Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የልጅ አመራር

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ክፍል 10—ሥርዓት ማስያዝ እና አያያዙ

    ምዕራፍ 41—የመግራት ዓለማዎች

    ዋናው ዓላማ የሆነው ራስን የመግዛት— የመግራት ዓላማው ልጅ ራሱን ይገዛ ዘንድ የሚሰጥ ሥልጠና ነው፡፡ ራስን መቻል እና ራስን መግዛትን መማር አለበት፡፡ ስለዚህ እርሱ ነገሮችን የማስተዋል አቅም ባገኘበት ቅጽበት፣ የመረዳት ችሎታው ከታዛዥነት ጎን መቆም አለበት፡፡ ከእርሱ ጋር የተያያዙትን አድራጎቶች ሁሉ ፍትሐዊ እና ምክንያታዊ ለመሆን ታዛዥነትን የሚያሳዩ አይነት ይኹን፡፡ ሁሉም ነገር በሕግ ሥር መሆኑን፣ እናም አለመታዘዝ በመጨረሻ ወደ ጥፋት እና ሥቃይ እንደሚያመራ ያይ ዘንድ እርዱት። እግዚአብሔር “አታድርግ” ሲል ከአደጋ እና ጥፋት እኛን ለማዳን በፍቅር የአለመታዘዝ ውጤት ምን እንደሆነ በማስጠንቀቅ ይናግረናል። 419Education, 287.CGAmh 211.1

    የፈቃድን ኃይል ጥቅም ላይ ማዋል— የእውነተኛ ተግሣጽ ዓለማ ግብ የሚመታው ጥፋተኛው ራሱ ስህተቱን ሲመለከት እና ለመስተካከል ፈቃዱን ጥቅም ላይ ሲያውል ነው። ይህ ሲፈጸም ወደ ይቅርታ እና የኃይል ምንጭን ይጠቁመት፡፡ 420Education, 291.CGAmh 211.2

    ተማሪዎቻቸውን ክብር እና ፋይዳ ያላቸው ወንዶች እና ሴቶች የመሆን ሃይል በውስጣቸው እንዳለ እንዲሰማቸው የሚያሠለጥኗቸው ሰዎች በዘላቂነት እጀግ ስኬታማ ናቸው። 421Fundamentals of Christian Education, 58.CGAmh 211.3

    ትክክለኛ ልማዶች፣ ዝንባሌዎች፣ የክፉ ዝንባሌዎች— መገደብ፣ መምራት እና መቆጣጠር የወላጆች ስራ ነው። ልጆቻቸው የልጅነታቸውን ፍላጎቶች እና የመሰላቸውን ሁሉ እንዲያረኩ እና የራሳቸውን ዝንባሌ እንዲከተሉ ከመፍቀድ የበለጠ ክፉ ነገር አያደርጉም፡፡ እራሳቸውን ለማስደሰት እና ለመዝናናት፣ የራሳቸውን መንገድ በመምረጥ እና የራሳቸውን ደስታ እና ጓደኛ በመፈለግ ለራሳቸው ይኖሩ ዘንድ አእምሮአቸው ላይ አሻራ ከመተው የበለጠ ከባድ ስህተት ሊሰሩ አይችሉም…፡፡ ወጣቱ የሚያስተምሯቸው እና ሥነ-ሥርዓት የሚያስይዟቸው መጥፎ ልማዶቻቸውን እና ዝንባሌዎቻቸውን የሚያስተካክሉ፣ ክፉ ዝንባሌዎቻቸውንም የሚከረክሙ ወላጆችን ይፈልጋሉ። 422Manuscript Releases 12:1898. CGAmh 211.4

    የሰይጣንን ብርቱ ምሽግ አፍርሱ— እናቶች ሆይ፣ የልጆቻችሁ እጣ ፈንታ በአብዛኛው በእጆቻችሁ ላይ ተጥሏል፡፡ ኃላፊነታችሁን መወጣት ካቃታችሁ እነርሱን በሰይጣን ተርታ በማሰለፍ ሌሎች ነፍሳትን ለማጥፋት የእርሱ ወኪሎች ታደርጓቸዋላችሁ፡፡ ወይም ታማኝ ተግሣጻችሁ እና አምላካዊው ምሳሌያችሁ ወደ ክርስቶስ ይመራቸው እና እነርሱም ደግሞ ሌሎች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ፣ በዚህም መንገድ ብዙ ነፍሳት በእናንት ምክንያት ሊድኑ ይችላሉ። 423The Signs of the Times, February 9, 1882. CGAmh 212.1

    በጥንቃቄ እንመልከት እና የወደቁትን የጥገና መሠሪያዎቻችን ማንሳት እንጀምር፡፡ የጠላትን ምሽጎች እንስበር፡፡ ውዶቻችንን በምሕረት በማረም ከጠላት ኃይል እንጠብቃቸው፡፡ ተስፋ አትቁረጡ።6The Review and Herald, July 16, 1895.CGAmh 212.2

    ለወላጅ እና ለመለኮታዊ ስልጣን አክብሮት እንዲሰጡ አስተምሯቸው— ልጆች… ለወላጆቻቸው ሥልጣን አክብሮት በመስጠት እስኪታዘዙ ድረስ መሰልጠን፣ መማር እና ሥነ-ሥርዓት መያዝ አለባቸው፡፡ በዚህ መንገድ ለመለኮታዊ ሥልጣን አክብሮት በልባቸው ውስጥ ይተከላል፣ እናም የቤተሰብ ስልጠና ለሰማይ ቤተሰብ እንደሚደረግ የመሰናዶ ሰልጠና ይሆናል፡፡ የልጅነት እና የወጣትነት ሥልጠና ልጆች ሃይማኖታዊ ተግባራቸውን ለመወጣት ዝግጁ የሚያደርጋቸው አይነት እና በዚሁ መንገድ የላይኛውን ቤት ለመግባት ብቁ የሚሆኑበት መሆን አለበት፡፡ 424The Review and Herald, March 13, 1894. CGAmh 212.3

    የእውቀት ምንጭ የሆነው እርሱ ወደ የሰማይ ተድላ ለመግባት ብቁ የምንሆንበትን ሁኔታ፣ “ወደ ሕይወት ዛፍ ለመድረስ ስልጣን እንዲኖራቸው በደጆችዋም ወደ ከተማይቱ እንዲገቡ ልብሳቸውን የሚያጥቡ ብጹአን ናቸው” በሚሉ ቃላት ተገልጿል፡፡ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት መታዘዝ የሰማይ ዋጋ ነው፣ እንዲሁም በጌታ ለወላጆች መታዘዝ ልጆች መማር ያለባቸው እጅግ ወሳኝ ትምህርት ነው።8Manuscript Releases 12a, 1896.CGAmh 212.4

    በግዴታ ሳይሆን በመርህ ላይ የተመሰረተ ታዛዥነት— በእርግጥ ከእነርሱ ምን እንደምትፈልጉ ለልጆቻችሁ ንገሯቸው፡፡ ከዚያም ቃላችሁ ሕግ እንደሆነ እና መታዘዝም እንዳለባቸው ይረዱ። በዚህ መንገድ “አድርግ” እና “አታድርግ” የሚሉ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት እንዲያከብሩ ማሰልጠናችሁ ነው፡፡ 425The Review and Herald, September 15, 1904.CGAmh 213.1

    አጠያያቂ ካልሆነ መተማመን የምናገኘው ትምህርት— ይስሐቅ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ በመናገሩ በሩህሩህ እና አፍቃሪ አባቱ እጆች ታስሯል፡፡ ልጁ በአባቱ ቅንነት ስለሚታመን ለመሰዋት ራሱን አሳልፎ ሰጠ…፡፡CGAmh 213.2

    ይህ የአብርሃም የእምነት ተግባር ለጥቅማችን ሲባል ተመዝግቧል፡፡ ምንም እንኳን ዝግ እና ጎጂ ቢሆን በእግዚአብሔር መስፈርቶች ላይ የመተማመንን ታላቅ ትምህርት ያስተምራል፣ እናም ልጆች ለወላጆቻቸው እና ለእግዚአብሔር ፍጹም መገዛት እንዳለባቸው ያስተምራል። በአብርሃም ታዛዥነት ለእግዚአብሔር መስጠት ከሚገባን አንዳችም ውድ ነገር እንደሌለ እንማራለን፡፡ 426Manuscript Releases3:368.CGAmh 213.3

    ወጣቶች ለኃላፊታቸው ምላሽ ይሰጣሉ— ወጣቶች ኃላፊነት የተጣለባቸው መሆኑን በማመን መነቃቃት አለባቸው፡፡ እነርሱ የመከበር ስሜት አላቸው፣ አክብሮትም ይፈልጋሉ፣ ይህም መብታቸው ነው፡፡ ተማሪዎች መውጣት ወይም መግባት፣ በጠረጴዛ ላይ መቀመጥ፣ ወይም ቁጥጥር ካልተደረገላቸው፣ የሚከታተላቸውና ሪፖርት የሚያቀርብባቸው አይን ከሌለ በስተቀር በማንኛውም ቦታ ላይ ሊሆኑ እንደማይችሉ ሲሰማቸው፣ ይህ ተስፋ የማስቆረጥ ተጽዕኖ ሲኖረው፣ አላፊ ጊዜዎችም በውስጣቸው ደስታ የሌላቸው ይሆናሉ፡፡ ይህ ቀጣይነት ያለው የቁጥጥር እውቀት ከወላጅነት ቁጥጥር በላይ ሲሆን፣ በጣም የከፋ ነው፣ ምክንያቱም ብልህ የሆኑ ወላጆች በብልሃት ብዙውን ጊዜ ከላይ ላይ ከሚታየው ባሻገር በጥልቀት በመለየት እረፍት የለሹ አእምሮ በወጣነት ምኞት ስር ወይም በፈተና ኃይሎች ስር መሆናቸውን በማየት በክፋት ተቃራኒ እንዲሰራ ዕቅዳቸው ያዘጋጁላቸዋል። ነገር ግን ይህ የማያቋርጥ ቁጥጥር ተፈጥሮአዊ አይደለም፣ እንዲሁም ለማስወገድ የተፈልገውን ክፋት ያመጣል፡፡ ለአካላዊ ጤንነት እና ሚዛናዊ ባህሪይ እድገት፣ የወጣት ጤናማነት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና በአስደሳች ሁኔታዎች ውስጥ መሆንን ይፈልጋል፡፡ 427Fundamentals of Christian Education, 114.CGAmh 213.4

    የራስ—አስተዳደር እና ፍጹም ፈላጭ ቆራጭነት— በሥነ-ሥርዓት ስልጠና ወቅት በደንብ የሰለጠኑ የሚመስሉ ብዙ የህጻናት ቤተሰቦች አሉ፤ ነገር ግን ህጎችን እንዲያወጡ ያስቻላቸው ስርዓት ሲጣስ ለራሳቸው ማሰብ፣ መተግበር ወይም መወሰን የማይችሉ ይመስላሉ፡፡ እነዚህ ልጆች የራሳቸው አመለካከት ኖሮአቸው በራሳቸው ውሳኔ እንዳይነቀሳቀሱ በአግባቡ ማድረግ ባለባቸው ነገር እንዲያስቡና እንዲተገብሩ ሳይቀድላቸው፣ ለረጅም ጊዜ በብረት አገዛዝ ሕግ ሥር ነበሩ፡፡ በራሳቸው ለመስራት ከወላጆቻቸው ተለይተው በሚወጡበት ጊዜ፣ በተሳሳተ አቅጣጫ በቀላሉ በሌሎች ሰዎች ውሳኔ ይመራሉ፡፡ የባህሪይ መረጋጋት የላቸውም፡፡ በተቻለ ፍጥነት እና ተግባራዊነት በራሳቸው ውሳኔ ላይ እንዲደገፉ አልተደረጉም፣ በመሆኑም አዕምሯቸው በአግባቡ አልጎለበተም፣ አልተጠናከረም፡፡ ሙሉ በሙሉ በእነርሱ ላይ እንዲተማመኑ ለረጅም ጊዜ በወላጆቻቸው ቁጥጥር ስር ስለነበሩ፤ ወላጆቻቸው አእምሮአቸው እና ውሳኔአቸው ናቸው፡፡CGAmh 214.1

    በሌላ በኩል ወጣቶች የወላጆቻቸውን እና መምህራኖቻቸውን ወሳኔ በመተው በራሳቸው እንዲያስቡ እና እንዲተገብሩ መተው የለባቸውም። ልጆች ልምድ ያላቸውን ሰዎች ውሳኔዎች እንዲያከብሩ እና በወላጆቻቸው እና በመምህራኖቻቸው እንዲመሩ መማር አለባቸው…፡፡ አእምሯቸው ከወላጆቻቸው እና ከመምህራኖቻቸው አዕምሮ ጋር እንዲዋሀድ የተማሩ መሆን አለባቸው፣ ምክሮቻቸውንም ተግባራዊ ማድረግን መማር አለባቸው። ከዚያም ከሚመሯቸው ከወላጆቻቸው እና መምህራኖቻቸው እጅ በሚወጡበት ጊዜ ባህሪያቸው በነፋስ እንደሚወዛወዝ ሸምበቆ አይሆንም፡፡CGAmh 214.2

    የወጣቶች አደገኛው ሥልጠና— በዚህ መንገድ የአስተሳሰብ ዕድገት፣ ራስን የማክበር ስሜት እና መስራት እንደሚችሉ በራሳቸው ችሎታዎች መታመን ይኖራቸው ዘንድ በራሳቸው አቅም እና የአዕምሮአቸው ዝንባሌ በፈቀደው እንዲያስቡ እና እንዲተገብሩ በአግባቡ አለማሰልጠን— በአእምሮ እና በስነ-ምግባራዊ ኃይል ደካማ የሆነ የማህበረሰብ ክፍልን ይፈጥራል፡፡ እናም በራሳቸው ለመስራት ዓለም ውስጥ ሲቆሙ፣ ልክ እንደ እንስሳት፣ የሰለጠኑ እና ያልተማሩ መሆናቸውን ያሳያሉ፡፡ ፈቃዳቸው ምሪት ከማግኘት ይልቅ፣ በወላጆች እና በመምህራን ከባድ ተግሣጽ እንዲገዛ ተገዷል። 428Manuscript Releases 3:132, 133..CGAmh 214.3

    የአንዱ አዕምሮ ሌላኛውን በሚገዛበት ጊዜ ክፉ ውጤት ይፈጠራል— በእንክብካቤያቸው ሥር ያሉትን ልጆች አዕምሮና ፈቃድ ላይ ሙሉ ቁጥጥር እንዳላቸው የሚኩራሩ ወላጆች እና መምህራን በኃይል ወይም በፍርሃት እንደዚያ የተገዙላቸውን ልጆች መጻኢ ሕይወት ዱካ ቢመለከቱ ኖሮ ኩራታዎቻቸውን ይተው ነበር፡፡ እነዚህ በሕይወታቸው ከባድ ኃላፊነቶች ውስጥ ለመሳተፍ ሙሉ በሙሉ ዝግጁ አይደሉም ማለት ይቻላል፡፡ እነዚህ ወጣቶች ከወላጆቻቸው እና ከመምህራኖቻቸው ሥር በማይሆኑበት እና በራሳቸው ለማሰብ እና ለመተግበር ሲገደዱ በተሳሳቱ መንገዶች እንደሚሄዱ እና ለፈተና ኃይል እንደሚያጎበድዱ እርግጥ ነው፡፡ እነርሱ ይህንን ሕይወት ስኬታማ አያደርጉትም፣ ተመሳሳይ ጉድለቶች በሃይማኖታዊ ህይወታቸውም ውስጥ ይንጸባረቃሉ። የልጆች እና የወጣቶች አስተማሪዎች የተሳሳተ አሰለጣጠን ሥልታቸው የወደፊት ዕጣ ፈንታ ከፊት ለፊታቸው የሚታያቸው ቢሆን ኖሮ የትምህርት ዕቅዳቸውን ይለውጡ ነበር፡፡ የተማሪዎቻቸውን ፈቃድ ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠራቸው የሚረኩ የአስተማሪዎች ክፍል ምንም እንኳን ለጊዜው ገጽታው የሚያኩራ ቢመስልም እጅግ የተሳካላቸው አስተማሪዎች አይደሉም።CGAmh 215.1

    አንድ የሰው አእምሮ በሌላው ሙሉ ቁጥጥር ስር እንዲሆን እግዚአብሔር አልፈጠረም፡፡ የተማሪዎቻቸው ግላዊነትን በእነርሱ ውስጥ እንዲዋሀድ እንዲሁም ለእነርሱ አዕምሮ፣ ፈቃድ እና ህሊና እንዲሆን ጥረት የሚያደርጉ አስፈሪ ሃላፊነቶች ይሸከማሉ፡፡ እነዚህ ምሁራን በተወሰኑ ሁኔታዎች በደንብ የተዋጣላቸው ሁኔታዎች ወታደሮች ሊመስሉ ይችላሉ፡፡ ግን እገዳው ሲወገድ በእነርሱ ውስጥ ካለው ጽኑ መርህ በነጻነት የመተግበር ፍላጎት ይታያል። 429Testimonies For The Church 3:133, 134.CGAmh 215.2

    በክህሎት እና ትዕግስት ጥረት ውስጥ— ወጣቱን በቀና መንገድ ለመቅረጽ የክህሎት እና የትዕግስት ጥረት ይጠይቃል። በተለይም የወላጆቻቸው ቀጥተኛ የኃጢአት ውጤት የሆነውን የወላጆቻቸውን ክፉ ውርስ በመሸከም ወደ ዓለም የመጡ ልጆች፣ ሥነ ምግባራዊ እና አዕምሮአዊ ችሎታቸውን ለማጎልበት እና ለማጠንከር እጅግ ጠንቃቃ እንክብካቤ ይፈልጋል፡፡ በእርግጥም የወላጆች ኃላፊነት በጣም ከባድ ነው፡፡ ክፉ ዝንባሌዎች በጥንቃቄ መገታት እና በርህራሄ መገሠጽ አለባቸው፤ አእምሮ ቀና ወደ ሆነው ነገር በማዘንበል መነቃቃት አለበት፡፡ ልጅ ራሱን ለመግዛት ሲጥር ማበረታታት አለበት፡፡ ይህም ሁሉ በቅንነት መከናወን አለበት፣ ካልሆነ የተፈለገው ዓላማ ይከሽፋል፡፡ 430Christian Temperance and Bible Hygiene, 138.CGAmh 216.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents