Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የልጅ አመራር

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ምዕራፍ 39—ፈቃድ እንደ አንድ የስኬት ምክንያት

    እያንዳንዱ ልጅ የፈቃድን ኃይል መገንዘብ አለበት— በሰዎች ተፈጥሮ ውስጥ ፈቃድ ሌሎች የተፈጥሮ ችሎታዎን በቁጥጥሩ ሥር የሚያደርግ ገዢ ሀይል ነው። ፈቃድ ስሜት ወይም ዝንባሌ አይደለም፣ ነገር ግን በሰው ልጆች ውስጥ ለእግዚአብሔር መታዘዝ ወይም አለመታዘዝን የሚሰራ የውሳኔ ኃይል ነው። 390Testimonies For The Church 5:513.CGAmh 198.1

    እያንዳንዱ ልጅ የፈቃድን ትክክለኛ ኃይል መገንዘብ አለበት። በዚህ ስጦታ ውስጥ ተካትቶ ያለውን ኃላፊነት ምን ያህል ትልቅ እንደሆነ እንዲመለከት መመራት አለበት፡፡ ፈቃድ… የውሳኔ ኃይል ወይም ምርጫ ነው፡፡ 391Education, 289.CGAmh 198.2

    ስኬት የሚመጣው ፈቃድ ለእግዚአብሔር ሲገዛ ነው—የማሰብ ችሎታ ያለው እያንዳንዱ ሰው ትክክለኛውን ነገር የመምረጥ ኃይል አለው፡፡ በእያንዳንዱ የሕይወት ልምምድ ውስጥ የእግዚአብሔር ቃል ለእኛ “የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ፡፡” (ኢያሱ 24፡15) የሚለው ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው ፈቃዱን በእግዚአብሔር ፍቃድ ጎን ማድረግ ይችላል፣ እርሱን ለመታዘዝ መምረጥ ይችላል፣ እናም እራሱን ከመለኮታዊ ወኪሎች ጋር በማጣማር አንዳችም ነገር ክፉን እንዲያደርግ በማያስገድደው ሥፍራ ላይ መቆም ይችላል፡፡ በእግዚአብሔር እርዳታ፣ የሐቀኝነትን ባህርይ ለመቅረጽ እና የጠቃሚነትን ሕይወት ለመኖር በእያንዳንዱ ወጣት፣ በእያንዳንዱ ልጅ ውስጥ ኃይል ተቀምጧል።CGAmh 198.3

    በእንደዚህ ዓይነቱ መመሪያ ልጁን እራሱን እንዲገዛ የሚያሠለጥን ወላጅ ወይም መምህር እጅግ ጠቃሚ እና በቋሚነት ስኬታማ ይሆናል፡፡ ለጥራዝ ነጠቅ ተመልካች ሥራው የተሻለ ጥቅም እንዳለው ላይታየው ይችላል፤ በፍፁም ስልጣን ስር የልጁን አእምሮ እና ፍላጎት እንደሚይዝ ሰው ያን ያህል ዋጋ ያለው ላይሆን ይችላል፤ ነገር ግን ከዓመታት በኋላ የተሻለውን የሥልጠና ዘዴ ውጤት ያሳያል።3Ibid.CGAmh 198.4

    የልጁን ፈቃድ ያቅኑ እንጂ አያዳክሙት—የፈቃድን ብርታት እንዳይጠፋ ያድርጉ፣ ምክንያቱም የሰው ልጅ ይህንን ይፈልገዋል፤ ነገር ግን ወደ ትክክለኛው አቅጣጫ ይምሩት፡፡ እንደ የተቀደሰ ሀብት በጥበብ እና በትህትና ይያዙት። እስኪሰባበር ድረስ አይቀጥቅጡት፣ ነገር ግን በመመሪያ እና እውነተኛ ምሳሌ ልጅዎ ኃላፊነት መቀበል እስከሚችልበት ዕድሜ ድረስ ያስተካክሉት፣ ይቅረጹትም፡፡ 392 Counsels to Parents, Teachers, and Students, 116.CGAmh 199.1

    ልጆች ፈቃዶቻቸውን እና ዝንባሌያቸውን ለወላጆቻቸው ፈቃድ እና ስልጣን እንዲያስገዙ ከልጅነታቸው መሰልጠን አለባቸው፡፡ ወላጆች ይህንን ትምህርት ልጆቻቸውን ሲያስተምሩ፣ ለእግዚአብሔር ፈቃድ እንዲገዙ እና ለእርሱ መጠይቆች እንዲታዘዙ እያስተማሯቸው እና የክርስቶስ ቤተሰብ አባላት እንዲሆኑ እያበቋቸው ነው፡፡393Manuscript Releases 11:9, 1899. CGAmh 199.2

    መምራት እንጂ መጭፍለቅ የለበትም— ተገቢ ባልሆነ ቁጥጥር ሳያስተጓጉሉ የልጅን እድገት መምራት የወላጅ እና የመምህር ጥናት መሆን አለበት። ከተፈለገው በታች ቁጥጥር ማድረግ እጅግ መጥፎ እንደሆነው ሁሉ ከመጠን በላይ የሆነ ቁጥጥርም እንዲሁ ነው፡፡ የልጁን “ፈቃድ ለማፍረስ” የሚደረግ ጥረት በጣም ትልቅ ስህተት ነው፡፡ አዕምሮዎች በተለያየ አይነት ሁኔታ የተፈጠሩ ናቸው፤ ኃይል ታይታዊ መገዛትን ሲያመጣ፣ አያሌ ልጆች ላይ ይበልጥ ቆራጥ የሆነ ልባዊ የአመጽ ውጤት ይኖረዋል፡፡ ወላጅ ወይም መምህር የሚፈልገውን ቁጥጥር በማድረግ ቢሳካለትም እንኳ በልጁ ላይ የሚያመጣው ውጤት ያን ያህል ቀላል ያለ አደጋ የሚኖረው አይሆንም…፡፡ CGAmh 199.3

    ለአንዳንድ ተማሪዎች ከሌላው ይልቅ ፈቃድን ማስገዛት በጣም ከባድ ስለሆነ፣ መምህሩ ለመጠይቆቹ መታዘዝን በተቻለው መጠን ቀላል ማድረግ አለበት፡፡ ፈቃድ ምሪት ማግኘት እና መቀረጽ አለበት እንጂ ችላ መባል እና መጨፍለቅ የለበትም። 394Education, 288, 189.CGAmh 199.4

    መምራት እንጂ በጭራሽ በኃይል መግፋፋት አይገባም— በእርሶ ቁጥጥር ስር ያሉት ልጆች ያራሳቸው ስብዕና እንዲኖራቸው ያድርጉ፡፡ ዘወትር ይምሯቸው እንጂ በጭራሽ በኃይል አይገፋፏቸው፡፡ 395Testimonies For The Church 5:65.CGAmh 200.1

    ፈቃድን ሥራ ላይ ማዋል አእምሮን ያሰፋል፣ ያጠነክራልም— አንድ ልጅ የገዛ ፈቃድ እንዳይኖረው… ተደርጎ የተመራ ሊሆን ይችላል። ግላዊ ስብዕናው እንኳን በሚያሰለጥነው ሰው ስብዕና ውስጥ ሊጨፈለቅ ይችላል፤ ፈቃዱ፣ በሁሉም ፍላጎቶችና ዓላማዎች ረገድ ለመምህሩ ፈቃድ ተገዢ ይሆናል። በእንደዚህ አይነት መንገድ የተማሩ ልጆች በሥነምግባር ሀይል እና በግለሰብ ኃላፊነት ሁል ጊዜ ደካማ ይሆናሉ፡፡ ከምክንያታዊነት እና መርኾ በመነሳት አንድ ነገር ማድረግን አልተማሩም፤ ፈቃዳቸው በሌላ ሰው ፈቃድ ቁጥጥር ሥር ሆኗል፣ አዕምሮን በማሰራት እንዲሰፋና እንዲጎለብት አልተደረገም፡፡ በተፈለገበት ጊዜ ከፍተኛ ኃይሎቻቸውን እንዳይጠቀሙ ከልዩ ችሎታዎቻቸው እና የአዕምሮ አቅማቸው ጋር በተያያዘ ምሪት አላገኙም፣ አልሰለጠኑምም፡፡ 396Counsels to Parents, Teachers, and Students, 74.CGAmh 200.2

    የፈቃድ ግጭት በሚኖርበት ጊዜ— ልጁ ግትር ፈቃድ ካለው፣ እናት ኃላፊነቷን የተረዳች እንደሆነ፣ ይህ ግትር ፈቃድ እርሷ በዘር ውርስ ከሰጣችው አንዱ ክፍል እንደሆነ ትገነዘባለች፡፡ የእርሱን ፈቃድ መሰበር የለበት ነገር እንደሆነ ማየት የለባትም፡፡ የእናት ውሳኔ ከልጇ ውሳኔ ጋር የሚስማማበት ጊዜ፣ ጽኑ እና በሳል የእናቲቱ ፈቃድ ምክንያታዊነት ከጎደለው የልጁ ፈቃድ ጋር የሚስማማበት ጊዜ፣ እና እናት እድሜዋ እና ልምዷ በሰጣት ዕድል የተነሳ የምትገዛበት ጊዜ፣ ወይም ታላቅ የታናሽን፣ ማለትም ያልሰለጠነ የልጁን ፈቃድ የሚገዛበት ጊዜ አለ። በእንደዚህ አይነት ጊዜያት ታላቅ ጥበብ ያስፈልጋል፤ ምክንያቱም ጥበብ በጎደለው አያያዝ፣ በከፋ ግዳጅ፣ ልጁ ለዚህ እና ለመጻኢው ህይወት ሊሞላቀቅ ይችላል፡፡ በጥበብ ጉድለት ሁሉም ነገር ሊበላሽ ይችላል፡፡ CGAmh 200.3

    ይህ አልፎ አልፎ እንዲመጣ የተፈቀደ ቀውስ ነው፣ ምክንያቱም እናት እና ልጅ ከባድ ትግል ስለሚኖራቸው ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱን ችግር ለማስወገድ ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረግ አለበት፡፡ ነገር ግን እንደዚህ ዓይነት ጉዳይ ከገባ በኋላ ልጅ ለላቀ የወላጅ ጥበብ እንዲገዛ መመራት አለበት፡፡ እናት ቃላቶቿን በፍጹም ቁጥጥር ሥር ማድረግ ይኖርባታል። የጩኸት ደምጽ ትዕዛዞች ሊኖሩ አይገባቸውም። በልጁ ውስጥ የእምቢተኝትን መንፈስን የሚያዳብር ምንም ነገር መደረግ የለበትም። እናት እርሱን ወደ ኢየሱስ መሳብ በሚቻልበት መንገድ እንዴት መያዝ እንደምትችል ማጥናት አለባት፡፡ ሰይጣን በልጇ ፈቃድ ላይ አሸናፊነትን እንዳያገኝ በእምነት መጸለይ አለባት፡፡ የሰማይ መላእክት ትዕይንቱን እየተመለከቱ ናቸው፡፡CGAmh 200.4

    እናት እግዚአብሔር ረዳቷ መሆኑን መገንዘብ አለባት፣ ያ ፍቅር ስኬትዋ፣ ኃይሏም ነው። ጥበበኛ ክርስቲያን ከሆነች ልጇ እንዲገዛላት ለማስገደድ አትሞክርም፡፡ ትፀልያለች፣ ስትጸልይም በውስጧ የመንፈሳዊ ሕይወት እድሳት እንሚሆን ታውቃለች። በእርሷ ውስጥ እየሰራ ያለው ኃይል በተመሳሳይ ጊዜ በልጁ ውስጥም እየሰራ መሆኑን ታያለች። ልጁ ከሚገደድ ይልቅ የተመራ እና ገር እየሆነ ያድጋል፤ ውጊያውም ላይ ድል ይገኛል። እያንዳንዱ የርህራሄ ሐሳብ፣ እያንዳንዱ የትዕግስት ተግባር፣ እያንዳንዱ የጥበብ ገድብ ቃል፣ በብር ምስሎች ውስጥ እንዳለ እንደ ወርቅ ፖም ነው። እናት ቋንቋ ሊገልፀው ከሚችለው በላይ ውድ የሆነ ድል አግኝታለች፡፡ ብርሃኗ ታድሷል፣ ልምዷም ጨምሯል፡፡ ወደ ዓለም ለሚመጣው ለእያንዳንዱ ሰው የሚያበራው “እውነተኛው ብርሃን” ፈቃዷን አስገዝቷል። ከዝናብ በኋላ ፀሐይ ብርሃን እንደሚያበራ ሁሉ፣ ከወጀቡ በኋላ ሰላም አለ። 397Letter 55, 1902.CGAmh 201.1

    ወላጆች የወጣትነት ስሜታቸውን ይዘው ማቆየት አለባቸው— የራሳቸውን የወጣትነት ስሜቶች እና በተፈጥሮአቸው ሀይለኛ እና ርህራሄ የሌላቸው አለመሆንን በተቻለ መጠን የማቆየትን አስፈላጊት የሚገነዘቡት በጣም ጥቂቶች ናቸው። የልጅን ለዛ ያለውን ቀለል ያለ የአኗኗር ዘይቤን ከጎልማሳ ወንድነት እና ሴትነት ብርታት፣ ጥበብ እና በሳልነት ጋር የሚቀላቅሉ ወላጆች እንዲኖሩት እግዚአብሔር ይመኛል፡፡ አንዳንዶች እውነተኛ የልጅነት ሕይወት አልነበራቸውም። የቀንበጥነት ሕይወት ነፃነትን፣ ቀላል የአኗኗር ዘይቤን እና አፍላነትን በጭራሽ አለጣጣሙትም። የልጁ የዋህነት እና የመተማመን ግልፀኝነት በፍርሃት፣ በምቀኝነት፣ በቅናት፣ እና በአታላይነት እስኪለወጥ ድረስ ተሰድቧል፣ ችላ ተብሏል፣ ተገስጿል እንዲሁም ተገርፏል፡፡ እንደነዚህ ያሉት የራሳቸውን ውድ ልጆች ልጅነትን አልፎ አልፎ ብቻ የሚያስደስት ባህሪይ አሏቸው፡፡398Good Health, March, 1880.CGAmh 201.2

    ታላቅ ስህተት— የመቆጣጠሪያ መስመሮች በልጁ እጅ ሲሆን እና ቤት ውስጥ እርሱ በበላይነት ጫና አንዲያደረግ እና እንዲቆጣጠር በማድረግ ትልቅ ስህተት ይፈጸማል። ይህ ለዚያ አስደናቂ ለሆነው የፈቃድ ሀይል አግባብነት የሌለው ምሪት መስጠት ማለት ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ሲደረግ ቆይቷል፣ ወደ ፊትም በቀጣይነት ይደረጋል፣ ምክንያቱም አባቶች እና እናቶች በማስተዋል እና በስሌታቸው እውሮች ናቸው፡፡ 399Manuscript Releases 12:6, 1897. CGAmh 202.1

    ለሚያለቅስ ልጇ የምትሸነፍ እናት— ልጅዎን… በትክክል ለመምራት የጥበብ እጅ ይፈልጋል፡፡ ይህንን የማድረግ ልማድ እስከሚፈጥር ድረስ ለፈለገው ነገር እንዲያለቅስ ይፈቀድለታል፡፡ ለአባቱ እንዲያለቅስ ይፈቀድለታል፡፡ ይህንን ነገር ጉዳይ እስኪያደርግ ድረስ እርሱ እየሰማ በተደጋጋሚ ለአባቱ እንዴት እንደሚያለቅስ ለሌሎች ይነገራቸዋል፡፡ ልጅዎ እኔ ጋር ቢሆን ኖሮ በሦስት ሳምንታት ውስጥ ይለወጥ ነበር፡፡ ቃሌ ሕግ መሆኑን እንዲገነዘብ አደርገዋለሁ፣ እናም በትህትና ነገር ግን በጽናት ዓላማዎቼን እፈጽማለሁ፡፡ የእኔን ፈቃድ ለልጁ ፈቃድ አላስገዛም፡፡ እዚህ ጋር የሚሠሩት ሥራ አለዎት፣ ከዚህም በፊት ይህን ባለማድረግዎ ብዙ ነገር ጠፍቷል፡፡12Letter 5, 1884..CGAmh 202.2

    የብልሹ ልጅ ደስተኛ ያልሆነ ሕይወት— እያንዳንዱ በጥንቃቄ እና በጸሎት ያልተገራ ልጅ በዚህ የሙከራ ጊዜ ውስጥ ደስተኛ አይሆንም፣ እንዲሁም ጌታ በሰማይ ካሉ ቤተሰቦቹ ጋር አንድ ሊያደርገው የማያስችለውን ክፉ ባሕርያትን ይቀርጻል። በብልሹ ልጅ ሕይወት ውስጥ መከናወን ያለበት በጣም ትልቅ ሸክም አለ፡፡ በመከራ፣ በተስፋ መቁረጥ፣ በፈተና ውስጥ ያልተማረ፣ በተሳሳተ አቅጣጫ የተመራ ፈቃዱን ይከተላል፡፡ 400Manuscript Releases 12:6, 1897.CGAmh 202.3

    የራሳቸውን መንገድ እንዲከተሉ የሚፈቀድላቸው ልጆች ደስተኞች አይደሉም፡፡ ያልሸነፈ ልብ በራሱ የዕረፍትና የዕርካታ መሰረተ ነገሮች የሉትም፡፡ ባህሪይ የእኛን ማንነት ከሚገዛው የጥበብ ህጎች ጋር እንዲስማማ አእምሮ እና ልብ በተገቢው ገደብ ስር መሆን አለባቸው። መቁነጥነጥ እና አለመርካት እንደፈለጉ የመሆን እና የራስ ወዳድነት ፍሬዎች ናቸው። 401Testimonies For The Church 4:202.CGAmh 202.4

    የብዙ ፈተናዎች መንስኤ— ለቤተክርስቲያን ብልጽግና እጅግ አደገኛ መሆናቸው የተረጋገጠላቸው፣ እና ዓለማውያን እንዲደናቀፉና በጥርጣሬ እና ባለመርካት ወደ ኋላ እንዲመለሱ ሰበብ የሆኑት፣ አሳዛኝ ፈተናዎች ብዙውን ጊዜ የሚነሱት ወላጆች በልጅነታቸው ልቅ ፍላጎትን የማርካት ፍሬ የሆኑት ያልተገራ እና የአመፅ መንፈስ ናቸው፡፡ አዕምሮ ተጽዕኖ ሥር መውደቅ በሚችልበት፣ ልብ ለቅን ነገር በቀላሉ ተጽዕኖ ሥር መሆን በሚችልበት ጊዜ እና ፈቃድ በእናት የፍቅር ቁጥጥር ሥር በነበረበት፣ በልጅነት ቁጥጥር ሥር መዋል ይችሉ በነበሩ በቅጽበተ በሚነሱ ስሜቶች ተጽዕኖ ሥር በመሆን ስንት ሕይወት ተጎዳ፣ ስንት ወንጀሎች ተፈጽመዋል፡፡ በቂ ያልሆነ የልጆች ሥልጠና በስፋት ለተንሰራፈው ምግበረ ብልሹነት ዋና መንስኤ ነው፡፡ 402IbidCGAmh 203.1