Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የልጅ አመራር

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ክፍል 6—ከተግባራዊ መልካምነት የሚገኝ ትምህርት

    ምዕራፍ 20—አጋዥነት

    ልጆች አጋዥ እንዲሆኑ ያስተምሯቸው —ቤት ባለው ትምህርት ቤት ውስጥ ልጆች በዕለት ተዕለት ኑሯቸው ተግባራዊ ኃላፊነቶችን እንዴት ማከናወን እንዳለባቸው መማር አለባቸው፡፡ እነርሱ ገና ልጆች ሆነው እያሉ እናት በየቀኑ የሚሰሯቸውን ቀላል ሥራ ልትሰጣቸው ይገባል፡፡ እርሷ ራሷ ከምትሰራው ይልቅ እንዴት መስራት እንዳለባቸው እነርሱን ለማስተማር ረዘም ያለ ጊዜ ይወስዳል፣ ነገር ግን የእነርሱን የአጋዥነት መሰረት የሆነውን የባህሪይ ግንባታ መሠረት መጣል እንዳለባት ታስታውስ፡፡ ቤት እርሷ ዋና አስተማሪ የሆነችበት ትምህርት ቤት መሆኑን ታስታውስ፡፡ የቤተሰቧን ተግባራት በፍጥነት እና በክህሎት እንዴት ማከናወን እንደሚችሉ ልጆቿን ማስተማር የእርሷ ኃላፊነት ነው፡፡ በተቻለ መጠን በልጅነታቸው የቤተሰብን ሸክም እንዲካፈሉ ሥልጠና ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ የቤተሰብ ድርጅት ሥራን በዕውቀት በማገዝ ከልጅነት ዕድሜ ጀምሮ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ከባድ እና ይልቅም ከባድ ሸክም መሸከምን መማር አለባቸው፡፡ 197Counsels to Parents, Teachers, and Students, 122.CGAmh 112.1

    የሕፃናት የልጅነት ስህተቶችን ችላ ማለት—በሺዎች የሚቆጠሩ በገዛ ቤታቸው ያልተማሩ ሆነው ቀርተዋል፡፡ እናትም “በጣም ብዙ ችግር ነው”፡፡ “እነዚህን ነገሮች እኔ እራሴ ብሰራቸው ይሻለኝ ነበር፤ ይህ ትልቅ ችግር ነው፤ ረብሻችሁኛል።” ትላለች፡፡ CGAmh 112.2

    እናት ራሷ አጋዥ ከመሆኗ በፊት ጥቂት በጥቂት ስትማር እንደነበረች አታስታውስምን? ልጆችን ጥቂት በጥቂት አለማስተማር ስህተት ነው፡፡ እነዚህን ልጆች ከእርስዎ ጋር ያቆዩ፡፡ እነርሱ ጥያቄዎችን እንዲጠይቁ ይፍቀዱላቸው እና እርሶ በትዕግስት ይመልሱላቸው። ለትንንሽ ልጆች የሚሰሩት ነገር ይሰጣቸው፣ እና እነርሱም ለእርሶ ረዳት መሆናቸውን በማሰብ ደስታ እንዲያገኙ ያድርጓቸው፡፡CGAmh 112.3

    ልጆች ተገቢ የሆኑ ነገሮችን ለመስራት ሲሞክሩ መቃወም አይገባም፡፡ ስህተት ከሠሩ፣ ድንገተኛ አደጋዎች ተከስተው ነገሮች ከተበላሹ፣ አይውቀሷቸው፡፡ መላ መጻኢ ሕይወታቸው የሚመሰረተው በልጅነት ዕድሜያቸው በሚሰጣቸው ትምህርት ላይ ነው፡፡ የሰውነት እና የአእምሮአቸው ችሎታዎችን ሁሉ እንዲጠቀሙበት እንደ ተሰጣቸው እና ሁሉም የጌታና ለእርሱ አገልግሎት ቃል የተገቡ መሆናቸውን አስተምሯቸው። ከእነርሱ ለአንዳንዱ ልጆች ጌታ ከልጅነታቸው የእሱን ፈቃድ እንዲያውቁ ይሰጣቸዋል። ወላጆች እና አስተማሪዎች፣ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ችሎታዎችን እንዲያዳብሩ ልጆችን ማስተማርን በጊዜ ይጀምሩ። 198Letter 104, 1897.CGAmh 113.1

    ልጆች የቤተሰብ ሸክሞችን ይጋሩ—የልጆቻችሁን ሕይወት አስደሳች እና በተመሳሳይ ሁኔታ እርሶ ትልልቅ ሸክሞችን ሲሸከሙ እነርሱም ትንንሽ ሸክሞችን በመሸከም ታዛዥ እና አጋዥ እንዲሆኑ አስተምሯቸው፡፡ ጠላት አዕምሯቸውን መስሪያ ቤት እንዳያደርግ የአምራችነትን ልማድ ያስተምሯቸው፡፡ በዚህ ዓለም እና በቀጣይ ሕይወት ጠቃሚ ለመሆን ብቁ ይሆኑ ዘንድ ለልጆቻችሁ የሚያስቡት እና የሚሰሩት አንድ ነገር ይሰጣቸው፡፡ 199Manuscript Releases 6:2, 1901.CGAmh 113.2

    ከመጀመሪያዎቹ ዓመታት ጀምሮ ከቤተሰብ ሸክም የድርሻቸውን እንዲሸከሙ ሥልጠና ማግኘት አለባቸው፡፡ ግዴታዎች የጋራ መሆናቸውን መማር አለባቸው፡፡ እንዲሁም በፍጥነት እና በጥንቃቄ እንዲሰሩ መማር አለባቸው፡፡ ይህ ትምህርት ከዓመታት በኋላ ለእነርሱ ትልቅ ዋጋ ያለው ይሆናል፡፡ 200The Signs of the Times, December 11, 1901.CGAmh 113.3

    እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ከሌላው ጋር ተባብሮ እንዲሠራ የሚጠበቅበትን ክፍል መገንዘብ አለበት፡፡ የስድስት ዓመት ሕጻን እና ከዛ በላይ የሆነ ሁሉ፣ የህይወታቸውን ሸክም ድርሻ መሸከም ከእነርሱ እንደሚጠበቅ ማወቅ አለባቸው፡፡ 5Testimonies For The Church 2:700.CGAmh 113.4

    የልምድ እና የደስታ ምንጭ—አባቶች እና እናቶች ለልጆቻቸው ከልጅነታቸው ጀምሮ ትክክለኛውን መመሪያ መስጠት ምን ያህል አስፈላጊ ነው! “አባትህንና እናትህን አክብር እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም” የሚለውን ትዕዛዝ እንዲታዘዙ ማስተማር አለባቸው፡፡ ልጆች በዕድሜ እያደጉ ሲመጡ ወላጆቻቸው የሚሰጧቸውን ሥራ ማድነቅ አለባቸው፡፡ እነርሱ አባት እና እናትን በመርዳት ከፍተኛ ደስታቸውን ለማግኘት ነው፡፡ 201Manuscript Releases 12:9, 1903.CGAmh 114.1

    ተራ የሆነውን ተግባር ደስታ ሊከብብ ይችላል—ልጆች ተራ የሆኑ የእለት ተእለት ተግባሮችን ጌታ ለእነርሱ ለይቶ እንዳስቀመጠ አድርገው እንዲመለከቱት፣ ታማኝ እና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት ይችሉ ዘንድ እንደሚያሰለጥን ትምህርት በመቁጠር ቢማሩ ኖሮ፣ ምን ያህል ሥራቸው የበለጠ አስደሳች እና ክቡር ሆኖ በታየ ነበር። እያንዳንዱን ተግባር ለጌታ እንደ ሆነ በመቁጠር ማከናወን ተራ በሆነ ሥራ ዙሪያ ደስታን ያመጣል እንዲሁም በምድር ላይ ያሉትን ሠራተኞች በሰማይ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ከሚያደርጉ ቅዱሳን ጋር ያገናኛል። በተሾምንበት ቦታም በከፍተኛ ሥፍራቸው ሀላፊነቶቻቸውን በታላቅ ታማኝነት እንደሚወጡ መልአክት መወጣት አለብን፡፡ 202The Signs of the Times, October 11, 1910.CGAmh 114.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents