Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የልጅ አመራር

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 79—ሰንበት—የደስታ ቀን

    ተስፋፍቶ ያለው ሰንበትን ችላ የማለት ጉዳይ— ለዚህ ጊዜ በጣም አስፈላጊ የሆነውን ክቡር መልእክት እናምናለን ከሚሉ ወላጆች መካከል አብዛኞቹ ልጆቻቸውን ለእግዚአብሔር እንዳላሠለጥኑ ተመልክቻለሁ፡፡ ራሳቸው አልገደቧቸውም ደግሞም እነርሱን ለመግታት በሚሞክር ማንኛውም ሰው ላይ ይበሳጫሉ፡፡ በየቀኑ ልጆቻቸውን በጌታ መሠዊያ ላይ በማድረግ በሕያው እምነት አልኖሩም። ከእነዚህ ወጣቶች መካከል ብዙዎቹ በአምላክ ቅዱስ ቀን የራሳቸውን ደስታ በመፈለግ አራተኛውን ትእዛዝ እንዲተላለፉ ተፈቅዶላቸዋል። ለራሳቸው ለመዝናናት በሰንበት ቀን ወደ ጎዳናዎች ሲሄዱ ምንም የሕሊና ጸጸት አይሰማቸውም፡፡ ብዙዎች ወደፈለጉበት ይሄዳሉ፣ ያሻቸውንም ያደርጋሉ፤ ወላጆቻቸውም እነርሱን ላለማሳዘን በጣም ፈርተው የኤሊን አመራር በመኮረጅ ምንም ትእዛዝ አይሰጧቸውም፡፡CGAmh 503.1

    እነዚህ ወጣቶች በመጨረሻ ለሰንበት ያላቸውን አክብሮት ሁሉ ያጣሉ እንዲሁም ለሃይማኖታዊ ስብሰባዎች ወይም ለቅዱስ እና ለዘላለማዊ ነገሮች ፍላጎት የላቸውም። 1056Testimonies For The Church5:36, 37.CGAmh 503.2

    የአራተኛው ትእዛዝ የመጀመሪያ ቃል አክብሩ— “አስብ” የሚለው በአራተኛው ትእዛዝ መጀመሪያ ላይ ተቀምጧል። ወላጆች ሆይ፣ የሰንበትን ቀን ትቀድሱት ዘንድ ራሳችሁ ማሰብ ይኖርባችኋል። ይህንንም ካደረጋችሁ ለልጆቻችሁ ተገቢውን መመሪያ እየሰጣችኋቸው ነው ማለት ነው፤ እነርሱም የእግዚአብሔርን ቅዱስ ቀን ያከብራሉ…፡፡ በቤቶቻችሁ ክርስቲያናዊ ትምህርት ያስፈልጋል፡፡ ያ ቀን ለእግዚአብሄር አገልግሎት መሰጠት ያለበት ስለሆነ ሳምንቱን በሙሉ የጌታን ቅዱስ ሰንበት ልብ ይበሉ፡፡ እጆች ከዓለማዊ ሥራ የሚያርፉበት፣ የነፍስ ፍላጎቶች ልዩ ትኩረት የሚሰጥበት ቀን ነው፡፡ 1057Testimonies For The Church 5:7, 1897.CGAmh 503.3

    ሰንበት በዚህ መንገድ ሲታወስ፣ ጊዜያዊ ጉዳይ በመንፈሳዊው ጥሶ ጣልቃ እንዲገባ አይፈቀድለትም። በስድስቱ የሥራ ቀናት የሚሰራ ማንኛውም ተግባር ሳይሰራ ለሰንበት ቀን አይቀርም፡፡ ጌታ ባረፈበትና ትንፋሽ በታደሰበት ቀን ከድካም የተነሳ በአገልግሎቱ ለመሳተፍ እንዳያቅተን በሳምንቱ ውስጥ ጉልበታችን በጊዜያዊ ተግባር ድካም እጅግ እንዲዝል አይደረግም፡፡ 1058Testimonies For The Church 6:354.CGAmh 503.4

    አርብን የዝግጅት ቀን አድርጉ— አርብ ለሰንበት ዝግጅት ይጠናቀቅ፡፡ ልብስ ሁሉ ዝግጁ መሆኑን፣ እና የምግብ ዝግጅት ሁሉ መጠናቀቅን እዩ። ቦት ጫማዎች ቀለም ይቀቡ፣ ገላም ይታጠብ፡፡ ይህንን ማድረግ ይቻላል፡፡ ይህንን ደንብ ካደረጋችሁት፣ መፈጸም ትችላላችሁ፡፡ ሰንበት ልብስ ለመጠገን፣ ምግብ ለማብሰል፣ ለተድላ ፍለጋ ወይም ለሌላ ዓለማዊ ሥራ ሊውል አይገባም፡፡ ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት፣ ዓለማዊ ሥራዎች ሁሉ ወደ ጎን ይተው፣ ዓለማዊ ወረቀቶች ሁሉ ከእይታ እንዲወገዱ ይደረግ፡፡ ወላጆች፣ ሥራዎን እና ዓላማዎትን ለልጆቻችሁ አስረዱ እና በትእዛዙ መሠረት ሰንበትን ለማክበር በዝግጅታችሁ ላይ እንዲካፈሉ አድርጓቸው፡፡ 1059Testimonies For The Church 6:355, 356.CGAmh 504.1

    በብዙ ቤተሰቦች ውስጥ [በሰንበት] ቦት እና ጫማዎች ቀለም ይቀባሉ፣ ይቦረሻሉ፣ ስፌትም ይሰፋሉ፣ ምክንያቱም እነዚህ ትናንሽ እንግዳ ነገሮች እና ተግባራት ዓርብ ስላልተከናወኑ ነው፡፡ እነርሱ “የሰንበትን ቀን እንዲቀድሱ አላሰቡም” ነበር።”…CGAmh 504.2

    አርብ የልጆች ልብሶች መፈለግ አለባቸው ፡፡ ያለ ምንም ግራ መጋባት ወይም ያለ የጥድፊያ እና የችኮላ ንግግሮች ፀጥ ብለው መልበስ ይችሉ ዘንድ ሁሉም ልብሶች በሳምንቱ ቀናት ውስጥ በእናት ምሪት በራሳቸው እጆች መቀመጥ አለባቸው፡፡5Testimonies For The Church . 5:7, 1897.CGAmh 504.3

    በዝግጅት ቀን ትኩረት ማግኘት ያለበት ሌላ ሥራ አለ፡፡ በዚህ ቀን በቤተሰብም ሆነ በቤተክርስቲያን ውስጥ በወንድማማቾች መካከል ያሉ ሁሉም ልዩነቶች መወገድ አለባቸው፡፡ 1060Testimonies For The Church 6:356.CGAmh 504.4

    ሰንበት ከቤተሰብ ጋር በአምልኮ ላይ ይከፈታል— ፀሐይ ከመግባቷ በፊት የቤተሰብ አባላት የአምላክን ቃል ለማንበብ፣ ለመዘመር እና ለመጸለይ ይሰብሰቡ፡፡ ብዙዎች ስለሚዘነጉት እዚህ ላይ ተሃድሶ ያስፈልጋል፡፡ ለእግዚአብሔር እና ለሌላው መናዘዝ አለብን፡፡ እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል እግዚአብሔር የባረከውን እና የቀደሰውን ቀን ለማክበር እንዲዘጋጅ ልዩ ዝግጅት ለማድረግ እንደገና መጀመር አለብን፡፡1061Testimonies For The Church 6:356, 357.CGAmh 504.5

    የሰንበት ሰዓቶች የእኛ ሳይሆኑ የእግዚአብሔር ናቸው— እግዚአብሔር ሥራችንን የምንሠራበትን ስድስት ቀናትን በሙሉ ሰጥቶን አንድ ቀን ብቻ ለራሱ አስቀረ፡፡ ይህ ለእኛ የበረከት ቀን ሊሆን ይገባል— ዓለማዊ ጉዳዮቻችንን በሙለሉ ወደ ጎን በመተው ሀሳባችንን ወደ እግዚአብሔር እና ወደ ሰማይ የምናደርግበት ቀን።8Testimonies For The Church 3:1879.CGAmh 505.1

    ሰንበት በሚጀምርበት ጊዜ በጥብቅ የጌታ የሆነውን ጊዜ ለራሳችን በማዋል እግዚአብሔርን እንዳንሰርቅ በድርጊታችን እና በቃላቶቻችን ላይ እራሳችንን መጠበቅ አለብን፡፡ የራሳችንን የኑሮ ተግባር ወይም በስድስቱ የሥራ ቀናት ውስጥ መከናወን ይችል የነበረ ማንኛውንም ነገር ራሳችን ማድረግ የለብንም፣ ልጆቻችንም እንዲያደርጉ መፍቀድ የለብንም፡፡ አርብ የዝግጅት ቀን ነው፡፡ ስለዚህ ለሰንበት አስፈላጊውን ዝግጅት ለማድረግ እና ስለ እርሱ ለማሰብ እና ለመወያየት ጊዜ ሊሰጥ ይችላል፡፡ በሰማይ ፊት ቅድስት ሰንበትን እንደ መጣስ የሚቆጠር መነገር ወይም መደረግ ያለበት ማንኛውም ነገር ሳይነገር ወይም ሳይሰራ መቅረት የለበትም፡፡ እግዚአብሔር በሰንበት ከአካል ሥራ እንድንቆጠብ ብቻ ሳይሆን አዕምሮ በቅዱስ ጭብጦች ላይ እንዲያተኩር ዘንድ እንዲማር ይፈልጋል፡፡ አራተኛው ትእዛዝ በዓለማዊ ነገሮች ላይ በመወያየት ወይም በወራዳ እና ከንቱ ውይይቶች ላይ በመሳተፍ ተጥሷል ማለት ይቻላል። በአእምሮ ውስጥ ሊመጣ በሚችለው በማንኛውም ነገር ወይም በእያንዳንዱ ነገር ላይ መነጋገር የራሳችንን ቃላትን መናገር ነው፡፡ ከቅን ነገር ማፈንገጥ ሁሉ ወደ ባርነት እና ኩነኔ ያመጣናል፡፡ 1062Testimonies For The Church 2:702, 703.CGAmh 505.2

    የሰንበት ሰዓታት በእንቅልፍ እንዳያልፉ ውድ ናቸው— ማናቸውም ሰዎች በሰንበት ቀን ለእግዚአብሔር የሚሰጡ አገልግሎት ላይ ብርታት ወይም ጉልበት እንዳያጥራቸው በሳምንቱ ውስጥ በጊዜያዊ ፍላጎቶቻቸው እጅግ እንዲጠመዱ እና ለዓለማዊ ጥቅም በሚያደርጉት ጥረት እጅግ እንዲዝሉ መፍቀድ የለባቸውም፡፡ በቅዱስ ቀኑ እርሱን ለማምለክ ብቁ እንዳንሆን ስናደርግ ጌታን እየዘረፍነው ነው፡፡ እራሳችንንም እየዘረፍን ነው፤ ምክንያቱም የህብረትን ሙቀት እና ድምቀት እንዲሁም ከሌሎች ክርስቲያኖች ጥበብ እና ተሞክሮ የምናገኘው ብርታት ያስፈልገናልና። 1063The Review and Herald, June 13, 1882.CGAmh 505.3

    የሰንበት ውድ ሰዓታት በአልጋ ላይ አይባክኑ፡፡ በእለተ ሰንበት ጠዋት ቤተሰብ ቀድሞ መንቃት አለበት፡፡ ዘግይተው ቢነቁ ለቁርስ እና ለሰንበት ትምህርት ዝግጅት ግራ መጋባት እና ግርግር ይኖራል፡፡ መቸኮል፣ መሮጥ እና ትዕግስት ማጣት ይኖራል፡፡ ስለዚህ የልተቀደሱ ስሜቶች ቤት ውስጥ ይገባሉ፡፡ ሰንበት፣ በዚህ መንገድ ይረክሳል፣ አድካሚ ይሆናል፣ በመሆኑም መምጣቱ ከመወደድ ይልቅ የሚፈራ ይሆናል።11Testimonies For The Church 6:357.CGAmh 506.1

    በሕብረት አምልኮ ላይ ከልጆች ጋር ተሳተፉ— አባቶች እና እናቶች ልጆቻቸው በሰንበት በሕብረት አምልኮ ላይ እንዲገኙ ደንብ ማውጣት አለባቸው፣ እንዲሁም ደንቡን ራሳቸው ምሳሌ በመሆን ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው፡፡ አብርሃም እንዳደረገው ልጆቻችንን እና ቤተሰባችን እኛን እንዲከተሉ ማዘዝ ግዴታችን ነው፡፡ በምሳሌ እንዲሁም በትእዛዝ የኃይማኖታዊ ትምህርት አስፈላጊነትን በውስጣቸው ማስረጽ አለብን፡፡ የጥምቀትን ቃል ኪዳን የገቡ ሁሉ ለእግዚአብሔር አገልግሎት ራሳቸውን በክብር ቀድሰዋል፤ በክርስቲያናዊ ሕይወት ውስጥ ማነቃቂያዎችን እና ማበረታቻዎችን ሁሉ ማግኘት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ እራሳቸውን እና ልጆቻቸውን የማድረግ የቃል ኪዳን ግዴታ ሥር ናቸው፡፡ The Review and Herald, June 13, 1882. 1064Testimonies For The Church 6:357..CGAmh 506.2

    ሆኖም ግን እግዚአብሔርን ስናመልክ ይህንን እንደ አድካሚ ሥራ ልንቆጥረው አይገባም፡፡ የጌታ ሰንበት ለእኛ እና ለልጆቻችን በረከት ሊሆን ይገባል፡፡ ሰንበትን እንደ አስደሳች ቀን፣ እግዚአብሔር እንደቀደሰው ቀን ሊያስቡት ይገባል፤ ደግሞም በትክክል መመሪያ ከተሰጣቸው እንዲሁ ያጤኑታል፡፡ 1065Manuscript Releases 3:1879.CGAmh 506.3

    ለአምልኮ ቤት ጥሩ ልብሶችን ልበሱ— ብዙዎች በሰንበት ቀን ለአምልኮ እንዴት መቅረብ እንዳለባቸው መመሪያ ይፈልጋሉ፡፡ በሳምንቱ ውስጥ በሚለብሱት የተለመዱ ልብሶች ወደ እግዚአብሔር መገኘት አይግቡ፡፡ ሁሉም በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ አገልግሎት ሲካፈሉ የሚለብሱት ልዩ የሰንበት ልብስ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ከዓለማዊ ፋሽኖች ጋር መመሳሰል ባይኖርብንም፣ ውጫዊ ገጽታችንን በተመለከተ ግድየለሾች መሆን የለብንም፡፡ ያለ ጌጣ ጌጦች ብንሆንም እንኳ ግሩምና ውብ መሆን አለብን። የእግዚአብሔር ልጆች ከውስጥ እና ከውጭ ንጹህ መሆን አለባቸው፡፡ 1066Testimonies For The Church 6:355.CGAmh 507.1

    የሰንበትን ስብከት ለልጆች አብራሩ— አገልጋዮች በተቀደሰውና በተከበረ ሥራ ላይ ተሰማርተዋል፣ ሆኖም ግን በሚሰሙት ላይ እንደ ቅዱስ ሀላፊነት ያርፋል፡፡ የዘላለምን ሕይወት የሚያገኙ ሁሉ ሊለማመዱት የሚገባውን መመሪያ ለመከተል በቁርጠኝነት መስማት አለባቸው። እያንዳንዱ ሰሚ በእምነት ለመቀበል እና በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ እያንዳንዱን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ለእርሱ እንደ መጣ የእግዚአብሔር መልእክት ለማስተዋል መጣር አለበት፡፡ በተግባር ከተተገበረ የተትረፈረፈ ፀጋን እና ሰላምን የሚያመጣውን እውቀት ወላጆች ለራሳቸው በመገንዘብ ከመድረክ ላይ የሚነገረውን ቃል ለልጆቻቸው ማስረዳት አለባቸው፡፡15Manuscript Releases 4:1, 1903.CGAmh 507.2

    በምግብ ሰዓት ልዩ መስተንግዶ አድርጉ— ለሰንበት ከሌሎቹ ቀናት ይበልጥ ብዙ አቅርቦት ወይም ብዙ የተለያዩ ምግቦችን ማቅረብ የለብንም፡፡ ከዚህ ይልቅ አእምሮ መንፈሳዊ ነገሮችን ለመረዳት ይችል ዘንድ ንጹህ እና ብርቱ እንዲሆን ምግቡ ይበልጥ ቀለል ያለ፣ እና አነስተኛ መጠን መበላት አለበት። ከመጠን በላይ መብላት አንጎልን በጭጋግ የተሸፈነ ያደርገዋል። በጣም ውድ የሆኑ ቃላት ሊሰሙ እና አድናቆት ሊያጡ ይችላሉ፣ ምክንያቱም አዕምሮ ተገቢ ባልሆነ አመጋገብ ግራ ይጋባል። በሰንበት ቀን ከመጠን በላይ በመመገብ ብዙዎች ከሚያስቡት በላይ እግዚአብሔርን አዋርደዋል፡፡ CGAmh 507.3

    በሰንበት ቀን ምግብ ማብሰል መወገድ ያለበት ቢሆንም፣ ቀዝቃዛ ምግብ መመገብ አስፈላጊ አይደለም፡፡ በቀዝቃዛ አየር ውስጥ ባለፈው ቀን የተዘጋጀው ምግብ እንዲሞቅ ይደረግ፡፡ እንዲሁም ምግቦቹ ቀላል ቢሆኑም አስደሳች እና ማራኪ ይሁኑ፡፡ ቤተሰቡ በየቀኑ የማያገኘውን፣ እንደ መስተንግዶ ሊቆጠር የሚችል አንድ ነገር አቅርቡ፡፡ 1067Testimonies For The Church 6:357.CGAmh 508.1

    የዕለቱ ዕረፍት ውድ ነው— የሰንበት ትምህርት እና የአምልኮ ስብሰባ የሰንበትን አንድ ክፍል ብቻ የሚይዙ ናቸው፡፡ ለቤተሰብ የቀረው ድርሻ ከሁሉም የሰንበት ሰዓቶች ሁሉ እጅግ ውድ እና ቅዱስ ወቅት ሊሆን ይችላል። የዚህን አብዛኛውን ጊዜ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ማሳለፍ አለባቸው፡፡ 1068Testimonies For The Church 6:358.CGAmh 508.2

    ምቹ ንባብ እና ውይይት ላይ እቅድ አውጡ— ሰንበት— አቤት!— የሳምንቱን በጣም ጣፋጭ፣ በጣም የተባረከ ቀን አድርጉት…፡፡ CGAmh 508.3

    እጅግ አስደሳች የሆኑትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን ለእነርሱ በማንበብ፣ የሰንበትን ቀን እንደ ትዕዛዙ በመጠበቅ እንዲያከብሩ በማስተማር ወላጆች ለልጆቻቸው ትኩረት መስጠት ይችላሉ፣ ማድረግም አለባቸው፡፡ ወላጆች ልጆቻቸውን ለመሳብ ምንም ሸክም የማይሰማቸው ከሆነ ይህ ሊደረግ አይችልም፡፡ ነገር ግን ትክክለኛውን አካሄድ ከተከተሉ ሰንበትን አስደሳች ማድረግ ይችላሉ፡፡ ልጆቹ በጥሩ ንባብ ወይም ስለ ነፍሳቸው መዳን መወያየት ላይ ፍላጎት ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ነገር ግን እነርሱ የተማሩ እና የሰለጠኑ መሆን አለባቸው፡፡ ተፈጥሮአዊው ልብ እግዚአብሔርን፣ ሰማይን ወይም ሰማያዊ ነገሮችን ማሰብ አይወድም፡፡ ዘወትር የወቅቱን ዓለማዊነት እና የክፋት ዝንባሌ ወደ ኋላ መግፋት እና የሰማይ ብርሃንን ወደ ውስጥ ማስገባት መኖር አለበት። 1069The Review and Herald, April 14, 1885.CGAmh 508.4

    ለህፃናት ተግባራት ግድየለሽ አለመሆን— በሰንበት ቀን ብዙዎች ግድየለሾች እንደሆኑ እና ልጆቻቸው የት እንዳሉ ወይም ምን እያደረጉ እንዳሉ የማውቁ ሆነው አግኝቻቸዋለሁ፡፡ 1070The Review and Herald, April 14, 1885.CGAmh 509.1

    ወላጆች ከሁሉም ነገር በላይ በሰንበት ቀን ልጆቻችሁን ጠብቋቸው፡፡ በቤት ውስጥ ወይም ከቤት ውጭ በመጫወት የእግዚአብሔርን የተቀደሰ ቀን እንዲጥሱ አትፍቀዱላቸው፡፡ ልጆቻችሁ ይህን እንዲያደርጉ ስትፈቅዱላቸው እራሳችሁም እንዲሁ ሰንበትን ትጥሳላችሁ፣ እናም ልጆቻችሁ ወዲያና ወዲህ እንዲንከራተቱ እና በሰንበት እንዲጫወቱ ስትፈቅዱላቸው፣ እግዚአብሔር ሰንበትን እንደጣሳችሁ ይቆጥራችኋል፡፡ 1071The Review and Herald, September 19, 1854.CGAmh 509.2

    ከቤት ውጭ ከልጆች ጋር— ወላጆች ልጆቻቸው በተፈጥሮ ውስጥ እግዚአብሔርን እንዲመለከቱ ወደ ውጭ ይዘው ሊወጡ ይችላሉ፡፡ ወደሚያብቡ አበቦች እና ወደሚፈኩ እምቡጦች፣ ግዙፍ ዛፎች እና የሳር ውብ ሾጣጣዎች በመጠቆም እግዚአብሔር እነዚህን ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ እንደሰራ እና በሰባተኛው ቀን እንዳረፈ እና እንደቀደሰውም መማር ይችላሉ፡፡ በዚህ መንገድ ወላጆች እነዚህ ልጆች ተፈጥሮን ሲመለከቱ የሁላቸው ታላቅ ፈጣሪ የሆነውን ወደ ትውስታቸው እንዲያመጡ ለማድረግ ትምህርታቸውን በልጆቻቸው ውስጥ ማስረጽ ይችላሉ፡፡ ሀሳባቸው ወደ ተፈጥሮው አምላክ ይወሰዳል— የሰንበት መሠረት በተጣለበት እና የእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ በደስታ ወደ ጮኹበት የዓለማችን ፍጥረት ማለት ነው። በልጆቻችን አእምሮ ውስጥ መስረጽ ያለባቸው ትምህርቶች እንደዚህ ያሉት ናቸው፡፡ CGAmh 509.3

    ልጆቻችን በሰንበት ደስተኛ መሆን እንደሌለባቸው፣ ከቤት ውጭ መሄዳቸው ስህተት መሆኑን ማስተማር የለብንም፡፡ በፍፁም ይህ መሆን የለበትም፡፡ ክርስቶስ በሰንበት ቀን ደቀ መዛሙርቱን ወደ ሐይቅ ዳርቻ ወስዷቸው አስተምሯቸዋል፡፡ በእለተ ሰንበት የእርሱ ስብከቶች ሁልጊዜ በተዘጉ ግድግዳዎች ውስጥ አይሰበኩም ነበር፡፡ 1072Manuscript Releases 3:1879.CGAmh 509.4

    ከተፈጥሮ የሚገኙ ሌሎች ትምህርቶች— የምሳሌ ትምህርቶች— ልጆች ክርስቶስን በተፈጥሮ ውስጥ እንዲመለከቱ አስተምሯቸው፡፡ ውጭ ወደ አየር፣ ወደ የከበሩ ዛፎች ሥር ወደ አትክልት ሥፍራ ውሰዷቸው፤ ደግሞም በሁሉም የፍጥረት ሥራዎች ውስጥ የፍቅሩን መገለጫ እንዲያዩ አስተምሯቸው። ህይወት ያላቸውን ነገሮች ሁሉ የሚቆጣጠሩ ህጎችን እንደፈጠረ፣ ለእኛም ህጎችን እንደፈጠረ፣ እና እነዚህ ህጎች ለደስታችን እና ለተድላችን እንደሆኑ አስተምሯቸው። በተፈጥሯዊ ምሳሌ ትምህርቶች የእግዚአብሔርን ሕግ እንዲታዘዙ አስተምሯቸው እንጂ በረጅም ጸሎቶች እና አሰልቺ በሆኑ ምክሮች እንዲዝሉ አታድርጓቸው፡፡ 1073The Desire of Ages, 516, 517.CGAmh 510.1

    የእግዚአብሔርን ባሕርይ እውነተኛ ግንዛቤ መስጠት— ልጆች አብዛኛውን ጊዜያቸውን ከቤት ውጭ በጨዋታ ከማሳለፍ ይልቅ ከወላጆቻቸው ጋር በመሆን ትክክለኛውን የእግዚአብሔር እውቀት እንዴት ማግኘት ይችላሉ? አእምሯቸውስ እንዴት በተሻለ ሁኔታ ይማረካል? የልጅነት አእምሯቸው በተፈጥሮ ውብ ትዕይንት አማካይነት ከእግዚአብሔር ጋር እንዲገናኝ አድርጉ፤ በተፈጥሮ ሥራዎቹ ውስጥ ትኩረታቸው እርሱ ለሰው ስላለው የፍቅር ምልክቶች ይሳብ፣ እነርሱም ይሳባሉ፣ ፍላጎትም ያድርባቸዋል። የእግዚአብሔርን ባሕርይ ከባድ እና አደገኛ ከሆኑ ነገሮች ሁሉ ጋር የማያያዝ አደጋ ውስጥ አይሆኑም፤ ነገር ግን ለሰው ደስታ የፈጠራቸው ውብ ነገሮችን ሲመለከቱ፣ እርሱ ርህሩህ፣ አፍቃሪ አባት እንደሆነ እንዲመለከቱ ይመራሉ። የእርሱ ክልከላዎች እና ትዕዛዞች የእርሱን ኃይል እና ስልጣን ለማሳየት ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ለልጆቹ ደስታ ዓላማ እንዳለው ይመለከታሉ። የእግዚአብሔር ባሕርይ የፍቅር፣ የርህራሄ፣ የውበት እና ማራኪ ገጽታ ላይ ሲሆን፣ እርሱን ወደ መውደድ ይሳባሉ። በደስታ መዝሞሮቻቸው አየርን በሙዚቃ የታጀበ ወደሚያደርጉት ተወዳጅ ወፎች፣ ወደ ሾጣጣ የሣር ጫፎች እና በጥሩ መዓዛቸው አየሩን ወደ የሚያውዱ ባለ ግርማ ፍጹም አበቦች አእምሯቸውን መምራት ትችላላችሁ፡፡ እነዚህ ሁሉ የሰማያዊውን አርቲስት ፍቅር እና ክህሎት ያውጃሉ፣ የእግዚአብሔርንም ክብር ያሳያሉ። CGAmh 510.2

    ወላጆች፣ ለልጆቻችን የእርሱን ትክክለኛ ባህሪይ እሳቤ ለመስጠት እግዚአብሔር በተፈጥሮ መጽሐፍ ውስጥ የሰጠንን ውድ ትምህርቶች ለምን አንጠቀምበትም? ቀላል ያለ የአኗኗር ዘይቤን ለፋሽን መሥዋዕት የሚያደርጉና የተፈጥሮ ውበቶችን ከራሳቸው የሚያርቁ ሰዎች መንፈሳዊ አዕምሮ ያላቸው መሆን አይችሉም፡፡ በተፈጠሮ ሥራዎቹ ውስጥ የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ችሎታ እና ኃይል ሊገነዘቡ አይችሉም፤ ስለዚህ ልባቸው በአዲስ ፍቅር እና ፍላጎት አይነቃቃም፣ ትርታውንም አይጀምርም፣ በተፈጥሮም ውስጥ እግዚአብሔርን በመመልከታቸው በፍርሃትና በአክብሮት አይሞሉም። 1074Testimonies For The Church 2:583, 584.CGAmh 511.1

    በኤደን ሕይወት የሚኖርበት ቀን— እንደ አንዱ የትምህርት ዘዴ የሰንበት ዋጋ ከሚገመተው በላይ ነው፡፡ እግዚአብሔር ከእኛ የሚጠይቀውን ማንኛውንም ነገር በራሱ ክብር አብዝቶ፣ ለውጦ እንደገና ይመልስልናል ...፡፡ CGAmh 511.2

    ሰንበት እና ቤተሰብ በኤደን ውስጥ ተቋቋሙ፣ ደግሞም በእግዚአብሔር ዓላማ ውስጥ እርስ በእርሳቸው ለዘላለሙ የተቆራኙ ናቸው። ከሌላው ጊዜ ይበልጥ በዚህ ጊዜ፣ የኤደንን ሕይወት መኖር እንችላለን፡፡ የቤተሰብ አባላት በሥራ እና በጥናት፣ በአምልኮ እና በመዝናኛ፣ አባት የቤተሰቡ ካህን እንደ መሆኑ መጠን፣ እና አባትም ሆነ እናት የልጆቻቸው አስተማሪዎች እና ጓደኞች እንዲሆኑ የእግዚአብሔር እቅድ ነበር፡፡ ነገር ግን የኃጢአት ውጤቶች የሕይወትን ሁኔታዎች በመለወጡ በከፍተኛ ደረጃ ይህንን ግንኙነት አግዷል፡፡ ብዙውን ጊዜ አባት ሳምንቱን በሙሉ የልጆቹን ፊት ላያይ ይችላል፡፡ እርሱ ባልደረባ ለመሆን ወይም ትምህርት ለመስጠት ዕድሉን ሙሉ በሙሉ ተነፍጓል ማለት ይቻላል፡፡ የእግዚአብሔር ፍቅር ግን ለልፋት ገደብ አበጅቷል፡፡ በእለተ ሰንበት ላይ መሐሪ እጁን ያሳርፋል፡፡ በራሱ ቀን ቤተሰብ ከእርሱ ጋር፣ ከተፈጥሮ እና ከሌሎች ጋር የሚገናኝበትን እድል አስቀርቶላቸዋል። 1075Education, 250, 251.CGAmh 511.3

    ሰንበትን አስደሳች አድርጉ— እግዚአብሔርን የሚወዱ ሁሉ ሰንበትን አስደሳች፣ ቅዱስ እና የተከበረ ለማድረግ የተቻላቸውን ሁሉ ማድረግ አለባቸው። በኃጢአት ውስጥ የራሳቸውን ተድላ፣ የተከለከሉ መዝናኛዎችን በመሻት ይህንን ማድረግ አይችሉም፡፡ ሆኖም ሰንበትን በቤተሰቦቻቸው ውስጥ ከፍ ለማድረግ እና የሳምንቱ አስደሳች ቀን ለማድረግ ብዙ ማድረግ ይችላሉ፡፡ ልጆቻችንን ለማስደሰት ጊዜ መስጠት አለብን፡፡ የአንድ ነገር ለውጥ በእነርሱ ላይ የደስታ ተጽዕኖ ይኖረዋል። ውጭ አየር ውስጥ ከእነርሱ ጋር አብረን መሄድ እንችላለን፤ ከእነርሱ ጋር ጫካ እና በደማቅ የጸሐይ ብርሃን ውስጥ በመቀመጥ በእግዚአብሄር ሥራዎች ላይ በመወያየት እረፍት የለሹ አዕምሮአቸው አንድ የሚመገበውን ነገር መስጠት እና ትኩረታቸውን ውብ ወደ ሆኑ የተፈጥሮ ቁሶች በመሳብ በፍቅር እና አክብሮት ልናነሳሳቸው እንችላለን፡፡ CGAmh 512.1

    የሰንበት በየሳምንቱ ተመልሶ መምጣት በደስታ እንዲወደስ ለቤተሰቦቻችን በጣም አስደሳች መደረግ አለበት፡፡ ወላጆች ትክክለኛውን የእግዚአብሔር ባህሪይ ገጽታ እና የክርስትና ባህሪይን ፍጹም ለማድረግ እና የዘላለም ሕይወትን እንዲያገኙ ከእኛ የሚጠብቀውን በማድረግ ተገቢውን መመሪያ ለቤተሰቦቻቸው ለመስጠት እና በመንፈሳዊ ጉዳዮች እንዲማረኩ ለማድረግ መንገዶችን ከመፈለግ በላይ ሰንበትን ከፍ ማድረግ እና የከበረ የሚያደርጉበት ሌላ መንገድ የለም፡፡ ወላጆች፣ ልጆቻችሁ በጉጉት እንዲጠብቁት እና በልባቸው ውስጥ ለእርሱ መልካም አቀባበል እንዲኖራቸው፣ ሰንበትን አስደሳች አድርጉ። 1076Testimonies For The Church 2:584, 585.CGAmh 512.2

    በጸሎት እና በመዝሙር ላይ እጅግ ምቹ ፍጻሜ— ፀሐይ በምትጠልቅበት ጊዜ፣ የጸሎት ድምፅ እና የውዳሴ መዝሙር ቅዱሳን ሰዓታትን በመዘጋት ምልክት ይሁኑ፣ እንዲሁም በሳምንቱ ሥራ ውስጥ የእግዚአብሔርን መገኘት ጋብዙ።CGAmh 512.3

    በዚህም መንገድ ወላጆች ሰንበትን፣ እንደሚገባውም፣ የሳምንቱ እጅግ አስደሳች ቀን ሊያደርጉት ይችላሉ። ልጆቻቸው እንደ ደስታ፣ የቀናት ሁሉ ቀን፣ የጌታ ቅዱስ፣ የተከበረ አድርገው እንዲመለከቱ ሊያደርጓቸው ይችላሉ። 1077Testimonies For The Church 6:359.CGAmh 513.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents