Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የልጅ አመራር

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ክፍል 15—ገጣሚ የሆነ አለባበስ

    ምዕራፍ 65—አግባብነት ያለው አለባበስ በረከቶች

    ተገቢ እና ተስማሚ— በሌሎች ነገሮች እንደምናደርገው ሁሉ፣ በአለባበስም ፈጣሪያችንን ማክበር ልዩ ዕድላችን ነው፡፡ እርሱ ልብሳችን ንጹህ እና ጤናማ እንዲሆን ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ተገቢ እና ተስማሚ እንዲሆንም ይመኛል፡፡ 808Education, 248.CGAmh 392.1

    እኛ ምርጥ ገጽታ እንዲኖረን መሻት ያስፈልገናል፡፡ እግዚአብሔር በቤተ መቅደስ አገልግሎት ውስጥ በእርሱ ፊት የሚያገለግሉትን ሰዎች አልባሳት በተመለከተ እያንዳንዱን ዝርዝር ለይቶ አስቀምጦ ነበር፡፡ ስለዚህ እርሱን ከሚያገለግሉ ሰዎች አለባበስ ጋር በተያያዘ ምርጫ እንዳለው እንማራለን፡፡ የአሮን አልባሳት ምሳሌ በመሆናቸው አለባበሱን በተመለከተ እጅግ ልዩ መመሪያዎች ተሰጥቶ ነበር፡፡ እንዲሁ የክርስቶስ ተከታዮች አለባበስ ምሳሌ መሆን አለባቸው፡፡ በሁሉ ነገር የእርሱ ወኪሎች መሆን አለብን፡፡ በሁሉ አንፃር ገጽታችን በግሩምነት፣ መጠነኛነት እና ንጽህና የሚታወቅ መሆን አለበት፡፡ 809Testimonies For The Church 6:96.CGAmh 392.2

    በተፈጥሮ ቁሶች ውስጥ ተብራርቷል— በተፈጥሮ ቁሶች [አበቦች] ክርስቶስ አለባበሳችን እርሱን የሚያስደስት እንዲሆን ሰማይ እሴት የሚሰጣውን ውበት፣ ዝግ ያለ ጸጋ፣ ቀለል ማለትን፣ ንጽህና እና ገጣሚነትን አብራርቷል፡፡ 810The Ministry of Healing, 289.CGAmh 392.3

    ባህሪይ በአለባበስ ዘይቤ ሊፈረጅ ይችላል— አለባበስ እና በሰውየው ላይ ያለው የአለባበስ ቅንጅታዊ ሁኔታ በአጣቃላይ የወንድ ወይም የሴት አመልካች ሆኖ ተገኝቷል፡፡ 811The Review and Herald, January 30, 1900.CGAmh 392.4

    የሰውን ባህሪይ በአለባበሱ ዘይቤ እንፈርጃለን፡፡ ዝግ ያለች፣ እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ዝግ ያለ አለባበስ ትከተላለች፡፡ ንጥር ምርጫ፣ የጎለመሰ አዕምሮ፣ ቀለል ያለ እና ተገቢ አልባሳትን በመምረጥ ይገለጣል…፡፡ በአለባበሷ እና በአኳኋኗ ቀለል ያለች እና የማታስመስል ሴት እውነተኛ ሴት በግብረ ገባዊነቷ እንደምትታወቅ መረዳቷን ታሳያለች፡፡ በመልካምነቱ ከመስክ አበባ ጋር የሚነጻጸረው ቀለል ያለ የአለባበስ ዘይቤ እንዴት አስደሳች፣ እንዴት ማራኪ ነው! 812The Review and Herald, November 17, 1904.CGAmh 392.5

    መሪ መርኾዎች ተገልጿል— ሕዝባችን በእግዚአብሔር ፊት በጥንቃቄ እና በአርቆ አሳቢነት እንዲመላለሱ እለምናቸዋለሁ፡፡ በአለባበስ ረገድ በተቻለ መጠን ከጤና መርኾዎች ጋር ስምሙ የሆነ ልማዶችን ተከተሉ፡፡ ብዙዎች እንደሚያደርጉት ጥሩ፣ ዕድሜ ያለው ዕቃ፣ ለዚህ ዘመን ተገቢ የሆነ ልብስ በማግኘት እህቶቻችን ቀለል ያለ አለባበስ ይኑራቸው፣ የአለባበስ ጥያቄም አዕምሮን አይሙላ፡፡ እህቶቻችን ቀለል ያለ አለባበስ መልበስ አለባቸው፡፡ በእፍረት እና ራስን በመቆጣጠር ዝግ ባለ አለባበስ አካላቸውን መሸፈን አለባቸው፡፡ በእግዚአብሔር ጸጋ የተዋበ የውስጣዊ ማንነት ሕያው ምስልን ለዓለም አሳዩ፡፡813Manuscript Releases 16:7, 1897. CGAmh 393.1

    ዝግ ያለ፣ ጤናማ እና አመቺ ከሆነ የተለመደውን ልማድ ተከተሉ— ክርስቲያኖች ከዓለም የተለየ አለባበስ በመልበስ ለእይታ እንደቀረበ ዕቃ በመሆን በዚህ ሳቢያ የሚመሰጣው ስቃይን በመቀበል የለባቸውም፡፡ ነገር ግን በዝግታ እና በጤናማ አለባበስ ረገድ የእምነታቸውን ኃላፊነት ሲከተሉ፣ ራሳቸውን ከፋሽን ውጭ ሆነው ያገኙታል፣ ዓለምን ለመምሰልም አለባበሳቸውን መቀየር የለባቸውም፤ ነገር ግን ሁሉ ዓለም ከእነርሱ የተለየ ከሆነ፣ ቀና ለመሆን የከበረ ኢጥገኝነት እና ግብረ ገባዊ ድፍረት ማሳየት አለባቸው፡፡ CGAmh 393.2

    ዓለም ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ተስማሚ የሆነ ዝግ ያለ፣ አመቺ እና ጤናማ የአለባበስ ዘይቤን ካቀረበ እንደዚህ አይነቱን የአለባበስ ዘይቤ መቀበል ከእግዚአብሔር ወይም ከዓለም ጋር ያለንን ግንኙነት አይለውጠውም፡፡ ክርስቲያኖች ክርስቶስን መከተል እና አለባበሳቸውን ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ማስማማት አለባቸው፡፡ እነርሱ የድጋፍ ጩኸት ወይም ዘለፋ ሳይገዳቸው በትህትና ቀጥተኛውን መንገድ መከተል እና የሚገባው በመሆኑ እውነት ላይ መጣበቅ አለባቸው፡፡ 814Testimonies For The Church 1:458, 459.CGAmh 393.3

    ጽንፈኝነትን ማስወገድ— በአለባበስ ረገድ የማይረባ ፋሽኖችን ሁሉ ለመከተል በመጣር ጊዜያችሁን አታጥፉ፡፡ በጥንቃቄ እና ባማረ ሁኔታ ልበሱ፣ ነገር ግን ከመጠን በላይ በመልበስ ወይም በግድየለሽነት፣ ንጽህና የጎደለውን አለባበስ በመልበስ ትኩረት ሳቢ አርዕስተ ጉዳይ ራሳችሁን አታድርጉ፡፡ የሰማይ ዓይን በእናንተ ላይ እንዳለ እና በእግዚአብሔር ድጋፍ ወይም ተግሳጽ ሥር እንዳላችሁ በማሰብ የምታደርጉትን ነገር አድርጉ፡፡ 815Manuscript Releases 5:3, 1912.CGAmh 394.1

    በአለባበስ ረገድ ጥንቃቄ ማድረግ ከኩራት ጋር መምታታት የለበትም— ያለማቋረጥ ስለ ኩረት እና ስለ አለባበስ የሚያወሩ፣ በአለባበሳቸው ግድየለሽ የሆኑ እና ቆሻሻ መሆን እና ያላ ደንብ እና ምርጫ መልበስን እንደ ጥሩነት የሚቆጥሩ ሰዎች አሉ፤ ልብሶቻቸው አብዛኛውን ጊዜ የሚበር እና ሰውነታቸው ላይ የተለጠፈ ይመስላል፡፡ ልብሶቻቸው ቆሻሻ ናቸው ፤ ሆኖም እንደነዚህ ያሉት ሰዎች ሁልጊዜ የኩራት ተቃዋሚዎች ናቸው። መልካም ምግባርን እና ንፅህናን በኩራት ጎራ ይመድባሉ፡፡ 816The Review and Herald, January 23, 1900.CGAmh 394.2

    በአለባበሳቸው ግድየለሾች እና ንጹህ ያለሆኑ ሰዎች በንግግራቸው እምብዛም የተከበሩ እና ብዙም ያልጣራ ሰሜት ያላቸው ናቸው፡፡ አንዳንዴ እነርሱ ራስን እንደ ማዋረድ የሚቆጥሩት ለየት ማለትን እና ከርዳዳ መሆንን ነው፡፡ 817The Review and Herald, January 30, 1900.CGAmh 394.3

    ክርስቶስ ጥንቃቄ አድርጓል— ክርስቶስ ሰዎች ለአለባበስ ያላቸውን ፍቅር በማስተዋል ተከታዮቹ በጣም ብዙ እንዳይጨነቁለት አዝዟል፡፡ ስለ ልብስስ ስለ ምን ትጨነቃላችሁ? የሜዳ አበቦችን እንዴት እንዲያድጉ ልብ አድርጋችሁ ተመልከቱ፤ አይደክሙም አይፈትሉምም፡፡ ነገር ግን እላችኋለሁ ፣ ሰሎሞንስ እንኳ በክብሩ ሁሉ ከእነዚህ እንደ አንዱ አልለበሰም።” … ኩራት እና በአለባበስ ረገድ ብኩን መሆን በተለይ ሴቶች ተጋላጭ የሆኑበት ኃጢአቶች ናቸው፣ ስለሆነም እነዚህ ትዕዛዞች በቀጥታ ከእሷ ጋር የተዛመዱ ናቸው። ከኢየሱስ ገርነት እና አስደሳችነት ጋር ሲወዳደር ወርቅ፣ ዕንቁ ወይም እጅግ ውድ ዋጋ ባለቸው ልብሾች ማሸብረቅ ምን ያህል ዋጋቸው አነስተኛ ነው! 818Christian Temperance and Bible Hygiene, 93, 94.CGAmh 394.4

    የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ለእግዚአብሔር ሕዝብ— ወደሚከተሉት ጥቅሶች ተወሰድኩ፡፡ መልአኩም “እነርሱ የእግዚአብሔርን ህዝብ ሊያስተምሩ ይገባል” አለኝ፡፡ 1ኛ ጢሞቴዎስ 2: 9, 10: - “እንዲሁም ሴቶች ደግሞ በሚገባ ልብስ ከእፍረትና ራሳቸውን ከመግዛት ጋር ሰውነታቸውን ይሸልሙ፤ እግዚአብሔርን እንፈራለን ለሚሉ ሴቶች እንደሚገባ፣ መልካም በማድረግ እንጂ በሽሩባና በወርቅ ወይም በእንቁ ወይም ዋጋው እጅግ በከበረ ልበስ ይሸለሙ፡፡” 1ኛ ጴጥሮስ 3: 3-5: - “ለእናንተም ጠጉርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጎናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ፣ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ፡፡ እንግዲህ በቀድሞ ዘመን በእግዚአብሔር ተስፋ ያደረጉት ቅዱሳን ሴቶች ደግሞ… እንዲሁ ተሸልመው ነበር፡፡” 819Testimonies For The Church 1:189.CGAmh 395.1

    ብዙዎች እነዚህን ትዕዛዛት ተቀባይነትን ያገኙ ዘንድ ጊዜ ያለፈበት በጣም ጥንታዊ ፋሽን አድርገው ይመለከታሉ፤ ነገር ግን ለደቀመዛሙርቱ የሰጠው እርሱ በዘመናችን ያለው የአለባበስ ፍቅር የሚያስከትለውን አደጋ ተገንዝቦ የማስጠንቀቂያ ማስታወሻ ወደ እኛ ልኮልናል። ማስጠንቀቂያውን ተግባራዊ አድርገን ጥበበኞች እንሁን? 820Testimonies For The Church 4:630.CGAmh 395.2

    በእውነት ክርስቶስን መከተል የሚሹ ሰዎች የሚለብሱትን አለባበሰ በተመለከተ ትክከለኛ የሕሊና ፍርድን መከተል አለባቸው፤ በግልጽ ጌታ በዚህ ላይ [1ኛ ጴጥሮስ 3፡3-5] የሰጠውን ትዕዛዝ መስፈርት ለማሟላት ጥረት ያደርጋሉ፡፡ 821Messages to Young People, 345, 346.CGAmh 395.3

    ልብስን የማፍቀር አደጋዎች— የልብስ ፍቅር ግብረ ገብን አደጋ ላይ በመጣል በዝግታ እና በአሳቢነት የሚታወቁ ሴቶችን የክርስቲያን ሴት ተቃራኒ ያደርጋቸዋል፡፡ የታይታና ውድ ልብስ አብዛኛውን ጊዜ ስጋዊ ፍላጎትን በለባሹ ልብ ውስጥ የሚያበረታታ እና በተመልካቹ ልብ ውስጥ ወራዳ ስሜቶችን የሚያነቃቃ ይሆናል፡፡ ትዕቢትን ማርካት እና የአለባበስ ከንቱነት የባህሪይ ብልሹነት ቀድሞ እንደሚመጣ እግዚአብሔር ተመልክቷል፡፡ ውድ ልብስ መልካም የማድረግን ፍላጎት እንደሚያፍን እርሱ ተመልክቷል፡፡15Testimonies For The Church 4:645.CGAmh 395.4

    ቀለል ያለ አለባበስ ምስክርነት— ቀላል፣ ግልጽ፣ ማስመሰል የሌለበት አለባበስ ለወጣት ሴቶቼ የሚመከር ነው፡፡ ቀለል ካለ አለባበስ እና አካሄድ ውጭ ብርሃናችሁ ለሌሎች እንዲበራ የምታደርጉበት ሌላ የተሻለ መንገድ የለም፡፡ ከዘላለማዊ ነገሮች ጋር ሲነጻጸር ለጊዜያዊ ሕይወት ተገቢ ግምት እንደምትሰጡ ለሌሎች ማሳየት ትችላላችሁ፡፡ 822Testimonies For The Church 3:376.CGAmh 396.1

    ዝግተኝነት ከሺዎች አደጋዎች ይከልላል— እህቶቼ፣ የክፉ ገጽታ እንኳን አስወግዱ፡፡ በብልሹነት እየሸተተ ባለ በዚህ ፈጣን ዘመን ውስጥ ካልተጠበቃችሁ በስተቀር ደህንነት የላችሁም፡፡ መልካም ባህሪይ እና ዝግተኝነት ብዙም አይታይም፡፡ ውድ፣ ዋጋው ሊገመት የማይችል የከበረውን ዝግተኝነትን እንድትንከባከቡ የከበረ ኃይማኖት እንዳላቸው እንደ ክርስቶስ ተከታዮች ጥሪ አቀርብላችኋለሁ፡፡ 823Testimonies For The Church 2:458.CGAmh 396.2

    ንጹህ ቀለል ያለ አለባበስ ከዝግተኝነት ባህሪይ ጋር አንድ ሲሆን እርሷን ከሺዎች አደጋዎች በመከለል ቅዱሱ ቁጥብነት በዙሪያ ወዳሉት ወጣት ሴቶች ሩቅ ይሄዳል፡፡ 824Education, 248.CGAmh 396.3

    የአሮጌ ፋሽን ሐሳብ— በጠባቧ የንጽህና እና ቅድስና መንገድ ላይ እንዲሄዱ ልጆችን ማሰልጠን ሙሉ በሙሉ አሮጌ እና የአሮጌ ፋሽን ሐሳብ እንደሆነ ይታሰባል፡፡ ይህ እግዚአብሔርን እናመልካለን በሚሉ ነገር ግን ሥራዎቻቸው ገንዘብን እንደሚያመልኩ በሚመሰክር ወላጆች ዘንድም ተስፋፍቶ ይገኛል፡፡ በራሳቸው እና በልጆቻቸው አለባበስ ከጎረቤቶቻቸው ጋር እና ራሳቸው አባላት በሆኑባቸው ቤተ ክርስቲየናት ጋር የመወዳደር እና ለራሳቸው ከፍተኛ ግምት የመስጠት ንጽጽር ውስጥ የመግባት ምኞት አላቸው፡፡825The Signs of the Times, September 10, 1894.CGAmh 396.4

    በሰማይ ቤት ተቀባይነት ያለው ብቸኛው ልብስ— እያንዳንዱ ልጅ እና ወጣት በየዋህነት ለማግኘት ሊሻው የሚገባ ልብስ አለ፡፡ እርሱም የጻድቃን ጽድቅ ነው፡፡ ልክ አለባበሳቸውን በዓለማዊ ማህበረተሰብ ፋሽን ደንብ እንደሚያደርጉት ሁሉ ይህን ለማግኘት እንደ ፈቃደኛ ሰው ፈቃደኛ እና ትጉሆች ቢሆኑ ወዲያው በክርስቶስ ጽድቅ ይሸፈኑ ነበር፣ ስሞቻቸውም ከሕይወት መዝገብ አይደመሰስም፡፡ እናቶች፣ ወጣቶች እና ልጆች “አቤቱ ንጹህ ልብን ፍጠርልኝ፣ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ” [መዝ. 51፡10] ሲሉ መጸለይ አለባቸው፡፡ ይህ የመንፈስ ንጽህና እና ተወዳጅነት ለጊዜውም ሆነ ለዘላለም ከወርቅ ይልቅ ውድ ነው፡፡ እግዚአብሔርን የሚያዩ በልባቸው ንጹሃን ያሆኑ ብቻ ናቸው፡፡ CGAmh 397.1

    ስለዚህ እናቶች ሆይ እነርሱ ለሰማይ ቤት ተቀባይነት የሚያገኙበት ብቸኛው ልብስ የክርስቶስ ጽድቅ ስለ ሆነ እና ይህን ልብስ ሲለብሱ በምደራዊ ሕይወት እግዚአብሔርን የሚያስከብር ሥራዎችን ዘወትር እንደሚሰሩ ልጆቻችሁን ሥርዓት በሥርዓት ትዕዛዝ በትዕዛዝ አስተምሯቸው፡፡ 826Christian Temperance and Bible Hygiene, 95.CGAmh 397.2