችን እንዲደረግልን የምንፈልገውን ለሌሎች የማድረግ ፈቃደኝነት የሕይወትን መቅሰፍቶች በግማሽ ይቀንሳቸዋል።1Signs of the Times, Sept. 9, 1886.AHAmh 307.1

    ደግነት ከቤት ይጀምራል፦ ልጆቻችን ቸርነት ደግነትና ፍቅር እንዲለማመዱ ከፈለግን እኛ ራሳችን ምሣሌዎች ልንሆንላቸው ይገባል።2.Signs of the Times, May 25, 1882.AHAmh 307.2

    በትንንሽ ነገሮች ያለው ደግነት በወላጆች የእርስ በእርስ ግንኙነት መንፀባረቅ አለበት። አድልኦ የሌለበት ቸርነት የቤቱ ሕግ ይሁን፤ ባለጌ ንግግር መነገሩ ይቁም፤ መራራ ቃላትም እንዲሁ።3Good Health, January, 1880.AHAmh 307.3

    ሁሉም ሰው ደስተኛ ፊት ለስላሳ ድምጽና ትሁት ባህርይ ሊኖረው ይችላል፤ እነዚህ የኃይል መሠረቶች ናቸው። በሚታይ ፍልቅልቅና ደስተኛ በሆነ አኳኋን ልጆች ይሳባሉ። ቸርነትና ደግነት አሳዩአቸው፤ ያዩዋቸውን ባህርያት ለእናንተና ለእርስ በእርሳቸው ያንጸባርቃሉ።4.Education, p. 240.AHAmh 307.4

    ደግነታችሁና ራሳችሁን መግዛታችሁ በወሬ ከሚቀረው ንግግራችሁ ይልቅ ከፍተኛ ተጽዕኖ አለው።5Review and Herald, June 13, 1882.AHAmh 307.5

    ወላጆች በጋራ የሚያሳዩት ቸርነት ቤትን ገነት ያደርገዋል፦ ወላጆች ልጆቻቸውን በቸርነት ሲያነጋግሩና መልካም ለማድረግ ሲሞክሩ ምሥጋና ከቸሯቸው ጥረታቸውን ያበረታታሉ፤ ደስተኛ እንዲሆኑ ያደርጓቸዋል። የደስታን የፀሐይ ብርሃን ወደ ቤት በመጋበዝ እያንዳንዱን የጽልመት ጥላ በማባረር የቤተሰቡን ክበብ በሐሴት ይከባሉ። የሁለትዮሽ ቸርነትና ይቅርባይነት ቤትን ወደ ገነትነት በመለወጥ መላእክት ወደ ቤተሰቡ ክበብ እንዲመጡ ይማርካቸዋል። ደስ የማያሰኙ ቃላት የሚነገሩበትን ንዝንዝና ጠብ ያለበትን ቤት ግን መላእክት ይሸሹታል። በጎነት የጎደለው ጠባይ፣ ምሬትና ብስጭት የሱስ ወደ ቤት እንዳይገባ በር ይዘጉበታል ።6Signs of the Times, April 17, 1884.AHAmh 307.6

    የዕለት ተዕለት የኑሮ በጎነቶች እንዲሁም በቤተሰቡ መካከል መኖር ያለበት ፍቅር በውጫዊ ሁኔታዎች የሚወሰን አይደለም።7Signs of the Times, Aug. 23, 1877.AHAmh 307.7

    ደስ የሚያሰኙ ንግግሮች ደግ ባህርያትና በድርጊት የሚገለጽ ልባዊ ፍቅር ከታታሪነት ከንጽህናና አግባብነት ካለው ቁጠባ ጋር ተዳምረው ደሳሳዋን ጎጆ እንኳ ከሁሉም የላቀችAHAmh 307.8

    ደስታ የሞላባት ቤት ያደርጓታል። እንደዚህ ዓይነቱን ትዳር ፈጣሪ በአዎንታ ይመለከተዋል።8Signs of the Times, Oct. 2, 1884.AHAmh 308.1

    ለውጫዊው ዓለም መብከንከናቸውን ቀንሰው ለራሳቸው የቤተሰብ አባላት የበለጠ መኖር ያለባቸው ብዙዎች ናቸው። ለእንግዶችና ለጎብኝዎች የምናሳየውን የይምሰል ደግነት ቀንሰን ከእውነተኛ ፍቅርና ርኅራኄ የሚመነጨውን በጎነት በምድጃችን ዙሪያ ላሉ ውድ አባላት ማሳየት ይጠበቅብናል።9Signs of the Times, Oct. 2, 1884.AHAmh 308.2

    እውነተኛ ደግነት ሲገለጽ፡- የእውነተኛ ንጥረት በቤት ውስጥ መጎልበት እጅግ አስፈላጊ ነው። ይህ እውነትን በመደገፍ ኃያል ምስክር ነው። በማንም ሰው ላይ የሚታዩ የቋንቋና የምልክት ባለጌነት ከተበላሸ ልብ የሚወጡ መሆናቸውን የሚጠቁም ነው። መነሻነቱ ሰማይ የሆነ እውነት ተቀባዩን ፈጽሞ ዝቅ አያደርገውም፤ ፈጽሞ ሻካራና ከርዳዳ አያደርገውም። እውነት የሚያለሰልስና የሚያጠራ ተጽዕኖ አለው። ልብ እውነትን ሲቀበል ወጣቶችን አክባሪና ትሁት ያደርጋቸዋል። ክርስቲያናዊ ደግነትን መቀበል የሚያስችለው የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ብቻ ነው። ከሰማይ የሆነ ደግነት አክባሪ ለመምሰል በመስገድና የይምሰል ፈገግታ በመቸር በለበጣ የሚኖር አይደለም። ይህ ዓይነቱ እጅ መንሳትና የሽርደዳ ፈገግታ በዓለም ባሉ ሰዎች ዘንድ የሚታይ ነው፤ እነርሱ በክርስቲያናዊ ደግነት የተራቆቱ ናቸው። እውነተኛ መልካምነትና እውነተኛ ደግነት ማግኘት የሚቻለው ከክርስቶስ ወንጌል ተግባራዊ እውቀት የተነሣ ብቻ ነው። እውነተኛ ደግነትና እውነተኛ በጎነት ማለት ከፍታ ዝቅታ ሀብታም ድኃ ሳይል ለሁሉም የሚበረከት ቸርነት ነው።10Manuscript 74, 1900.AHAmh 308.3

    ለሌሎች አሳቢ መሆን የእውነተኛ ደግነት መገለጫ ነው። አስፈላጊውና የማይዋዥቀው ትምህርት ማለት ርኅራኄን የሚያሰፋውና ቸርነት በሁሉም ቦታ ማሳየት ይቻል ዘንድ የሚያበረታታው ነው። ወጣቶች ለወላጆች ክብር እንዲሰጡ፤ ችሎታቸውን እንዲያደንቁ፤ በጥፋታቸው ይቅር እንዲሉ፤ በሚያስፈልጋቸውም ነገር ሁሉ ረዳት ይሆኑ ዘንድ የማይገፋፋቸው ጠባይ፤ እንዲሁም ለወጣቶችም ሆነ በዕድሜ ለገፉትና ላልታደሉት ለጋስ ረዳትና ለሁሉም በጎ ይሆኑ ዘንድ የማይለውጣቸው ልማድ የውድቀት ባህል ነው።11Education, p. 241.AHAmh 308.4

    ክርስቲያናዊ ደግነት በእያንዳንዱ ቀን የበለጠ የተቀራረቡና የጠነከሩ ይሆኑ ዘንድ የቤተሰቡን አባላት አንድ የማድረግ አቅም ያለው የወርቅ ማቀፊያ ነው።12Signs of the Times, Nov. 29, 1877.AHAmh 308.5

    ወርቃማውን መመሪያ የቤተሰብ ሕግ አድርጉት፦ ለማህበራዊም ሆነ ለቤተሰብ ግንኙነት ወደር የሌላቸው ደንቦች ያሉት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ነው። ተወዳዳሪ የሌለውና ፈጽሞ ንጹህ የሆነ የግብረ-ገብነት ደረጃ ብቻ ሳይሆን እጅግ ውድ የሆነ የደግነት ደንብ አለው። በአዳኛችን በተራራው ላይ የተሰበከው ስብከት በሁሉም የዕድሜ ክልል ላለ ዋጋና ተመን ሊወጣለት የማይችል ትምህርት ነው። ሁልጊዜም በቤተሰቡ ክበብ ሊነበብና ወርቃማው አስተምህሮቱም በዕለት ተዕለት ኑሮ በምሣሌነት ሊተገበር የሚገባው ነው። ወርቃማው ሕግ፡- “ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እንዲህ ደግሞ እላንትም አድርጉላቸው” እንዲሁም የሐዋርያው “እርስ በእርሳችሁ በማክበር ተቀዳደሙ” የሚሉት ቃላት የቤተሰባችሁ ሕግ ይሁኑ። በክርስቶስ መንፈስ ሐሴት የሚያደርጉ ሁሉ ደግነትን በቤታቸው ያንፀባርቃሉ። በጥቃቅን ነገር እንኳን በጎ ማድረግን በተግባር ያሳያሉ። ለሌሎች በሚሰጡት የቸርነት ትኩረት ውስጥ እራሳቸውን በመርሳት በዙሪያቸው ያለውን ሁሉ ደስተኛ ለማድረግ ያላሠለሰ ጥረት ያደርጋሉ። ይህ በክርስቲያን ዛፍ ላይ የሚያድግ ፍሬ ነው።13Signs of the Times, July 1, 1886.AHAmh 308.6

    ወርቃማው ደንብ የእውነተኛ በጎነት መመሪያ ነው። ፍጹም ተግባራዊነቱ በየሱስ ሕይወትና ባህርይ ተገልጿል። ኦ! ምን ዓይነት የልስላሴና የውበት ጮራ ነው ከአዳኛችን የዕለት ተዕለት ኑሮ ሲወጣ የነበረው! ከመገኘቱም ይፈስ የነበረው ጣፋጭነት! ያ መንፈስ በልጆቹም ላይ ይገለጻል። ክርስቶስ በእነርሱ ያለ ሁሉ በመለኮታዊ ከባቢ አየር የተጀቦኑ ይሆናሉ። የንጽሕናቸው ምልክት የሆነው ነጭ ካባቸው ከጌታ የአትክልት ሥፍራ በሚወጣው ጣፋጭ መዓዛ የታወደ ይሆናል። ከእርሱ የሚመጣውን ብርሃን በማንፀባረቅ የሚደናቀፉና የዛሉ እግሮች አረማመዳቸው ቀና ይሆን ዘንድ መንገዳቸውን በብርሃን ይሞላሉ።14Thoughts from the Mount of Blessing, pp. 192, 193AHAmh 309.1

    ወደር የማይገኝለት የሥነ-ምግባር ጽሑፍ፦ መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያው ጳውሎስ የተናገረውን ጨምሮ ስለ ሥነ-ምግባር የተጻፈ ተወዳዳሪ የሌለው ጽሑፍ በአዳኛችን የተሰጠው ነው። እነዚህ ቃላት በወጣትም ሆነ በአዛውንት በእያንዳንዱ ፍጡር አዕምሮ ሊፋቅ በማይችል ሁኔታ ሊጻፉ ይገባቸዋል። AHAmh 309.2

    “እኔ እንደ ወደድኋችሁ እናንተም ደግሞ እርስ በእርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ”AHAmh 309.3

    “ፍቅር ታጋሽ ናት በጎም ናት
    ፍቅር አትቀናም
    ፍቅር አትመካም
    አትነፋም [አትታበይም]
    ፊትዋን አታጠቁርም
    ገንዘቧን አትሻም
    ቶሎ አትቆጣም
    በክፉ አታስብም
    በኃጢአት ደስ አይላትም
    በእውነት ደስ ይላታል እንጂ
    ሁሉን ትችላለች ሁሉን ታምናለች
    ሁሉን ተስፋ ታደርጋለች
    በሁሉ ትታገሳለች
    ፍቅር ከቶ አትወድቅም።” 15Education, p. 242.
    AHAmh 309.4

    መጽሐፍ ቅዱስ ደግ መሆንን ያዝዛል፤ ራስ-ወዳድ ያልሆነውን መንፈስ፣ ገራሙን ፀጋ፣ መልካሙን ጠባይ እንዲሁም የእውነተኛ ደግነት ባህርይ የሆኑትን ሁሉ በተግባር የሚያሳይበት ብዙ መገለጫዎች ያቀርባል። እነዚህ የክርስቶስ ባህርይ ነፀብራቅ ናቸው። በዓለም ያለው የዋህነትና መልካም እርዳታ ሁሉ ለስሙ ዕውቅና በማይሰጡ ሰዎች መካከል እንኳን ቢሆን ይህም ከእርሱ ነው። እነዚህ ባህርያቱ በፍጽምና በልጆቹ ይንፀባረቁ ዘንድ ጥልቅ ፍላጎቱ ነው። በእኛ በሰዎች ላይ የርሱን ውበት ማየት ዓላማው ነው።16Id., pp. 421, 242.AHAmh 310.1

    ክርስትና አንድን ሰው ጨዋ ያደርገዋል። ክርስቶስ ለአሳዳጆቹ እንኳ ደግ ነበር፤ እውነተኛ ተከታዮቹም ይህንን ባህርይውን ያንፀባርቃሉ። ጳውሎስ በገዢዎቹ ፊት ሲቀርብ ተመልከቱ። በአግሪጳ ፊት የተናገረው ንግግር እውነተኛ ደግነቱንና አሳማኝ አንደበተ-ርቱዕነቱን ያስመሰከረ ነበረ። ወንጌሉ አሁን በዓለም የሚንፀባረቀውን ዓይነት ደግነት አያበረታታም፤ ከእውነተኛና ቸር ልብ የሚመነጨውን ደግነት እንጂ።17Ministry of Healing, pp. 289. 290.AHAmh 310.2

    ዓለም ደግነት ብሎ የሚጠራውን በጎነት ማሳየት እንችል ዘንድ አንለምንም፤ ለቅዱሳን ወደ ተዘጋጁት እልፍኞች እያንዳንዱ ሰው ሊወስደው የሚችለውን ዓይነት ደግነት እንጂ።18Signs of the Times, Aug. 13, 1912.AHAmh 310.3

    እውነተኛ ደግነት ቆስቋሽ ፍቅር መሆን አለበት፦ ውጫዊ ባህርያትን ለማጎልበት የሚደረገው ጥንቁቅ ጥረት ብስጭትን ፍትሐዊ ያልሆነ ፍርድንና አስጸያፊ ንግግርን ለማስወገድ በቂ አይደለም። ራስ የበላይ እስከሆነ ድረስ እውነተኛ ንጥረት ሊገለጽ አይችልም። ፍቅር በልብ ውስጥ መኖር አለበት። በጥንቃቄ የሚራመድ ክርስቲያን የድርጊቱን ምክንያት የሚያገኘው በጌታ ባለው ጥልቅና ልባዊ ፍቅር ነው። በክርስቶስ ባለው የፍቅር ሥራሥሮቹ አማካይነት ለወንድሞቹ የሚኖረው ራስ-ወዳድነት የሌለበት ፍላጎቱ ወደ ላይ ይፈነጥቃል።19Ministry of Healing, p. 490.AHAmh 310.4

    ከሚፈለጉት ሊጎለብቱ ከሚገባቸውና ከሚወደዱት ባህርያት ሁሉ በሠላምና በአመሥጋኝነት እንደተሞላ ንጹህ ልብ በእግዚአብሔር እይታ የበለጠ ዋጋ ያለው የለም። AHAmh 310.5

    የእውነትና የፍቅር መለኮታዊ መስማማት ልብ ውስጥ ካለ በቃልና በተግባር ወደ ፊት ያበራል። ለሌሎች የማድረግ እውነተኛ መንፈስ በልብ ውስጥ መኖር አለበት። ፍቅር ተካፋዩ ለሆነ ሁሉ ፀጋን ሥነ-ሥርዓትንና የሰከነ ባህርይን ያካፍላል። ፍቅር ድምፅን ለሆሳስ ፊትን የፈካ ያደርጋል። የሰውን ሁለንተና ያነጥረዋል፤ ከፍ ከፍም ያደርገዋል። ሰማያዊ ባህርይ በመሆኑ ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር ወደ መስማማት ያመጣዋል።20Testimonies for the Church, Vol. 4, pp. 559, 560.AHAmh 310.6

    የሥነ-ምግባር ሕጎችን በመተግበር ብቻ እውነተኛ ደግነትን መማር አይቻልም። የጠባይ ግብረ-ገብነት ምንጊዜም ሊጠበቅ ይገባል። መመሪያው እስካልተጣሰ ድረስ ለሌሎች በጎ ማድረግ በሁሉም ሰው ዘንድ ተቀባይነት ካላቸው ባህሎች ጋር ስምምነት መፍጠር ያስችላል። እውነተኛ ደግነት ግን መርሆውን ለዘልማዳዊ አሠራር መሠዋት የለበትም። በዘር የሚወረስ የማህበራዊ መደብ ክፍፍልን አይቀበለውም። ሰው በሰውነቱ ያለው ማዕረግ በክብር እንዲጠበቅ በታላቁ የሰው ዘር ወንድማማችነት ውስጥ ለእያንዳንዱ አባል አክብሮ ት ይኖር ዘንድ ራስ ን ስለማክበር ጭምር ያስተምራል።21Education, p. 240.AHAmh 310.7

    ፍቅር በፊት ገጽታ በቃላትና በተግባር ይገለፃል፦ ከምንም ነገር በላይ ወላጆች በደስተኛነት በደግነትና በፍቅር ከባቢ አየር ልጆቻቸውን ሊከቧቸው ይገባል። ፍቅር የሚኖርበት፣ በፊት ገጽታ በቃላትና በተግባር የሚገለጽበት ቤት መላእክት በደስታ መኖር የሚፈልጉበት ዓይነት ሥፍራ ነው። ወላጆች ሆይ የፍቅር የሐሴትና የደስታ ይዘት ያለው ብርሃን በልባችሁ ይብራ፤ ጣፋጩ ተጽዕኖውም ቤቱን ሁሉ ያውደው። የቤት ውስጥ ሕይወትን በብርሃን የሚሞሉትን ፀጋዎች በማሳደግ የቸርነትና የይቅር-ባይነት መንፈስ አንፀባርቁ፤ ይህም በልጆቻችሁ ይታይ ዘንድ አበረታቷቸው። እንደዚህ ሲሆን የሚፈጠረው ሁኔታ የልጆች ጤናን በማሻሻል ለአዕምሮና ለአካል ብርታት በመስጠት ልክ አየርና የፀሐይ ብርሃን ለእፀዋት የሚለግሱት ዓይነት ጠቀሜታ ይኖረዋል።22Counsels to Teachers, Parents and Students, p. 115.AHAmh 311.1

    ጨዋ ባህርይ፣ በደስታ የተሞላ ንግግር እንዲሁም የፍቅር አድራጎት የልጆችን ልብ ከወላጆቻቸው ጋር በፍቅር የሐር ዕትብት ያስተሳስረዋል። ቤትንም ማራኪ በማድረግ ረገድ በወርቅ ሊገዙ ከሚችሉ እጅግ ብርቅዬና ውድ ከሆኑ ጌጣጌጦች ሁሉ ይበልጣል።23Signs of the Times, Oct. 2, 1884.AHAmh 311.2

    የተለያዩ ባህርያት መዋሐድ አለባቸው፦ የተለያየ ጠባይ ያላቸው ሰዎች ይጎዳኙ ዘንድ በእግዚአብሔር ሥርዓት የተካተተ ነው። ይህ ሁኔታ ሲፈጠር እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል የሌሎችን ስሜት በመጠበቅና መብታቸውን በማክበር በቅድስና ሊመላለስ ይገባዋል። በዚህ ሁኔታ የጋርዮሽ አሳቢነትና ይቅር-ባይነት ይጎለምሳል፤ ሚዛን-አልባነት ይስተካከላል፤ የባህርይ ሸካራ ነጥቦች ይለሰልሳሉ፤ መስማማት ይረጋገጣል፤ የተለያዩ ባህርያት ውህደት ለእያንዳንዱ ጥቅም ይሆናል።24Signs of the Times, April 4, 1911.AHAmh 311.3

    የደግነትን እጦት ምንም ነገር አይተካውም፦ የክርስቶስ ተከታዮች እንደሆኑ የሚናገሩ ሆኖም ሸካራ የሆኑ በጎነት የሌለባቸውና በንግግራቸውም ሆነ በጠባያቸው ትሁት ያልሆኑ እነርሱ ከየሱስ አልተማሩም። የሚደነፋ ጨቋኝና ስህተት ፈላጊ ሁሉ ክርስቲያን አይደለም። የአንዳንድ ክርስቲያኖች ፀባይ ቸርነትና ደግነት ስለሚጎድለው መልካምነታቸው ሁሉ በክፉ ይወራል። ሐቀኛነታቸው ጥርጥር ውስጥ ላይገባ ይችላል፤ ጽድቃቸው ጥያቄ ውስጥ ላይገባም ይችላል፤ ሐቀኛነትና ቀጥተኛነት ግን የቸርነትንና የደግነትን እጦት ሊያካክሱ አይችሉም። አንድ ክርስቲያን ሩኅሩኅና እውነተኛ አዘኔታ የሚያሳይ ትሁት እንዲሁም ጻድቅና ታማኝ መሆን ይጠበቅበታል።25The Youth’s Instructor, March 31, 1908.AHAmh 311.4

    ወንድም ለወንድሙ የሚያሳየው አክብሮትና ደግነት ቸል ከተባለ፤ በቤተሰብ ክበብ ውስጥ ወላጆች ለልጆቻቸው፤ ልጆች ደግሞ ለወላጆቻቸው የሚናገሩአቸው ቸርና የሚያበረታቱ ቃላት ዋጋ የማይሰጣቸው ከሆነ እየተተገበረ ያለው ባህርይ ክርስቶሳዊ መልክ እንደሌለው የሚያረጋግጥ ነው። እነዚህ ጥቃቅን ሆኖም አስፈላጊ ነገሮች ግን ሥራ ላይ ከዋሉ ወደ ታላቅነት ያድጋሉ፤ መጠናቸው እጅግ ይገዝፋል። እንደ ቅዱስ እጣን ወደ እግዚአብሔር የሚወጣ መልካም መዓዛ በነፍስ ዙሪያ ይተነፍሳሉ።26Manuscript 107, 1898.AHAmh 311.5

    ብዙዎች አሳቢነትን ይናፍቁታል፦ የርኅራኄን ነፀብራቅ ብዙዎች ይናፍቃሉ….በጥቃቅን ነገሮች እንኳ ከሌሎች ለተቀበልነው መልካምነት ምሥጋናችንን ለመግለጽ አጋጣሚዎችን በመፈለግ ራሳችንን የረሳን መሆን አለብን። በቸርነት አድራጎቶችና በጥቃቅን የፍቅር ተግባራት ሰዎችን ለማስደሰት ሸክማቸውን ለማቅለልና መከራቸውን ለማስታገስ አጋጣሚዎችን መፈለግ ይጠበቅብናል። እነዚህ በቤተሰባችን ውስጥ ተተግብረው የሚቀጥሉት የአሳቢነት አድራጎቶች ከቤተሰብ አልፈው ወደ ውጭ በመፍሰስ በሕይወት ሊገኝ የሚችለውን የደስታ ክምችት ይገነባሉ። እነዚህን ጥቃቅን ነገሮች ቸል ማለት ደግሞ በኑሯችን የሚገጥመንን የምሬትንና የሐዘንን ድም ር ይቆልላል።27Testimonies for the Church, Vol. 3, pp. 539, 540.AHAmh 312.1

    በማህበራዊ ግንኙነቶች ምክንያት ከዓለም ጋር መነካካት ይፈጠራል፦ ክርስትና ከዓለም ጋር የተነካካው በማህበራዊ ግንኙነት አማካይነት ነው። እያንዳንዱ/ዷ የክርስቶስን ፍቅር የቀመሰ/ችና በልቡ/ቧ መለኮታዊ ብርሃን የበራለት/ላት ወንድ ወይም ሴት የዚህ እውቀት የሌላቸውን ሰዎች የጨለማ መንገዶች በማብራትና የተሻለ ጎዳና እንዲያሳይ/እንድታሳይ እግዚአብሔር ይፈልግበታል/ ይፈልግባታል።28Id., Vol. 4, p. 555.AHAmh 312.2

    በልዝብ ቃላትና በመልካም የፊት ገጽታዎች አንድ ሺህ የሚሆኑ ጥቃቅን በጎነቶች ማንፀባረቅ እንችላለን፤ እነዚህ ነገሮችም ተመልሰው ለእኛ ይንፀባረቁልናል። ለሌሎች ግድ-የለሽ በመሆን አሳቢነትን የማያንፀባርቁ ክርስቲያኖች ከክርስቶስ ጋር ሕብረት እንደሌላቸው ያረጋግጣሉ። ከክርስቶስ ጋር አንድ ከሆንን ለሌሎች ቸርነት የማናሳይና መብታቸውንም የምንዘነጋ እንሆን ዘንድ ከቶ አይቻለንም።29Id., Vol. 3, p. 539.AHAmh 312.3

    እኛ ሁላችን የየሱስ ምሥክሮች መሆን አለብን። በክርስቶስ ፀጋ የተቀደሰ ማህበራዊ ኃይል ለአዳኙ ነፍሳትን በማሸነፍ መበልፀግ አለበት። በራስ-ወዳድ ፍላጎቶቻችን ብቻ የሰመጥን እንዳልሆንን፤ መታደላችንና በረከቶቻችንን ለሌሎች ለማካፈል ጽኑ መሻት እንዳለን ዓለም ሁሉ ሊያይ ይገባዋል። እምነታችን ርኅራኄ-ቢስ በቃኝ የማንልና አቃቂር አውጪ እንደማያደርገን ሊያዩ ይገባል። ክርስቶስን እንዳገኙ የሚናገሩ ሰዎች እርሱ ለሰው ጥቅም ሲል ያደረገውን ሁሉ ይድገሙት። ክርስቲያኖች ድንግዝግዝ ያለባቸውና ደስታ-ቢስ ሰዎች እንደሆኑ የሚያመላክተውን የተሳሳተ ገጽታ ለዓለም ፈጽሞ ማሳየት የለብንም።30Desire of Ages, p. 152.AHAmh 312.4

    በቤታችን ትሁትና ገራም ከሆንን ከቤት ውጭም መልካም ጠባይ የሚንፀባረቅበትን መልክ ይዘን እንታያለን። ይቅር-ባይነት፣ ትዕግሥት፣ ደግነትና ጽናት በቤት ውስጥ የምናሳይ ከሆነ ለዓለም ብርሃን እንሆን ዘንድ ይቻለናል።31Signs of the times, Nov. 14, 1892.AHAmh 312.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents