Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የልጅ አመራር

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 42—ሥልጠና መጀመር ያለበት ጊዜ

    የማይታዘዙ ልጆች ከመጨረሻ ዘመን ምልክት አንዱ ነው— ከ “መጨረሻው ዘመን” ምልክቶች አንዱ የልጆች ለወላጆቻቸው አለመታዘዝ ነው። እና ወላጆች ሀላፊነታቸውን ይገነዘባሉ? ብዙዎች በማንኛውም ጊዜ በልጆቻቸው ላይ ሊኖራቸው የሚገባውን የክትትል እንክብካቤ የረሱ እና በክፉ ምኞት እንዲረኩ እና ለእነርሱም ሳይታዘዙ እንዲቀሩ የሚተውአቸው ይመስላሉ። 431The Review and Herald, September 19, 1854.CGAmh 217.1

    ልጆች የጌታ ርስት ናቸው፣ በመሆኑም ወላጆች የጌታን መንገድ እንዲጠብቁ የሚያስችላቸውን ዓይነት ስልጠና ካልተሰጧቸው በስተቀር የከበረውን ኃላፊነታቸውን ቸል ይላሉ፡፡ ልጆች ባለጌ፣ ሥርዓት አልባ፣ ይሉኝታ ያሌላቸው፣ የማይታዘዙ፣ የማያመሰግኑ፣ ቅድስና የሌላቸው፣ በስሜት የሚጦዙ፣ እብሪተኞች፣ እግዚአብሔርን ከመውደድ ይልቅ ተድላን የሚወዱ እንዲሆኑ የእግዚአብሔር ፈቃድ ወይም ዓላማ አይደለም፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍት ይህ የኅብረተሰቡ ሁኔታ የመጨረሻው ዘመን ምልክት እንደሚሆን ይገልፃሉ፡፡ 432The Signs of the Times, September 17, 1894.CGAmh 217.2

    ልል ወላጆች ለሰማያዊ ሥርዓታዊነት ብቁ አይደሉም— በመንግሥተ ሰማይ ፍጹም ሥርዓት፣ ፍጹም መግባባት እና ስምምነት አለ፡፡ ወላጆች እዚህ ልጆቻቸውን በተገቢው ስልጣን ሥር ማድረግን ችላ ያሉ እንደሆነ፣ ሰላምና ስምምነት በሚኖርበት ዓለም ውስጥ ከቅዱሳን መላእክቶች ጋር ጓደኛ ለመሆን ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ ብለው እንዴት ተስፋ ያደርጋሉ? 433Manuscript Releases 4:199.CGAmh 217.3

    በዚህ ሕይወት ለሕግ ወይም ለሥርዓት አክብሮት ያልነበራቸው ሰዎች በሰማይ ለታየው ሥርዓት አክብሮት አይኖራቸውም። በጭራሽ ወደ ሰማይ ለመግባት ፈቃድ አያገኙም፣ ምክንያቱም እዚያ ለመግባት ፈቃድ የሚያገኙ ሁሉ ሕግን የሚወዱ እና ስርዓትን የሚያከብሩ ናቸው። በዚህ ሕይወት ውስጥ የተገነቡት ባህሪያት የወደፊቱን ዕጣ ፈንታ የሚወስኑ ናቸው፡፡ ክርስቶስ በሚመጣበት ጊዜ የማንንም ግለሰብ ባህርይ አይለውጥም...፡፡ ወላጆች ልጆቻቸውን ለመጥቀም ሲሉ ማንኛውንም ዓይነት ግዴታቸውን ችላ ማለት የለባቸውም፡፡ እነርሱ እዚህ ለህብረተሰቡ በረከት እና ከዚያም በኋላ የዘላለም ሕይወትን ሽልማት መቀበል በሚያስችላቸው መልኩ እነርሱን ሠልጠን አለባቸው፡፡ 434Testimonies For The Church 4:429.CGAmh 217.4

    ሥልጠና መጀመር ያለበት መቼ እንደሆነ— ልጅ የራሱን ፍላጎት እና መንገድ መምረጥ ሲጀምር፣ በዚያው ቅጽበት ሥልጠናው መጀመር አለበት። ይህ ምናልባት ሳይታወቅ የሚከናወን ትምህርት ተብሎ ሊጠራ ይችላል፡፡ ያኔ ሥራው፣ የታሰበበት እና ኃያል የሆነው ሥራ መጀመር ያለበት ነው፡፡ የዚህ ሥራ ትልቁ ሸክም የግድ እናት ላይ ያርፋል፡፡ ለልጁ መጀመሪያ እንክብካቤ የምትሰጠው እርሷ ናት፣ በመሆኑም ልጁ ጠንካራ እና ሚዛናዊ ባህሪይ እንዲያዳብር የሚረዳውን የትምህርት መሠረት መጣል ይኖርባታል።CGAmh 218.1

    ብዙውን ጊዜ ገና ሕፃናት የሆኑ ልጆች በጣም ቆራጥ አቋም ያሳያሉ። ይህ ፈቃድ ካልተገራው የልጁ ምኞቶች ይልቅ ጥበብ ባለው ሥልጣን እንዲገዛ ካልተደረገ በስተቀር ሰይጣን አዕምሮውን ይቆጣጣርና ባህሪይውን ከፈቃዱ ጋር በሚስማማ መልኩ ይቀርጻል። 435Letter 9, 1904.CGAmh 218.2

    ጠማማ አመለካከት እስከሚበረታ ድረስ የስነስርዓት እና የሥልጠና ስራ ችላ ማለት ልጆች ላይ እጅግ ከባድ ስህተት መፈጸም ነው፤ ምክንያቱም እነርሱ ራስ ወዳድ፣ ግትር እና የማይወደዱ ሆነው ያድጋሉ፡፡ ከሌሎቹ በተሻለ የእራሳቸውን ቡድን ማግኘት አይችሉም፡፡ ስለዚህ ሁል ጊዜ በቅሬታ ይሞላሉ፡፡ ሰይጣን የልጆቻቸውን አእምሮ እና ዝንባሌ እንዳይቆጣጠር እድል ባለመስጠት ልጆች ገና በልጅታቸው ጊዜ ላይ ሳሉ የእናቶች ሥራ መጀመር አለበት፡፡ 436Manuscript Releases. 43, 1900.CGAmh 218.3

    ክፋት ለመጀመሪያ ጊዜ ብቅ ሲል አምቆ ያስቀሩ— ወላጆች፣ ልጆቻችሁ በክንዳችሁ ላይ ባሉበት ጊዜ የመጀመሪያውን የስነ-ስርዓት ትምህርት መጀመር አለባችሁ። ፈቃዳቸውን ለእርስዎ እንዲያስገዙ አስተምሯቸው፡፡ ይህ የማያዳላ እጅ በማንሳት እና ጽኑነትን በማንጸባረቅ ሊከናወን ይችላል። ወላጆች መንፈሳቸውን በፍጹም መቆጣጠር አለባቸው፣ እንዲሁም በእርጋታ እና ነገር ግን በጽኑነት ልጁ ለፍላጎታቸው ከመሸነፍ ውጭ ሌላ ምንም እስከማይጠብቅ ድረስ ፈቃዱን መግራት አለባቸው፡፡ CGAmh 218.4

    ወላጆች በወቅቱ አይጀምሩም፡፡ የመጀመሪያው ግልፍተኝነት ሲገለጽ አልተገታም፣ እናም ልጆቹ ሲያድጉ ከእነርሱ ጋር የሚያድግና ሲጠነክሩ ከእነርሱ ጋር የሚጠነክር ግትርነትን ይዘው ያድጋሉ፡፡ 437Testimonies For The Church 1:218.CGAmh 219.1

    “ለመቅጣት ገና ጨቅላ ናቸው?”— ኤሊ ቤተሰቡን እግዚአብሔር ለቤተሰብ ባስቀመጠውን ሕግ መሰረት አላስተዳደርም፡፡ የራሱን ፍርድ ተከትሏል፡፡ አፍቃሪው አባት ልጆች ሲያድጉ ክፉ ዝንባሌዎቻቸውን ይተዋሉ በማለት ራሱን በማታላል የልጆቹን የልጅነት ስህተት እና ኃጢአት በንቀት ችላ አለ፡፡ ብዙዎች አሁን ተመሳሳይ ስህተት እየሠሩ ነው፡፡ እግዚአብሔር በቃሉ ከሰጠው ይበልጥ ልጆቻቸውን የሚያሰለጥኑበት የተሻለ መንገድ እንደሚያውቁ ያስባሉ፡፡ “ለመቅጣት ገና ጨቅላ ናቸው፡፡ እስኪያድጉና ምክርን መቀበል እስኪችሉ ድረስ ጠብቋቸው” እንደ ሰበብ በማቅረብ የተሳሳቱ ዝንባሌዎችን በውስጣቸው ያሳድጋሉ፡፡ በዚህ መንገድ የተሳሳቱ ልማዶች ሁለተኛ ተፈጥሮ እስኪሆኑ ድረስ እንዲጠናከሩ ይተዋሉ። ልጆች ለእነርሱ የእድሜ ልክ እርግማን እና ሌሎች ላይ ለመስፋፋት ተወቃሽ ሊያደርጋቸው ከሚችል ባህሪይ ጋር ገደብ ሳይደረግባቸው ያድጋሉ፡፡ CGAmh 219.2

    ለቤተሰቦች ወጣቶች የራሳቸውን መንገድ እንዲከተሉ ከመፍቀድ የላቀ እርግማን የለም፡፡ ወላጆች የልጆቻቸውን ምኞት ሁሉ ሲያሟሉ እና ለጥቅማቸው እንደማይሆን በሚያውቁት ነገር ፍላጎታቸውን ሲያረኩ፣ ብዙም ሳይቆይ ልጆቻቸው ለወላጆቻቸው ያላቸውን አክብሮት፣ የእግዚአብሔር ወይም የሰው ስልጣን ይተዋሉ፣ በሰይጣን ፈቃድም ተማርከው ይወሰዳሉ፡፡8Patriarchs and Prophets, 578, 579.CGAmh 219.3

    የቤት ውስጥ ሥልጠናን ከሌሎች ጉዳዮች አስቀድሙ— ብዙዎች አገልጋዮች፣ መምህራንን እና ሌሎች በትምህርታቸው እና በኃይማኖተኝነታቸው ከፍተኛ አክብሮት ያላቸውን ሰዎች በመጠቆም፣ እነዚህ የላቀ ዕድል ያላቸው ሰዎች በቤተሰብ አስተዳደር ረገድ ካልተሳካላቸው በጥሩ ሁኔታ ላይ የሌሉ ሰዎች ስኬታማ ለመሆን ተስፋ የላቸውም ሲሉ አጥብቀው ይከራከራሉ፡፡ ሊፈታ የሚገባው ጥያቄ፣ እነዚህ ሰዎች መብታቸው የሆነውን— ጥሩ ምሳሌ፣ የታማኝነት መመሪያ፣ እና ትክክለኛውን ገደብን ለልጆቻቸው ሰጥተዋልን? እንደነዚህ አይነቶቹ ወላጆች በአእምሮ ሚዛናዊነት የጎደላቸው፣ ገደብ ሲደረግባቸው ትዕግሥት የሌላቸውን እና የተግባራዊ ህይወት ግዴታዎችን የማያውቁትን ልጆች ለህብረተሰቡ የሚሰጡት እነዚህን ወሳኝ ነገሮችን ችላ በማለት ነው፡፡ በዚህ መንገድ እነርሱ በሥራቸው ከሚያከናውኗቸውን መልካም ነገሮች ሁሉ ይልቅ ዓለም ላይ ጉዳት እያደረሱ ነው፡፡ እነዚያ ልጆች የራሳቸውን የባህሪይ ጠማማነት ለልጆቻቸው በውርስ ያስተላልፋና በተመሳሳይ ጊዜም ክፉ ምሳሌነታቸው እና ተጽዕኖአቸው ማህበረሰቡን ብልሹ ያደርጋል፣ በቤተክርስቲያንም ውስጥ ከፍተኛ ጥፋትን ይሰራሉ፡፡ ማንም ሰው ችሎታው እና ጠቃሚነቱ ታላቅ ቢሆንም እንኳ የራሱን ልጆች ችላ በማለት ጊዜውን ለሌሎች ነገሮች በመስጠት ላይ ሳለ፣ እግዚአብሔርን ወይም ዓለምን ለማገልገል የተሻለ ነው ብሎ ማሰብ አንችልም፡፡ 438The Signs of the Times, February 9, 1882.CGAmh 219.4

    ሰማያዊ ትብብር ቃል ገብቷል— እግዚአብሔር ፍትሃዊ እና ትክክለኛ ሥልጠናን ይባርካል። ነገር ግን “ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም” ይላል ክርስቶስ፡፡ የሰማይ አካላት ልጆቻቸውን ለማሠልጠን ችላ ከሚሉ፣ ትንሹን የሕጻኑ መሳሪያ የሆነውን የወጣትነት አዕምሮ ሰይጣን ከመንፈስ ቅዱስ አሠራር በተቃራኒ ለመስራት እንዲጠቀምበት ከሚፈቅዱለት አባቶች እና እናቶች ጋር መተባበር አይችሉም፡፡ 439Manuscript Releases 126, 1897.CGAmh 220.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents