Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የልጅ አመራር

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 38—ዕድሜ፣ ፀባይ እና ስሜትን ያጥኑ

    ልጆች ከልጅነታቸው እንዲወጡ አታስቸኩሏቸው—ወላጆች ልጆቻቸውን ከልጅነታቸው እንዲወጡ ፈጽሞ ማስቸኮል የለባቸውም፡፡ የሚሰጣቸው ትምህርት ልባቸውን ለከበሩ ዓላማዎች የሚያነቃቃ አይነት ባህርይ ያለው ይሁን፤ ነገር ግን ልጆች እንደሆኑ እና ወደ መንግስተ ሰማይ ለመግባት የሚዘጋጃቸውን ከየዋህነት እምነት፣ ከቅንነት እና ከእውነትኛነት ጋር ይደጉ። 378 Good Health, March, 1880.CGAmh 193.1

    ለእያንዳንዱ ዕድሜ ተገቢ የሆነ ውበት አለ—ወላጆች እና መምህራን ወጣቶች በእያንዳንዱ የዕድሜ ደረጃ ልክ ተክሎች በአትክልት ሥፍራ እንደሚያደርጉት ተፈጥሮን በማንጸባረቅ ለተወሰነ ዕድሜ ተገቢ የሆነ ውበትን እንዲያሳዩ ዝንባሌዎቻቸውን ለማሳደግ ማቀድ አለባቸው፡፡2Education, 107.CGAmh 193.2

    ከክርስቶስ ምሳሌዎች መካከል አንዱ እጅግ በጣም ውብ እና አስደናቂ የሆነው የዘሪው እና የዘሩ ምሳሌ ነው…፡፡ ይህ ምሳሌ የሚያስተምራቸው እውነቶች በራሱ በክርስቶስ ሕይወት ውስጥ ሕያው እውነታ ሆኖ ነበር፡፡ እርሱ በአካላዊም ሆነ በመንፈሳዊ ተፈጥሮው ውስጥ ወጣቱ ሁሉ እንዲያደርገው የሚመኘውን በተክሎች የተገለፀውን መለኮታዊ የእድገት ቅደም ተከተል ተከትሏል። ምንም እንኳን የሰማይ ባለ ግርማ፣ የክብር ንጉስ ቢሆንም፣ በቤተልሔም ሕፃን ሆነ፣ ለተወሰነ ጊዜም በእናቱ እንክብካቤ ሥር አቅመ ቢስ ሕፃን ሆኗል።CGAmh 193.3

    ኢየሱስ በልጅነቱ አንድ ታዛዥ ልጅ የሚሰራቸውን ሥራዎችን ሠርቷል፡፡ ወላጆቹን በማክበር እና በልጅ አቅም አጋዥ በሆነ መንገድ ምኞቶቻቸውን በማከናወን፣ በአዋቂ ሰው ጥበብ ሳይሆን በልጅ ጥበብ ይናገር፣ ያደርግም ነበር፡፡ ነገር ግን በእያንዳንዱ የእድገት ደረጃው ኃጢአት አልባ የሆነው ሕይወቱ በየዋህና ተፈጥሮአዊ ጸጋው ፍጹም ነበር፡፡ ቅዱሱ መዝገብ ስለ ልጅነትነቱ እንዲህ ይላል፣ “ሕፃኑም አደገ፣ ጥበብም ሞልቶበት በመንፈስም ጠነከረ፤ የእግዚአብሔርም ጸጋ በእርሱ ላይ ነበር፡፡” እንዲሁም ስለ ወጣትነቱ እንዲህ ተብሎ ተመዝግቧል “ኢየሱስም ደግሞ በጥበብና በቁመት በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ያድግ ነበር።” ሉቃስ 2:40፣ 52፡፡ 379Counsels to Parents, Teachers, and Students, 140, 141.CGAmh 193.4

    በቤተሰብ አባላት ውስጥ ያለው የፀባይ ልዩነት—በተደጋጋሚ ጉልህ የፀባይ እና የባህርይ ልዩነቶች በአንድ ቤተሰብ ውስጥ ይገኛሉ፣ ምክንያቱም የተለያዩ ስሜት ያላቸው ሰዎች አንድ ላይ እንዲሆኑ የእግዚአብሔር አሰራር ነው፡፡ ጉዳዩ እንደዚህ በሚሆንበት ጊዜ እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ስሜቶች ዋጋ እንዳላቸው በመመልከት የሌሎችን መብት ማክበር አለበት። በዚህ መንገድ የጋራ መከባበር እና መቻቻል ያድጋል፣ ጭፍን ጥላቻ ይቀዘቅዛል፣ የባህሪይ አስቸጋሪ ነጥቦችም የተስተካከሉ ይሆናሉ። ስምምነት ሊገኝ ይችላል፣ የተለያዩ ፀባዮች ውህደትም ለእያንዳንዱ ሰው ጥቅም ሊሆን ይችላል፡፡ 380The Signs of the Times, September 9, 1886.CGAmh 194.1

    የግለሰብ አእምሮዎችን እና ባህሪዎችን ማጥናት—ወደ ዓለም እንዲመጣ የተደረገ እያንዳንዱ ልጅ ወላጆች ላይ ኃላፊነትን ይጨምራል…፡፡ ፀባዮቻቸው፣ ዝንባሌዎቻቸው፣ ባህሪዎቻቸው መጠናት አለባቸው። የተሳሳቱ ዝንባሌዎችን ለመቆጣጠር እና ትክክለኛ ተፅዕኖዎችን እና መርሆዎችን ለማበረታታት እንዲችሉ የወላጆች የማስተዋል ኃይሎች እጅግ በጥንቃቄ የሰለጠኑ መሆን አለባቸው። CGAmh 194.2

    በዚህ ሥራ ውስጥ ኃይለኝነት ወይም ጨቋኝነት አያስፈልግም። ራስን መግዛት መቻል ማደግና በልጁ አእምሮ እና ልብ ላይ ተጽዕኖውን እንዲያሳርፍ መተው አለበት፡፡ 381 Manuscript Releases 12:1898.CGAmh 194.3

    የሰው አእምሮ ላይ መስራት በጣም ጥሩ ሥራ ነው፡፡ በአንዱ ልጅ ላይ መደረግ ያለበት ቁጥጥር የሌላውን ሕይወት ሊጨፈለቅ ስለሚችል ሁሉም ልጆች በተመሳሳይ መንገድ መያዝ የለባቸውም፡፡ 382Manuscript Releases 3:2, 1899.CGAmh 195.1

    የደከሙ ባህርያትን ማነቃቃት፤ የተሳሳቱትን መቆጣጠር—ወላጆች የደከሙ ባህሪያትን ለማነቃቃት እና የተሳሳቱትን ለመቆጣጠር እጅግ ግድ የለሾች በመሆናቸው ሚዛናዊ አዕምሮ ያላቸው ጥቂቶች ብቻ ሆነዋል፡፡ ወላጆች የእያንዳንዱን ልጅ ዝንባሌ የመመልከት እጅግ የከበረ ግዴታ ሥር መሆናቸውን፣ ልጆቻቸውን በትክክለኛ ልማዶች እና ትክክለኛ የአስተሳሰብ ጎዳና ማሠልጠን የእነርሱ ግዴታ መሆኑን አያስታውሱም፡፡ 383The Signs of the Times, January 31, 1884.CGAmh 195.2

    የእያንዳንዱን ልጅ ፀባይ ይማሩ—ልጆች የማያቋርጥ እንክብካቤ ሊኖሯቸው ይገባል፣ ነገር ግን እናነተ ሁል ጊዜ እንደምትጠብቋቸው እንዲያዩ መፍቀድ የለባችሁም፡፡ ከሌሎች ልጆች ጋር ባላቸው ሕብረት ውስጥ ይፋ እንደሚሆነው የእያንዳንዳቸውን ባህርይ ተማሩ፣ ከዚያም ተቃራኒ ባህሪያትን በማበረታታት ስህተቶቻቸውን ለማስተካከል ሞክሩ፡፡ ልጆች የአእምሮም ሆነ የአካል ኃይል እድገታቸው በእነርሱ ላይ የተመሠረተ መሆኑን መማር አለባቸው፣ እርሱም የጥረት ውጤት ነው። ደስታ የራስ ወዳድነት ስሜቶችን በማርካት የሚገኝ አለመሆኑን ቀደም ብለው መማር አለባቸው፤ እርሱ ለኃላፊነት ንቁ መሆንን ተከትሎ የሚመጣ ነው። በተመሳሳይ ሁኔታ እናት ልጆቿን ለማስደሰት መሻት አለባት፡፡ 384The Signs of the Times, February 9, 1882.CGAmh 195.3

    የአእምሮ ፍላጎቶች እንደ አካላዊው ሁሉ አስፈላጊ ናቸው—አንዳንድ ወላጆች የልጆቻቸው ጊዜያዊ ፍላጎት በጥንቃቄ ይከታተላሉ፤ ሲታመሙ በርህራሄና በታማኝነት ይንከባከቧቸዋል፣ ከዚያም በኋላ ሥራቸውን እንዳጠናቀቁ ያስባሉ። እዚህ ጋር ተሳስተዋል፡፡ ሥራቸው ገና ነው የጀመረው፡፡ የአእምሮ ፍላጎቶችን መንከባከብ ተገቢ ነው። የተጎዳ አእምሮን ለመፈወስ ተገቢ መፍትሄዎችን ተግባራዊ የማድረግ ችሎታን ይጠይቃል፡፡ CGAmh 195.4

    ልጆች እንደ ጎልማሳ ሰዎች አስቸጋሪ፣ ሊሸከሟቸው ከሚችሉት በላይ የሆነ ፈተና አለባቸው፡፡ ወላጆች እራሳቸውም ሁል ጊዜ ተመሳሳይ ስሜት አይሰማቸውም፡፡ አእምሯቸው ብዙውን ጊዜ ግራ መጋባት ውስጥ ይገባል። በተሳሳተ አመለካከት እና ስሜቶች ውስጥ በመሆን ይሰራሉ። ሰይጣን ያላጋቸዋል፣ ለፈተናዎቹም ይሸነፋሉ። በልጆቻቸው ላይ ቁጣ በሚቀሰቅስ መልኩ በብስጭት ይናገራሉ፣ አንዳንድ ጊዜም ስህተት የሌሽ እና ቁጡ ፍራቻ ይሆናሉ። ሚስኪኖቹ ልጆች ተመሳሳይ መንፈስን ይጋራሉ፣ ወላጆችም ሊረዷቸው ዝግጁ አይደሉም፣ ምክንያቱም የችግሩ መንስኤ ራሳቸው ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሁሉም ነገር በተሳሳተ መንገድ የሚሄድ ይመስላል። በሁሉም ሥፍራ ቁጡነት አለ፣ እናም ሁሉም ምቾት የሌለው፣ ደስተኛ ያልሆነ ጊዜ ያሳልፋሉ፡፡ ወላጆች ወቀሳቸውን ሚስኪን ልጆቻቸው ላይ ይጥላሉ፣ ራሳቸው የችግሩ መንስኤ ሆነው ሳሉ ልጆቻቸው እጅግ የማይታዘዙ እና ስድ፣ በዓለም ላይ ካሉት በጣም መጥፎዎች እንደሆኑም ያስባሉ፡፡ 385Testimonies For The Church 1:384.CGAmh 196.1

    ትህትናን ያበረታቱ—ሚዛናዊነት የጎደለው አዕምሮ፣ ቶሎ ስሜታዊ የሚሆን፣ ቁጡነት፣ ምቀኝነት ወይም ቅናት፣ በወላጅ ቸልተኝነት ላይ ይመሰክራሉ። እነዚህ ክፉ ባህሪዎች ባለቤቱ ላይ ትልቅ ሐዘን ያመጣሉ፡፡ ይበልጥ ትሁት ቢሆኑ ኖሮ ከባልደረቦቻቸው እና ከጓደኞቻቸው ሊያገኙት የሚችሉትን ፍቅር እንዳይቀበሉ የተሳናቸው ስንቶች ናቸው፡፡ በሄዱበት እና በሚሳተፉበት ነገር ሁሉ ችግር የሚፈጥሩ ስንቶች ናቸው! 386Fundamentals of Christian Education, 67. CGAmh 196.2

    የተለያዩ ስሜቶች የተለያዩ ስልጠና ያስፈልጋቸዋል—ልጆች የተለያዩ ስሜቶች አሏቸው፣ እናም ወላጆች ሁል ጊዜ እያንዳንዱን በተመሳሳይ መንገድ ማሰልጠን የለባቸውም። የተለያዩ የአእምሮ ችሎታዎች አሉ፣ እናም እግዚአብሔር ያቀደውን አላማ ለማሳካት እንዲቀረጹ በጸሎት ጥናት ሊያደረጉ ይገባል፡፡ 387 Good Health, July, 1880.CGAmh 196.3

    እናቶች ሆይ፣ …ከልጆቻችሁ ጋር ለመላመድ ጊዜ ውሰዱ፡፡ እነርሱን እንዴት መያዝ እንዳለባችሁ ታውቁ ዘንድ ጸባያቸውን እና ስሜታቸውን አጥኑ፡፡ አንዳንድ ልጆች ከሌሎቹ የበለጠ ትኩረት ይፈልጋሉ፡፡ 388 The Review and Herald, July 9, 1901.CGAmh 196.4

    ተስፋ አስቆራጭ የሆኑ ልጆች አያያዝ—ከሌሎች ይልቅ የበለጠ ትዕግሥት የተሞላበት ተግሳጽ እና ርህራሄ የተሞላበት ሥልጠና የሚሹ አንዳንድ ልጆች አሉ። እነርሱ ተስፋ አስቆራጭ ባህሪዎችን እንደ ቅርስ ተቀብለዋል፣ በዚህ ምክንያት የበለጠ ርህራሄ እና ፍቅር ያስፈልጋቸዋል። እነዚህ ዓመፀኞች ትጋት በተሞላበት ሥራ በጌታ ሥራ ውስጥ ለአንድ መደብ ሊዘጋጁ ይችላሉ፡፡ እነርሱ ያልጎለበቱ ኃይሎች ሊኖራቸው ይችላል፣ እነዚህም ሲነቃቁ፣ ከተጠበቁት ሰዎች ይልቅ ክፍት ቦታዎችን እንዲሞሉ ያስችላቸዋል፡፡CGAmh 197.1

    ልዩ ስሜት ያላቸው ልጆች ካሉዎት፣ በዚህ ምክንያት የተስፋ መቁረጥ አደጋ በህይወታቸው ላይ እንዲያርፍ አይፍቀዱ…። ትዕግስት እና ርህራሄን በመግለጽ መገለጫዎች ይርዷቸው፡፡ የባህሪያቸውን ጉድለቶች ለማሸነፍ በፍቅር ቃላት እና በደግነት ተግባሮች ያበረታቷቸው። 389 Counsels to Parents, Teachers, and Students, 115, 116. CGAmh 197.2

    ከምትገምቱት በላይ ማሠልጠን ትችላላችሁ—እናት ኢየሱስን መውደድ በጀመረችበት ቅጽበት፣ ልጆችን ለእርሱ ማሠልጠን ትፈልጋለች፡፡ የልጆቻችሁን ፀባይ ከልጅነታቸው ጀምሮ ማሰልጠን ከምትገምቱት በላይ ማሰልጠን ትችላላችሁ፡፡ ያ ውድ የኢየሱስ ስም የቤት ቃል መሆን አለበት።14Manuscript Releases 17:1893.CGAmh 197.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents