Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የልጅ አመራር

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ክፍል 2—ስልቶችና መጽሐፍት

    ምዕራፍ 4—የማስተማሪያ ስልቶች

    የወላጆች አስተዳደር ሊጠና ይገባል — የወላጅ ሥራ እንደሚጠበቅበት የሚሰራው አልፎ አልፎ ብቻ ነው….፡፡ ወላጆች፣ የልጆቻችሁን ፈቃድና ስሜት በብልሃት ማሰልጠን ትችሉ ዘንድ የወላጅትን አስተዳደር ታጠናላችሁን? ለጋ ቀንበጦቻችሁ ለእርዳታ እግዚአብሔር ላይ መጠማጠም ይችሉ ዘንድ አስተምሯቸው፡፡ እንዲሰሩ የተፈለገው ነገር ላይ ግድ የለሽ በመሆን ይህን አድርግ ወይም ያን አታድርግ ማለት በቂ አይደለም፣ እንዲህም ሲሆን ልጆዎ ትዕዛዝዎን ለመተግበር ጠንቃቃ አይሆንም፡፡ ልጅዎ ትዕዛዝዎን ይተገብር ዘንድ ሁኔታዎችን ያመቻቹ፤ ልጆች ኢየሱስን እንዲጠማጠሙ ያስተምሯቸው…፡፡ በሕይወት ውስጥ በሚገጥሟቸው ጥቃቅን ነገሮች ላይ የጌታን እርዳታ መጠየቅ እንዲችሉ፤ መወጣት ያለባቸውን ትናንሽ ኃለፊነቶቻቸውን ለማወቅ በውል ይነቁ ዘንድ፤ እና ቤት ውስጥ ለመርዳት ዝግጁ ይሆኑ ዘንድ አስተምሯቸው፡፡ እናንት የማታስተምሯቸው እንደሆነ፣ የሚያስተምራቸው ሌላ አካል አለ፣ ምክንያቱም ሰይጣን በልባቸው ውስጥ የእንክርዳድ ዘር ለመዝራት መልካም አጋጣሚዎችን ይጠብቃል፡፡ 32Manuscript Releases 5:1896.CGAmh 29.1

    በእርጋታ መንፈስና በፍቅር ልብ ሥራዎን ይጀምሩ — እህቴ፣ እግዚአብሔር የእናትነትን የኃላፊነት አደራ ሰጥቶሻልን? ... ልጆችሽ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ፣ ለማሰልጠን ትክክለኛውን ዘዴ መማርና ብልሃትን ማግኘት ይኖርብሻል፡፡ ለልጆቻችሁ ትምህርትና ስልጠና የዕረፍትን መንፈስ ታመጡ ዘንድ፤ በቅዱስ ተስፋ እነርሱን ለመሙላት እና ቅን፣ ንጹህና ቅዱስ ነገሮችን ማፍቀርን በውስጣቸው ለማሳደግ፣ ከፍተኛውን የአዕምሮና የነፍስ ብልሃት ማሳደግ ያስፈልግዎታል፡፡ እንደ ትሁት የእግዚአብሄር ልጅ፣ በክርስቶስ ትምህርት ቤት ይማሩ፣ በቤት ውስጥ መመሪያ በመስጠት እና ተምሳሌት በመሆን እጅግ ፍጹም፣ ጥንቃቄ የተሞላበት ስራን እንድትፈጽሙ ሃይልዎን ለማሻሻል በየጊዜው ይፈልጉ፡፡ 33 The Review and Herald, September 15, 1891.CGAmh 29.2

    የጸጥታና የጨዋነት ባህሪይ ውጤት—ሕጻናትን በመንከባከብም እንኳ የእርጋታና የጽኑነትን ውጤት የሚገነዘቡ ጥቂቶች ናቸው፡፡ የእናት ወይም የአሳዳጊ ረጋ ያለ ባሕሪይ የሕጻናትን ነርቭ (ሕብረ-ሕዋስ) የማረጋጋት ዝንባሌ ሲኖረው፣ ብስጩና ትዕግስት የሌላት ስትሆን ግን በእቅፏ ባለ ሕጻን ውስጥ የብስጩነትን ባህሪይ ትፈጥራለች፡፡ 34 Pacific Health Journal, January, 1890.CGAmh 30.1

    ጽንሰ-ሐሳቦች መፈተን ይኖርባቸዋል— በመጽሐፍት ጥናት የተገኙ ሐሳቦች ወደ የዕለት ተዕለት ተግባር ያልተተረጎሙ እንደሆነ ጠቀሜታቸው አናሳ ነው፡፡ እናም የሌሎች ሰዎች እጅግ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው አመለካከቶች ሳይታሰብበትና ሳይመረመሩ ተቀባይነት ሊኖራቸው አይገባም፡፡ እነዚህ ሀሳቦች ለእያንዳንዱ እናት ወይም በቤተሰቡ ውስጥ ላለው ለእያንዳንዱ ልጅ ልዩ ሁኔታን ወይም ባህሪይን በእኩልነት በማገናዘብ ተግባር ላይ የሚውሉ አይደሉም፡፡ እናቶች የሌሎችን ልምምድ በጥንቃቄ ይመርምሩ፣ በሚጠቀሙባቸው ዘዴዎች መካከል ያለውን ልዩነት ልብ ይበሉ፣ እውነተኛ ዋጋም ያላቸው እንደሆኑ በጥንቃቄ ይፈትኑ፡፡ 35The Signs of the Times, February 9, 1882.CGAmh 30.2

    በድሮ ጊዜያት የሚጠቀሟቸው ዘዴዎች— ከቀደምት ጊዜያት ጀምሮ ተማኞች የሆኑ እስራኤላውያን ለትምህርት ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረት ይሰጡ ነበር፡፡ ልጆች ገና ከሕጻንነታቸውም ጀምሮ እንኳን በተለይም በሕጉ እንደተገለጠውና በእስራኤል ታሪክ እንደታየው ስለ እርሱ መልካምነትና ታላቅነት መማር አለባቸው፡፡ አዕምሮን ለመክፈት በታለመ መዝሙር፣ ጸሎት እና የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች፣ የእግዚአብሔር ሕግ የባህርይው መገለጫ እንደሆነ እና የሕጉም መርሆዎች ልብ ላይ ተቀባይነትን ሲያገኝ የእግዚአብሔር አምሳል አዕምሮና ነፍስ ላይ እንደሚቀረጽ አባቶችና እናቶች ልጆቻቸውን ማስተማር አለባቸው፡፡ በትምህርት ቤትም ሆነ በቤት ውስጥ የአብዛኞቹ ትምህርቶች የማስተማሪያ ዘዴ ቃል ነበር፣ ነገር ግን ወጣቶች የዕብራይስጡንም ጽሑፎች ይማር ነበር፡፡ የብሉይ ኪዳንን የብራና ጽሁፎችንም ያጠኑ ዘንድ ክፍት ነበር፡፡ 36Fundamentals of Christian Education, 442.CGAmh 30.3

    በርህራሄና በፍቅር አስተምሯቸው— ልጆቻቸውን በርህራሄና ፍቅር ማስተማር የአባቶችና የእናቶች ልዩ ተግባር ነው፡፡ እንደ ወላጆች እነርሱ ናቸው መስመሩን መያዝ፣ በልጆቻቸው መመራት ሳይሆን መምራት እንዳለባቸው ማሳየት አለባቸው፡፡ ታዛዥነት ከእነርሱ እንደሚጠበቅ ልጆቻቸውን ማስተማር አለባቸው፡፡ 37Letter 104, 1897. CGAmh 31.1

    በተፈጥሮ እረፍት የለሽ መንፈስ ወደ አደጋ ያዘነብላል፤ ንቁ አዕምሮ በተሻለ ነገር እንዳይያዝ የተተወ ከሆነ ሰይጣን የሚያቀርበውን ሐሳብ ይቀበላል፡፡ ልጆች ደህንነት ያላው ጎዳና ላይ እንዲሄዱ፣ ከመጥፎ ምግባር እንዲርቁ፣ በርህራሄ እንዲሸነፉ እና መልካም የመሥራት ማረጋገጫን እንዲያገኙ ምሪት ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ 38Letter 28, 1890. CGAmh 31.2

    አባቶችና እናቶች የተከበረ ሥራ አለባችሁ፡፡ የልጆቻችሁ የዘላለም ድነት በተግባራችሁ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ልጆቻችሁን በተሳካ መልኩ ማስተማር የምትችሉት እንዴት ነው? በቁጣ አይሁን ምክንያቱም ምንም መልካም ውጤት አይኖረውም፡፡ ልክ በችሎታቸው ላይ እምነት እንዳለው ሰው ከልጆቻችሁ ጋር ተነጋገሩ፡፡ ከእርሱ ጋር አብሮ ሠራተኞች ይሆኑ ዘንድ መማር እና መሠልጠን እንዳለባቸው እግዚአብሔር እንደሚፈልግ ንገሩአቸው፡፡ የድርሻችሁን ከተወጣችሁ ጌታ ድርሻውን እንደሚወጣ ማመን ትችላላችሁ፡፡ 39Manuscript Releases 3:3, 1909.CGAmh 31.3

    የውይይት ጊዜን መመደብ— እያንዳንዷ እናት የልጆቿን ስህተቶች ለማረም እና ትክክለኛውን መንገድ በትዕግስት ለማስተማር ከእነርሱ ጋር ለመወያየት ጊዜ መመደብ አለባት፡፡ CGAmh 31.4

    መመሪያ የሚሰጥበትን መንገድ መቀያየር— ታላቅና ድንቅ የአዕምሮ ኃይልን ለመማረክ ሲባል መመሪያ የሚሰጥበትን መንገድ በመቀያየር፣ የወጣቶችን ትምህርት ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረግ አለበት፡፡… አዕምሮ በእጅጉ የሚፈልጋቸውን ነገሮች፣ እድገት ላይ ያለውን አዕምሮ እንዴት መምራት እንዳለባቸው፣ እና በማደግ ላይ ያሉ አስተሳሰቦችና ስሜቶችን የሚረዱ ጥቂቶች ናቸው፡፡ 40Counsels to Parents, Teachers, and Students, 73.CGAmh 31.5

    የመጀመሪያዎቹን ትምህርቶች ከቤት ውጭ ያስተምሩአቸው— እናቶች ሆይ ልጆቻችሁ ከቤት ውጭ አየር ላይ ይጨወቱ፤ የወፎችን ዝማሬ በመስማት ውብ ሥራዎቹ ውስጥ የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ፍቅር ይማሩ፡፡ ከተፈጥሮ መጽሐፍ እና ስለ እነዚህ ጉዳዮች ቀለል ያሉ ትምህርቶችን አስተምሩአቸው፤ አዕምሮአቸውም እየሰፋ ሲሄድ ትምህርቶች ከመጽሐፍት ሊታከሉ እና ልቦናቸው ላይ በደንብ እንዲሰርጹ ማድረግ ይቻላል፡፡ 41Counsels to Parents, Teachers, and Students, 146CGAmh 32.1

    እርሻ ለሕጻናት እና ለወጣቶች መልካም ሥራ ነው፡፡ ይህም ከተፈጥሮና ከተፈጥሮ አምላክ ጋር በቀጥታ እንዲገናኙ ያደርጋቸዋል፡፡ ይህንንም ዕድል እንዲያገኙ በተቻለ መጠን ከትምህርት ቤቶቻችን ጋር ተቆራኝተው ሰፊ የአበባ መስኮችና የእርሻ መሬቶች መኖር አለባቸው፡፡ CGAmh 32.2

    ከእንደዚህ አይነቶቹ አከባቢዎች ውስጥ የሚገኝ ትምህርት እግዚአብሔር ለወጣቶች ትምህርት ይሆን ዘንድ ከሰጠው መመሪያ ጋር የሚስማማ ነው፡፡CGAmh 32.3

    በተለይም የመጽሐፍ ትምህርት አድካሚና ለማስተወስ ከባድ ለሚሆንበት ስልቹ ልጅ ወይም ወጣት ይህ ጠቃሚ ይሆናል፡፡ ተፈጥሮን በማጥናት ጤና እና ደስታን ያገኛል፤ ሁል ጊዜ በፊቱ ከሚኖሩ ነገሮች ጋር የተቆራኘም በመሆኑ፣ በዚህ ሁኔታ የተፈጠረ አሻራ ከአዕምሮ ሊደበዝዝ አይችልም፡፡ 42Counsels to Parents, Teachers, and Students, 186, 187.CGAmh 32.4

    ትምህርቶቹን አጭር እና ማራኪ ያድርጉ— ወላጆች በጥንቃቄ፣ ሥርዓት በሥርዓት፣ እና ትዕዛዝ በትዕዛዝ፣ ትምህርቶችን አጭርና ማራኪ በማድረግ፣ መመሪያን በመስጠት ብቻ ሳይሆን ምሳሌ በመሆንም ጭምር ትምህርት በመስጠት ድርሻቸውን ሲወጡ ጌታ ከጥረቶቻቸው ጋር በመስራት ብቁ መምህራን ያደርጋቸዋል፡፡ 13 The Signs of the Times, August 13, 1896.The Signs of the Times, August 13, 1896CGAmh 32.5

    “ቀለል አድርጎ፣ ደጋግሞ መናገር”— ልጆችን የሚያስተምሩ ሰዎች የአሰልቺነትን አሰተያየት ማስወገድ አለባቸው፡፡ አጭር እና ጉዳዮ ላይ ብቻ ያተኮረ አስተያየት አስደሳች ተጽዕኖ ይኖረዋል፡፡ ብዙ ማባል ያለበት ጉዳይ ካለ ድግግሞሹ እንዳለ ሆኖ አጭርና ግልጽ ይሁን፡፡ ሁሉንም ነገር በአንዴ ከመናገር ይልቅ በወቅቱ የተፈለጉ ውስን ቃላትን ደጋግሞ መናገሩ ጠቃሚ ነው፡፡ ረጅም ንግግር የልጆች ጨቅላ አዕምሮ ላይ ሸክም ይሆናል፡፡ ከልክ በላይ መመገብ ጨጓራ ላይ ሸክም በመሆን እና የምግብ ፍላጎትን በመቀነስ ምግብን ወደ መጥላት እንደሚያመራ ሁሉ እጅግ ረጅም ንግግር ልጆች መንፈሳዊውን መመሪያ እንኳ እንዲጠሉ ይመራቸዋል፡፡ የሰዎች አዕምሮ ከመጠን በላይ በመናገር ተሞልተዋል፡፡ 43Testimonies For The Church 2:420. 15Education, 119.CGAmh 33.1

    ገለልተኛ አስተሳሰብን መበረታታት— ልጆችና ወጣቶች እውነታዎችን ከአስተማሪዎችና ከመማሪያ መጻሕፍት እውቀት ማግኘት ቢኖርባቸውም እንኳ በራሳቸው ትምህርት ለማግኘት እና እውነትን ለይቶ ለማወቅ ይማሩ፡፡ በእርሻ ሥራ ላይ ዕፅዋትን በመንከባከብ ያገኙት ትምህርት ምን እንደሆነ ይጠይቋቸው፡፡ ውብ የሆነውን መልክአ ምድርን ሲመለከቱ እግዚአብሔር መስኮችን እና እንጨቶችን በማሩና የተለያዩ ቀለማት ለምን እንደሸፈነ ይጠይቁአቸው፡፡ ሁሉም ጥቁር ቡኒ ቀለም ያልኖራቸው ለምንድነው? አበቦችን ሲለቅሙ ከኤደን ተለይተው የወጡትን እነዚህን ውበቶች ለምን እንዳስቀረልን እንዲያስቡ ምሯቸው፡፡ በየትኛውም ሥፍራ የሚገኙት ማስረጃዎች እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን አስተሳሰብ በግልጽ የሚያሳዩ እንደሆነ፤ ሁሉም ነገር በአስደናቂ ሁኔታ ስምሙ የሆነው ለእኛ ጥቅም እና ደስታ እንደሆነ እንዲያስተውሉ አስተምሯቸው፡፡ 15.CGAmh 33.2

    የልጅነት ተግባራት ላይ ምሪት መስጠት—ወላጆች የልጆቻቸውን የልጅነት ተግባራት ላይ ጫና መፍጠር አስፈላጊ እንደሆነ ሊሰማቸው አይገባም፣ ነገር ግን ትክክለኛ እና ተገቢ ወደ ሆነው አቅጣጫ እነርሱን መምራትና ማሰልጠን አስፈላጊ እንደሆነ መረዳት አለባቸው፡፡ እነዚህ ንቁ ስሜቶች ልክ እንደ ሐረግ ያልተገሩ እንደሆነ እያንዳንዱ ጉቶና ጭራሮ ላይ በመሮጥ ሀረጎቻቸውን ያልረባ ድጋፍ ላይ እንዲጠመጠም ያደርጋሉ፡፡ ሐረጎቹ ተገቢ ወደ ሆነው ድጋፍ ያልተመሩ እንደሆነ ዓላማ በሌለው ነገር ላይ ጉልበታቸውን ያባክናሉ፡፡ ልጆች ላይም የሚከሰተው ተመሳሳይ ነገር ነው፡፡ ተግባሮቻቸው ወደ ትክክለኛው አቅጣጫ መመራት አለበት፡፡ አካላቸውን እና አዕምሮአቸውን ማጎልበት የሚችል ነገር እንዲሰሩ ለእጆቻቸውና ለአዕምሮአቸው ሥራ ስጡአቸው፡፡ 44The Signs of the Times, August 13, 1896. CGAmh 33.3

    በለጋ ዕድሜአያቸው ሌሎችን መርዳት እንዳለባቸው ያስተምሩአቸው— ልጆች በለጋ እድሜያቸው ሌሎችን ስለ መርዳት መማር አለባቸው፡፡ ልክ ጥንካሬና የምክንያታዊነት ኃይል እንደጎለበተ፣ ቤት ውስጥ የሚወጣው ኃላፊነት ሊሰጠው ይገባል፡፡ አባትና እናትን ለመርዳት በሚያደርገው ሙከራ ሊበረታታ ይገባል፣ ራሱን እንዲክድ ሊበረታታ ይገባል፣ ከራሱ በፊት የሌሎችን ደስታ እና ምቾት እንዲያስቀድም፣ ወንድሞቹን፣ እህቶቹን እና የጨዋታ ጓደኞቹን ለማስደስት እና ለመርዳት አጋጣሚዎችን እንዲፈልግ፣ እና ለአረጋውያን፣ ለታማሚዎች እና ለችግረኞች ርህራሄን እንዲያሳይ ሊበረታታ ይገባል፡፡ እውነተኛ የአገልግሎት መንፈስ ቤት ውስጥ በሙላት በሰፈነ ቁጥር፣ ሙሉ በሙሉ በልጆች ሕይወትም እድገትን ያገኛል፡፡ ለሌሎች ሰዎች ጥቅም በመገልገልና መስዋዕት በመሆን ደስታን መፈለግን ይመራሉ፡፡ 45The Ministry of Healing, 401.CGAmh 34.1

    ወላጆች፣ ልጆቻችሁ እንደ ቤተሰብ አባልነት በእርግጥ ያለባቸውን ኃላፊነት በመወጣት የእግዚአብሔርን ፍቃድ እንዲያደርጉ እርዱአቸው፡፡ ይህ እጅግ ዋጋ ያለውን ተሞክሮ ይሰጣቸዋል፡፡ ራሳቸውን በማስደሰት ሐሳቦቻቸውን ወደ ራሶቻቸው እንዳያደርጉ ያስተምራቸዋል፡፡ በቤተሰብ ውስጥ የራሳቸውን ድርሻ እንዲወጡ በትዕግስት አስተምሯቸው፡፡ 46The Review and Herald, November 17, 1896.CGAmh 34.2

    ጥቂት በጥቂቱ ትኩረት በማድረግ፣ ብዙ ጊዜ በመደጋገም ባህሪዎቻቸውን ይቅረጹ—ወላጆች፣ ልጆችን በማሰልጠን ረገድ እግዚአብሔር በተፈጥሮ ውስጥ የሰጠውን ትምህርት ያጥኑ፡፡ ስለ ሐምራዊ ወይም ስለ ሮዝ ወይም ስለ ነጭ አበባ ማስተማር ብትፈልጉ በምን መልኩ ነው ይህን የምታደርጉት? እያንዳንዱ ቅርንጫፍ እና ቅጠል በምን ሂደት ውብ ሆኖ እንደበለጸገ እና በሚዛናዊነትና አስደሳችነት እንዳደገ አትክልተኛውን ይጠይቁ፡፡ ትህትና በጎደለው ንክኪ ወይም በኃይለኛ ጥረትም እንዳልሆነ ይነግራችኋል፣ ምክንያቱም እንዲህ አይነቱ ንክኪና ጥረት አደጋ የማይችለውን ግንድ ከመስበር ውጭ ሌላ ምንም ሊያደርግለት አይችልም፡፡ ይህ ሊሆን የሚችለው ጥቂት በጥቂቱ ሆኖ የድግግሞችሽ ትኩረት በመስጠት ነው፡፡ አፈርን በማርጠብ በዕድገት ላይ ያሉ ተክሎችን ከሀይለኛ ነፋስና ከጸሐይ ቃጠሎ በመከላከል ውብ ሆነው እንዲበለጽጉና እንዲያብቡ እግዚአብሔር ያደርጋቸዋል፡፡ ከልጆቻችሁ ጋር ባላችሁም ግንኙነት የአትክልተኛውን ዘዴ ተጠቀሙ፡፡ የፍቅር አገልግሎት በተሞላበት ረጋ ያላ ንካት ባህሪያቸውን በክርስቶስ ምሳሌ ቅረጹ፡፡ 47The Desire of Ages, 516.CGAmh 34.3

    ለጥቃቅን ነገሮች ትኩረት ይስጡ— ልጆችና ወጣቾችን በማሰልጠን ረገድ እነርሱን ባለሟል ማድረግ፣ ማሞላቀቅ እና ከተገቢው በላይ ብርቅዬ በማድረግ እንዴት ያለ ትልቅ ስህተት ይሰራል! በሕይወት ጎዳና ውስጥ በሚገጥሟቸው ጥቃቅን ጉዳዮች ላይ ራስ ወዳዶች፣ ብቃት እና ኃይል የሌላቸው ይሆናሉ፡፡ ምንም እንኳ ተራ ቢሆኑም እንኳ የዕለት ተዕለት ተግባራትን ለማከናወን የሚያስችላቸውን ሥልጠና አላገኙም፡፡ …CGAmh 35.1

    ማንም ሰው ትናንሽ ኃላፊነቶችን በተማኝነት ሳይወጣ ታላቅና ከፍተኛ ለሆነ ሥራ ብቁ ሊሆን አይችልም፡፡ ባህሪይ የሚቀረጸው እና እንዲከናወን ከታለመው ሥራ ጋር ተመጣጣኝ ጥረትና ኃይል እንዲያወጣ ነፍስ የሚሰለጥነው ደረጃ በደረጃ ነው፡፡ 48Testimonies For The Church 3:46, 47 CGAmh 35.2

    ተሰጥኦ ያላቸው ልጆች ከፍተኛ ጥንቃቄ ይፈልጋሉ— ልጆች እንዳሰኛቸው ይሄዱ እና ይገቡ፣ ይለበሱ እና ያደርጉ ዘንድ የራሳቸው እንዳልሆኑ በአዕምሮአቸው ላይ መቅረጽ አለብን፡፡… ማራኪ ተክለ ሰውነትና እና ከተለምዶ ውጭ የሆነ የተፈጥሮ ችሎታዎች ያሏቸው እንደሆነ እነዚህ ተሰጥኦዎች ወደ እርግማን እንዳይለወጡባቸው እና ራስን መቆጣጠርን ለሚሹ የሕይወት እውነታዎች እነርሱን ብቃት የሌላቸው ለማድረግ ጥቅም ላይ እንዳይውሉ፣ እና በከንቱ ውዳሴ፣ ከንቱነት እና ለታይታ ባላቸው ፍቅር ለተሻለ ሕይወት ገጣሚ ያልሆኑ እንዳያደርጋቸው በትምህርታቸው ላይ ከፍተኛ ጥነቃቄ ሊደረግ ይገባል፡፡ 49The Signs of the Times, December 9, 1875.CGAmh 35.3

    ተገቢ ያልሆነ ትኩረት ወይም ከንቱ ውዳሴ ከመስጠት ይታቀቡ— ልጆች ትንሽ ትኩረት ይሰጣቸ፡፡ ራሳቸውን በራሳቸው እንዴት ማስደሰት እንዳለባቸውም ይማሩ፡፡ ልዩ የአዕምሮ ችሎታ ወይም ጥበብ እንዳላቸው ጎብኚዎች ፊት ማሳያ አታድርጓቸው፣ ነገር ግን በተቻለ መጠን በልጅነታቸው የተለመደ አቀራረብ ተውአቸው፡፡ እጅግ ብዙ ልጆች አይን አውጣ፣ ደፋር እና ባለጌ የሚሆኑበት ትልቁ ምክንያት ከፍተኛ ተገቢ ያሆነ ትኩረት ስለሚሰጣቸው፣ ከመጠን በላይ ስለሚወደሱ እና የብልጠት እና የብልሃት ቃላቸው እነርሱ እየሰሙ ስለሚደጋገም ነው፡፡ ከልክ በላይ አትገስጹአቸው፣ በከንቱ ውዳሴም አትሙሉአቸው፡፡ ሰይጣን በጨቅላ ልባቸው ላይ ወዲያው ክፉ ፍሬ ስለሚዘራ በተግባሩ ልትተባበሩት አይገባም፡፡ 50The Signs of the Times, February 9, 1882.CGAmh 36.1

    ለልጆቻችሁ አንብቡላቸው— አባቶች እና እናቶች መጽሐፎቻችን እና ሕትመቶቻችን በማጥናት ማግኘት የምትችሉትን እርዳታ ሁሉ አግኙ፡፡ ለልጆቻችሁ ለማንበብ ጊዜ ውሰዱ፡፡…. እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል የየዕለቱን የሥራ ውጥረትን ወደ ጎን በመተው ለጥናት የሚተባበርበትን የቤተሰብ የንባብ ጊዜ ይኑረው፡፡ በተለይም ልብ ወለድ እና ርካሽ የታሪክ መጽሐፍትን ከማንበብ ጋር የተላመዱ ወጣቶች የቤተሰብን የምሽት ጥናትን በመቀላቀል ተጠቃሚዎች ይሆናሉ፡፡ 51Counsels to Parents, Teachers, and Students, 138. CGAmh 36.2

    “መንገር” ሳይሆን “ማሰልጠን”— ልጆቻቸውን ለወደፊቱ የዘላለም ሕይወት የማስተማር እና የማሰልጠን ታላቅ ሥራ ወላጆች ላይ ተጥሎባቸዋል፡፡ አያሌ ወላጆች ጨቅላ ልጆቻቸውን ከመገቧቸውና ካለበሷአቸው፣ እንደ ዓለማዊ መስፈርትም ካስተማሯቸው ኃላፊነታቸውን እንደተወጡ ያስባሉ፡፡ የልጆቻቸውን ትምህርት የሕይወታቸው ጥናት እነዳያደረጉ በሥራቸው ወይም በተድላቸው እጅግ ተወጥረዋል፡፡ ተሰጥኦአቸውን ለአዳኛቸው ክብር ማዋል እንዳይችሉ እነርሱን ማሰልጠን አይፈልጉም፡፡ ሰለሞን “ልጅ የሚሄድበትን መንገድ ንገረው፣ በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም፡፡” ሳይሆን “ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው፣ በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም፡፡” ነው ያለው፡፡ 24The Review and Herald, June 24, 1890.CGAmh 36.3

    ራስን መቆጣጠርን አስተምር—እስካሁን በሰው ልጅ ከተከናወኑ ሥራዎች ውስጥ ለልጆችና ለወጣቶች ተገቢ ስልጠናና ትምህርትን ከመስጠት በተሻለ ከፍተኛ ጥንቃቄና ጥበብን የሚጠይቅ ሌላ ተግባር የለም፡፡ በልጅነት ጊዜያችን የሚከቡን አይነት ኃይለኛ ተጽዕኖዎች በማናቸውም ዕድሜ ውስጥ የሉም፡፡… የሰው ልጅ ተፈጥሮ ሦስት ድርብ ሲሆን ስልጠና የአካል፣ የአዕምሮና የግብረ-ገብ ትክክለኛ እድገቶችን ማጠቃለል እንዳለበት ሰለሞን ምክር ይሰጣል፡፡ ይህንን ሥራ በትክክል ለመስራት ወላጆችና መምህራን “ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው” የሚለውን ራሳቸውም ማወቅ አለባቸው፡፡ ይህም ከመጽሐፍ እውቀት ወይም ትምህርት ቤት ከሚገኝ ትምህርት የላቀ እውቀትን የሚያቅፍ ነው፡፡ መሻትን መግዛትን፣ ወንድማዊ ርህራሄን እና እግዚአብሔርን መምሰልን፤ ለራሳችን፣ ለባልንጀሮቻችን እና ለእግዚአብሔር የሚጠበቅብንን ኃላፊነት መወጣትን የሚይዝ ነው፡፡ CGAmh 37.1

    የልጆች ስልጠና ማገናዘብ የማይችሉ እንስሶች ከሚሰለጥኑበት መርህ የተለየ መሆን አለበት፡፡ እንስሳው ለጌታው እንዲገዛ ብቻ ሲሆን፣ ልጅ ግን ራሱን እንዲገዛ መማር አለበት፡፡ ፈቃድ ለምክንያታዊነት እና ለህሊና ትዕዛዝ እንዲገዛ መሰልጠን አለበት ፡፡ ልጅ ምናልባት እንደ እንስሳ የራሱ ፈቃድ፣ የራሱ ስብእና በመምህሩ ስብእና እንዲደበቅ ተደርጎ ሊሰለጥን ይችላል፡፡ እንዲህ አይነቱ ሥልጠና ጥበብ የጉደለው እና አውዳሚ ውጤትም የሚያስከትል ነው፡፡ በዚህ መንገድ የተማሩ ልጆች የጽናትና የውሳኔ ብቃት የሌላቸው ይሆናሉ፡፡ ተግባራቸው ከመርሕ የመነጨ አንዲሆን አልተማሩም፤ የማገናዘብ ኃይላቸውም በልምምድ አልጠነከረም፡፡ በተቻለ መጠን እያንዳንዱ ልጅ ራሱን እንዲችል ተደረጎ ስልጠና ሊሰጠው ይገባል፡፡ የተለያዩ የተፈጥሮ ችሎታዎችን ወደ ተግባር በማምጣት፣ ምን ላይ ጠንካራ እንደሆነና ምን ላይ ጉደለት እንዳለው መማር ይችላል፡፡ ጥበበኛ መምህር ደካማ የሆነው የልጁ ባህሪይ እንዴት እያደገ እንደሆነ ልዩ ትኩረት በመስጠት፣ ሚዛናዊና ቅንጅታዊ ባህሪይ እንዲኖረው ማድረግ ይችላል፡፡ 52Fundamentals of Christian Education, 57.CGAmh 37.2