Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የልጅ አመራር

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 5—መጽሐፍ ቅዱስ እንደ መመሪያ መጽሐፍ

    የልጅ የመጀመሪያ መጽሐፍ—መጽሐፍ ቅዱስ የልጅ የመጀመሪያ መማሪያ መጽሐፍ መሆን አለበት፡፡ ከዚህ መጽሐፍ ውስጥ ወላጆች ጥሩ መመሪያ ሊሰጧቸው ይገባል፡፡ የእግዚአብሔር ቃል የሕይወት መመሪያ ሕግ ሊሆን ይገባል፡፡ ከእሱ ልጆች እግዚአብሔር አባታቸው መሆኑን መማር አለባቸው፣ ከቃሉም ውብ ትምህርቶች ውስጥ ስለእርሱ ባህሪይ እውቀት ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡ መርሆዎቹን በማስረጽም ፍትህና ፍርዱን ማድረግን ይማራሉ፡፡ 53Counsels to Parents, Teachers, and Students, 108, 109 CGAmh 39.1

    የተስፋ ቃል፣ የበረከት እና የተግሳጽ መጽሐፍ— እናት ልጆቿ ስህተትን ሲሰሩ የእግዚአብሔርን ቃል ለግሳጼ ማቅረብ ትችል ዘንድ እና ምን ያህል እነርሱ የእግዚአብሔርን መንፈስ እንዳሳዘኑ ለማሳየት በእግዚአብሔር ቃል ተስፋዎች እና በረከቶች እንዲሁም ክልከላ በተደረገባቸው ነገሮች አዕምሮዋን ማደስና መሙላት አለባት፡፡ የኢየሱስ ማረጋገጫና ፈገግታ በምድር ላይ እጅግ ሐብታም ከሆኑ፣ እጅግ ከተከበሩ፣ እና እጅግ ከተማሩ ሰዎች ወዳሴ ወይም ቁልምጫ ወይም አድናቆት ይልቅ ታላቅ ዋጋ እንዳለው አስተምሯቸው፡፡ በፍቅር፣ በርህራሄና በቅንነት ቀን በቀን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ምሯቸው፡፡ በእናንተና በዚህ ታለቅ ሥራ መካከል ምንም ይገባ ዘንድ አይፍቀዱ፡፡ 2The Review and Herald, April 14, 1885.CGAmh 39.2

    መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ባህሪይን ይገነባል— የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች የሕይወት ልምምድ ሲሆኑ ባህሪይ ላይ የግብረ ገብና የኃይማኖት ተጽዕኖ ይኖራቸዋል፡፡ ጢሞቴዎስ እነዚህን ትምህርቶች ተምሯል ተግባራዊም አድርጓቸዋል፡፡ ታላቁ ሐዋርያ ብዙውን ጊዜ በቅዱሳት መጻሕፍት ታሪክ ላይ ጥያቄ በመጠየቅ እርሱ መልስ እንዲሰጥበት ያደርግ ነበር፡፡ እያንዳንዱን ክፉ መንገድ የመሸሽ አስፈላጊነትን ለእርሱ በማሳየት እና በረከት በእርግጥም ተማኞች እና እውነተኞ ላይ በመውረድ ታማኝ እና የከበረ ስብዕና እንደሚያጎናጽፋቸው ነገረው፡፡ የከበረ እና ሙሉ በሙሉ የተዋጣለት ስብዕና በእድል የሚመጣ አይደለም፡፡ ይህ የሚመጣው ከልጅነት ጊዜያት ጀምሮ በሂደት የተቀረጸ ባህሪይ እና ቤት ውስጥ የእግዚአብሔርን ሕግጋት የመለማመድ ውጤት ነው፡፡ እርሱ እንዳዘዘው ልጆቻቸውን የሚያሰለጥኑትን በሙሉ እግዚአብሔር ታማኝነት የተሞላበት ጥረቶቻቸውን ይባርካል፡፡ 54Letter 33, 1897.CGAmh 39.3

    የእግዚአብሔርን ፍቅር እንደ አስደሳች ርዕሰ-ጉዳይ ያቀርባል— በእያንደንዱ ቤተሰብ ውስጥ ያሉ ልጆች ጌታ በሚፈልገው አይነት አስተዳደግና ግሳጼ ማደግ አለባቸው፡፡ ክፉ ዝንባሌዎች እና ስሜቶች ቁጥጥር ሥር መሆን አለባቸው፤ ልጆች በእርሱ ውድ ደም የመጡ የእግዚአብሔር ንብረት እንደሆኑ እና የተድላና የከንቱናትን ሕይወት በመኖር፣ የራሳቸውን ፈቃድ በመፈጸምና ሐሳባቸውን ተግባራዊ እያደረጉ ከእግዚአብሔር ልጆች ጋር መቆጠር እንደማይችሉ ሊማሩ ይገባል፡፡ ልጆች ርህራሄና ትዕግስትን መማር አለባቸው፡፡… ወላጆች በቤተሰብ ውስጥ የእግዚአብሔርን ፍቅር ደስ የሚያሰኝ ርዕሰ-ጉዳይ አድርገው ያስተምሩአቸው፤ ቤተ ክርስቲያንም በመንጋው ውስጥ ያሉ ጠቦቶችና በጎችን የመመገብ ኃለፊነት ትውሰድ፡፡ 55The Review and Herald, October 25, 1892.CGAmh 40.1

    ታሪኩ ለፈሪ ልጅ ዋስትናን ያመጣለታል— ሕይወት ሸክም ለሆነበት ፈሪ ልጅ ፍርሃቱን ማስወገድ የሚችለው የእግዚአብሔር መገኘት ሲሰማው ብቻ ነው፡፡ “የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ዙሪያ ይሰፍራል፣ ያድናቸውማል” መዝ. 34፡7 የሚለውን ተስፋ በልቦናው ውስጥ ያስርጽ፡፡ በተራራዋ ከተማ ውስጥ በኤልሳዕና በታጠቁ የጠላት ሠራዊት መካከል የተከሰተውን የሰማይ መላእክትን ሠራዊት ታለቅ ከበባ አስገራሚ ታሪክ ያንብብ፡፡ ጴጥሮስ በእስር ቤት ውስጥ ሞት ተፈርዶበት ሳለ የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦ የታጠቁ ጠባቂቆችን፣ ግዙፉን የብረት በር መቀርቀሪያዎች እና ዘንጎችን አሳልፎ እንዴት በሰላም እንደመራው ያንብብ፡፡ ባሕር ላይ አውሎ ነፋሱ ወታደሮችና መርከበኞቸን ባናወጠ ጊዜ፣ በሥራ ዝሎ የነበረው ለረጅም ጊዜያት ሲጠባበቅና ሲጾም የነበረው እስረኛው ጳውሎስ ለምርመራና ፍርድ ሊሰጥበት በሚሄድበት ጊዜ የተናገራቸውን ታላላቅ የማደፋፈሪያና የተሰፋ ቃላትን ተናገረ፣ “አይዞአችሁ፣ ከእናንት አንድ ነፍስ እንኳ አይጠፋምና፡፡ …የእርሱ የሚሆንና ደግሞ የማመልከው የእግዚአብሔር መልአክ በዚች ሌሊት በአጠገቤ ቆሞ ነበርና፡፡ እርሱም፡- ጳውሎስ ሆይ፣ አትፍራ፣ በቄሳር ፊት ልትቆም ይገባሃል፤ እነሆም እግዚአብሔር ካንተ ጋር የሚሄዱትን ሁሉ ሰጥቶሃል አለኝ፡፡” በዚህ ተስፋ ጳውሎስ እንዲህ ሲል ለጓደኞቹ አረጋገጠላቸው፣ “ከእናንተ ከአንዱ የራስ ጠጉር እንኳ አትጠፋምና፡፡” እንዲሁም ሆነ፡፡ አንድ እግዚአብሔር በእርሱ ውስጥ የሚሰራ ሰው መርከቡ ውስጥ በመኖሩ ምክንያት መርከቡን የሞሉ የአሕዛብ ወታደሮችና መርከበኞች በሰላም ተጠበቁ፡፡ “ሁሉ በደህና ወደ ምድር ደረሱ፡፡” የሐዋ. ሥራ 27፡22-24፣34፣44፡፡ CGAmh 40.2

    እነዚህ ነገሮች የተጻፉት አንብበን እንድንደነቅ ብቻ ሳይሆን፣ በጥንቶቹ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ላይ የሰራው ያው እምነት በእኛ ውስጥም እንዲሰራ ነው፡፡ ያኔ ከሰራበት ጉልህ መንገድ ባላነሰ መልኩ የኃይሉ መተላለፊያ የሚሆኑ እምነት ያላቸው ልቦች ባሉበት ሥፍራ ሁሉ ዛሬም ይሰራል፡፡ 56Education, 255, 256. CGAmh 41.1

    በእምነት ጠንክራ ይሁኑና ሁላችንም እግዚአብሔር ላይ እንደምንደገፍ ልጆችዎን ያስተምሩ፡፡ የአራቱን የዕብራይስጥ ወጣቶችን ታሪክ ለልጆቻችሁ ያንብቡላቸው፣ እናም በዳንኤል ዘመን መልካም ተፅዕኖ እንዲሆን ያደረገው ለመርህ በጥብቅ መገዛታቸው መሆኑን አዕምሮአቸው ላይ ያስርጹ፡፡ 57Manuscript Releases 3:3, 1909.CGAmh 41.2

    የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶችን ለመረዳት ቀላል አድርጉላቸው— ወላጆች የመጽሐፍ ቅዱስን ትምህርት ቀለል በማድረግ ልጆቻቻው ያለ ምንም ችግር በሚረዱት መልኩ ማስተማር አለባቸው፡፡ 7Letter 189, 1903.CGAmh 41.3

    የእግዚአብሔር ሕግጋት የሕይታቸው መምሪያ እንደሆነ ልጆቻችሁን አስተምሩ፡፡ ከወላጆቻቸውና ከቤቶቻቸው እነርሱን የሚለዩ ሁኔታዎች ሊፈጠሩ ይችላሉ፣ ነገር ግን በልጅነት እና በወጣትነት የሚሰጧቸው መመሪያዎች በሕይወት ዕድሜያቸው ሁሉ በረከት ይሆንላቸዋል፡፡ 58Manuscript Releases 5:7, 1897. CGAmh 41.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents