Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የአድቬንቲስት ቤት

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ ሃምሳ—ዘጠኝ የሸመገሉ ወላጆች

    “አባትህንና እናትህን አክብር”፦ ወላጆቻቸውን ስለማክበር ልጆች ላይ የተጣለው ግዴታ የዕድሜ ልክ ነው። ወላጆች ደካማና ያረጁ ቢሆኑም የልጆች ፍቅርና ትኩረት በሚያስፈልጋቸው መጠን ሊቸራቸው ይገባል። እያንዳንዱ የጭንቀትና ግራ የመጋባት ሐሳብ ከወላጆቻቸው ይወገድ ዘንድ እራስን መካድ አስፈላጊ ቢሆን እንኳ ልጆች የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ በጨዋነትና በቆራጥ ውሳኔ ሊያስተካክሉት ይገባቸዋል…. 1Manuscript 18, 1891..AHAmh 261.1

    የዋህነት የተላበሰ ፍቅርና እንክብካቤ ለወላጆቻቸው ይኖራቸው ዘንድ ልጆች መማር አለባቸው። ልጆች ሆይ እራሳችሁ ተንከባከቧቸው፤ ምክንያቱም ሌላ ማንም ሰው እያንዳንዱን ጥቃቅን የቸርነት አድራጎት እናንተ በምትፈጽሙት ዓይነት ማድረግ አይችልም። እኛ ለእነርሱ ያለን ፍቅር የእነርሱም ለእኛ በዓመታት ብዛት ወይም በቦታ ርቀት አይለካም፤ ያለብን ኃላፊነትም ወደ ጎን ሊገፋ ፈጽሞ አይችልም። 2Review and Herald, Nov. 15, 1892.AHAmh 261.2

    ሁሉም ነገር ቢመቻችላቸው እንኳ ዕድሜ የጠገቡ ወላጆች ያላቸው ደስታና ምቾት ከእርጅናቸው የተነሣ እጅግ አነስተኛ እንደሆነ ልጆች በጥንቃቄ ሊያስታውሱ ይገባቸዋል። ልጆቻቸው ቸል ሲሏቸው ከማየት የባሰ የወላጆችን ልብ ሊያሳዝንና ሊያቆስል የሚችል ምን ነገር አለ? ለአረጀ አባት ወይም እናት ሐዘን ከማምጣት የባሰ ልጆች ሊሠሩት የሚችሉት ምን ዓይነትስ ኃጢአት ሊኖር ይችላል? 3Review and Herald, Nov. 15, 1892.AHAmh 261.3

    መንገዱን ደልድሉ፦ ልጆች ከጎለመሱ በኋላ ወላጆቻቸው ለመኖር የሚያስፈልጋቸውን ዕርዳታ ከማድረግ ውጪ ሌላ ኃላፊነት የሌለባቸው አድርገው ያስባሉ። ምግብና መጠለያ ሲያቀርቡላቸው ሳለ ፍቅርና ርኅራኄ ግን ይነፍጓቸዋል። በወላጆቻቸው የእርጅና ሰዓት፣ ለፍቅርና ለርኅራኄ ነፀብራቅ በሚናፍቁበት ጊዜ በጎነት በጎደለው አኳኋን ልጆቻቸው ትኩረት ይነፍጓቸዋል። ልጆች አክብሮታቸውንና ፍቅራቸውን ከወላጆቻቸው የሚገቱበት ምንም ጊዜ ሊኖር አይገባውም። ወላጆቻቸው በሕይወት እስካሉ ድረስ ሊያከብሯቸው፣ ከፍ ከፍ ሊያደርጓቸውና ይህም የልጆች የደስታ ምንጭ ሊሆን ይገባዋል። የሚችሉትን ሁሉ የደስታና የፈገግታ ነፀብራቅ ወደ አረጁት ወላጆቻቸው ሕይወት ያምጡ። ወደ መቃብር የሚወስደውን መንገዳቸውን ያለስልሱ። ልጅ ወላጆቹን እንደሚያከብር ከሚነገርለት ምሥክርነት የተሻለ ሙገሳ በዚህ ዓለም የለም፤ አባትና እናቱን እንደወደደና እንዳከበረ ከተጻፈ የሰማይ መጽሐፍ የበለጠ መዝገብ የለም። 4Review and Herald, Nov. 15, 1892.AHAmh 261.4

    ለወላጆች ምሥጋና-ቢስ መሆን፦ በማይታክት እንክብካቤና መሰጠት አቅማቸው በፈቀደ መጠን የሐዘናቸው መንስዔ የሆኑትን ጉዳዮች ሁሉ በፈቃዳቸው ለማስወገድ የማይፈልጉና ወላጆቻቸው ለሚጠይቋቸው ነገሮች ጭራሽ የሞቱ መሆን ልጆች ይቻላቸዋልን? ወላጆቻቸው ካሳለፏቸው ዘመናት ይልቅ የመጨረሻዎቹ ቀናት እጅግ ያማሩ ይሆኑላቸው ዘንድ ማድረግ ቢቻል ይህ ለልጆች ደስታ የማይሰጣቸው ሊሆን ይችላልን? አባታቸውና እናታቸው በእንግዳ እጆች እንክብካቤ ይደረግላቸው ዘንድ ወንድ ወይም ሴት ልጅ እንዴት ፈቃደኛ ሊሆኑ ይችላሉ! እናት የማታምንና ስምምነት የሌላት ብትሆን እንኳ ወላጁን ለመንከባከብ እግዚአብሔር ከጣለበት ኃላፊነት ማንንም ነፃ ሊያደርገው አይችልም። 5Review and Herald, Nov. 15, 1892.AHAmh 262.1

    አንዳንድ ወላጆች ለውርደታቸው ተጠያቂዎች ናቸው፦ ወላጆች ልጃቸው በሕፃንነቱ ጊዜ ትዕግሥትና አክብሮት የሌለው ባህርይ እንዲያሳያቸው መፍቀዳቸው በኋለኞቹ ዓመታት መጥፎ ምርት እንዲሰበስቡ ምክንያት ይሆናል። ወላጆች ፈጣንና ፍጹም የሆነ መታዘዝ ከልጆቻቸው መሻት ሲሳናቸው በትናንሾቹ ፍጥረቶቻቸው የትክክለኛውን ባህርይ መሠረት መጣል ሳይሆንላቸው ይቀራል። የክርስቶስ ፀጋ የልጆቻቸውን ልብ ካልቀየረውና ባህርያቸውን ካልለወጠው በስተቀር በእርጅናቸው ጊዜ ያዋርዷቸው ዘንድ፤ ወደ መቃብራቸው በተቃረቡ ጊዜ ለልባቸው ሐዘን ያመጡባቸው ዘንድ ልጆቻቸውን ያዘጋጇቸዋል። 6Manuscript 18, 1891.AHAmh 262.2

    ፍርደ-ገምድል ለሆኑ ወላጆቻችሁ አጸፋውን አትመልሱ፦ አንዲት ሴት ስለ እናትዋ እንዲህ አለች “እናቴን ሁሌም እጠላት ነበር፤ እርስዋም ትጠላኝ ነበር።” እነዚህ ቃላት በሰማይ መጽሐፍ ተመዝግበው እያንዳንዱ እንደሥራው ይከፈለው ዘንድ በፍርድ ቀን ሲቆም ተከፍተው ይነበባሉ።AHAmh 262.3

    ልጆች የሕፃንነት አስተዳደጋቸው ጭካኔ የተሞላበት እንደነበር ማሰባቸው በክርስቶስ ፀጋና እውቀት እንዲያድጉ ይረዳቸዋል? የእርሱን መልክ እንዲያንፀባርቁ ያደርጋቸዋል? ወይስ ወላጆቻቸው በእድሜ የገፉና ደካማ በሚሆኑበት ጊዜ አጸፋ የመመለስና የመበቀል መንፈስን ያበረታታል? እራሳቸውን መርዳት የማይችሉና አቅመ-ደካማ መሆናቸው የልጆች ፍቅር አያስፈልገውምን? ያረጀው አባት ወይም እናት ፍላጎቶች የልብን መልካም ስሜት በመቀስቀስ በክርስቶስ ፀጋ አጋዥነት ወላጆች በክብርና ቸር በሆነ ትኩረት በአብራካቸው ክፋዮች እንክብካቤ ይደረግላቸው ዘንድ አያስችልም? ኦ ለአባትና ለእናት ልባችሁ እንደ ብረት የጠነከረ አይሁን! በተለይም እናትዮዋ ሕመምተኛና ባልቴት ከሆነች አንዲት የክርስቶስን ስም የምትጠራ ሴት እንዴት ለእናትዋ ጥላቻ ሊኖራት ይችላል? የክርስቲያን ሕይወት ጣፋጭ ፍሬዎች የሆኑት ቸርነትና ፍቅር ለወላጆቻቸው ምቾት ሲባል በልጆች ልብ ውስጥ ቦታ ያግኙ። 7Manuscript 18, 1891.AHAmh 262.4

    ለአካላዊና ለአዕምሮአዊ ደካማነት ትዕግሥት ይኑራችሁ፦ በማርጀትዋና ደካማ በመሆንዋ የምታሳየውን የሁለተኛ ልጅነትዋን ባህርያት ጉድለቶች በመቃወም ልጅ ለእናቱ ጥላቻ ሲያሳይ ይህ በተለየ ሁኔታ አሳዛኝ ነው። በእንዴት ዓይነት ልስላሴና ትዕግሥት እንደዚህ ዓይነትዋን እናት ሊሸከሟት ይገባል! መንፈስን የሚያለዝቡ የለሆሳስ ቃላት ሊነገሩ ይገባል። እውነተኛ ክርስቲያን ቸርነት የሌለው፤ በምንም ዓይነት [አስቸጋሪ] ሁኔታ ውስጥ ቢሆን እናቱን ወይም አባቱን ፈጽሞ የሚተው አይሆንም፤ “እናትና አባትህን አክብር” የሚለውን ትዕዛዝ ያከብራል እንጂ። እግዚአብሔር አለ “በሽበታም ፊት ተነሣ፣ ሽማግሌውንም አክብር።” ልጆች ሆይ እራሳቸውን መርዳት የማይችሉት ጉድለት ያለባቸው ወላጆቻችሁ የመጨረሻዎቹ ቀኖቻቸው በእርካታ፣ በሠላምና በፍቅር የተሞሉ ይሁኑላቸው። ለክርስቶስ ስትሉ በቸርነት፣ በፍቅር፣ በምህረትና በይቅርታ ቃላት ብቻ ወደ መቃብራቸው ይውረዱ። ጌታ እንዲወድዳችሁ እንዲቀድሳችሁና ይቅር እንዲላችሁ በህመማችሁ ጊዜ ሁሉ ማረፊያ እንዲሆንላችሁ ትፈልጋላችሁ፤ ታዲያ ለራሳችሁ እንዲደረግላችሁ የምትፈልጉትን ለሌሎች አታደርጉምን? 8Manuscript 18, 1891.AHAmh 263.1

    በሽማግሌዎች እንክብካቤ ረገድ እግዚአብሔር ያለው እቅድ፦ ቤት ለሌላቸው በዕድሜ ለገፉ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እንክብካቤ የማድረጉ ጉዳይ በተደጋጋሚ የሚነሣ ርዕስ ነው። ምን ሊደረግላቸው ይችላል? እግዚአብሔር የሰጠኝ ብርሃን እንደገና ተደግሟል፤ በአንድነት ተሰብስበው ይረዱ ዘንድ ለአረጋውያን መልካም አይደለም፤ ከቤት ወጥተው ወደ መጦሪያ ቦታ ሊላኩም አይገባቸውም። እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል የራሱን ወገን ይንከባከብ። ይህ የማይቻል ከሆነ ኃላፊነቱ የቤተ-ክርስቲያን ነው፤ እንደ ግዴታም እንደ ዕድልም ሊታይ ይገባዋል። የክርስቶስ መንፈስ ያላቸው እነርሱ ደካሞችንና በዕድሜ የገፉትን በተለየ አክብሮትና የዋህነት ይመለከቷቸዋል። 9Testimonies for the Church, Vol. 6, p. 272.AHAmh 263.2

    እርካታና ደስታ የሚያመጣ ዕድል፦ ለወላጆቻቸው ምቾትና እንክብካቤ የለፉ ልጆች ያለፈውን ሲያስታውሱት የዕድሜ ልክ እርካታ ይሰማቸዋል። እነርሱ እራሳቸው ርኅራኄና ፍቅር የሚፈልጉበት ጊዜ ሲመጣ ደግሞ የበለጠ ደስታ ይሰጣቸዋል። ልባቸው በፍቅር የተሞላ ሁሉ ወደ መቃብር የሚወስደውን የወላጆቻቸውን መንገድ ለማለስለስ ያገኙትን ዕድል ዋጋ የማይገኝለት ሥጦታ እንደሆነ ይቆጥራሉ። የተወዳጅ ወላጆቻቸውን የመጨረሻዎቹን ቀናት የምቾትና የሠላም በማድረግ ጥረት ውስጥ አስተዋጽኦ ማበርከት ደስ ይላቸዋል። ከዚህ ውጪ የሆነ ተግባር በወላጆች ላይ መፈጸም፤ እነዚህን ረዳት የሌላቸው ሽማግሌዎች በወንዶችና በሴቶች ልጆቻቸው ሊደረግላቸው የሚገባቸውን በጎነት የተላበሰ አገልግሎት መንፈግ፤ ልባችን እንደ ድንጋይ የጠነከረና የቀዘቀዘ ካልሆነ በስተቀር ነፍስን በቁጭት ቀኑን በፀፀት የሚሞላ መሆኑ አይቀሬ ነው። 10Review and Herald, Nov. 15, 1892.AHAmh 263.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents