Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የልጅ አመራር

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 23—ራስን መካድ፣ ራስን አለመውደድ እና አሳቢነት

    በእያንዳንዱ ቤት ውስጥ የሚያስፈልጉ ትምህርቶች—በእያንዳንዱ ቤት ራስን የመካድ ትምህርቶች ሊስተማር ይገባል። አባቶችና እናቶች፣ ልጆቻችሁን ቁጠባ አስተምሯቸው፡፡ ሳንቲሞቻቸውን ለሚስዮናዊ ሥራ እንዲቆጥቡ አበረታቷቸው፡፡ ምሳሌያችን ክርስቶስ ነው፡፡ በእርሱ ድህነት እኛ ባለ ጠጎች እንድንሆን እርሱ ስለ እኛ ድሀ ሆነ። ሁሉም በፍቅር እና በአንድነት ወደ አንድነት እንዲመጡ፣ እርሱ እንደሰራ እንዲሰሩ፣ እርሱ መስዋእት እንደ ሆነ ሁሉ መስዋዕት እንዲሆኑ፣ እንደ እግዚአብሔር ልጆች መዋደድ እንዳለባቸው አስተምሯል፡፡ 224Testimonies For The Church 9:130, 131.CGAmh 124.1

    ራስን የመካድ ትምህርት በመማር ልጆችዎንም ያስተምሯቸው። ራስን በመካድ ሊቆጠቡ የሚችሉ ሁሉ አሁን ሊሰራ ላለው ሥራ ተፈላጊ ነው፡፡ የሰዎችን ሥቃይ ያስታግሱ፣ እርቃናቸውን ያሉትን አልብሱ፣ የተራቡ ይመገቡ፤ ለዚህ ጊዜ አስፈላጊ የሆነ እውነት ለማያውቁት ሰዎች መነገር አለበት። 225Messages to Young People, 314.CGAmh 124.2

    መስዋእትነት ልማድ መሆን አለበት—በሕግ እና ምሳሌ ራስን መካድን፣ ቁጠባን ፣ ልበ ሰፊነትን እና በራስ መደገፍን ያስተምሩአቸው። እውነተኛ ባህሪይ ያለው ማንኛውም ሰው ችግሮችን ለመቋቋም ብቁ እና “ጌታ እንዲህ ይላል” የሚለውንም ለመከተል ፈጣን ይሆናል፡፡ ሰዎች በክርስቶስ ትምህርት ቤት ውስጥ ራስን የመገደብን ቀንበር መሸከምን እና መታዘዝን እስኪማሩ ድረስ ለእግዚአብሔር ያላቸውን ግዴታ ለመረዳት ዝግጁ አይሆኑም፡፡ መስዋእትነት እውነትን ለማስፋፋት እና ተቋማትን ለማቋቋም የሥራችን መጀመሪያ ነው። ይህ የትምህርት አስፈላጊው አካል ነው፡፡ በእጆች ያልተሠራ ሕንፃ በመንግሥተ ሰማይ ውስጥ ለዘላለም ለመኖር ከፈለግን፣ መስዋዕትነት በዚህ የምድር ሕይወት ባህሪያችንን በመገንባት ሂደት ውስጥ ልማዳዊ መሆን አለበት፡፡ 226Testimonies For The Church 6:214.CGAmh 124.3

    ራስን የመካድ ሣጥን—ልጆች እራሳቸውን መካድ የተማሩ መሆን አለባቸው፡፡ በአንድ ወቅት፣ ናሽቪል ውስጥ ስናገር፣ ጌታ በዚህ ጉዳይ ላይ ብርሃን ሰጠኝ፡፡ በሁሉም ቤት ውስጥ ራስን የመካድ ሳጥን መኖር አለበት፣ እናም በዚህ ሳጥን ውስጥ ልጆች ለከረሜላ እና ለሌሎች አላስፈላጊ ነገሮች የሚያውሏቸውን ሳንቲሞች ማስቀመጥ እንደሚኖርባቸው በታላቅ ኃይል ብርሃን በእኔ ላይ በራብኝ…፡፡ CGAmh 125.1

    ልጆች ሳንቲሞቻቸውን በእነዚህ ሳጥኖች ውስጥ ሲያኖሩ፣ ትልቅ በረከት እንደሚያገኙ ታያላችሁ…፡፡ እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል፣ ከታላቅ እስከ ታናሹ ራስን መካድን መለማመድ አለበት። 227The Review and Herald, June 22, 1905.CGAmh 125.2

    ልጆች የስበት ማዕከል መሆን የለባቸውም—ከሁለት እስከ አራት ዓመት ዕድሜ ያላቸው ልጆች የፈለጉትን ሁሉ ማግኘት አለብን ብለው እንዲያስቡ መበረታታት የለባቸውም፡፡ ወላጆች ራስን የመካድ ትምህርቶችን ሊያስተምሯቸው እና በጭራሽ እነርሱ ማዕከል እንደሆኑ እና ሁሉ ነገር በእነርሱ ዙሪያ መሽከርከር እንዳለበት እንዲያስቡ በሚያደርግ መንገድ መያዝ የለባቸውም፡፡ CGAmh 125.3

    ብዙ ልጆች የራስ ወዳድነትን ከወላጆቻቸው ወርሰዋል፣ ነገር ግን ወላጆች ከተፈጥሮዎቻቸው ውስጥ የዚህን ክፉ አዝማሚያ ሥር ሁሉ ለመንቀል መሻት አለባቸው። ክርስቶስ ስግብግብ እና ራስ ወዳድ የሆኑ ብዙዎችን ገስጸዋል፡፡ ወላጆች፣ በልጆቻቸው ፊት ወይም ከሌሎች ልጆች ጋር በሚሆኑበት ጊዜ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገለጡ የራስ ወዳድነትን ባሕሪያትን ከልጆቻቸው ባህሪይ ውስጥ መገደብ እና መንቀልን መሻት አለባቸው። 228The Signs of the Times, August 13, 1896.CGAmh 125.4

    አንዳንድ ወላጆች ልጆቻቸውን ለማዝናናት ብዙ ጊዜ እና ትኩረት ይሰጣሉ፣ ነገር ግን ልጆች እራሳቸውን ለማዝናናት፣ የራሳቸውን ብልሃትና እና ችሎታ እንዲጠቀሙ ስልጠና ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ በዚህ መንገድ በጣም ቀለል ባሉ ደስታዎች መርካትን ይማራሉ፡፡ ትናንሽ ተስፋ አስቆራጭ ነገሮችን እና ፈተናዎችን በድፍረት እንዲሸከሙ መማር አለባቸው፡፡ ለእያንዳንዱ ትናንሽ ህመም ወይም ጉዳት ሁሉ ትኩረት ከመስጠት ይልቅ፣ ትኩረታቸውን ይቀይሩ፤ ትናንሽ የሚያበሳጩ ወይም ምቾት የማይሰጡ ነገሮችን በቀላሉ ማለፍ ይችሉ ዘንድ አስተምሯቸው። 229The Ministry of Healing, 389CGAmh 125.5

    ራስን የመርሳት ጸጋ—እያንዳንዱ ልጅ በተለይም ሊንከባከባቸው እና ሊያዳብራቸው ከሚገባው ባህሪዎች አንዱ ሳይታሰብ ወደ ሕይወት የሚመጣውን ጸጋን የሚያላብሰውን ያን ራስን መርሳት ነው፡፡ ይህ ከሁሉም ምርጥ ባህሪያት ውስጥ እጅግ በጣም የሚያምር እና ለሁሉም እውነተኛ የሕይወት ሥራዎችም በጣም አስፈላጊ ከሆኑት ብቃቶች አንዱ ነው፡፡ 230 Education, 237. CGAmh 126.1

    ልጆች ለሌሎች አሳቢ እንዲሆኑ እንዴት ማስተማር እንዳለባችሁ አጥኑ። ወጣቶች መገዛትን፣ ራስን መካድ እና ለሌሎች ደስታ ትኩረት መስጠትን ገና ከልጅነታቸው መማር አለባቸው። ግልፍተኝነትን ማሸነፍን፣ ስሜት ቀስቃሽ ቃላትን መግታትን፣ ተለዋዋጭ ያልሆነ ደግነትን፣ ጨዋነትን እና ራስን መግዛትን ለማሳየት መማር አለባቸው፡፡ 231Counsels to Parents, Teachers, and Students, 123, 124. CGAmh 126.2

    እያንዳንዷን የራስ ወዳድነት ዝንባሌን ለማስቀረት ወላጆች ልጆቻቸውን እንዴት በጥንቃቄ መያዝ ይኖርባቸው ይሆን! ልጆቻቸው ለሌሎች ማሰብ እንዲችሉ እና ሁሉንም ነገር ለሚያደርጉላቸው ለአባቶቻቸው እና እናቶቻቸው አንድ ነገር መስራትን ለመማር የሚያስችሏቸው መንገዶች ላይ በቀጣይነት ሐሳብ ማቅረብ አለባቸው፡፡ 9The Signs of the Times, August 13, 1896.CGAmh 126.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents